الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.3K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
924 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💌::::::እውነተኛ ፍቅር::::::💌

🍃:::::::ክፍል 1⃣

በአሁኑ ዘመን እዉነተኛ ፍቅር ከፊልም ከቃናtv..እና ከአማረኛ ፊልም እያዩ የሚመኙ አሉ ፡፡ ግን እዉነተኛ ፍቅር ገና ማህበሪዊ ሚዲያ ሳይመጣና እንደ አሁኑ ሞደርን ስልጣኔ ሳይመጣ በፊት የተጀመረ ነዉ ..በፊት እዉነተኛ ፍቅር ምን ይመስል ነበር፡፡ እንደ ዘመኑ ፊልም ተጣልቶ መታረቅ ይሆን ?? እስከ ተከታታይ ታሪክ ጀምረናል እስከምንጨርስ አብረዉ ይከተሉን


#በቅድመ ኢስላም በጃህሊያ ዘመን ወደ ኢስላም ጥሪ ከመጀመሩ በፊት አስራአምስት አመት ገደማ አንድ ውብና ተክለ ሰውነቱ ያማረ ወጣት ካዕባ አጠገብ ከሚገኘው በኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረዐ) ቤት አጠገብ አለፈ፡፡
#ወጣቱ ሲያዩት ፊቱ እንደ በድር ጨረቃ የፈካ ፤ መልከመልካም ፣ የዐይኖቹ ጥቁረት የበረታ ፣ የሽፋሽፍቶቹ ፀጉር ረዥም ፣ ፀጉሩ በጣም የጠቆረ ፣ አንገቱ መለሎ፣ አይኖቹ በተፈጥሮ የተኳሉ ፣ ቅንድቡ ቀጭን እና ረዥም ከሩቅ ሲያዩት እጅግ ሲበዛ ቆንጆ ሲቀርቡት ተወዳጅ #ጥርሱ #ነጭ አፍንጫው ቀጥ ያለ ነበር፡፡
#በወቅቱ የከድጃ ቤትና የዳረል አሰድ ቢን አብድልዑዛ ፣ ቤት ከካዕባው ጥቂት እርምጃ ነበር የሚርቀው፡፡ አንድ የአይሁድ መነኩሴ በከድጃ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ሳለ መልከመልካሙን ወጣት አየው ፣ ከድጃንም ወጣቱ ተጠርቶ እንዲመጣ አዘዛት ፣ ወጣቱም በከድጃ አገልጋይ ተጠርቶ መጣ፡፡
#አይሁዳዊው #መነኩሴ ወጣቱን በትህትና ልብሱን ከትከሻው አካባቢ ገልጦ እንዲያሳየው ጠየቀው ፣ ወጣቱም እንደተጠየቀው አደረገ ፣ አይሁዳዊው ትከሻው አካባቢ ባየው አስደናቂ ነገር ተደሰተ አቅፎም ሳመው፡፡
#ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ከድጃ ለአይሁዱ "ይህንን ድርጊትህን ቁረይሾች ቢያዩህ አንተን ከመቅጣት ትዕግስት የላቸውም " አለች፡፡
#በርግጥ #የአይሁዱ #ድርጊት ለምን እንደሆነ ከድጃን (ረዐ) የገባት ነገር የለም ፣ ወጣቱን ስታየው ፊቱ የፈካና የሚያምር አንደበተ ርቱዕ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ አይሁዱ ለከድጃ እንዲህ አላት፡፡
"በተውራትና በኢንጂል ኪታቦች ላይ ሰፍሮ እንዳየሁት የአንድ ብርቱ ሰው መምጫ እየተቃረበ ነው፡፡ ይህ ሰው የተወለደው እዚሁ በመካ ነው ፣ እናትና #አባቱ #በልጅነቱ #ይሞታሉ ፣ አጎቱ ያሳድጉታል ወደ መዲናም ይሰደዳል ፣ የሻምን ስልጣን በእጁ ያደርጋል ፣ በመካ ያሉትን ጣኦታት በሙሉ ሰባብሮ በማስወገድ ካዕባን ንፁህ ያደርገዋል፡፡"
#ከድጃ አይሁዱ የተረከላትን በጥሞና አዳመጠች ፣ በንግግሩም ተማረከች ልቧ ጓጓ ወጣቱንም ለማወቅ ፈለገች፡፡
#በሌላ #ጊዜ አጎቷ ወረቃን ስለዚው ጉዳይ ጠየቀችው ፤ ወረቃም ወደ ሻምና ሶሪያ በመሄድ የኢንጅልን መፅሀፍ ስላጠናና ስለመረመረ ይመጣል ተብሎ የተተነበየው ታላቅ ሰው ከቁረይሾች እንደሚያገባ በገንዘብ እንደምትረዳውና ከጎኑ እንደምትሆን አረጋገጠላት፡፡


ይ.....ቀ......ጥ......ላ.......ል

💌::::::::::Telegram::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
💌:::::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::💌

ክፍል 2⃣

#የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ #ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ #ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡
ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ #እሷ #ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ #ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ #ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ #ሀብትና #ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡
ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡
#አላህ #በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡
#ከድጃ #ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ #የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ #ይህን #ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡
#አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው #ስሙ #አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ #ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ #የተከበረችው #ከድጃ #ስትቀር

❥ሀያት ቢንት ከድር❥

ይ...ቀ....ጥ.... ላ....ል

💌:::::::::Telegram:::::::::::💌


https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
💌:::::::እዉነተኛ ፍቅር::::::💌

ክፍል::::6⃣

#አቡጣሊብ ወጣቱ ያለውን ባለማመን እንዴት ብለው ጠየቁት፡፡ መሀመድም "የጋብቻ ጥያቄ አቅርባልኝ ሽማግሌ እንድልክ ተስማምቼ ነው የመጣሁት "
አቡጣሊብም "አትሸንገል የከድጃ ንግግር እጅግ ሚስጥር ያለው ነው" አሉ፡፡ መሀላቸው የነበረው አቡለሀብም " #የወንድሜ #ልጅ ሆይ አንተ ከድጃን ማግባት አትችልም አትመጥንህምና የአረቦች መሳለቂያ አታድርገን" አለ፡፡
ሌላኛው አጎታቸው አባስም እንደመቆጣት ብሎ "ለምንድነው የምትዘላብዱት ወላሂ መሀመድ በመካ ውስጥ እጅግ በጣም ውብና ጥሩ ስነምግባር ያለው በህዝቡ ዘንድ መሀመዱልአሚን የሚል ስም የተሰጠው ታማኝ ልጅ ነው ታድያ ከድጃ ለእሱ በምኗ ነው የምትከብደው ንግግርን ማጥላላት ምንም የሚጠቅም ነገር አይደለም፡፡ ተነሱ ሄደን የከድጃን ወላጅ እንጠይቅለት" አሉ፡፡
#መሀላቸው ፀጥታ ሰፈነ አክስታቸው ሶፊያ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ከድጃ ቤት ሄደች፡፡ እንደደረሰችም በሩን በዝግታ አንኳኳች በሩን የከፈተችው ከድጃ ነበረች፡፡ ከዚያም አርሂቡ ብላ በፈገግታ ወደ ውስጥ እንድትገባ ጋበዘቻት #የሚቀመስ #ነገር ለማምጣት መነሳቷን ባወቀች ጊዜ ሶፊያ እንዲህ አለቻት
"እኔ ምግብ ፈልጌ አልመጣሁም ወንድሞቼ እየጠበቁኝ ነው፡፡ በርግጥ አንቺ ጋር የመጣሁት የሰማሁት ጉዳይ እውነት መሆኑን ላጣራ ነው " አለቻት፡፡ ከድጃም (ረዐ) "የመጣሽበት ወሬ በርግጥ እውነት ነው፡፡ #ከፈለጋችሁ በአደባባይ ማውራት ትችላላችሁ እኔው ነኝ ጥያቄውን ለመሀመድ ያቀረብኩለት የፈለገው ቢመጣ መሀመድን ከማግባት የሚያግደኝ ማንም የለም" አለች፡፡
ሶፊያም በከድጃ ንግግር ተገረመች፡፡ ከዚያም " #ከድጃ #ሆይ እውነት አለሽ መሀመድን የመሰለ ውብ ሰው በመውደድሽ የሚያጋጥምሽ ነውር የለም" አለቻት፡፡
#ከድጃም በሶፊያ ንግግር ተደስታ ወደ ጓዳ በመግባት ውድ ቀሚስ አምጥታ አለበሰቻት ደስታውን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስ እቅፍ አድርጋም ሳመቻት፡፡ ከዚያም ብስራቱን እንድትናገር ወደ ወንድሞቿ ሸኘቻት፡፡ ሶፊያ ቤት እንደደረሰች ዠወንድሞቿና የመሀመድ (ሰዐወ) ፊት በፈገግታ ተቀበላት ሁሉም ጥሩ ዜና ይዛ የመጣች መሆኑን ያወቁት በውድ ልብስ አሸብርቃ መመለሷን ሲያዩ ነው፡፡ ወንድሟ አቡጣሊብም "አንቺ እውነተኛይቱ ልጅ ሆይ በምን መጣሽ" አሉ፡፡
#ሶፊያም "ከድጃ እውነቷን ነው በመሀመድ ፍቅር ወድቃለች በርሷ በኩል ያለው ጣጣ አልቋል፡፡ አሁን የሚቀረው አባትየውን መጠየቅ ብቻ ነው፡፡ ከከድጃ የምትሻል ሌላ ሴት ለማግኘት ሊከብድ ይችላል " አለቻቸው፡፡
#የመሀመድ #አጎቶች ደስ አላቸው ፤ አቡለሀብ ሲቀር ፣ ወድያው ምርጥና የክብር ልብስ ለብሰው መሀመድን (ሰዐወ ) ከኋላ አስከትለው ወደ ኩወይልድ ቤት አመሩ፡፡
#እግረመንገዳቸውን አቡበከር (ረዐ) ወደ እነሱ ሲመጣ አገኙት፡፡ ከዚያ አቡጣሊብ
" #የአቡቀሀፉ ልጅ ወዴት እየሄድክ ነው" አሉት ፤ አቡበከርም (ረዐ ) "የአብድልሙጠሊብ ልጆች በርግጥ ወደ እናንተ ለጉዳይ እየመጣሁ ነበር" አሉ፡፡
#አቡጣሊብም "ጉዳይህ ምን ነበር " ሲሉት አቡበከርም "ማታ ህልም አይቼ ነበር እናም ፍቺውን ልጠይቃችሁ መምጣቴ ነበር " አሉ፡፡ ህልሙ ምን እንደሆነ ጠየቁት፡፡
#አቡበከርም "ከአቡጣሊብ ቤት አንዲት ኮከብ ወደ ሰማይ ትሄድና ከሌሎች ኮከቦች ጋር ትደባለቃለች ከዚያም ተመልሳ ወደ ሁለት ቤቶች ትገባለች፡፡ አንደኛው ቤት የከድጃ ቤት ነው አንዱ ደሞ የሱዩዋን ቤት ነው፡፡ "
#አቡጣሊብም "እኛ አሁን ወደ አልካቸው ቤት ለጉዳይ እየሄድን ነው ህልምህ ጥሩ ብስራት አለው፡፡ ኩወይልድ ፍቃደኛ ከሆነ ለመሀመድ አሚን ከድጃን ለጋብቻ ልንጠይቅለት ነው፡፡ #ኮከቡ መሀመድ ነው የገባበት ቤት ያው እንዳየኸው የከድጃ ቤት ነው" በማለት #ህልሙን ፈቱለትና መርቀውት

❥ሀያት ቢንት ከድር ❥

ይ....ቀ.....ጥ....ላ.....ል

💌:::::::::ቴሌግራማችን::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg