TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአስሩ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ብዛት ቁጥራዊ መረጃ ፦

• አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር - 7,414 ሰዎች
• ሱማሌ ክልል - 602 ሰዎች
• ኦሮሚያ ክልል - 571 ሰዎች
• ትግራይ ክልል - 498 ሰዎች
• አማራ ክልል - 438 ሰዎች
• ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር - 319 ሰዎች
• ጋምቤላ ክልል - 274 ሰዎች
• አፋር ክልል - 180 ሰዎች
• ሲዳማ ክልል - 96 ሰዎች
• ሐረሪ ክልል - 78 ሰዎች
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 22 ሰዎች
• ደ/ብ/ብ/ሕ ክልል - 19 ሰዎች

በአጠቃላይ በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠው ሰዎች ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 75.5 በመቶን እንደሚይዝ ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
Thank You Telegram!

ውድ አባላት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ገፅ የነበረው ችግር ተፈቷል ፤ የቲክቫህ ፐብሊክ ሊንክ በቀጣይ ቀናት በቴሌግራም በኩል ወደነበረበት ይመለሳል።

በአጠቃላይ ' የቴሌግራም አስተባባሪዎችን ' በሙሉ ለሰጡን ፈጣን ምላሽ እና የተፈጠረውን ጉዳይ ለማጣራት ለሰሩት ስራ እናመሰግናለን።

በሌላ በኩል ቴሌግራም ባለው እጅግ ጥብቅ የሆነ አሰራር ምክንያት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም ለየትኛውም ወገን / ቲክቫህ አባል ሀሰተኛ መረጃ በውስጥ በኩል እንዳልተሰራጨ አረጋግጠናል።

በድጋሚ 'ቴሌግራም' የቲክቫህ አባላት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ ለመደጋገፍ፣ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመመካከርና ለመነጋገር የተሰባሰቡበትን ትልቁንና ሁሉን አቃፊውን መድረክ ደህንነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲጠበቅ ስላደረገ እናመሰግናለን !

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሠጠ ማሳሰቢያ!

ከጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ በደቡብ ኦሞ ዞን ስር ለምትገኙ የዳሰነች ፣ ሰላማጎ ፣ ኛንጋቶም ፣ ሀመር ፣ ኦሞራቴ ፣ ካንጋቶን ከተማ ነዋሪዎችና የኦሞ ስኳር ፋብሪካ እንዲሁም በመስኖ ልማት ላይ የተሰማራችሁ ባለኃብቶች በሙሉ ከሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የግድቡ ውሃ ሊለቀቅ ስለሚችል ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው!

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፊት ለፊት እና በኦንላይን ያስተማራቸውን ከ,5600 በላይ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ #በvirtual እያስመረቀ ይገኛል። የምርቃት ስነ ስርዓቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /etv/ በቀጥታ እየተላለፈ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations!

ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በ Virtual እየተመረቃችሁ ለሚትገኙ ተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ መጪው ጊዜ ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ጥብቅ ማሳሰቢያ!

በኳታር ነዋሪ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ዜጎች የኳታር መንግስት ያስቀመጠው የNational Address የምዝገባ ቀነ ገደብ #ነገ ይጠናቀቃል።

መንግስት ሊወስድ ከሚችለው ማንኛውም እርምጃ ራሳችሁን ለመጠበቅ እስካሁን መረጃውን ያልሞላችሁ ምዝገባውን በ #Metrash2 የሞባይል መተግበሪያ ወይም በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ ገጽ www.moi.gov.qa አማካኝነት እንድታከናውኑ በዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጥብቅ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#FDREDefenseForce

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ እና ግጭት በመፍጠር ፣ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎችን እየፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ አይኖራቸውም ሲሉ አስታውቀዋል።

ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያጋጩ ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት ፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት #እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ሬድዋን አማና እና የሱፍ በሽር በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወሰነ!

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሦስት (3) የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል።

ከነዚሁ 3 የአሜሪካ ዜግነት ካለቸው መካከል በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው #ለBBC ተናግረዋል።

ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ እንደተናገሩት ፤ ሁለቱ ግለሰቦች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በ6 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከእስር እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል።

ሦስተኛው የአሜሪካ ዜግነት ያለው እና በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ ሚሻ ጪሪ የሚባል ሲሆን ፤ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ቴክኒሺያን ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

ሚሻ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት ለፍርድ ቤት ተናግሮ እንደነበር #BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#Emirates

ኤሚሬትስ አየር መንገድ ከነሐሴ 1 ቀን 2020 ጀምሮ በሳምንት ሶስት በረራዎች ወደ አዲስ አበባ ማድረግ እንደሚጀምር ከ251 ኮሚኒኬሽን የተላከልን መረጃ ያሳያል፡፡

በተጨማሪ አየር መንገዱ ከትላንት ሐምሌ 17 ጀምሮ ወደ ቴህራን በረራ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ከሐምሌ 25 ጀምሮ ደግሞ ጉንጉዙ እና ኦስሎ በረራ ይጀምራል፡፡

የዱባይ ነዋሪዎች የወቅቱን የጉዞ መስፈርቶችን በ www.emirates.com/returntoDubai ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaOfficial @tikvahethmagazine
#GERD

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በ2014 ዓ/ም ኃይል ማንጨት የሚጀምሩ 11 ተርባይኖች ተከላ በቀጣዩ አመት እንደሚካሄድ መናገራቸውን አል አይን ዘግቧል።

በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ዌቢናር (የኦንላይን ቨርቹዋል ውይይት) ለተሳተፉ አምባሳደሮች እና ምሁራን የግድቡን የድርድር ሂደቶች እና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ሰፊ ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት (2013 ዓ/ም) ኃይል እንደሚያመነጩ የሚሞከሩትን ሁለት (2) ተርባይኖች ውሃ ማስተላለፊያ ‘ፔንሰቶኮች’ እና ‘ቦተም አውትሌት’ ለማጠናቀቅ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ የተርባይኖቹን እና የኤሌክትሪክ ስራዎቹን ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ውሃው ሳይቋረጥ እንዲያልፍ ፣ የግድቡ ከፍታም ወደ 590 ሜትር እንዲያድግ ከማድረግ እና ተጨማሪ 13 ነጥብ 4 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ከመያዝ ባለፈ በ2014 ዓ/ም ኃይል ማንጨት የሚጀምሩ የአስራ አንድ (11) ተርባይኖች ተከላ እንደሚካሄድም ማስረዳታቸውን ከአል ዓይን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማሳሰቢያ!

የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በነገው እለት የሚከበረውን ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል በየቤታቸው አንዲያከብሩ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር መሳፍንት ሙሉጌታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአገራችን በተለይም በሀዋሳ ከተማ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመር በመምጣቱ ህብረተሰቡ ንክኪ ሊያስከትል ከሚችል መሰባሰብ ሊቆጠብ ይገባል ብለዋል።

በነገው እለት (ሐምሌ 19) የሚከበረው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓልም የእምነቱ ተከታዮች በየቤታቸው አንዲያከብሩት ከእምነቱ የሃይማኖት አባቶች ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱን ኮሚሽነር መሳፍንት ተናግረዋል።

አገሪቱ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች ያሉት ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ የወጣውን አዋጅ በማክበር ራሱን ፣ ቤተሰቡንና ማህበረሰቡን ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#AtoLidetuAyalew

ትላንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉትን አቶ ልደቱ አያሌውን የኢዴፓ ፕሬዘዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ፣ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባላት አቶ ኤርሚያስ ባልከው እና አቶ ኤርሚያስ ጋሹ በቢሾፍቱ ከተማ በታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት ከ 5 ደቂቃዎች ላልበለጠ ጊዜ አነጋግረዋቸዋል።

አቶ ልደቱ ስለ ሁኔታው የሚከተለውን ብለዋል ፦

"በቁጥጥር ስር ከዋልኩበት ጊዜ ጀምሮ ፖሊሶቹ በጥሩ ሁኔታ ይዘውኛል። ስርዓት ያላቸው ፖሊሶች ናቸው። እነርሱ የሚተኙበትን ፍራሸም ሰጥተውኛል። በአንዲት አነስተኛ ክፍል ውስጥ ከአንድ ሌላ ሰው ጋር እገኛለሁ። ፖሊስ ቃሌን በአማርኛ ቋንቋ የተቀበለኝ ሲሆን ሰነዱ ላይ የተፃፈው ግን በኦሮምኛ ቢሆንም ፖሊሱን በማመን ፈርሜበታለሁ።"

ከዚህ በተጨማሪ ከፖሊስ የቀረበላቸው ጥያቄ "ከአቶ ጅዋር መሃመድ ጋር ያለህ ግንኙነት ምንድን ነው?" የሚል እንደሆነ ገልፀዋል። በመቀጠል የክስ ቻርጁ እንደተነበበላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ትንሽ አስጊ የሚሆነው የኮሮና ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው በአንዲት አነስተኛ እስር ቤት ውስጥ ከታሰሩ 35 እስረኞች ውስጥ አብዛኞቹ ምንም ዓይነት ራሳቸው ከቫይረሱ መከላከያ እንደማይጠቀሙ ለፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ገልጠውላቸዋል።

አቶ ልደቱ አያሌው በመጪው ሰኞ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን የፓርቲው ጠበቃ ከዋና ጸሃፊው ጋር በመሆን በቦታው ይገኛሉ ሲል ፓርቲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይ በንግድ ቦታዎች እና በመንግስት ተቋማት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል።

የተቋማት አመራሮችም ቫይረሱን ለመከላከል የሚያግዙ ግብዓቶችን በማቅረብና ሠራተኞች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ በማድረግ ተጋላጭነትን ሊቀንሱ ይገባል ብለዋል።

አመራሮች ራሳቸውም የቫይረሱን መከላከያዎችን በአግባቡ በመጠቀም አርዓያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 555 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,490 የላብራቶሪ ምርመራ 555 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 181 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 13,248 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 209 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 5,966 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#ETHIOPIA

እስከዛሬ በሀገራችን የተደረገው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የላብራቶሪ ምርመራ 372,812 ደርሷል ፤ ከነዚህ መካከል 13,248 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ሲገኝ የ209 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 5,966 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 7,071 ሰዎች ሲሆኑ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች ደግሞ በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ከላይ በቲክቫህ እና በCARD ትብብር የተዘጋጀውን ዕለታዊ የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሪፖርት መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#ATTENTION

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ያለአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) መንቀሳቀስ እንደማይቻል ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በእግርም ይሁን በተሽከርካሪ የሚንቀሳቀስ ፤ በመንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ባልሆነ ተቋም አገልግሎት የሚገለገል ተገልጋይ የግዴታ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) መጠቀም ይኖርበታል።

የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ይህን ለማሥፈፀም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የፀጥታ አካሉም ኃላፊነት እንደተሰጠው አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#COVID19

ሰሜን ኮሪያ ውስጥ የመጀመሪያ የተባለው በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተጠረጠረ ሰው መገኘቱ ተሰምቷል።

KCNAን ጠቅሶ BBC እንደዘገበው ከሆነ ቫይረሱ እንዳለበት የተጠረጠረው ግለሰብ ከ3 ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድቶ ሄዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በድንበር በኩል ወደ ሰሜን ኮሪያ ከተመለሰ በኋላ የቫይረሱ ምልክቶች ታይተውበታል።

ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከፍተኛ በለስልጣኖቻቸውን ሰብስበው ከደቡብ ኮሪያ ጋር በምትዋሰነው የድንብር ከተማዋ ኬሶንግ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አድገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የብራዚል ፕሬዝዳንት ከኮቪድ-19 ነፃ ሆኑ!

የብራዚሉ ፕሬዝደንት ያር ቦልሶናሮ ለ4ኛ ጊዜ በተደረገላቸው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን በትላትናው ዕለት ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡን የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዳ ኦልጅራ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ ገዳ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት አካባቢ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል የሊቀመንበሩን ደኅንነት ለመጠበቅ መሰማራቱን ከፖሊስ መስማታቸውንም ተናግረዋል።

የአቶ ዳውድ ቤት መከበቡን ያረጋገጡት አቶ ገዳ የታጠቁ ኃይሎች በመኖሪያ ቤቱ ዙሪያ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።

ኃላፊው፤ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣትና መግባት እንዳልቻሉና ወደ ውጪ የሚወጡ ከሆነም በጸጥታ ኃይሎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ስጋተቸውን ተናግረዋል https://telegra.ph/OLF-07-26 #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በ5 ቀናት ብቻ የ36 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 5 ቀናት ብቻ በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰላሳ ስድስት (36) ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተጨማሪ ባለፉት 5 ቀናት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 2,737 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ያለው መዘናጋት አሁንም ካልተቀረፈ ወረርሽኙ ከፍተኛ አደጋ መፈጠሩና ፍፁም ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ እንዲሁም የብዙ ሺዎችን ህይወት መቅጠፉ አይቀሬ ነው።

ጥንቃቄ አይለየን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,527 የላብራቶሪ ምርመራ 720 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 250 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 13,968 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 223 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,216 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial