TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

መቼም በአዲስ አበባ ከተማ የመኪና በር ተከፍቶ በውስጥ የተቀመጠ ስልክ፣ ቦርሳ ሌሎችም እቃዎችን ሰዎች ሲዘረፉ ብዙ ሰምተን ሆናል።

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱ ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ " መገናኛ " አካባቢ ከመኪና ላይ ለመዝረፍ የሚደረገውን ሙከራ እና ወከባ የሚያሳይ ነው።

በአካባቢው የነበረ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል (ስም ጌድዮን) ሁኔታውን ሁሉ በቪድዮ ቀርፆ ልኮልናል ፤ የፋይሉ መብዛት ወደናት ለመላክ ቢያስቸግርም የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሳቸው ለማድረግ እንጥራለን፤ በግልፅ ሰዎቹም ስለሚታዩ።

መገናኛ አካባቢ ግን እጅግ ልዩ ትኩረት የሚፈልግ ቦታ ነው።

ለማንኛውም ውድ ቤተሰቦቻችን #ጥንቃቄ በየትኛውም አጋጣሚ የመኪና በር መቆለፋችሁን ለአፍታም ቢሆን አትዘንጉ።

ተጨማሪም ትላንት ጥዋት አንድ የቲክቫህ አባል ኢምፔሪያል አካባቢ ፦ በመኪና የነበሩ 4 ሰዎች አንድን መገደኛ አንቀው መሬት በማስተኛት ዝርፊያ ሲፈፅሙ እንደነበር በኃላም እሱ እንዳያቸው ሲያውቁ ከአራቱ አንደኛው መሳሪያ አውጥቶ እንዳሳየው በኃላም መኪናቸውን አስነስተው በፍጥነት ከአካባቢው መሸሻቸውን አጫውቶናል።

አዲስ አበባ ውስጥ በየጊዜው እየሰማን ያለውነው ዝርፊያ እጅግ የከፋ ነው። በግልፅ በቀን ሳይቀር ሰዎች ሲዘረፉ እየሰማን እንገኛለን።

የሚመለከታቸው አካላት የነዋሪዎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ማስጠበቅ ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰሩበት የሚገባ ሲሆን አጥፊዎችንም በተገቢው መንገድ ሌላውን በሚያስተምር ሁኔታ መቅጣት ይገባል ፤ የሚሰጡ ጥቆማዎችም ያለ ቸልታ መቀበል ይገባል ፤ አንዳንድ በፖሊስ ውስጥ ያሉ እና ኃላፊነታቸውን የማይወጡ አባላትንም መፈተሽ ይገባል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል። " ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች።…
#ድርድር

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በሰላም መቋጫ ያገኝ ዘንድ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም አንዳንድ የውጭ ሀገር ሚዲያዎች ድርድርን በተመለከተ በግልፅ ምንጫቸው የማይታወቁ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ከርመዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ንግግር አለመጀመሩን ነገር ግን ለዚሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል።

ትላንት ፓርላማ የቀረቡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ መሆኑን፤ እስካሁን ውጤቱን አለማሳወቁን እና የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ መሆኑን ጠቁመው ነበር። ድርድር ሲጀመር መንግስት የሚደብቀው ነገር እንደሌለም ገልፀው ነበር።

ይህ የጠቅላይ ሚስትሩ ንግግር ከተሰማ ብዙም ሳይቆይ በህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የተፃፈ ደብዳቤ ተሰራጭቷል።

ይኸው ደብዳቤ ህወሓት በኬንያ መንግስት በተጠራ ድርድር የሚሳተፍ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱን ይገልጻል።

ደብዳቤው በኬንያ መንግስት የተጠራ ድርድር #በናይሮቢ ስለመኖሩ ፍንጭ የሰጠ ነው።

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሰላም ድርድሮችን በማስመልከት የትግራይ ክልልን አቋምን ለማሳወቅ ደብዳቤውን የፃፉት ለአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበርና የሴናጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፣ ለኬንያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ፣ ለተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልናህያን እና ለታንዛኒያዋ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን እንዲሁም የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ነው።

ያንብቡ ; https://telegra.ph/Dr-Debretsion-GMicahel-06-15

@tikvahethiopia
#ሰከላ

በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰከላ ወረዳ ከፍተኛ በረዶ ቀላቀሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ምርት እና በአርሶ አደሮች መኖሪያ ቤት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

ጉዳቱ የደረሰው በቀን 6/10/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ስዓት ጀምሮ ያለማቋረጥ ከሁለት ሰዓት በላይ በጣለው በረዶ የቀለቀለ ከፍተኛ ዝናብ ነው።

በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል በባህር ዛፋ፤ በጅግሪታ በአምቢሲና በአባይ ቀበሌዎች የድንች ሰብል ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን ጉዳት በባህር ዛፋ ቀበሌ በአርሶ አደሮች መኖሪያ ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድንች፣ የገብስ፣ በመስኖ የለማና ያልደረሰ በቆሎ ላይም ጉዳት ደርሷል።

የጉዳቱ ሰለና አርሶ አደሮች መንግስት አቅም በፈቀደ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ከዞን እና ክልል ጋር በሚደረግ ግንኙነት ድጋፍ የሚገኝ ከሆነ አቅም የሌላቸው ተጎጂ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ብሏል።

መረጃው የሰከላ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ መቼም በአዲስ አበባ ከተማ የመኪና በር ተከፍቶ በውስጥ የተቀመጠ ስልክ፣ ቦርሳ ሌሎችም እቃዎችን ሰዎች ሲዘረፉ ብዙ ሰምተን ሆናል። ከላይ በፎቶው የምትመለከቱ ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ " መገናኛ " አካባቢ ከመኪና ላይ ለመዝረፍ የሚደረገውን ሙከራ እና ወከባ የሚያሳይ ነው። በአካባቢው የነበረ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል (ስም ጌድዮን) ሁኔታውን ሁሉ በቪድዮ ቀርፆ ልኮልናል ፤ የፋይሉ መብዛት ወደናት…
" አመሰግናለሁ "

ትላንት አንድ የአዲስ አበባ ቤተሰባችን አባል ከ24 ወጥቶ ወደ ኢምፔሪያል በሚወስደው መንገድ አንድ እግረኛን በመኪና የነበሩ 4 ሰዎች አንቀውት መሬት አስተኝተው ሲፈትሹት መመልከቱን ጥቆማ ሰጥቶ ነበር።

ምናልባት ይህ የዝርፊያ ተግባር የተፈፀመበት ወገናችን ታርጋውን ካላየው በሚልም ታርጋውን አጋርቶ ነበር።

ይህንንም ጥቆማ ተከትሎ አንድ የቤተሰባችን አባል ጥቃቱ የተፈጸመው በእርሱ ላይ መሆኑንና ዘራፊዎቹ ስልኩንና ዋሌት ቦርሳውን እንደወሰዱበት ገልጿል።

ይሄው የቤተሰባችን አባል ወንጀሉ የተፈጸመበትን የመኪና ተርጋ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጉን አስታውቋል።

ጥቆማውን ላደረሰው የቲክቫህ ቤተሰብ አባልም ምስጋና አቅርቧል።

መልዕክቶቻችን ማጋሪያ ፦ @tikvahethiopiaBOT

Via @tikvahethmagazine
#Alert🚨

በራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የተነሳውን እሳት መቆጣጠር አልተቻለም።

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ 016 ቀበሌ በተለምዶ ራስ ጠቆሮ እየተባለ በሚጠራ ጥብቅ ደን ላይ ሰኔ 6/2014 ሌሊት ጀምሮ የተከሰተው የእሳት አደጋን እስካሁን ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም።

በጥብቅ ደኑ ውስጥ ወይራ፣ ጥድ፣ ኮሶ፣ ዝግባና ሌሎች የደን ሐብቶች እንዲሁም የተለያዩ እንሰሳትና አዕዋፋት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ከመልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ አመቺ አለመሆን እና በደኑ ውስጥ ተቀጣጣይ ሳር ከመብዛቱ ጋር ተያይዞም የእሳት አደጋውን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገው ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤ በተመለከተ እሳቱ ከግለሰብ ማሳ ተነስቶ ወደ ደኑ እንደተዛመተ የአምባሰል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ለአንድ ዓመት ጊዜ ዝግጅት ተደርጎበታል የተባለው የመጀመሪያው የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ሰኔ 22 ይካሄዳል።

የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ሰኔ 22 በሚካሄደው መጀመሪያው ዙር የሽልማት መርሐግብር አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ጀምሮ እስከ ዓመት ከስምንት ወር ያሉ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎችን ለመሸለም የታቀደ መሆኑን ባለቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው ተናግረዋል።

ሰኔ 22 መርሐግብሩን ለማዘጋጀት የታቀደው ቀኑ አርቲስቱ የተገደለበት ዕለትና ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያውን ለማድረግ መሆኑን በመግለጫው ተገልጿል።

ሽልማቱ በአስር ዘርፎች የሚከናወን ሲሆን 70 በመቶ የዳኞች ድምጽ 30 በመቶ ከህዝብ በሚሰበሰብ ድምጽ አሸናፊዎቹ ይለያሉ ተብሏል።

የድምጽ መስጫው በዌብሳይቱ ለቀጣይ 2 ቀናት ይቆያል።

በቀጣይ ይህንን የሽልማት መርሐግብር በአፍሪካ ደረጃ ለማከናወን እቅድ መኖሩን ተገልጿል።

ይህ መርሐግብር ፋውንዴሽኑ የአርቲስቱን ሌጋሲ ለማስቀጠል ብሎ ከያዛቸው ሥራዎች አንዱ ነው።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ እና ከስዊድን ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ማቲልዳ ኧርንክራንስ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው ትኩረቱን ያደረገው ፦
- በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ስለሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ፣
- በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ ስለተወሰደው ተጠያቂነት እና መተማመን ለመፍጠር በመንግስት በተወሰዱ እርምጃዎች ዙሪያ
- በክላስተር በለማ የስንዴ እርሻ እና በከተማ ግብርና ዙሪያ እንደነበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

ዛሬ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ)
አመራር የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከታሰሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ክሱን ያቀረበውም የፌዴራል ፖሊስ መሆኑን የፓርቲው መረጃ ያመለክታል።

ፖሊስ አቶ ስንታየሁ ፤ ሕዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ ሲያሰራጩ እንደነበርም ጠቅሷል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው ባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ እየተዘጋጁ እንደነበር እና ጉባኤውን ለማደናቀፍ የደረገ ድርጊት ነው ፤ ውንጀላውም የፖለቲካ ተሳትፎ ተከትሎ የመጣ ፖለቲካዊ ጥቃት እንደሆነ ገልፀው ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ስንታየሁ ባሉበት መዝገብ ስር የቀድሞው የአማራ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን(አሥራት) ባልደረባ ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬ ፣ ዋሴ በመረሳው እና ደምስ አያሌው የተባሉ ወጣቶች ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባቸው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። እነሱም ሕዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ ሲያሰራጩ እንደነበርም ተጠቅሷል።

ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ 12 የምርመራ ቀናት በመፍቀድ ለሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

4ቱም ተከሳሾች ከየነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ ወደ ባሕር ዳር ሰባታሚት ወህኒ ቤት መወሰዳቸውን ባለደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦገት.pdf
የአፋር ባህላዊ እርቅ (1).pdf
267.3 KB
#2

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ !

የአፋር ህዝብ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት ፦

አዘጋጅ፦ ሩት ኃይሌ

- የአፋር ማህበረሰብ እንቅስቃሴው በዳጉ የተደገፈ ነው። ይህ ፈጣንና እውነተኛ የመረጃ ልውውጥ መንገድ በማህበረሰቡ የሚፈጠርን ችግር ወይም ግጭት በቶሎ ወደ ሽማግሌዎች እንዲደርስ ያስችላል፡፡

- በአፋር ባህላዊ እርቅ ውስጥ የፍትህ ማስከበርን ብቻ ሳይሆን የምንመለከተው ቀድመው ወደ ነበሩበት መልካሙ ግንኙነት እንዲመለሱ የሚረዳ የእርቅ ሥርአት መሆኑን ነው።

- በአፋር ማህበረሰብ የተለያዩ ጎሳዎች ቢኖሩም ነገር ግን የባህላዊዉ የዕርቅ ትግበራና ቅጣቶች ወይም የካሳ ክፍያዎች እንዲሁም ወደ ሽማግሌዎች ቀርበው የሚታዩት ግጭቶች ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው። ስያሜውም ከአንዱ ዞን ወደ ሌላ ዞን ስንሄድ የተለየ ነው።

በዚህ ጹሑፍ የተዳሰሱት የእርቅ ሥርዓቶች፦

#ቢሉ፡- ከፍተኛ ግጭት ወይም ነፍስ ማጥፋት የሚሸመገልበት ባህላዊ የእርቅ ስርአት ነው፡፡

#ኢረና፡- በዚህ ሽምግልና በሰው ልጅ በየእለት እንቅስቃሴ የሚገጥመውን ጨምሮ ስርቆትም በዚህ ይዳኛል።

#መብሎ፡- ከፍተኛ ግጭት ወይም ነፍስ ማጥፋት የሚሸመገልበት ባህላዊ የእርቅ ስርአት ነው፡፡ በዚህ የእርቅ ስርአት የሰው አብሱማ ማለትም ለሌላ የታጨችን ሴት ማግባት ከነፍስ ግድያ እኩል ነው የሚታየው የካሳ ክፍያውም ተመሳሳይ ነው፡፡

#ኢዶሊና፡- ይህ የእርቅ ሥርዓት ከኢረና ጋር ትግበራውም የቅጣቱም አይነቶች እንዲሁም ግጭቶቹ ተመሳሳይ ናቸው፡፡

- የባህላዊ የእርቅ መንገዳችን ከፍርድ እና ከካሰ ይልቅ ሰዎች ላይ ያተኮረ እና ግጭት ውስጥ የገቡት ሰዎች ቀድሞ ወደነበራቸው ሰላማዊ ግንኙነት እንዲመለሱ የሚሰራ የእርቅ መንገድ ነው። በተጓዳኝም ካሳ ክፍያን በመፈጸም ፍትህን ከሰላሙ ጎን ለጎን የሚሰራ ነው፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Gambella የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገለፁ። ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለፁት የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። " በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል " ያሉት አቶ ኡሞድ " በጥቃቱ በጠላት በኩል ከፍተኛ…
#Gambella | " ታጣቂዎቹ ከጋምቤላ ከተማ ውጭ ያሉ ቦታዎች ላይ ሊኖሩ ይችላሉ ፤ የት ቦታ ነው ያሉት የሚለውን ለማወቅ ጥናት እያደረግን ነው " - አቶ ኡጌቱ አዲንግ

ትላንት ታጣቂዎች ጋምቤላ ከተማን ለመቆጣጠር ጥቃት ከፍተው እንደነበር ነገር ግን በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ መክሸፉ ይታወቃል።

የክልሉ ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡጌቱ አዲንግ ለሪፖርተር በሰጡት ቃል ፤ የክልሉ መንግስት ታጣቂዎቹ በከተማው ጥቃት ለመክፈት ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆኑ መረጃ እንደነበረው ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የክልሉ ፀጥታ ም/ቤት ሰኞ 5 ቀን 2014 ግምገማ ማድረጉንና የክልሉ መንግሥት በመረጃው ላይ ተመሥርቶ ጥቃቱን ለመመከት የተቀናጀ የፀጥታ ኦፕሬሽን ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

" ጥቃት ለመፈጸም እንደተዘጋጁ መረጃ ነበረን፡፡ በዚህ መረጃ ነው ወደ ኦፕሬሽን የተገባው፡፡ ዞሮ ዞሮ [ወደ ከተማው] ገብቷል ግን ቢገባም መመለሻ እንደሌለው ነው የነበረን ውይይት " ብለዋል።

" ጋምቤላ ከተማን በሙሉ ለመቆጣጠር ሙከራ ቢያደርጉም በተደረገው ትግል ከተማው ነፃ ሆኗል " ያሉት ኃላፊው ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ በደረሰባቸው ጥቃት " በአንዳንድ ቦታዎች ተደብደቀው ወደ ቤቶች የገቡ " ታጣቂዎች በመኖራቸው የፀጥታ ኃይሉ ' ለቀማ ' ላይ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በንፁኃን ላይ ስለ ደረሰ ጉዳት በተመለከተ ፥ " ጦርነት ባለበት ሁሉ ሰው መሞቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በወታደርም በሲቪሊያን ላይም ችግር ደርሷል፡፡ ቁጥሩን ገና አላጣራንም ስናጣራ እናሳውቃለን " ብለዋል።

ታጣቂዎቹ በክልሉ ከከተማው ውጭ ያሉ ቦታዎች ላይ ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቅሰው " የት ቦታ ነው ያሉት የሚለውን ለማወቅ ጥናት እያደረግን ነው " ብለዋል ለጋዜጣው።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia