الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.3K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
924 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💌:::::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::💌

ክፍል 2⃣

#የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ #ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ #ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡
ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ #እሷ #ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ #ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ #ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ #ሀብትና #ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡
ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡
#አላህ #በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡
#ከድጃ #ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ #የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ #ይህን #ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡
#አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው #ስሙ #አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ #ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ #የተከበረችው #ከድጃ #ስትቀር

❥ሀያት ቢንት ከድር❥

ይ...ቀ....ጥ.... ላ....ል

💌:::::::::Telegram:::::::::::💌


https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
🚫:::::::::::አይኖች ይከደኑ:::::::::::::🚫

እህቴ ሰምተሻል አልልሽም ስለ ሃቅ «ሙዱ»አይመቸኝም #ግን_ሃያቲ!📌 አንብቢው ከተመለከተሽ ታረሚ በት ካልተመለከትሽ አልሃምዱሊላህ የሚመለከተው ይኖራልና አሰተላልፊው።

እህት አለምዬ! ወደ ትዳር አለም ከመዝለቅሽ ቀደም ብሎ ለትዳር አጋርነት ጥያቄ ያቀረቡልሽ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ።

ይሆን እና የሚወደቀው ወድቆ የአላህ ፍቃድ የገጠመው አብሮሽ ህይወትን ይገፍል አንቺም አላህ እሱን መርጦልሽ ጉዞን ጀመራችኋል።

ከዚህ በኋላ በፊይት ይቀርቡልሽ የነበሩትን ያገብቻ ጥያቄዎች ከቀልብሽ አሰወግጃቸው
ከእሱ ሌላ አይኖችሽን ማንንም ለመመልከት አይሰንዘሩ እንዲሆም አካሎችሽ ከእሱ ሌላ ማንንም ለማማለል አይዋቡ

አይንሽ ከማለለ፣ልብሽ ለሌላ ከተልፈሰፈስ አደጋ ላይ ነሽ ይህ ድርጊት ከአላህ ዘንድ የሚያሰጥሽን ምህረት ያሳጣሻል።
የምታተረፊ ነገር ቢኑሮ ጭንቀትና ራስን በዱኒያም በአኼራም አደጋ ውስጥ መክተት ነው።
ያማር እና ዘላቄታነት ያለው ይሆን ዘንድ ትዳርሽ እነዚህን ባዶ ተሰፍዎችሽን አሰወግጃቸው

1ኛ☞☞እከሌን ባገባሁት ኖሮ
2ኛ☞☞ባለቤቴ እከሌን በመሰለልኝ
3ኛ☞☞ባሌ እንደ እንተና ኋብታም በሆነልኝ
4ኛ ☞☞ይህ በሆነ ያበሆን አትበይ
እነዚህ ቃላቶ በአላህ ቀደር ላይ ያለሽን የቂንንት ይቀጭጨዋል ለሰይጣንም በርከፍች መሆኑን የአላህ መልዕክተኛ {ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም}ተናግረዋል።

☞አላህ እንዲህ ይላል፦ «አይኖቻቸው ባሎቻቸው ላይ ብቻ የተገደበ» #አረህማን_56

ሀሰኑል በስሪይ እንዲህ ይላሉ፦«አይኖቻቸው ባሎቻቸው ላይ ብቻ የተገደበ»

📌«ወላሂ እነሱ የሚገላለጡ አይደሉም እንዲሁም ሌላን ወንድ ለማየት አይከጅሉም»

ከዚህ የምንረዳው ሃያእ የሚባለው ስነምግባ እስከ አኼራ {ጀነት} ድረስ አብሮ የሚጓዝ ባህሪ ነው።

እህቴ ባልሽ ያምንሽ ዘንድ ከባአድ ወንድ ጋር አትቀራረብ አትቃለጂ እንዲሆም ሌሎች ወንዶችን አታድንቂ

አላህ ሆይ!ከባላቸው ውጪ ሌላን ከሚመለከቱ ሰዎች ጠብቀን ለባሎቻችን ታማኝ እና ተንከባካቢ አድርገን ።አሚን🤲🤲

💍:::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

የተወደዳችሁ ወንድም እና እህቶቼ እንዴት ናቹልኝ? ??አልሃምዱሊላህ እኔ ሰላም ነኝ
#ግን_አንድ_ጉዳይ_ሰላሜን_ነስቶኛል👇 ❗️ እሱም በአሁኑ ሰአት ከልክ በላይ እየተስፋፋ ያለዉ 🚫ዝሙት እና የእህቶቼ ሀያዐ መጣት ሰላሜን ነስቶኛል plessssssss‼️

እስከመቼ ነዉ እንደዚህ አይነት አስጠያፊ ተግባር ዉስጥ የምንዘፈቀው?????እስከመቼ ነዉ ያልተፈቀደልንን ፎቶ በሚዲያ የምንፖስተዉ ⁉️

እስከመቼ ነዉ ፎቶ ፕሮፋይል የምናደርገዉ⁉️ ይህ ሁሉ እኮ አልተፈቀደልንም። ቆይ ለምንድነዉ ለአኼረችን መሰብ ያቀተን??
ኧረ ግድ የለም አላህን እንፍራ ❗️ ሞት ሰይመጣብን እንቶብት ዉዶቼ ።
ለማንኛዉም ዛሬ ልነግራቹ የፈለኩት ነገር ብኖር ለዚህ አስጠያፊ ድርጊት/ወይንም እንደ ቀልድ እየታዬ ለለዉ 🚫ዝሙት ፁሁፍ ላቀርብላቹሁ እገደዳለዉ ። የፁሁፉ ርዕስም እንዲህ ይላል👇

🚫#ዝሙትን_እንጠየፍ ከቁራኣን አያዐ ጋር የተያያዘ ነዉ። ይቅረብልን የምትሉ 👍 ለይክ በማድረግ አሳዩኝ ☝️

ለይካቹን በማየት ነገ በአላህ ፍቃድ ፕሮግራሙን አቀርብላችኃለሁ!! ኢንሻአላህ ለይክ ለደረጋቹኃሁ👍
ጀዛከላሁኸይረን አህሰነል ጀዛእ ለማንበብም ተዘጋጁ👌👌👌👌