TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

" በ7 ቀናት ማስረጃ አቅርቡ ካልሆነ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎች በ7 ቀናት የሴትና የአካል ጉዳተኛ አባሎቻቸውን መረጃ እንዲያቀርቡ አሳሰበ።

የተባለውን የማይፈጽሙ ከሆነ ሕጋዊ የሆነ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አሳውቋል።

ቦርዱ ሀገሪቱ ውቅጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግሥት የሚመደብ የ2014፤ 2015 እና 2016 በጀትን አከፋፍሏል።

ይሀንን የበጀት ድጋፍ ለማከፋፈል በሕጉ ከተቀመጡ መሥፈርቶች መካከል የፖለቲካ ፖርቲዎች ያሏቸውን ሴት እና አካል ጉዳተኛ አባላት ቁጥር በቃለ-መኃላ አስደግፈው ማቅረብ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ፥ 21 ፖለቲካ ፖርቲዎች በ2016 ዓ/ም ለቦርዱ ያሰወቁት የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባሎቻቸው በ2014 እና 2015 ዓ.ም ካቀረቡት ቁጥር አንጻር የተጋነነ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚህም ምክንያት ፖርቲዎቹ የአባሎቻቸውን ሙሉ መረጃ ለቦርዱ እንዲያቀርቡ መጋቢት 25/2016 ዓ/ም አሳውቆ ነበር።

10 የፖለቲካ ፖርቲዎች የተለያዩ ምላሾችን የሰጡና በእጃቸው የሚገኙ መረጃዎችን አቅርበዋል።

11 ፖርቲዎች ማለትም ፦

➡️ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት
➡️ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ
➡️ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
➡️ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር
➡️ ብልጽግና ፓርቲ (ገዢው ፓርቲ)
➡️ ራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
➡️ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
➡️ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
➡️ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት
➡️ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
➡️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ግን በአንድ ዓመት ውስጥ ከ10,000 እስከ 900,000 የሴት አባላትና የአካል ጉዳተኛ አባላት ቁጥር ነው ያቀረቡት።

ፓርቲዎቹ ላቀረቡት ለዚህ ቁጥር ያላቸውን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠየቁም እስካሁን ሳይሰጡ እንደቀሩ ተገልጿል።

በመሆኑም በ7 ቀን ውስጥ ማስረጃውን ካላቀረቡ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቦርዱ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከነገ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
🎓 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25-26/2016 ዓ.ም
🎓 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ሠመራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
🎓 ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26 እና 27/2016 ዓ.ም
🎓 ቦረና ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ዲላ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
🎓 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
🎓 ደምቢ ዶሎዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም

Via @tikvahuniversity
#Amhara

ከሰሞኑን በአማራ ክልል፣ በባህርዳር ከተማ የተለያዩ የመንግሥት አካላት ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ከተካሄደ የሰላም ኮንፈረንስ በኃሏ ተቋቁሟል የተባለው ' አመቻች የሰላም ምክር ቤት ' በአማራ ክልል እየተደረገ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት ነው ብሏል።

ምክር ቤቱ በዚህ ጦርነት ፥ " ወንድም ከወንድሙ፣ ልጅም ከአባቱ ጋር ነው እየተገዳደለ ያለው " ሲል ገልጿል።

ለፌዴራል መንግሥት / ለአማራ ክልላዊ መንግሥት እና ለፋኖ ኃይሎች ሲል በስም ጠርቶ ባቀረበው የሰላም ጥሪ " የወገናችሁን ስቃይ ተረድታችሁ ምንም መሸናነፍ በማትችሉት ጦርነት ከመቆየት ሁለታችሁም ማሸነፍ ወደምትችሉት ንግግር እና ድርድር እንድትመጡ እንጠይቃለን " ብሏል።

ም/ ቤቱ መንግሥት እና የፋኖ ኃይሎች ወደ ሰላም መድረክ እንዲመጡ ለማመቻቸት እንደሚሰራ አመልክቷል።

" በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ንጹሃን ይገደላሉ፣ በጠራራ ጸሃይ ያለ ከልካይ ይዘረፋሉ  " ያለው ምክር ቤቱ ከ12 እስከ 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን አመልክቷል።

መንግሥት ጦርነቱን በድርድር ለመቋጨት ፍቃደኛ እንደሆነ ገልጾ " ብዙ መሪ እና አደረጃጀት ያላቸው የፋኖ ታጣቂዎች ለመደራደር ወደ አንድ መምጣት አለባቸው በማለቱ ይህ የሰላምና ድርድር አመቻች ምክር ቤት መቋቋሙ ተነግሯል።

ምክር ቤቱ 15 አባላት ያሉት ነው።

በሌላ በኩል ፥ ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በክልሉ መገደላቸው ተሰምቷል።

በሰሜን ጎንደር ዞን ፤ በዳባት ወረዳ፣ በመንግስት የጸጥታ አካላት እና ፋኖ ኃይሎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የፓሊስ አባላት መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ሁነቱን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ ነዋሪ ፤ " ከተማው ውስጥ አሁንም ሀዘን/ልቅሶ አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሀዘኑ የተፈጠረው በአካባቢው ላይ ከ ‘ ፋኖ ’ ጋር በነበረ ውጊያ በርካታ የአካባቢው የጸጥታ አባላት ስለተገደሉ መሆኑን አረጋግጫለሁ " ብለዋል።

የሟቾች ቁጥር ምን ያህል ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ " የሟቾች ቁጥር ከ115 በላይ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሟቾቹን በተመለከተም አድማ ብተና ሚሊሻና ፖሊስ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ሌሎች ነዋሪዎች የሟቾች ቁጥር እስከ 130 እንደሚደርስ ንጹሐን እንደቆሰሉ ገልጸው ሰሞኑን ከተማዋ ከባድ ሀዘን እንዳስተናገደች ተናግረዋል።

ስለግድያው ምላሽ የጠየቅነው የዳባት ወረዳ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ጉዳዩን በጽሞና ከሰማ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም።

በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንትም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ባአዊ ዞን የቲሊሊ ወረዳ ነዋሪዎች ደግሞ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 3 ሰዎችን ከቲሊሊ ሆቴል አውጥተው ገድለዋል ሲሉ ከሰዋል።

ሌሎች 2 ሰዎችም ተገድለዋል። በድምሩ 5 ንጹሐን በቲሊሊ ወረዳ መገደላቸውን ተናግተዋል።

በቦታው የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነበር እንዴ ? በሚል ለነዋሪዎቹ ለቀረበው ጥያቄ ምንም ተኩስ እንዳልነበር፣ ግማሾቹን መንገድ ላይ በሚጓዙበት፣ ሌሎቹን ደግሞ ከሆቴል አስወጥተው እንደገሏቸው አስረድተዋል።

የመንግስት አካላት ስለሁኔታው እንዲያብራሩልን ብንጠይቅም ፍቃደኛ አልሆኑም።

ከዚህ ባለፈም ፥ በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ  " ሾላ  ሜዳ " በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና 4 የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ አማርኛው ዘግቧል።

በጥቃቱት ከአያቶቹ ጋር የሚኖር የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሉን ፥ አንድ የአይን እማኝ ደግሞ አንድ ሻይ ቤት 11 ሰዎች መገደላቸውን በ20ዎቹ እድሜ የሚገኝ ወንድማቸው ተገድሎ ሜዳ ላይ እንዳገኙት ተናግረዋል።

ሌላ የአይን እማኝ የ11ዱ ሟቾችን ስም ዝርዝር መሰብሰብ እንደቻሉ ሰኔ 20 ቀን/2016 ዓ/ም 4 ተጨማሪ አስከሬን እንደተገኘ ገልጸዋል።

የጸጥታ ኃይሎቹ በአካባቢው ለለቅሶ መጥተዋል የተባሉ 3 የፋኖ ታጣቂዎችን ተከትለው ሳይመጡ እንዳልቀረና ስለ ታጣቂዎቹ መረጃ በመፈለግ ግድያውን እንደተፈጸመ አክለዋል።

በተመሳሳይ በሰሜን ጎጃም ዞን ፤ በይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 11 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፥ በእለቱ የፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግሥት ኃይሎች ለሰዓታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ይህን ተከትሎ ጥቃቱ መፈጸሙን አንድ ሴትና 10 ወንዶች እንደተገደሉ ገልጸዋል።

ግድያው የ ' ፋኖ ታጣቂዎች ' ከተማይቱን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ 02 ቀበሌ እርሻ ሰብል በተባለ ሰፈር መንገድ ላይ እና ቤት ለቤት መፈጸሙን ገልጸዋል።

" ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ " በሚል ግድያው ተፈጽሟል ሲሉ ከሰዋል።

ፋኖ በከተማው ተቆጣጥሮ ውሎ በወጣበት ሰዓት የመንግስት ጸጥታ ኃይል ተመቶ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በተፈጠረው ክስተት ከተማዋ በከባድ ሀዘን ውስጥ መውደቋን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ፤ ያለው ጦርነት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በተለያየ ጊዜ በተለያየ ቦታ እየተፈጠረ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው።

ከሰሞኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ህዝቡ በሰላም እጦት የከፋ ችግር ላይ ወድቆ እንደሚገኝ ተናግረው ፥ መገዳደሉና ፣ በጠላትነት መፈላለጉ እንዲያበቃ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ አገኘሁ ተሻገር፥ " በቃ! እስኪበቃን ተገዳድለናል ፣ እስኪበቃን ተዋጋን ስለዚህ አሁን ላይ ይብቃን ፣ መፍትሔው ንግግር ነው ፣ መነጋገር ነው ፣ መከባበር ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

#Ethiopia
#AmharaRegion

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ነው ተጠንቀቁ " - የጠ/ሚ ጽ/ቤት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘው ተደረጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው። የጠ/ሚ ጽ/ቤት ያወጣው መግለጫ አስመስሎ አንድ የተቀነባበረ የጠ/ሚ ጽ/ቤት አርማ ያለበት መግለጫ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል። ይኸው መግለጫ ፦ - ኢትዮጵያ ከሶማሊያ…
#Ethiopia

ይህ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በተለይ በ X መተግበሪያ ላይ እየተራጨ ያለው መግለጫ ሀሰተኛ እና የተቀነባበረ ነው።

የሚኒስቴሩን የቀድሞ ሎጎ በመጠቀም እየተሰራጨ ያለው ይህ መረጃ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ፦
- በUN
- በEU
- BRICS (ኢትዮጵያ እራሷ አባል የሆነችበት)
- በኢስላሚክ ሀገራት ከፍተኛ ጫና እንደሰረዘችው የሚገልጽ ነው።

ይኸው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አወጣው የተባለው መግለጫ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ፣ ቱርክ ውስጥ ለውይይት መቀመጣቸውን እና በሚቀጥሉት ቀናት የጋራ መግለጫ (ከላይ ባለው ውሳኔ) እንደሚሰጡ ያመለክታል።

ከቀናት በፊት በጠ/ሚ ጽ/ቤት ሎጎ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሀሰተኛ መግለጫ ሲሰራጭ ነበር።

መግለጫው  በኢትዮጵያ የውጭ  ጉዳይ  ሚኒስቴር ስም በሀሰት ተዘጋጅቶ የተሰራጨ ሲሆን ያሰራጩት አካላት የመ/ቤቱን የቀድሞ ሎጎ ነው የተጠቀሙት።

ሚኒስቴሩ በመግለጫዎቹ አዲሱን ሎጎ መጠቀም ከጀመረ ወራት ተቆጥሯል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፥ በቱርክ አግባቢነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ቱርክ ውስጥ ለውይይት እና ንግግር እንደሚቀመጡ የሚገልጹ ሪፖርቶች ሲወጡ ነበር። ነገር ግን ምንም ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት በይፋዊ የ X ገጹ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው በቱርክ አሸማጋይነት ከኢትዮጵያ ጋር ለሚደረግ ንግግር ወደ አንካራ ቱርክ እንዳቀኑ የሚገልጽ አንድ መረጃ ካሰራጨ በኋላ ሳይቆይ አጥፍቶታል።

ስለ ውይይቱ ሆነ እየተወራ ስላለው ጉዳይ እስካሁን ኢትዮጵያ ያለችው ነገር የለም።

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ይህ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በተለይ በ X መተግበሪያ ላይ እየተራጨ ያለው መግለጫ ሀሰተኛ እና የተቀነባበረ ነው። የሚኒስቴሩን የቀድሞ ሎጎ በመጠቀም እየተሰራጨ ያለው ይህ መረጃ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ፦ - በUN - በEU - BRICS (ኢትዮጵያ እራሷ አባል የሆነችበት) - በኢስላሚክ ሀገራት ከፍተኛ ጫና እንደሰረዘችው…
#Ethiopia #Somalia

" ልዑካኑ የቀጥታ የፊት ለፊት ንግግር / ውይይት አላደረጉም " - የሶማሊያው ፕሬዜዳንት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ትላንት አንካራ ውስጥ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

በቱርክ ጋባዥነት በተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም የመሯቸው ልዑካን አንካራ ተገኝተው ነበር። 

ከውይይቱ በኃሏ የሶስቱ ሀገራት የጋራ መግለጫ ወጥቷል።

መግለጫው ፥ ሚኒስትሮቹ ያላቸውን ልዩነቶች ለሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎችን እንደዳሰሱ ገልጿል።

ሚኒስትሮቹ በተናጥል በግልጽነት ፣ ወዳጅነት ባለው እና የወደፊቱን ያለመ ውይይት እንደነበራቸው ነው የተመላከተው።

ሁለቱ አገራት ችግሮቻቸውን ለመፍታትና ቀጣናው እንዲረጋጋ የጀመሩትን ውይይት ለመቀጠል ተስማምተዋል የተባለ ሲሆን ለሁለተኛ ዙር ውይይት በአንካራ ነሐሴ 27/ 2016 ዓ.ም እንደሚገናኙ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ከ6 ወራት በፊት የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ በይፋ ተገናኝተው ሲመጋገሩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።

የጋራ መግለጫው ሁለቱ አገራት ልዩነታቸውን ለሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎችን እንደዳሰሰ ቢገልጽም እነዚህ ተቀባይነት አላቸው ስለተባሉ ጉዳዮች የተጠቀሰ ጉዳይ የለም።

በሌላ በኩል ፥ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ትላንት ውይይቱ ካበቃ በኃሏ ባሰሙት ንግግር ፦
- ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ወደኋላ የምትመለስበትን ምንም ምልክት አላሳየችም፤
- ከያዘችው መንገድ እየተመለሳች ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ፤
- አንካራ ውስጥ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ልዑካን ቀጥተኛ ንግግር አላደረጉም ይልቅም ቱርክ በመሃል እንደ አስታራቂ ሆና እየሰራች ነበር ብለዋል።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ከዛም የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ሎጎ በመጠቀም አንካራ ውስጥ በተደረገ ውይይት " ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት  ሰርዛለች " የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

#Ethiopia #Somalia #Turkey

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia " ልዑካኑ የቀጥታ የፊት ለፊት ንግግር / ውይይት አላደረጉም " - የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ትላንት አንካራ ውስጥ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል። በቱርክ ጋባዥነት በተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም የመሯቸው ልዑካን…
ኢትዮጵያ ስለ አንካራው ውይይት ምን አለች ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንካራው ውይይት ጉዳይ የፕሬስ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋባዥነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ትላንት ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ተገናኝተው መወያየታቸውን አረጋግጧል።

" በቱርኪዬ መንግስት አመቻቺነት የተካሄደው የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነበር " ብሏል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን አመልክቷል።

የቱርኪዬ መንግስት ውይይቱን ለማመቻቸት ስለተጫወተው ገንቢ ሚናም ምስጋና እንደቀረበ ገልጿል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮችን ለመቀጠልም እንደተስማሙ አረጋግጧል።

ሁለቱም ሚኒስትሮች የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምከከሩን አገራቸው ለማስተናገድ የወሰዱትን ተነሳሽነት በማድነቅ ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ለመቀጠል እንደተስማሙ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
#Ethiopia🕊

ቅዱስነታቸው ሁሉም ለሰላም በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ።

" የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን " በሚል ርእስ በአዲስ አበባ አንድ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህም መድረክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወክጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ " ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ጠብ፣ ክርክር፣ ሞኝ መሆኑን እያወቅን እዚያ ላይ እንንከባለላለን። የሰው ልጅ ህልውናውን ለመጠበቅ ሰላምን መምረጥ እና መከተል ይኖርበታል " ብለዋል።

" የሰላምን እጦት ያመጣነው ራሳችን ነን። ማንም አምጥቶ አልጫነብንም " ያሉ ሲሆን " ሰላም ከሌላ መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋማት ምንም መሰራት እንደማይችሉ አውቀን ለሰላም በአንድነት መቆምና ሰላምን መከተል ይኖርብናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለዚህም ሁላችንም ከቀደመው እየተማርን መጪውን ሰላማዊ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ፥ " የሔድንበት መንገድ ጎድቶናል ስለሆነም ወደ ሰላም እንመለስ ብለን መወሰን አለብን። ለዚህም ሁላችንም ወደ አእምሮችን ተመልሰን ሰላምን እንከተላት " ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።

#EOTC
#Ethiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ አቶ ካሳሁን ጎፌን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።

ወ/ሮ ሽዊት ሻንካን ደግሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ከዛሬ ሰኔ 26 /2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደ ተሾሙ ታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል። ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው…
#Update

የሀገር መከላከያው ስለ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንቅስቃሴ ምን አለ ?

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነትን መሰረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሀገር መከላከያው ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንዲያስተባብር አቅጣጫ ተሰጥቶ እየሰራ እንዳለ አመልክተዋል።

የፀለምት እና አካባቢው ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ኃላፊነት የተሰጠው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መሆኑን ተናግረው " ስራው እጅግ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው " ብለዋል።

ዛሬን ረቡዕ ጨምሮ ባለፉት ቀናት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቄያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሌ/ጄነራሉ ፥ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ያሉት አስፈላጊና መሟላት አለባቸው የተባሉ ቅድመ ሁኔታዎች ከጎን እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ስራው በፍጥነት እየሄደ ያለው አብዛኛዎቹ አርሶ አደር የክረምቱ ወቅት ሳያልፍ እርሻውን እንዲሰራና ህይወቱን እንዲመራ በማሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በፀለምት ካሉ 25 ቀበሌዎች አብዛኛው ተፈናቃይ ከ22 ቀበሌዎች ነው አሁን ባለው ሁኔታ በአስራዎቹ ቀበሌዎች ተፈናቃይ ተመልሷል ፤ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀሪ 11 ቀበሌዎች  አብዛኛው እንዲገባ ይደረጋል ሲሉ አሳውቀዋል።

የቀረውም ስራ በቀጣይ ይሄዳል ብለዋል።

ስለ ታጣቂዎች መውጣት ምን አሉ ?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የትግራይ ታጣቂዎች በኃይል ገብተዋል " ስለሚባለው ጉዳይ ሌ/ጄነራሉ ፥" ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ በፀለምትም ይሁን በወልቃይት በኃይል የገባባቸው ቦታዎች የሉም " ሲሉ መልሰዋል።

ፀለምት ካሉት ቀበሌዎች 3 ቀበሌዎች ላይ የትግራይ ታጣቂዎች እንዳሉ እነዚህም ጦርነት ሲቆም ባሉበት የቆሙ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

ባለው መግባባት ከሁለቱም ክልል ጋር የሁለቱም ክልል ታጣቂ መውጣት ስላለበት ተፈናቃዮችን በመመለስ ታጣቂዎቹን የማስወጣት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ፀለምት ያለው የትግራይ ታጣቂ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ እንዳይመለስ ስለሚሰራ ስራ ምን አሉ ?

በአማራ በኩል " ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ ይገባል " የሚል ስጋት እንዳለ ያልሸሸጉት አዛዡ ፥ በትግራይ በኩልም " ታጣቂዎች (በአማራ በኩል ያሉ) እንደ አዲስ ተደራጅተዋል ስጋት ናቸው " የሚል ነገር እንዳለ ገልጸዋል።

" የሀገር መከላከያው ከሁለቱም በኩል ከተፈናቃዮች እና እዛው ከነበሩት ነዋሪዎች ( ካልተፈናቀሉት ) ሽማግሌዎች እንዲውጣጡ አድርጎ የተፈናቃዮችን ዝርዝር ለመከላከያ ተሰጥቶ ከዛም መከላከያው ከሽማግሌዎቹ ጋር አብሮ ሰዎቹ የዛ ቦታ ነዋሪ መሆናቸውን እየጠየቀና እያረጋገጠ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ " ብለዋል።

' ይሄ ታጣቂ ነው ፣ ይሄ ሚሊሻ ነው ' የሚል ክርክር በሽማግሌ ደረጃ ከተነሳ ወደ ህዝብ ተወስዶ ህዝቡ እራሱ ይፈርዳል ሲሉ ተናግረዋል።

" እንግዳ ሰው ሲገባ ይታወቃል ይህ ጉዳይ አሳሳቢ አይደለም " ያሉት አዛዡ ፥ ገጠር ይሁን ከተማ መሬት ከሌላቸው / ሊገቡበት የሚችሉበት ቤት ከሌላቸው ተለይቶ ይታወቃል ብለዋል።

#Ethiopia
#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ  ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#HoPR

" ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦

" ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ።

ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና ለመዋጋት ብሔራዊ የጸረሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ብንሰማም አርቂ ስራ ሲሰራም ሆነ በሙስና ምክንያት ያንዣበበውን ሀገራዊ አደጋ ለመቀልበስ እርባና ያለው ስራ ሲሰራ አልታየም።

በአጠቃላይ መንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ይሄ ነው የሚባል መፍትሄ እየሰጠ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም ላይ ጥያቄ ይነሳል።

ምክንያቱም የህዝብ እና የመንግስት ሀብት በዘረፉ ሙሰኛ ባለስልጣናት ላይ መቀጣጫ የሚሆን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ተጨማሪ ሹመት እና የቦታ ዝውውር በመስጠት መንግስት ሙሰኞችን አብሮ አቅፎ ይኖራል ማለት ይቻላል።

ከዚህ የተነሳ ፦

የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል።

ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል።

ዜጎች የዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በአደባባይ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው።

ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከሀገር ወጥቶ እየሸሸ ነው።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት እያባከኑ ነው።

በኦዲት ሪፖርት መሰረት በየመ/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ይታያል።

መ/ቤቶች ገንዘብ ያለማስረጃ ወጪ በማድረግ ይጠቀማሉ ፣ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ በወጪ ይመዘግባሉ፣ ከፋይናንስ መመሪያና ደንብ ውጭ የገንዘብ ክፍያ ይፈጸማል።

እንደሚታወቀው ብዙ ሀገራት ለችግሩ በሰጡት ትኩረት የማያወላውል እርምጃ ስለወሰዱ ችግሩን ማቃለል ችለዋል።

ለምሳሌ በቅርቡ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ለልምድ ልውውጥ የጎበኟቸው የእስያ ሀገራት እነ ሲንጋፖር ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ስንመለከት ለእድገታቸው ዋናው መሰረት በሙስና ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ነው።

በሀገራችን የሌብነት ችግር ለመቅረፍ አፋጣኝ እና አስተማሪ የሚሆን እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር የጸረ ሙስና ህጋችንን አሻሽለን ቢሆን በሀገራችን አሁን የምናያቸው ፈተናዎች ተደምረው ሙስና የሀገራችንን ህልውና መፈተኑ አይቀርም።

ክቡር ጠ/ሚኒስትር በህዝቡ የሚቀርበው ተደጋጋሚ ቅሬታና የጄነራል ኦዲተር መ/ቤት በማስረጃ አስደግፎ ያቀረበልን ስር የሰደደ የሙስናን ችግር ለመቅረፍ መንግስትዎ ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ?

በተደጋጋሚ እንደታዘብነው ቃል ከመግባት ባለፈ ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቧል ?

ህዝቡስ ከመንግስትዎ ምን ይጠብቅ ? "

#Ethiopia

@tikvahethiopia