TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbiyAhmed ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። በአሁን ሰዓት በፀጥታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ነው። በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ መከታተል ይቻላል። ዋና ዋና ነጥቦችን ተከታትለን እናሳውቃለን። እስካሁን ድረስ ያነሷቸው ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸው (ከፀጥታ ጉዳዮች…
#ድርድር

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር።

ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል።

" ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች። ሕዝብ ሳያውቀው የሚደረግ ድርድር የለም። " ብለዋል።

አክለውም ፥ " በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ ሲሆን፣ እስካሁን ውጤቱን አላሳወቀም። የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ ነው። " ብለዋል።

" ውጊያ ሲመጣ ለሕዝብ አሳውቀን የጀመርን ሰዎች፣ ድርድር ከተጀመረ የሚያስደብቀን ነገር የለም። ነገር ግን፣ የብቻ ጠላት የለም የሀገር ጠላት እንጂ፣ ለብቻም የሚሰራ ሥራ የለም በጋራ እንጂ። " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የእኛም የሕዝባችንም ፍላጎት ለጥይት የሚወጣ ውጪ ለልማት እንዲወጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፦
- በፀጥታ ተቋማት ዝግጅት፣
- በህግ ማስከበር፣
- በ ' ተረኝነት ' ጉዳይ ፣
- በማህበራዊ ሚዲያዎች ጉዳይ ፣
- ሌብነትን በተመለከተ፣
- የብሄራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጧቸው ምላሽ እና ማብራሪያዎች በዚህ ታገኛላችሁ https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14-2 (#PMOEthiopia)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጋምቤላ ከተማ የተኩስ ልውውጡ መንግስት አሸባሪ ካለው ሸኔ ወታደሮች (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው) እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ጋር መሆኑን ክልሉ ገልጿል። " በጋምቤላ ከተማ ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ሲካሄድ ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት ከተማው መጠነኛ መረጋጋት ይታያል " ሲል ክልሉ ገልጿል። ክልሉ…
#Update #Gambella

የጋምቤላ ክልል ፤ ጋምቤላ ከተማን ማረጋጋት መቻሉን አሳወቀ።

ክልሉ ፥ " ተኩስ ከፍተው በነበሩ የሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ላይ በፀጥታ አካላት በተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ከተማዉን ማረጋጋት ተችሏል " ሲል አሳውቋል።

አክሎም በተወሰደዉ እርምጃ በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል ሲል አመልክቷል።

ክልሉ የከተማው ህብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት ለፀጥታ ሀይሉ እያደረገ ላለው ትብብር ምስጋና አቅርቧል።

በከተማው ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ያለማቋረጥ ለረጅም ሰዓት የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር አስታውሶ በአሁኑ ሰዓት ተቆርጠው የቀሩ የቡድኑ አካላትን የማጥራት ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድቷል።

" ታጣቂ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ በመንግስት ፀጥታ አካላት እየተወሰደ ያለዉ የማያዳግም እርምጃም ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲልም የክልሉ አስተዳደር አስታውቋል።

የደረሰው ጉዳት በቀጣይ እንደሚገለጽ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ከጋምቤላ መልዕክት የላኩ የቲክቫህ አባላት ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ በነበረው የተኩስ ልውውጥ በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸው በአይናቸው መመልከታቸውንና በአንዳንድ የከተማው ቦታ የሞቱ ሰዎች አስክሬን ይታይ እንደነበር አስረድተዋል። በመንግስት የፀጥታ ኃይል በኩል የሞት ስለመኖሩም መስማታቸውን ገልፀዋል።

በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት ግን ለጊዜው የሰሙት ነገር እንደሌላቸው አመልክተዋል።

ዛሬ በሆነው ደረጃ በከተማው የተኩስ ልውውጥ ሰምተው እንደማያውቁ የገለፁት የቤተሰብ አባላቶቻችን ታጣቂዎች ከተማ ድረስ እንኪደርሱ ቀደም ብሎ መከላከል ያልተቻለበት ሁኔታ ምርመራ ይፈልጋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gembi #Dmbidolo ዛሬ ከጋምቤላ በተጨማሪ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተማ ከማለዳ 12:30 ጀምሮ በጣም የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ነዋሪውም በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ እንደሆነ የጊምቢ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል። በሌላ ደምቢዶሎ ከተማ ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ ከባድ የተባለ ተኩስ ልውውጥ እንደነበር የቲክቫህ ደምቢ ዶሎ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል። የተኩስ ልውውጡ መንግስት ሽብርተኛ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

ጊምቢ ጥዋት የጀመረ የተኩስ ልውውጥ አሁንም ድረስ መቀጠሉን የጊምቢ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

ጥዋት የነበረውን ሁኔታ የሚያስረዳ ቪድዮም አያይዘዋል።

በተኩስ ልውውጡ ጉዳት ስለ መድረሱ እንደሰሙ ያመለከቱት የቤተሰብ አባሎቻችን ከቤት መውጣት እንዳልቻሉና የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደተዋረጠባቸውም ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ።

የአርቲስት ዳዊት ነጋ ስርዓተ ቀብር ወዳጅ ዘመዶቹ ፤ አድናቂዎቹ በተገኙበት በአ/አ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ዛሬ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ተፈፅሟል፡፡

ፎቶ ፦ ኦቢኤን / ሳምሶን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Gambella የጋምቤላ ክልል ፤ ጋምቤላ ከተማን ማረጋጋት መቻሉን አሳወቀ። ክልሉ ፥ " ተኩስ ከፍተው በነበሩ የሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ላይ በፀጥታ አካላት በተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ከተማዉን ማረጋጋት ተችሏል " ሲል አሳውቋል። አክሎም በተወሰደዉ እርምጃ በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል ሲል አመልክቷል። ክልሉ የከተማው ህብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት ለፀጥታ…
#Update #Gambella

የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገለፁ።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለፁት የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

" በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል " ያሉት አቶ ኡሞድ " በጥቃቱ በጠላት በኩል ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል ፤ ከወገን ጦር በኩልም መጠነኛ ጉዳት ደርሷል " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ኡሞድ ፤ በጋምቤላ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ገልፀው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የርዕሰ መስተዳድሩን ጽህፈት ቤት ተቆጣጥረዋል [ ታጣቂዎቹን ማለታቸው ነው ] በሚል የተናፈሰው ወሬ #ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።

" ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት በከተማው በአንዳንድ አካባቢ ተደብቆ የሚገኝ የጠላት ሀይል ካለ በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የፀጥታ ሀይል ጥቆማ ይስጡ " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ በተለይም #ከምሽቱ_2_ሰዓት ጀምሮ በቤቱ በመቀመጥ ለሠላሙ ተባባሪ መሆን ይኖርበታልም ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ " በጥቃቱ ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት በክልሉ መንግስት እና ህዝብ ስም መጽናናትን እመኛለሁ " ማለታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህፃን ማርኮን እስካሁን አልተገኘም። በአዲስ አበባ ከተማ በጎርፍ የተወሰደው ማርኮን ይገረም እስካሁን አለመገኘቱ ታውቋል። ዛሬ 7ኛ ቀን ነው። አሁንም ፍለጋ መቀጠሉ ተገልጿል። በሌላ በኩል የላዛርስት አከባቢ ልጆች በጎርፍ አደጋ በጠፋው ህፃን ማርኮን ሀዘናቸውን ገልፀው ከምሽቱ 12 ሰዓት (ዛሬ) በላዛርስት ት/ቤት በር ላይ የፀሎት እና የሻማ ማብራት ፕሮግራም ይካሄዳል ብለዋል። @tikvahethiopia
ፎቶ - ቪድዮ ፦ ለህፃን ማርኮን የሻማ ማብራትና የፀሎት ሰነ ሰርአት በላዛርስት ትምህርት ቤት አካባቢ እየተከናወነ ይገኛል። እጅግ ብዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

ህፃን ማርኮን ከትምህርት ቤት ሲወጣ በጎርፍ ከተወሰደ እንሆ ወደ 8ኛ ቀን እየተሸጋገርን ሲሆን እስካሁን ሊገኝ አልቻለም ፤ ፍለጋው ግን ቀጥሏል ።

(ዳኒ - Tikvah Family)

@tikvahethiopia
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለቀጣይ አምስት ወር በመኖሪያ ቤት ተከራዮች ላይ ጭማሪ ማድረግም ሆነ ተከራዮችን ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ አሳልፏል።

ከተማ አስተዳደሩ ፤ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ እና አለአግባብ ከፍተኛ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተለያየ መንገድ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ይህን ተከትሎ ነው ለ 5 ወራት ተከራዮች ላይ ጭማሪ ማድረግ ሆነ ከተከራዩት ቤት ማስወጣት እንደማይቻል ውሳኔ ያሳለፈው።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#HACHALU_HUNDESSA_AWARD

የመጀመሪያው የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ሊካሄድ ነው።

የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የመጀመሪያውን የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ይህን አዋርድ በተመለከተ ነገ ሰኔ 8-10-2014 የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን መግለጫ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

መግለጫውን ባለቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው የቦርድ አባል እና አስተባባሪ ኮሚቴ እንደሚሰጡ ታውቋል።

የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ዕጩዎችን ለማየት እና ድምፅ ለመስጠት የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተረጋገጠ ድረገፅ ይጠቀሙ : https://hachaluhundessaaward.org/vote-now/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Gambella የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገለፁ። ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለፁት የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። " በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል " ያሉት አቶ ኡሞድ " በጥቃቱ በጠላት በኩል ከፍተኛ…
#ማስታወሻ

የጋምቤላ ነዋሪዎች #ከምሽት_2_ሰዓት_በኃላ ቤት በመቀመጥ / ከቤት ባለመውጣት እና አካባቢን በንቃት በመጠበቅ ለሰላም ተባባሪ እንዲሆኑ ክልሉ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፦

የቲክቫህ አባላት በጋምቤላ ትላንት የነበረው ሁኔታ እየተረጋጋ መምጣቱን የገለፁ ሲሆን አንዳች ስጋት ያደረባቸው ሁኔታ መኖሩን አመልክተዋል።

ይኸውም የኦነግ ሸኔ / OLA ታጣቂዎች በከተማ መታየታቸው እና ተኩስ መለዋወጣቸውን ተከትሎ አንዳንድ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ሆነው በተለይ ንፁሃን ላይ የማዋከብ እና አንዳንድ ቦታም የማጠቃት ምልክት ታይቷል።

ከተማው ሰላሙ እየተመለሰ ነው ያሉን የቤተሰባችን አባላት አንዳንድ ወጣቶች በፖሊስ ታግዘው የዛው የክልሉ ተወላጅ ያልሆነን ሰው መደብደብ፣ ማዋከብ፣ ድርጊት እየፈፀሙ ነው ብለዋል።

ይህን መሰል ኢፍትሃዊ ድርጊት ቶሎ መቆም አለበት ፤ TPLFም ሁሉንም ኦሮሞ እንደ OLF ይቆጥር ነበር ይህ ግን እውነት አልነበረም። አሁን እያየን ያለነው ምልክት ይኸው ነው ይህ ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ ያደርጋል ንፁሃንን ከአማፅያን ጋር አንደባልቆ ማየት ተገቢ አይደለም ብለዋል።

በአሁን ሰዓት መድሃኒዓለም ፣ ጎንደሬ፣ ወሎ ሰፈር ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ፤ በአግባቡ ህግ ሊከበር እና ንፁሃን እንዳይሳቀቁ ማደረግ ተገቢ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia