TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.1K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

በ “ብሩህ ንግድ ፈጠራ ሀሳብ ” ውድድር ከተመዘገቡ 1,375 ተሳታፊዎች መካከል 150 አሸናፊዎች 2 ሺህ ዶላር ለሚያሸልመው ለመጨረሻው ዙር ውድድር መለየታቸው ተነግሯል።

እነዚህ 150 ተወዳዳሪዎች መካከል በአንድ ማዕከል ሆነው በቀጣዮቹ ቀናት ስልጠና ይወስዳሉ።

ከ150ዎቹ ተወዳዳሪዎች መከካል በፈጠራ ሃሳባቸው ለሚያሸንፉ 50 ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው 2 ሺሕ ዶላር እንደሚሸለሙ ተመላክቷል፡፡

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-26

@tikvahethiopia
#Mpox #Ethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተገኝቷል ?

“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” - ጤና ሚኒስቴር

ኦክስፋም ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የተጠረጠረ ኬዝ መገኘቱን የሚያሳይ አጭር ሪፖርት ትላንት ይፋ አድርጎ ነበር፡፡

ሌላ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ድርጅትም እዛ ካሉ ሰዎቹ የበሽታው ኬዝ በሶማሌ ክልል መገኘቱን እንደሰማ ገልጿል።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሶማሌ ክልል ባለስልጣን ግን " ምንም የተገኘ ነገር የለም ውሸት ነው ያወጡት ሪፖርት " ብለውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ እውነት ተከስቷል ? የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት ሞክሯል፡፡

ጤና ሚኒስቴርንም በሽታው ወደ ሀገራችን ገብቷል እንዴ ? ሲል ጠይቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ደረጀ ጉዱማ (ዶ/ር) በሰጡን ምላሽ፣ “ አላጋጠመም፡፡ ያው ለነገሩ ትላንትም አረጋግጠን ነበር፤ ሰዎቹ (ኦክስፋም ኢትዮጵያን ማለታቸው ነው) የለጠፉትን እንዲያነሱ እያደረኩ ነበር፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” ሲሉ ገልጸውልናል፡፡

“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው፡፡ በእርግጥ ይመሳሰላል ሲምፕተማቸው፡፡ እንደ ቤተሰብ ሀፕን ያደረገ ነው፡፡ ኦረዲ ሌሎቹም ሪከቨር ስላደረጉ ሳምፕልም ወስደን ቼክ አድርገናል ሞንኪይፖክስ አይደለም ” ነው ያሉት፡፡

“ ቺክንፖክስ የሚባል አለ ፤ ሌላ በሽታ አለ ቀለል ያለ፡፡ ይህ ብዙ ቦታዎች አለ፤ ሰሞኑን ይሄኛው ስለተነገረ፣ ሰው ሲጠራጠር ቁስል፣ ቀላል የቆዳ ኢንፌክሽን እየመጣ ስለሆነ ከጥርጣሬ የተነሳ ነው ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“ በእርግጥ ጥሩ ነው እንደዛ መሆኑ ግን ውዢምብርም ሊፈጠር ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ፣ ፖስት እንዳታደርጉ ሚኒስቴሩ ነው ፖስት ማድረግ ያለበት ቼክ አድርጎ ከተፈጠረም፡፡ ሰስፔክትም አይባልም፡፡ ሰስፔክት በራሱ የራሱ ደፊኔሽን አለው ” ብለዋል፡፡

ቺክንፖክስ ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ ነው እንዴ ? ስንል የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከ100 በላይ ተመሳሳይ ምልክቶች ያሏቸው የቆዳ ኢንፌክሽኖች፣ ሌሎችም ኢንፌክሽኖች አሉ ” ብለዋል፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ ደረጃ ተከስቷል ? አልተከሰተም ? ለህዝቡስ ምን የጥንቃቄ መልዕክት ታስተላልፋለችሁ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ምንም ነገር የለም በርካታ ሳምፕሎችን ወስደን ቴስት አድርገናል፡፡ የእኛ ልጆች በየክልልም እየወረዱ በሁሉ ቦታ ላይ ሩመር ሲነሳ ያያሉ፡፡ ኢንቨስቲጌት ያደርጋሉ፡፡ ሳምፕል ይወስዳሉ፡፡ ሳምፕሉ ወደ እኛ ወደ ላብራቶሪ ይላክል፡፡ በርካታ ቴስቶች አድረገናል፡፡ ግን ምንም የለም ኔጌቲቭ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“ ኤርፖርት ላይ ሥራችንን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የተያዩ ምልክቶችን እናያለን በተለይ ትኩሳት ያላቸውን ሰዎች እንለያለን፡፡ የትኛውም ቆዳቸው እብጠት ካለ እያረጋገጥን  እንገኛለን ” ብለዋል፡፡

“ ማህበረሰቡ ግን ይህን አይነት ምልክት ካለ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን በተለይ ለጤና ተቋማት ሪፖርት እንዲያደርግ ነው የሚጠበቀው፡፡ እንደዛ አይነት ሰው ካለ ደግሞ ንክኪ እንዳይኖር ጥንቃቄ  ማድረግ፡፡ ንክኪም ካለ ቶሎ በአግባቡ እጅን መታጠብ፣ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ከጤና ሚኒስቴር ጠይቆ ባዘጋጀበት ሰዓት ኦክስፋም ኢትዮጵያ " በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠረ ኬዝ ተገኝቷል  " የሚለውን መረጃ ከገጹ ላይ አጥፍቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹

" በዝምታ አንመለከትም " - ኢትዮጵያ

በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በቀጣይ የሚኖረው አዲስ የሰላም ተልዕኮ አወቃቀር ሁኔታ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ አዲስ ስጋት ይዞ መምጣቱ ኢትዮጵያን እንዳሳሰባት አሳውቃለች።

" የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዚሁ አዲስ ሽግግር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፣ ቀጠናው ሊተነበይ ወደማይቻል ፈተና ውስጥ እየገባ ይገኛል"ም ብላለች።

በሁኔታው ላይ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ ወታደር ያዋጡ አገሮች ተደጋጋሚ ጥሪዎችና አስተያየቶች ትኩረት እንዳልተሰጣቸው አስገንዝባለች።

" የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት መልካም ስምና ዝናን እንዲሁም መስዋዕትነት የሚያጠለሹ ተከታታይ መግለጫዎች ሲወጡ ኢትዮጵያ በዝምታ እንድታልፍ ከአንዳንድ ወገኖች በኩል ፍላጎት መኖሩ ይታያል " ብላለች።

ሌሎች ተዋናዮች የአፍሪካ ቀንድ ክልልን ለማተራመስ እርምጃ ሲወስዱ ኢትዮጵያ በዝምታ እንደማትመለከት አሳውቃለች።

ይህም በመሆኑ በቀጣናው የብሄራዊ ደህንነቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ሁሉ በንቃት እየተከታተለች እንደሆነም አመልክታለች።

የሶማሊያ መንግስት በቀጠናው ሰላም ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች ከማጠናከር ይልቅ ቀጠናውን ለማተራመስ ከሚሹ የውጭ ኃይሎች ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ አጽንኦት ሰጥታ ገልጻለች።

በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደውን አዲስ የሰላም ተልዕኮ የማዘጋጀትና የመፍቀድ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ሁሉ በቀጠናው የሚገኙና ቀደም ሲል ወታደር አዋጭ የሆኑ አገራትን ተገቢ የሆኑ ስጋቶች ሁሉ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ብላለች።

ኢትዮጵያ ፥ " ለአጭር ጊዜ ፍላጎታቸውና ከንቱ አላማቸው ሲሉ በክልሉ ውጥረትን ለማቀጣጠል የሚሞክሩ ኃይሎች ዕኩይ ተግባራቸው የሚያስከትሏቸዉን መዘዞች መሸከም ይኖርባቸዋል " ብላለች።

ቀደም ሲል አህጉራዊና አለምአቀፋዊ አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን አበረታች ውጤት አደጋ ላይ የሚጥሉና የሚቀለብሱ ድርጊቶችን እንደማትታገስ ተናግራለች።

ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ከሶማሊያ ህዝብና ከአለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል አሁንም ቁርጠኛ አቋም እንዳላት አመልክታለች።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GRED🇪🇹 የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 3ኛው እና 4ኛውን ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሳውቀዋል። " ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉም " ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል " ብለው " የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA #GERD 🇪🇹

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መስሪያ ቤት ምን አለ ?

(ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት / አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የሰጠው ቃል)

- በቅርቡ 2 የግድቡ ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸው ከግድቡ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል።

- ከዚሕ ቀደም ብሎ ሥራ የጀመሩ ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ።

- ከሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫሉ።

- ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከ5 ሺሕ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

- የግድቡ ግንባታ አሁን ወደ መጠናቀቁ ነው።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት እና ብዙ ቢሊዮን ዶላር ያፈሰሰበት ግድብ ከአፍሪቃ ትልቁ የኃይል ማመነጫ ነው።

ቪድዮ ፦ PM OFFICE

#Ethiopia #AFP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #GERD 🇪🇹 የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መስሪያ ቤት ምን አለ ? (ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት / አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የሰጠው ቃል) - በቅርቡ 2 የግድቡ ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸው ከግድቡ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል። - ከዚሕ ቀደም ብሎ ሥራ የጀመሩ ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ።…
#GERD🇪🇹

ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ የላብና ደም አሻራ ያረፈበት የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ የአይን ብሌኑም ጭምር ነው።

ተማሪው ፣ ሰራተኛው ፣ ወጣቱ ፣ አዛውንቱ ለዚህ ግድብ ካለው ላይ ፤ ከሚበለው ቀንሶ ሰጥቶ ያሰራው ለትውልድ የሚያወርሰው ሀብቱና ቅርሱ ነው።

ይህ ግድብ ሀገር ውስጥ በየጊዜው በሚፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ሀዘን፣ መከፋት፣ መበደል ሲመጣ እንኳን ሁሉም የውስጡን በውስጡ ይዞ " ሀገሬ ትቅደም " ብሎ ተጠናቆ በአይኑ ለማየት ሲል ብዙ ዋጋ የከፈለለት ነው።

በፖለቲካ አቋም፣ በሃሳብ፣ በአመለካከት እየተለያየ እንኳ የሀገሩን ጥቅምና ግንድቡን የሚነካበት ነገር ሲመጣ ሁሉን ጥሎ ሽንጡን ገትሮ የተራከረለት ፣ እስከመጨረሻው ድረስም ዋጋ የሚከፍልለት ነው።

ይህ ግድብ ገና ከመሰረቱ እንዳይገነባ ፤ ድጋፍም እንዳይመጣ ሲሯሯጡ የነበሩ ብዙ ናቸው።

እንዳይሳካ ያልፈነቀሉት ድንጋይ ፤ ያልሄዱበት ቦታ የለም። ግን አልሆነም ፤ ወደፊትም አይሆንም።

ዛሬም እነዚህ አካላት ለኢትዮጵያ እንደማይተኙ ግን ግልጽ ነው።

ኢትዮጵያ " የሰው ድርሻ አንድም አልነካም፤ የራሴን ግን እጠቀማለሁ " ማለቷ የሚያንጨረጭራቸው ሀገራት በግንባታው ወቅት ዛቻ ሲያዘንቡ ፣ እንዲቆም ለማስፈራራት ሲሞክሩ ፣ በአንድም በሌላ በዓለም አቀፍ መድረክ በውስጥ እና በይፋ ጫና ለማድረግ ሲሰሩ እንደከረሙ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ብዙ ብዙ ቢሞክሩም መክነው ቀርተዋል። አሁንም ግን ጩኸታቸው እንደቀጠለ ነው።

ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረትም እንደዛው እንደቀጠለ ነው።

አንዴ " የመሬት መንቀጥቀጥ ቢመጣ አይፈርሳል " ፤ አንዴ " ጥራቱ አስተማማኝ አይደለም ይደረመሳል " ፤ አልሆን ሲላቸው " በአየር እንመታዋለን ፣በቦንብ እናጋየዋለን " በማለት ብዙ ሲያወሩ ከርመዋል።

ከወሬ የዘለል ግን ምንም ማድረግ አይችሉም።

እዛው ያሉበት ሆነው የፈለጉትን ማሰብ ይችላሉ ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እያለ ግን ማድረግ መንካት ግን ፈጽሞ አይቻልም።

#Ethiopia
#GERD
#TikvahEthiopia
#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የገንዘብ ሚኒስቴር ፥ በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ስለሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ ማብራሪያ ሰጥቷል።

አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመኖሪያ ቤቱ የሚጠቀመውን አማካይ ወርሃዊ የውሃና ኤሌክትሪክ ፍጆታ ከታክሱ ነፃ የሚያደርግ ሲሆን ከታክሱ ነፃ ከተደረገው በላይ የውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል።

የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆን መብት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር ከስምንት መቀመጫ በታች ያላቸውን ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንዳይመለከት ተደርጓል፡፡

አሁንም የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ ሲሆን ባለሦስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር፣ አሽከርካሪውን ጨምሮ ከስምንት ሰው በታች የመጫን አቅም ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በመጠቀም የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልበት መደረጉን ገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል።

(ሙሉ ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
❤️

ከአሜሪካ ሃገር በመጡ ሐኪሞች የልብ ሕክምና ተልዕኮ (Mission) አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የልብ ማዕከል-ኢትዮጵያ ውስጥ " ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ' በተሰኘ በአሜሪካን ሃገር በሚገኝ በዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶ/ር ኦብሲኔት መርዕድ የተመሰረተ የግብረ ሰናይ ድርጅት የነጻ የልብ ሕክምና ተልዕኮ አገልግሎት ከነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እየሰጠ ነው።

ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የሕክምና ተልዕኮ መርሐግብር ነው።

የሕክምና አገልግሎቱ ከማዕከሉ በተጨማሪም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ100 በላይ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ታካሚዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያቀደ ነው።

የሕክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከ17 በላይ የልብ ሕክምና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የጤና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ነው።

ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኦብሲኔት ፥ " በዚህ ዙር ደረት ሳይከፈት ከሚሰሩ ሕክምናዎች በተጨማሪ የልብ ቀዶ ሕክምና እና የልብ ምት ችግር ላለባቸው ሕሙማን የሚሰጡ ሕክምናዎች ተካተዋል " ብለዋል።

ድርጅቱ ለሕክምና ተልዕኮው ከ1.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሰባስቦ ነው ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነው የጠቆሙት።

ወደፊት ተጨማሪ ተልዕኮዎችን እንደሚያካሂድ አመልክተዋል።

የልብ ማዕከል ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኅሩይ ዓሊ ፥ " በዚህ የሕክምና ተልዕኮ ላይ በርካታ ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሕሙማን ተጠቃሚ ናቸው። " ያሉ ሲሆን " ተልዕኮው ስኬታማ እንዲሆን ማዕከሉ ከዝግጅት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ ሥራዎችን ሲሰራ ነበር ቆይቷል " ነው ያሉት።

#Ethiopia

@tikvahethiopia @thechfe
#ETHIOPIA🇪🇹

ከሰሞኑን በፔሩ፣ ሊማ ሲካሄድ በቆየ የዓለም ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ:- 
6️⃣ የወርቅ፣
2️⃣ የብር
2️⃣ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት ነው ከዓለም ሁለተኛ ከአፍሪካ ደግሞ #አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀችው።

Via @tikvahethsport   
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

የውጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን የብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የውጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አውጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል።

የውጪ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ በሰጡት ቃል ፥ የውጪ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ባንኩ ተቀብሏል።

" ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለው ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል ፤ ይህም በድፍረት የተደረገ ነው ማለት ይቻላል " ሲሉ እርምጃውን አድንቀውታል።

ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ በ100 ዶላር የውጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia