TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ልዑካን ቡድኑ በሰላም መቐለ ደርሷል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዜዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተመራው የትግራይ ተወላጅ አትሌቶችን ያቀፈው የልዑካን ቡድን መቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ደርሷል። Photo Credit : Demtsi Woyane @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን 2 ሚሊዮን ብር አበረከተ።

ዛሬ መቐለ የገቡት የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና በእሷ የተመራው ልዑካን ቡድን ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር እና ከሌሎች የትግራይ ክልል አስተዳደር አካላት ጋር ተገናኝቶ ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉቱ ለትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን 2 ሚሊዮን ብር አበርክተዋል።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
#ዱቤ_አለ

ዳሽን ባንክ በተራዘመ የክፍያ ጊዜ ግብይት መፈጸሚያ መተግበሪያ ይፋ አደረገ።

ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር "ዱቤ አለ" የተሰኘ ተለምዷዊውን ዱቤ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የሚያቀርብ መተግበሪያ በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ በይፋ አስመርቋል።

"ይህ ዱቤ" አለ የተሰኘው ይህ መተግበሪያ የዳሽን ባንክ ደንበኛ የሆኑ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ተገልጋዮች ከሚሰሩበት መስሪያቤት ቤት ስለ ሥራቸውና ደሞወዛቸው የሚገልጽ ደብዳቤ በማጻፍ ተመጣጣኝ ብድር የሚያገኙበት ዘዴ ነው።

በተመሳሳይ በግል ሥራ የሚተዳደሩ ደግሞ ንግድ ፈቃዳቸውና ህጋዊ የገቢ ማስረጃዎችን በማቅረብ ዱቤ ማግኘት ይችላሉ። ለዚህም ተገልጋዮች በአቅራቢያቸው በሚገኝ ዳሽን ባንክ በማመልከት ተጠቃሚ መሆን ያስችላቸዋል።

ተገልጋዮች ዛሬ ለሚገዙት እቃ የአገልግሎት ክፍያውን በ3 ወር፣ በ6ወር፣ በ12 ወር መክፈል የሚችሉ ሲሆን ለዚህም ላገኙት የእፎይታ ጊዜም ተመጣጣኝ ክፍያ የሚከፍሉ ይሆናል። በተጨማሪም አገልግሎቱ ከሞባይል መተግበሪያ በተጨማሪ በስልክ ቁጥራቸውና በሚሰጣቸው DubeAle ID መሰረት መጠቀም ይችላሉ።

ይህ አገልግሎት ለየት የሚያደርገው ተጠቃሚዎች ለሚያገኙት የዱቤ አገልግሎት የሚፈልጉትን አገልግሎት ይሸምቱበታል እንጂ በጥሬ ገንዘብ መቀየር ወይም ገንዘብ ወጪ ማድረግ አይቻልም።

ይህ መተግበሪያ ከተጠቃሚዎች በተጨማሪ ማንኛውም አገልግሎት አቅራቢዎች ሰጪዎች ተመዝግበው ምርትና አገልግሎታቸውን መሸጥ ይችላሉ ተብሏል።

ባንኩ ለእያንዳንዱ ደንበኞች የዱቤ ገደብ (Spending Limit) የሚያስቀምጥ ሲሆን በዚህ መሰረት ለጊዜው የተፈቀደው የዱቤ ጣሪያ እስከ 700,000 ብር መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 27 ቀን 2015 እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ ፈረመዋል።

ስምምነቱ ዋነኛው ተግባር ምንድነው ? ፋይዳውስ ? ስለ ስምምነቱስ በጋራ ምን አሉ ?

" የትብብር ስምምነቱ ፓርቲዎቻችን በሚከተሉት አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራና በትብብር እንዲሠሩ ማዕቀፋዊና ሞራላዊ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡

በሀገራዊ መግባባት፣ በምርጫ፣ በሰላም ማስፈን እና መሰል ጉዳዮች  ላይ የጋራ አቋሞችን በማራመድ #በሰላማዊ_መንገድ በትብብር #እንታገላለን፡፡

በተለይ በየዕለቱ ለሚሞተው እና በድርሱልኝ ሲቃ ለሚቃትተው ወገናችን ድምጽ በመሆን ከገባበት ችግር እንዲላቀቅ መሥራት ከግንባር ቀደም ተግባሮቻችን ዋናው ነው፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" እናቴን አላገኘኋትም " - አሠልጣኝ ኃይለ ኢያሱ

ዛሬ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ወደ #መቐለ ከተጓዘው የትግራይ ተወላጆችን ያቀፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት መካከል የአትሌት ለተሰንበት ግደይ አሰልጣኝ ኃይለ ኢያሱ አንዱ ነው።

አሰልጣኙ ከ2 ዓመት መለያየት በኋላ ዛሬ ከቤተሰቦቹ ጋራ መተያየቱን የገለፀ ሲሆን እናቱን ግን በህይወት እንዳላገኛቸው ገልጿል።

" #ሰላም_ያመጡ ሰዎችን አመሰግናቸዋለሁ " ያለው አሰልጣኝ ኃይለ ኢያሱ " ወደ ሀገሬ በመምጣቴም በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። ሆኖም #እናት እና ሀገር አንድ ናቸው። ባጋጠመው ሊሆን በማይገባው ሁኔታ #በመድኃኒት_እጦት ምክንያት ሕይወቷ ማለፉን ነግረውኛል " ሲል ለቪኦኤ ሬድዮ ተናግሯል።

Credit : ቪኦኤ

@tikvahethiopia
40/60 የንግድ ቤቶች ጨረታ !

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የከተማ አስተዳደሩ በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸውን 5,397 በጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚፈልግ ዛሬ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 3/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 6/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

የት ነው የጨረታው ሰንድ የሚገዛው ?

- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ
- ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4
- የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ
- የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ
- 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት
- 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት

የጨረታ ሳጥን የካቲት 6/2015 ከቀኑ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ የካቲት7/2015 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደሚያገኙም ከኮርፖሬሽኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የፌዴራል መንግስት እና ህወሃት በስምምነቱ መሰረት የከባድ መሳሪያዎችን  መረካከብ ጀምረዋል።

በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት አመራሮች መካከል በደቡብ አፍሪካ እና በኬኒያ የተደረሰዉን ስምምነት ተከትሎ በትላንትናዉ ዕለት የመጀመሪያ ዙር ከባድ መሳሪያ ርክክብ መደረጉ ተገልጿል።

ርክክቡ ከመቐለ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አጉላ ካምፕ የተከናወነ ሲሆን በርክክቡ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ ታዛቢዎች ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

በቀጠናው የተሰማራው የሰራዊት አመራር ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለ ፤ " በመንግስታችንና በህዋሃት አመራሮች መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የተለያዩ ዓይነት ከባድ መሳሪያዎችን ተረክበናል " ብለዋል።

ህወሃት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያስረከባቸዉ የመሳሪያ ዓይነቶች፦

-  ብረት ለበስ ታንኮች፤
- የተለያዩ ሚሊ ሜትር መድፎች፤
- ሮኬቶች፤
- ዙዎች፤
- ሞርተሮች እና ፐምፐን ያጠቃለለ መሆኑን ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለ ተናግረዋል፡፡

የርክክብ ስነ-ስርዓቱን ለመታዘብ የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ አረካካቢ ኮሚቴዎች የተገኙ ሲሆን ከአረካካቢዎች መካከል ብርጋዴር ጄኔራል አድዋ ልቡካን ፒተር በሁለቱም ወገኖች በኩል እየተደረገ ያለዉ የከባድ መሳሪያ ርክክብ የተጀመረዉን የሰላም ጉዞ የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

" በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐፕሊክ መንግስትና በህወሃት  መካከል የተደረሰው ሰላምን የማስፈን ተግባር ዓለምን የሚስደንቅ ስለሆነ ለመላው ህዝብና ስምምነቱን ተግባራዊ እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋናዬን አቀርባለሁ " ብለዋል፡፡

Credit : የሀገር መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የፌዴራል መንግስት እና ህወሃት በስምምነቱ መሰረት የከባድ መሳሪያዎችን  መረካከብ ጀምረዋል። በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት አመራሮች መካከል በደቡብ አፍሪካ እና በኬኒያ የተደረሰዉን ስምምነት ተከትሎ በትላንትናዉ ዕለት የመጀመሪያ ዙር ከባድ መሳሪያ ርክክብ መደረጉ ተገልጿል። ርክክቡ ከመቐለ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አጉላ ካምፕ የተከናወነ ሲሆን በርክክቡ የተለያዩ ሀገራት…
ስለ ከባድ መሳሪያ ርክክብ ማን ምን አለ ?

የትግራይ ኃይሎች ተወካይ የሆኑት ሙልጌታ ገብረክርስቶስ ፦

"  በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት መሬት ላይ ወርዶ ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው ትጥቅ የመፍታት ሂደት በይፋ ተጀምሯል።

በዓጉላ ተከማችቶ የነበረውን የከባድ መሳሪያ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ተግባራዊ አድርገነዋል።

ሰላማዊ የሆነ የርክክብ እና የመተጋጋዝ ሂደት ነበር። ወደፊትም ይሄ ትጥቅ የመፍታት ሂደት በሌሎችም ካምፖች ተጠናክሮ ይቀጥላል። "

የሀገር መከላከያ ተወካይ ኮሎኔል አለሜ ታደለ ፦

" የተለያዩ ሀገራት ሳይሆን አንዲት ኢትዮጵያ ነን። ከዚህ በመነሳት ሁለቱም የታጠቀው ኃይል የጋራ ስምምነት አድርጎ ትጥቆች መፈታት አለበት ብሎ በውሉ መሰረት በተግባባነው መሰረት እኛም ካለንበት የመከላከል ቀጠና ፤ ቲዲኤፍም (TDF) ምሽግ ከያዘበት በሰላም ፣ በመግባባት፣  በፍቅር ወደ ዓጉላ መጥተናል።

በዓጉላ የከባድ መሳሪያዎች በተሰበሰቡበት ቦታዎች ተገናኝተን ትጥቆችን ቆጥረን ተረክበናል።

የከባድ መሳሪያዎችን ትጥቆች ስንረከብ ዝርዝር ሁኔታዎችንና የቴክኒክ ሁኔታዎችን ቀጣይ የምናያቸውና የምናረጋግጣቸው ይሆናል፤ ሆኖም ግን በውላችን መሰረት ትጥቁን በሰላም ፣ በፍቅር ከቲዲኤፍ (TDF) ተወካዮች ተረክበናል። የአፍሪካ ህብረቶችም በሰላም አስረክበውናል።

እኛ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማናቸውም ጊዜ ለህዝብ እስከቆምን ድረስ የትግራይም ህዝብ ህዝባችን ነው ሌላውም ህዝብ ህዝባችን ነው በሰላም በጋራ ከዚህ በፊት እንደነበርነው አብረን ሰላማችንን ጠብቀን አብረን የመኖርና አብረን የማደግ ፣ አብረን የመበልፀግ አንድ ህዝብ እስከሆንን ድረስ በፍቅር ተባብረን ሰላማችንን መጠበቅ አለብን። "

@tikvahethiopia