TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነዳጅ #Update

ወደ ትግራይ ክልል #ነዳጅ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፤ ወደ መቐለ 10 ቦቴ ነዳጅ መግባቱን ያመለከተ ሲሆን ወደ ኩዊኃ እና ዓጉላም ነዳጅ መግባት መጀመሩን ጠቁሟል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጥሩ ትብብር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮ " እናተ ጋር ካለው ችግር አንፃር ቅድሚያ እንሰጣለን " ተብለናል ሲል ገልጿል።

ጦርነት ለመፈጠሩ በፊት በወር 12 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ይገባ እንደነበር የገለፀው ቢሮው አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ ከሚፈለገው አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ብሏል።

መቐለ ውስጥ ካሉት 15 ማደያዎች ነዳጅ የገባው በ4ቱ ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ነዳጅ ለማግኘት እነማን ቅድሚያ አላቸው ?

አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ በተወሰነ መልኩ ስለሆነ ፦

- አምቡላንስ
- እሳት አደጋ
- ውሃ አቅራቢ ቦቴዎች
- የመንግስት ተሽከርካሪዎች
- የእርዳታ አከፋፋይ አካላት
- ባንክ፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል
- በትራንስፖርት ቢሮ ታሪፍ የወጣላቸው ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቅድሚያ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

የፋይናንስ እጥረት በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን ያሳወቀው ቢሮው ችግሩን ለማፍታት ከባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቤንዚን እና ናፍጣ ስንት እየተሸጠ ነው ?

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከፌዴራል መንግስት ለክልሉ እንደተላከ ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ #ቤንዚን በሊትር 60 ብር ከ57 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን #ናፍጣ 66 ብር ከ58 ሳንቲም እየተሸጠ መሆኑን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit : Tigrai Television

@tikvahethiopia
በደቡብ ክልል፤ ወላይታ ዞን ዉስጥ በጤና ስርዓት ላይ ያለው ችግር እንዲፈታ የፌደራል መንግስት አስቸኳይ የእርምት እርምጃ ይውሰድ ሲሉ የጤና ባለሞያዎች ጠየቁ።

ባለሞያዎቹ ይህን የጠየቁት ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የጤና ባለሞያዎች፤ በዞኑ የጤና ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች ቸልተኝነት የተነሳ የህክምናዉን አገልግሎት እንደ ሌሎች አካባቢዎች ግዜዉን የሚመጥን አልሆነም ብለዋል።

ባለሞያዎቹ እንደሚሉት የደንገተኛ ቀዶ ህክምና ከአንድ ሆስፒታል (ኦቶና) ዉጭ ማግኘት የማይታሰብ ሆኗል።

መድኃኒት፣ የምርመራ መሳሪያ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ የለም የሚሉት ባለሞያዎቹ፤ ባልተሰራ ነገር "የዉሸት ሪፖርት" እንድናቀርብም እንገደዳለን ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላው ባለሙያዎች የሰሩበት #ደመወዝ እና #ጥቅማጥቅም ባለማግኘታቸዉ ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዞኑ የተለያዩ ሆስፒታሎች የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ ስራ ለመስራት ስለመቸገራቸውም አስረድተዋል።

ያለውን ችግር ለበላይ አካላትና ለሚዲያ እንዳይገለፅ ጫና እንደሚደርስ እንዳንድ ባለሞያዎችንም እስከ ማሰር የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።

በዞኑ የፋይናንስ ችግር ሳይሆን የመልካም አስተዳደር ችግር ጎልቶ እንደሚታይ አሳውቀዋል።

የጤና ሚኒስቴር፤በዞኑ የሚታየው ችግር እንዲፈታ፣በተለይም በወላድ እናቶች ላይ እያደረሰ ያለው ችግር እንዲቀረፍ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በዞኑ አብዛኞቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ላይ ችግሩ አለ ያሉት የጤና ባለሞያዎቹ በዚህም ስራ መስተጓጎሉን አመልክተዋል።

ስለጉዳዩ ከዞን ጤና መምሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ ለማግኘት ለአንድ አመራር ስልክ ብንደውልም ስልኩ አልተነሳም።

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሲሚንቶ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በልሁ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ስለሆነው የሲሚንቶ ስርጭትና ግብይት መመሪያ ምንድነው ያሉት ? አቶ ተሻለ በልሁ ፦ " ... አዲሱ መመሪያ አንደኛ የቀየረው ሲሚንቶ በገበያ ስርዓት ይመራ ነው። በገበያ የሚመራ ሲባል ምን ማለት ነው አከፋፋዮቻቸውን ፤ ቸርቻሪዎቻቸውን የመምረጥ ነፃነት #የፋብሪካዎች ነው። እስከዛሬ ማን ነበር የሚመርጥላቸው ?…
መመሪያ ቁጥር 940/2015

የሲሚንቶ #ግብይት እና #ስርጭትን ለመቆጣጠር የወጣው መመሪያ ቁጥር 908/2014 ተሽሮ መመሪያ ቁጥር 940/2015 መፅደቁ ታውቋል።

አዲሱ መመሪያ ምን ይላል ?

- በኬላዎች አከባቢ ሲሚንቶ ምርት ላይ የሚደረግ ማንኛውም ቁጥጥር ተነስቷል።

- ቸርቻሪዎችን እና አከፋፋዮችን መምረጥ የፋብሪካዎች ሃላፊነት እንዲሆን ተደርጓል።

- ያለደረሰኝ ምንም አይነት ግብይት እንዳይካሄድ ተደርጓል።

- ከፋብሪካዎች የሚወጣ ማንኛውም የሲሚንቶ ምርት በቂ ሰነድ ሊኖረው ይገባል።

ይኸው መመሪያ የሲሚንቶ ጅምላ እና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ግዴታ እንዳለባቸው የሚደነገግ ሲሆን ግዴታዎቹም ፦

👉 የሲሚንቶ ጅምላ ነጋዴ ሲሚንቶ የሚገዛውን ቸርቻሪ ድርጅት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመመዝገብ በህጋዊ የረሰኝ ሽያጭ የማከናወን ግዴታ አለበት።

👉 በግዥ የተረከበውን ሲሚንቶ በተቀመጠው የዋጋ ጣሪያ መሠረት ለማንኛውም ተጠቃሚ የመሸጥ ግዴታ አለበት።

👉 ሲሚንቶን ከህጋዊ መስመር ውጭ አላግባብ አከማችቶ መያዝና ከተተመነው የዋጋ ጣሪያ በላይ ያለመሸጥ ግዴታ አለበት።

👉 የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴ የያዘውን የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በንግድ  መደብሩ በግልፅ በሚታይ ቦታ ላይ የመለጠፍ ግዴታ አለበት።

👉 ማንኛውም ሲሚንቶ ገዢና ሻጭ የንግድ እንቅስቃሴውን መረጃ በአግባቡ የመያዝ እና  በተቆጣጣሪ አካላት ሲጠየቅም የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጉዳዩ እንዲህ ነው ፦ የአቶ ሙላቱ ጉጆ የወንድሙ ልጅ በሁላ ወረዳ ጫልቤሳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አግብታ ሄዳለች። በሲዳማ ባህል መሰረት ሴት ልጅ አግብታ ከአከባቢ ከሄደች በኃላ የልጅቷ ቤተሰብ የዘመድ ልጆችን እና የልጅቷን ጓደኞች ሰብስቦ የተዳረችውን ልጅ ጥየቃ ፤ የሚበላ ነገር አስይዞ ይልካል። በዚህ መሰረት የአቶ ሙላቱ ጉጆ ልጅ የአጓቷ ልጅ አግብታ ወደሄደችበት በቀን 11/03/15 ዓ.ም ከቤተሰብ…
#Update

15 ዓመት ተፈርዶበታል !

ከሁለት ሳምንት በፊት በሲዳማ ክልል ፤ " የሁላ ወረዳ ፍርድ ቤት " አንዲት የ13 አመት ታዳጊን የደፈረ ግለሰብ ላይ የ3 አመት ከ9 ወር የፍርድ ውሳኔ መስጠቱ #ብዙዎችን_ያስቆጣ እንደነበር አይዘነጋም።

የተበዳይ ቤተሰቦች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ባንሳ አከባቢ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ዛሬ ጥር 3 ቀን 2015 በይርጋለም የቀረበውን አቤቱታ በመመርመር የቀድሞውን ውሳኔ በመሻር አጥፊው በ15 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ማስታወሻ : https://t.me/tikvahethiopia/75508

Credit : Ermias Elias (HO)

@tikvahethiopia
የ17 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የአራት አመቷን ህጻን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በአማራ ክልል ፤ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ 018 ቀበሌ ንዋሪ የሆነው ክንድየ ግዛቸው የተባለ ግለሰብ ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ/ም የዚሁ ቀበሌ ንዋሪ የሆነች  የ4 ዓመት ህጻን ከምትጫወትበት ቦታ አታሎ ወደ ጫካ ውስጥ ካስገባት በኋላ ደፍሯት ለመሰወር ይሞክራል።

ምንም እንኳን ግለሰቡ ለመሰወር ቢሞክርም የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፀጥታ ኃይል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ተጣርቶበት መዝገቡ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ይላካል።

ጉዳዩን የተመለከተው የጎንቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማረጋገጡ ዛሬ ጥር 3 ቀን 2015    ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ክንድየ ግዛቸው በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

የተደፈረችው ህጻን ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰባት በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በባህር ዳር ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላት እንደሚገኝ ታውቋል።

ምንጭ፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዛሬ ረቡዕ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ተመርቋል።

ስለ ማዕከሉ ምን ይታወቃል ?

- ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የተገነባ ነው።

- የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

- የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።

-  የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ 25 ወራትን  ፈጅቷል።

- ማዕከሉ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን፣ የመረጃ፣ የላብራቶሪ፣ የስልጠና ፣ የኮንፈረንስ ማዕከል ፣ ቢሮዎች እና አፓርትመንቶች አሉት።

- የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ (አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች) እየተካሄደ ነው።

- ማዕከሉ በቅርቡ ሙሉ ስራው ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል።

- በግንባታው ላይ #ቻይናውያንና #ኢትዮጵያውያን የህንፃ ባለሞያዎች እየተሳተፉበት ነው።

Info : ENA
Photo Credit : Tesfaye Wube (Tikvah Family)

@tikvahethiopia