TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሬድዋን አማና እና የሱፍ በሽር በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወሰነ!

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሦስት (3) የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል።

ከነዚሁ 3 የአሜሪካ ዜግነት ካለቸው መካከል በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው #ለBBC ተናግረዋል።

ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ እንደተናገሩት ፤ ሁለቱ ግለሰቦች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በ6 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከእስር እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል።

ሦስተኛው የአሜሪካ ዜግነት ያለው እና በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ ሚሻ ጪሪ የሚባል ሲሆን ፤ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ቴክኒሺያን ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

ሚሻ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት ለፍርድ ቤት ተናግሮ እንደነበር #BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የትግራይ ክልል ምርጫ!

የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ነሐሴ መጨረሻ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ በሙሉ ቀርበው እንዲመዘገቡ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ተወዳዳሪዎች ከማክሰኞ (ሐምሌ 21/2012) እስከ ሐሙስ (ሐምሌ 23/2012) ባሉት 3 ቀናት ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም #ለBBC ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ህመም አጋጥሞት በህክምና ላይ ይገኛል !

የ73 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ላለፉት 2 ሳምንታት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

አርቲስት አሊ ቢራ ስላለበት ሁኔታ ለBBC ተከታዩን ብሏል ፦

"በፊት ላይ በጣም አሞኝ ነበር። አሁን ግን ተሽሎኛል። አሁን ያለሁበት ሆስፒታል ጥሩ ክትትል እያደረጉልኝ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን እየተሻለኝ ነው።

አንዳንድ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስለ እኔ ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት ሰዎችን እያስደነገጡ መሆኑን ሰምቻለሁ። ሰዎች የመረጃዎችን እውነትነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።"

አርቲስት አሊ ቢራ አሁኑ የውስጥ ደዌ ህክምና እየተደረገለት ሲሆን ከዚህ ቀደምም የልብ እና የስኳር በሽታዎች ታማሚ መሆኑን #ለBBC ተናግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ በምዕራብ ወለጋ ትናንት የተገደሉት ሰዎች ለስብሰባ በተጠሩበት ስፍራ መሆኑን #ለBBC አረጋግጠዋል።

አቶ ጌታቸው እንደተናገሩት ከሆነ በሐሰተኛ መልኩ ነዋሪዎች ለስብሰባ ከተሰበሰቡ በኋላ በተወረወረባቸው ቦምብ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

"በ ኦነግ ሸኔ ስም የሚንቀሳቀስው ቡድን ትናንት በስበሰባ ስም ሰዎችን ከሰበሰቡ በኋላ ቦምብ ወርውረውባቸው ጉዳት መድረሱን የሚጠቁም መረጃ ነው ያለን" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ፥ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው መረጃ አጣርቶ የሚልክ ቡድን ወደ ሥፍራው ተልኳል ብለዋል።

በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አሃዝ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia