TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ የምርመራ አቅም እያደገ ነው!

በኢትዮጵያ የሚደረገው ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ አቅም ከዕለት ወደዕለት እየጨመረ ይገኛል።

ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 9,527 ሲሆን ይህም አጠቃላይ በሀገሪቱ የተደረገውን ምርመራ ወደ 382,339 አድርሶታል።

በሌላ በኩል ዛሬ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንደሀገር ኮቪድ19ን የመመርመር ዐቅም ማደጉን አሳውቀዋል።

መንግስታቸው ኮቪድ-19ን ከመመርመሪያ 1 ሚልዮን ኪቶች መካከል የመጀመሪያውን ዙር ዛሬ እንደተቀበለም ገልፀዋል።

ከዚያም ውስጥ 50 በመቶው በቅርቡ በሀገራችን የማምረት ሥራውን በሚጀምር ሀገር በቀል ኩባንያ አማካኝነት የተለገሰ መሆኑን አሳውቀዋል።

መመርመሪያዎቹ ሀገር ውስጥ የምርመራ ኪቶች ለማምረት የሚደረገው ዝግጅት እስከሚጠናቀቅበት እስከ ጥቅምት 2013 ዓ.ም ድረስ ዕለታዊ የምርመራ ዐቅምን ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ከሀሰተኛ መረጃ እራሳችሁን ጠብቁ!

'የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ' ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ክብረአብ ተወልደ በቤታቸው ውስጥ እያሉ ከ 30 ሚልዮን ብር ካሽ ጋር በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።

አቶ ክብረአብ ተወልደ ፥ መረጃው ውሸት እንደሆነ፣ እሳቸው በስራ ላይ እንደሚገኙና አሁንም ወደፊትም እንዲህ አይነት ነገር እንደማይኖር በራሳቸው እርግጠኛ መሆናቸውን ለአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
3 ዓመት ከቲክቫህ ቤተሰቦች ጋር!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተመሰረተ ዛሬ ሐምሌ 19/2012 ዓ/ም ሦስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

ቤተሰባዊ ትስስርን በመፍጠር ሚዛናዊና ታማኝነት ያላቸው መረጃዎችን እርስ በእርስ በመለዋወጥ፣ ለውይይት የተመቸ መድረክ በመፍጠር እንዲሁም ሰብዓዊነትን በማጉላት በቅንነት ላይ የተመሰረተ የመረዳዳት ባህልን ለማሳደግ ጥረቶችን ተደርገዋል።

ቲክቫህ በመጀመሪያው ዓመት የነበሩት አባላት 100,000 የሚደርሱ አልነበሩም፤ ባለፉት 2 ዓመታት ግን ከ900,000 በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች አባል ሆነውበታል።

ባለፉት ዓመታት የተሰሩትን ሥራ ለማስታወስ ያክል (በቅርብ ለተቀላቀሉ አባላት) ፡-

• ከ2007-2011 ድረስ በየዓመቱ ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ የመማሪያ መጽሐፍት ማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ነው።

• የበጎ አድራጎት ሥራዎች
- ለህክምና ወጪ በተለያየ ጊዜ የተሰበሰበ ወደ 600,000 ብር የሚጠጋ
- ለተፈናቀሉ ዜጎች (ጌዴዮ አካባቢ) የተሰበሰበ ከ160,000 ብር በላይ
- ለሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ማሰባሰቢያ መርኃግብር 25,000 ብር የሚጠጋ
- ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ወደ 25,000 ብር የሚጠጋ
- ለኢንፊኒቲ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር ለተሰራው የበጎ አድራጎት ሥራ 10,000 ብር

• በ2011 በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተከናወነው የጥላቻ ንግግሮችን እናቁም ንቅናቄ (ወላይታ - አርባምንጭ - ወልቂጤ - ሀዋሳ - ደብረ ብርሃን - ወልዲያ - ወሎ - መቐለ - ጅማ- ዋቻሞ -ሀረማያ)

TIKVAH - ETHIOPIA በየትኛውም መንግስታዊም ሆነ የግል ተቋማት አይደገፍም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ ገንዘብም ሆነ ቁሳቁስ የሚሰባሰበው ከቲክቫህ አባላት ብቻ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በቀጣይ በTIKVAH የሚሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ ሥራዎች፦

• ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓቶችን ወጣቱ ትውልድ እንዲረዳቸውና እንዲገነዘባቸው የሚያስችል አጭር የዳሰሳ ጹሑፍ ውድድር ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር (በቀጣይ በዚህ ጉዳይ መረጃ ይሰጣል)

• በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በኮቪድ ምክንያት ጫና ውስጥ ላሉና 'በቀይ መስቀል ማህበር' የተለዩ 1,500 ዜጎችን ለመመገብ የሚውል ድጋፍ ማስተባበር ስራ።

• ሁሉን አቃፊ የሰከነ፣ ከስሜታዊነት የራቀ ሀገራዊ የውይይት መድረክ በተለይም ከወጣቶች ጋር በመፍጠር የመፍትሔ ሃሳቦችን ማሰባሰብ ማደራጀትና ማወያየት ስራ፤ ሀገራችን ላለችበት አደገኛ አካሄድ ከመነጋገርና ከመወያየት የተሻለ ነገር የለም።

• ማስታወቂያ በመስራት ከገቢው ግማሹን እንዲሁም እቅድ በማቅረብ ከቤተሰቡ አባል በመነጋገር ገንዘብ በመፈለግ ለትንንሽ ስራ የሚሆኑ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የእውቀት፣የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ማድረግ።

በቀጣይ አቅማችን በፈቀደበት ሁሉ መሬት ወርደው የዜጎችን ህይወት የሚቀይሩ ተግባሮችን ከእናንተው ከቤተሰቦቻችን ጋር በመተባበር የምንሰራ ይሆናል፡፡

TIKVAH ጥቂት አስተባባሪዎች ያሉት እንጂ በባለቤትነት የሚመራው ከ1 ሚሊዮን በላይ በሆኑት አባላት ነው።

አሁንም ቲክቫህ ቤተሰብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጎችን በማቀፍ ፣ ሁሉንም በማክበር ፣የሰዎችን አመለካከት በማክበር፣ እርስ በእርስ በመዋደድ፣ በመፋቀር ይቀጥላል።

እርስ በእርስ መረጃ ከመለዋወጥ በተረፈ ይህ ወቅት እጅግ በጣም የሰከነ አካሄድ የምንሄድበት በመሆኑ ለሀገራችን ችግር መፍትሄዎችን በማቅረብ ፣ መፍትሄ ላይ በማተኮር በአብሮነት በዝተን ዓመቱን እንጨርሰዋለን ብለን እንመኛለን!

እናመሰግናለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ለምትፈልጉ በሙሉ!

(የኢትዮጵያ አየር መንገድ)

ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሲያቅዱ ከመግባትዎ በፊት ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ተመርምረው ከኮቪድ-19 ነፃ መሆንዎትን የሚገልፅ የምርመራ ውጤት (PCR SAR-CoV) መያዝዎን ያረጋግጡ።

ቀናቱም ለምርመራ ናሙና ከሰጡበት ቀን አንስቶ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት እስከደረሱበት ሰዓት የሚታሰብ ይሆናል።

እንዲሁም በቦሌ አለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ እንደደረሱ የኮቪድ ምርመራ ተደርጎልዎት ለ14ቀናት በቤትዎ እንዲቆዩ የሚያደርግ መመሪያም ወጥቷል።

ከኮቪድ 19 ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያልያዙ መንገደኞች ለ7 ቀናት በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ በራሳቸው ወጪ እንዲቆዩ ይደረጋል።

ከላይ የተዘረዘሩት መመሪያዎች ትራንዚት መንገደኞችን አይመለከትም።

@tikvahethiopiaOfficial @tikvahethiopiaBOT
አቶ ልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት ቀረቡ!

አቶ ልደቱ አያሌው በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡

ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 በቢሾፍቱ ከተማ ለወጣቶች ገንዘብ በመስጠት ለብጥብጥና አመፅ በማነሳሳት በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸው አስታውቋል።

ባለፈው አርብ አራት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸውና በዚህም ወቅት ሁለት ሽጉጦች ማግኘቱን አስታውቋል።

የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለማቅረብም የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜንም የኦሮሚያ መርማሪ ፖሊስ ጠይቋል።

አቶ ልደቱ በበኩላቸው ቋሚ አድራሻቸው አ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፣ መታወቂያቸውም በዚያው መሆኑን በማንሳት በፌደራል ፍርድ ቤት ነው መቅረብ ያለብኝ በሚል መቃወሚያ አንስተዋል።

በተጨማሪ በዋስ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን የዛሬ ዓመት የልብ ቀዶ ጥገና ወዳደረጉበት ሀገር ዛሬ 4 ሰዓት ላይ ለመጓዝ የተዘጋጁ መሆናቸውንና ትኬት ያላቸው ቢሆንም አሁን ታስረው እንደሚገኙና የአስም በሽተኛ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።

የእስር አያያዙም ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳያጋልጠኝ ያሰጋኛል በማለት ይህ ታሳቢ ተደርጎ በዋስ ይፍታኝ ብለዋል።

መርማሪ ፖሊስ የእስር አያያዛቸው ምቹ እና ጥንቃቄ ያለው መሆኑን እና ከእስር ቢፈቱ ማስረጃ እንደሚሸሽበት በማሳወቅ ዋስትናውን ተቃውማል : https://telegra.ph/fbc-07-27

@tikvahethiopiaOfficial
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID19 ሰሜን ኮሪያ ውስጥ የመጀመሪያ የተባለው በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተጠረጠረ ሰው መገኘቱ ተሰምቷል። KCNAን ጠቅሶ BBC እንደዘገበው ከሆነ ቫይረሱ እንዳለበት የተጠረጠረው ግለሰብ ከ3 ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድቶ ሄዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በድንበር በኩል ወደ ሰሜን ኮሪያ ከተመለሰ በኋላ የቫይረሱ ምልክቶች ታይተውበታል። ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከፍተኛ…
#UPDATE

በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተጠረጠረው የመጀመሪያው ሰሜን ኮሪያዊ #ነጻ መሆንኑን በምርመራ ማረጋገጧን ደቡብ ኮሪያ ገልፃለች።

ግለሰቡ ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ከሦስት (3) ዓመታት በፊት መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ግን ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ ነበር።

ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተሻገረው በደቡባዊ ደሴቲ አካባቢ በሚገኝ የቱቦ ማስተላለፊያ ውስጥ በመሹለከለክና በመዋኘት እንደነበር #BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ ሁሉ በመተግበር በሳምንት አራት ቀናት ወደ #ዱባይ በረራ መጀመሩን አስታውቋል።

በተጨማሪ አየር መንገዱ ከምዕራብ አፍሪካ መዳረሻዎች መካከል የቤኒን ፣ አይቮሪ ኮስት እና ካሜሩን ከተማዎች በረራ መቀጠሉን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ዛሬ ጥዋት የONLF ሊቀመንበር አብድራህማን ማሃዲ ፣ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ሙሃመድ ፣ የሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ (PP) እና የONLF ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አድርገዋል ፤ በውይይታቸው የሱማሌ ክልልን ሰላም ፣ መረጋጋት እና መልካም አስተዳደር #ለማጠናከር መስማማታቸው ተሰምቷል - #ONLF

@tikvahethiopiaOfficial
2 ልጆቿን በኮቪድ-19 ያጣችው እናት!

ፍሎሪዳ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ' ሞንቴ ሂክስ ' የምትባል እናት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሁለት (2) ልጆቿን ህይወት አጥታለች።

የመጀመሪያው የ20 ዓመት ልጇ ሲሆን እሱ ህይወቱ ካለፈ ከ11 ቀን በኃላ ደግሞ የ22 ዓመት ሴት ልጇን በዚህ አስከፊ በሽታ ተነጥቃለች።

እስካሁን ድረስ እጅግ መሪር በሆነ ሀዘን ውስጥ የምትገኘው ሞንቴ ሂክስ ከ NBC ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ ' ሰዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ ፣ ወረርሽኙን እንደቀልድ እንዳያዩት ' መክራለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ችሎት!

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አመራር አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አቶ ኮርሳ ደቻሳ በኮሮና በሽታ ተይዘው በሆስፒታል ህክምና ላይ በመሆናቸው ፤ ዛሬ በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸውን ጠበቆቻቸው ገለጹ።

ፖሊስ አቶ ደጀኔን ጨምሮ በተመሳሳይ መዝገብ የተካቱቱ ሶስት ተጠርጣሪዎችን ፤ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ፣ ቡራዮ እና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ሁከት ፤ 'ተሳትፎ አላቸው' በሚል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤት አስታውቋል።

የሶስቱን ተጠርጣሪዎች የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ እየተመለከተ የሚገኘው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ የ8 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ መፍቀዱን ጠበቃቸው ተናግረዋል። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በዛሬው ችሎት የቀረቡት አቶ ሚሻ አደም ብቻ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር (Ethiopia Insider)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ችሎት!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ·ም ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎች ለማድረግ 14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን፤ የሂሩት ክፍሌ ጠበቃ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲያደርግ በተሰጠው 10 ቀን በቂ ምርመራ ሳያደርግ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን ዘግቶ የደንበኛቸውን የዋስትና መብት እንዲያስከብር ጠይቀው ነበር።

ፍርድ ቤቱ ክርክሩን አዳምጦ መዝገቡን ለመመርመር ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ ካየ በኋላ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ እንዲያቀርብ ተጨማሪ 8 ቀን ፈቅዷል።

በሌላ መረጃ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ባልደረባ የነበሩት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20/2012 የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው እንደነበር ጠበቃቸው ተናግረዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 8 የምርመራ ቀናት ተፈቅዶለታል።

ምንጭ፦ Ethiopia Insider/ኢዜማ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#Qatar

በኳታር ከነገ ጀምሮ 80 ከመቶ የሚሆኑ የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ። ስብሰባዎች መደረግ የሚችሉት ግን ቢበዛ በአስር (10) ሰዎች ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

የኳታር መንግስት ጥሏቸው የቆዩ እገዳዎችን ቀስ በቀስ ለማንሳት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሶስተኛ ደረጃ (Third Phase) ማሻሻያዎች ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራሉ።

በኳታር የምትኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከነገ ጀምሮ የተደረጉ ማሻሻያዎችንና መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ከላይ ባለው ምስል (በዶሃ - የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተዘጋጀ) መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ14 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,009 የላብራቶሪ ምርመራ 579 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 170 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 14,547 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 228 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,386 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የትግራይ ክልል ምርጫ!

የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ነሐሴ መጨረሻ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ በሙሉ ቀርበው እንዲመዘገቡ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ተወዳዳሪዎች ከማክሰኞ (ሐምሌ 21/2012) እስከ ሐሙስ (ሐምሌ 23/2012) ባሉት 3 ቀናት ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም #ለBBC ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
አቶ ዳውድ ኢብሳ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል ?

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ያለ ግንባሩ ሊቀመንበር ያካሄደው ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁን አስታውቋል።

ስብሰባው ከሳምንት በፊት በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ የአባላቱ መታሰር እና የግንባሩ የወደ ፊት ስራዎች ላይ ለመምከር የተጠራ መሆኑን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

አቶ ቀጀላ የኦነግ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከ10 ቀናት አንስቶ በመንግስት የፀጥታ አካላት ሲጠበቁ ስለነበር አስቀድሞም እንደማይሳተፉ የተገመተ በመሆኑ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን ገልጸዋል።

ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ 'ከእውነት የራቀ' ሲሉ አስተባብለዋል።

አቶ ቀጄላ አሁን የአመራር ለውጥ ለማድረግ ፓርቲው ምንም እቅድ እንደሌለውም ገልጸዋል።

አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ ማየት አልቻልንም ያሉት የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስልካቸውም ከባለፈው አርብ ጀምሮ መዘጋቱን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial