💌:::::::::እውነተኛ ፍቅር::::::::💌
🍃:::::ክፍል 4⃣ት
ከሻም ጉዞ መልስ ከድጃ (ረዐ) #ለሙሀመድ (ሰዐወ) "ለአንተ እኔ ዘንድ ጥሩ ደስታና ስጦታ ተቀምጦልሀል ከሁሉም ሰራተኞች የበለጠ እጥፍ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፈልሀል" አለችው፡፡ #ሙሀመድም (ሰዐወ) ከጉዞ መልስ አጎቱ ጋር ተመለሰ፡፡ #አቡጣሊብም አባት ለልጅ አቀባበል ከሚያደርገው በላይ በደስታ ተቀበሉት፡፡ ከዚያም እንዲህ አሉት
"#ልጄ #ሆይ ከድጃ ከፈለችህ"
ሙሀመድም "ከውሉ በተጨማሪ ትርፍ ገንዘብ ጨምራ እንደምትሰጠኝ ቃል ገባችልኝ " አለ
#አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ የወላጆችህ አደራ አለብኝ እንደምታዬኝ አርጅቻለሁ የሞትም ምልክቱ እየታየብኝ ነው ስለዚህ አንተን ድሬ ወግ ማዕረግህን ማየት እፈልጋለሁኝ እናም ከቁረይሾች ጥሩ ሚስት ብፈልግልህና ብድርህስ " አሉ፡፡
#ሙሀመድም "አጎቴ ሆይ አንተ እንደፈለክ ማድረግ ትችላለህ እኔ ያንተን ትዕዛዝ ለመፈፀም ዝግጁ ነኝ " አለ፡፡
ከሻም መልስ በሁለተኛው ቀን ታላቁ ሙሀመድ (ሰዐወ) ገላቸውን ታጥበው አቡጣሊብ በገዙላቸው ልብስ ተውበው ወደ ከድጃ ሄዱ፡፡ ከድጃም እውነተኛ ፣ ታማኝ ፣ ፍትሀዊ ፣ አዛኝ ፣ መልካም ሰሪን ታላቁን ወጣት በውበቱ ላይ አዲስ ልብስን ተጎናፅፎ ስታየው ተደነቀች ከዚያም "#እንዲህ #አምረህ የመጣኸው ከኔ አንድ ነገር ፈልገህ ሳይሆን አይቀርም ምን ልታዘዝ ሀጃህ ምንድነው?" አለችው፡፡
"#ከአንቺ ዘንድ ያለኝን ገንዘብ ፈልጌ ነው " አላት፡፡
"#መሀመድ ሆይ ይህ ውዐትና ገንዘብ ይዘህ በንደዚህ ሁኔታህ ምን ልትሰራበት ነው" አለችው፡፡
"አጎቴ ከቁረይሽ የሆነችን ሚስት እድርልሀለው ስላለኝ ተስማምቼ ነው የመጣሁት " አላት፡፡
"#ሚስት ልታገባ አስበህ ከሆነ እኔ እጅግ ቆንጆ የሆነች ገንዘብ ያላት ለዘርህ ቅርብ የሆነች ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች በሰዎች ዘንድ የተከበረች አዕምሮዋ የተረጋጋና የሞላ አንተን እንጂ ከአንተ ምንም የማትፈልግ ሚስት አዘጋጅቼልሀለው፡፡" አለችና #እንዲህ ስትል ቀጠለች "ከአንተ የማልደብቀው ሁለት ነውር አላት አንደኛው ነውሯ አግብታ ታውቃለች ሁለተኛው በዕድሜ ከአንተ ትበልጣለች " አለች፡፡
#መሀመድም "አንቺ ጥሩዋ ሴት ሆይ ማናት እሷ የትስ ነው ያለችው " አላት
"ያንተ ምርኮኛ ናት እዚሁ ቅርብ አጠገብህ ታያታለህ ስሟም ከድጃ ይባላል" አለችው፡፡
#መሀመድም ሁሉም ነገር በተገለጠለት ጊዜ ምንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡
ከድጃም "የእሺታ መልስ ስጠኝና ልቤን አሳርፈው" አለችው፡፡
አሁንም ከወጣቱ መልስ ስታጣ "አላህ ካለ እኔ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አንተንም በምንም አልወነጅልህም" አለች፡፡
#መሀመድም (ሰዐወ) "ከድጃ ሆይ አንቺ የተከበርሽና ባለብዙ ሀብት እኔ ደግሞ የአንቺ ተቀጣሪና ከምትሰጪኝ ገንዘብ ሌላ ምንም የለኝም እናም ገንዘብ የሌለው ፈልጎም ቢሆን ቢጤውን ያገባል" አላት፡፡
.
.
አላለቀም
❥ሀያት ቢንት ከድር❥✍
ይ...ቀ...ጥ...ላ....ል✍✍✍
💌:::::::::::Telegram:::::::::💌
https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg