الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
21.9K subscribers
372 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💌::::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::::💌

🍃:::::ክፍል 3⃣

#የከድጃ ሀብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ በውክልና እሷ ዘንድ በኮሚሽን መቀጠር ከቻሉ ሰዎች መካከል ሙሀመድ (ሰዐወ) አንዱ ነበር፡፡ ወጣቱ ትሁት ሰው አክባሪ የሰውን ገንዘብ ያለ ሀቁ የማይፈልግ ታታሪ ቸር ስራውን ወዳድ በመሆኑ ከድጃ ጋር #ከተቀጠረ ጀምሮ ከመካ ከተማ ርቆ በመሄድ እየነገደ ገንዘቧን በእጥፍ አሳደገው፡፡ በዚህም ከድጃ በወጣቱ ኮርታበታለች፡፡ #ሙሀመድ ከድጃ ጋር የተቀጠረው እንዲሁ በአጋጣሚ አልነበረም፡፡ የሚያሳድጉት አጎቱ ጥሪት አነስተኛ በመሆኑ እንጂ፡፡
የሙሀመድ አባት አብደላህ ገና ሳይወለዱ ነበር የሞቱት፡፡ እናታቸውን ያጡት ደግሞ በ6 አመታቸው ነበር፡፡ ቢሆንም በአያቱ ዘንድ አደገ፡፡ አያቱ ሲሞቱ አጎቱ ተረከቧቸው፡፡
#መሀመድ አጎቱ ጋር መኖር ሲጀምር ፍየል በመጠበቅ ተግባር ተሰማራ፡፡ ግን ብዙም ሳይቆይ አጎትየው የገቢያቸውን መጠን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡
#አንድ #ቀን ከድጃ ወንዶችን ወደ ምድረ ሻም በመላክ እንደምታሰማራ ስላወቁ ነጋዴው ወደተባለው ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ሳሉ ሙሀመድን አስጠርተው ስለሁኔታው ሊነግሯቸው ወሰኑ፡፡
"የወንድሜ ልጅ ሆይ እንደምታውቀው አንዳች የሌለኝ ደሀ ነኝ ፤ ግዜው ደግሞ በድርቅ ተመቷል፡፡ ከድጃ ሰው ቀጥራ እንደምታስነግድ ሰምቻለው በርግጥ የምትከፍለው ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ደስ አያሰኝም፡፡ #እናም ስለዚህ ጉዳይ እሷኑ ባነጋግርልህ " ሲሉ አቡጧሊብ ጥያቄ ለመሀመድ አቀረቡ፡፡ ሙሀመድም እንዲህ አላቸው "አጎቴ ሆይ እንዳሻህ ማድረግ ትችላለህ ሀሳብህ የኔም ሀሳብ ነው መጭው አለም ከዱንያ አለም በላጭ ነው" አሏቸው፡፡
#አቡጧሊብ ጊዜ ማጥፋት አልፈለጉም ወንድሞቻቸውን አስከትለው ወደ ኸድጃ ቤት አመሩ፡፡ እሷም ከሀር በተሰራ ባማረ ልብስ ተውባ በፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡
አቡጧሊብም "የተከበርሽው ከድጃ ሆይ እኛ የመጣነው ለጉዳይ ነው ሰዎችን ገንዘብ እየከፈልሽ እንደምታስነግጂ ሰምቻለው፡፡ ለሌሎች በምትከፊይው ላይ ጨምረሽ ተመሳሳይ ስራ እንዲሰራልሽ መሀመድን አትቀጥሪምን? " አሉ
ከድጃም "እንኳንስ ለሚወደድ ለቅርብ ዘመድ ለማይታወቀውም ቢሆን ጥያቄዎ በኔ ዘንድ ተቀባይነት አለው" በማለት አስደሳች መልስ ሰጠች፡፡
አቡጧሊብ አስደሳቹን ዜና ይዘው ወደ መሀመድ (ሰዐወ) ተመለሱ፡፡ ብስራቱን ከነገሩት በኋላ "ይህ ፈጣሪ ላንተ የላከው ሲሳይ ነው " አሉ፡፡
ሩህሩሁ አጎት መጪው ጊዜ ያረገዘውን ቢረዱ ይህ ለከድጃ ከሰማይ የወረደ ፀጋ ነው ባሉ ነበር፡፡ ሆኖም ከዚህ መልካም ዜና በስተጀርባ የሚመጣውን የላቀ ዕጣ የሚያውቅ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
እድለኛዋ ከድጃ አቡጧሊብ ያቀረቡትን ጥያቄ በደስታ ተቀበለች ፤ ይህም ሙሀመድ (ሰዐወ) እና ከድጃ (ረዐ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁበት አጋጣሚ ፈጠረ፡፡ ጉዳዩ በመካ ነዋሪዎች ዘንድ ተዳረሰ፡፡ በየአጋጣሚው የታላቁን ሰው መልካም ትሩፋት እውነተኛነት ዘረዘሩላቸው፡፡ ከድጃም ይበልጥ ደስ አላት፡፡ #መይሰራ ከተባለው አገልጋይ ጋር ወደ ሻም እንዲሄዱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታወቀች፡፡ ሙሀመድም የተሰጣቸውን አማና ተቀብለው ለንግድ ከመይሰራ ጋር ወደ ሻም አመሩ፡፡

❥ሀያት ቢንት ከድር❥

ይ-----ቀ-----ጥ---ላ------ል

💌:::::::::::::Telegram:::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
💌:::::::እዉነተኛ ፍቅር::::::💌 ክፍል::::6⃣ #አቡጣሊብ ወጣቱ ያለውን ባለማመን እንዴት ብለው ጠየቁት፡፡ መሀመድም "የጋብቻ ጥያቄ አቅርባልኝ ሽማግሌ እንድልክ ተስማምቼ ነው የመጣሁት " አቡጣሊብም "አትሸንገል የከድጃ ንግግር እጅግ ሚስጥር ያለው ነው" አሉ፡፡ መሀላቸው የነበረው አቡለሀብም " #የወንድሜ #ልጅ ሆይ አንተ ከድጃን ማግባት አትችልም አትመጥንህምና የአረቦች መሳለቂያ አታድርገን"…
💌::::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::::::💌

🍃:::::ክፍል 7⃣

#ከድጃን ያፈራው ቤተሰብ በማህበረሰቡ ዘንድ ጥንታዊ ከበሬታ የነበረው ለህዝብ ግንኙነት የቅርብ ተጠሪና ነገር ቆራጭ የነበረ ነው፡፡ በቁሰይ አማካኝነት በካዕባው አቅራቢያ ዳረል ነድዋ በሚል ስያሜ በሚታወቀው #ታላቅ #አዳራሽ ውስጥ የነገዱ ታላላቆችና ነገር አዋቂዎች በህዝባዊ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጡ ናቸውና ይከበራሉ፡፡
#የመሀመድ (ሰዐወ) አጎቶች ኩወይልድ ቤት ደረሱ ፤ እንግዶቹ እንደሚመጡ በአገልጋዩ መልዕክት ደርሶት የነበረው የከድጃ አባትም በጥሩና በከፍተኛ ክብር ተቀበላቸው፡፡ ኩወይልድ እንግዶቹ የመጡበትን ምክንያት ባያውቅም ከድጃን ግን ለጋብቻ ይጠይቃሉ የሚል ግምት በጭራሽ የለውም፡፡
#እንግዶቹ ለመስተንግዶው ምስጋና አቀረቡ ከዚያም አቡጣሊብ እንዲህ አለ "ምስጋና ለአላህ ይሁን ኩወይልድ ሆይ እንደምታውቀው እኛ የአጎታሞች ጎሳዎች ነን፡፡ #አንዳችን ለአንዳችን ጋሻና መከታ ሆነን በቋሚነት በመሀከላችን ምንም መበዳደል ሳይኖር ተከባብረን በጨዋ ደንብ ኖረናል፡፡ #እናም ካንተ ጉዳይ አለን አንተ ደሞ ጉዳያችንን እንደምትቀበለውና እንደምትፈታው ባለሙሉ ተስፋ ሆነን ነው የመጣነው " #ሲሉት ኩወይልድ ጉዳያቸው ምን እንደሆነ ጠየቃቸው፡፡
"ልጅህን ከድጃ ለጋብቻ እንድትሰጠን ነው የመጣነው" አሉት፡፡
#ኩወይልድም "ለመሆኑ የሚያጫት ሰው ማነው"፡፡ አቡጣሊብም "ታማኙና ፀባየሸጋው መልከመልካሙ መሀመዱልአሚን ነው" አሉት፡፡
ቁረይሾች በሚጠሩት አጠራር ኩወይልድ የተጠራውን ስም ሲሰማ ፊቱን እንደማጨፍገግ አደረገና ከዚያም " #የአብድልሙጠሊብ ልጆች ወደ ኀላ ቀራችሁ ልጄ ከድጃ እንደምታውቋት የተከበረችና እድለኛ ሴት ናት፡፡ #ከቁረይሾች ሴቶችም ትበልጣለች ፤ አላህ በሀብት ያበለፀጋት እጅግ የተከበሩና በሀብታቸው አንቱ የሚባሉ ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት ከነሱ የተብቃቃችና እንቢ ያለች ናት፡፡ ታዲያ ደሀና የቲም ለሆነ ሰው እንዴት ፍቃደኛ ትሆናለች አትሆንም " አላቸው፡፡
ለሽምግልና የመጡት የመሀመድ አጎቶች #ኩወይልድን በጥሩ አነጋገር ሊያሳምኑት ሞከሩ እሱ ግን ጭራሽ እንደማይሆን ነገራቸው፡፡ #መሀመድን ከከድጃ ጋር በንፅፅር እያቀረበ እንደማይሆን ገለፀላቸው፡፡ አቡጣሊብም በብስጭት
" #ኩወይልድ #ሆይ መሀመዱልአሚን ሚስት ፈልጎ ቢጠይቀን ኖሮ ከቁረይሽ ውስጥ ምርጧን እናቀርብለታለን ሀብት ፈልጎ ቢጠይቀን እኛ ዘመዶቹ አሱን ባለሀብት እናደርገዋለን" አሉት፡፡ ሀምዛም "ፀሀይንና ጨረቃን እኩል ማነፃፀርህ ጅልነት ነው" #በማለት በቁጣ ተናገረውና ወንድሞቹን አስከትሎ ከቤቱ ወጡ፡፡
ከድጃ የሽማግሌዎቹ መምጣት ቀድማ ታውቅ ስለነበር አገልጋይዋን ሁኔታውን እንድታጣራላት ልካት ነበር፡፡ አገልጋይዋም የኩወይሊድ እንቢ ማለት ነገረቻት፡፡ ወድያውኑ ከድጃ አጎቷ ወረቃ በአስቸኳይ ተጠርቶ እንዲመጣ ላኸችበት፡፡ አጎቷም መጣ፡፡ ከድጃ ቤት ሲጀርስ ከድጃ አንድ ስፍራ ትክዝ ብላ ቁጭ እንዳለች አያት አጠገቧ ቁጭ አለና
.
.
. ❥ ሀያት ቢንት ከድር ❥

ይ----ቀ----ጥ---ላ---+ል

💌:::::::Telegram:::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
❥::::::::::እህቴ__ሆይ:::::::::::::❥

በሶሻል ሚድያ ያመጣሽው ትዳር ላያዛልቅሽ
ገብተሽ ከማልቀስ ከአሁኑ ታቅበሽ
መኖሩ ይሻላል በቤትሽ ተከብረሽ

#እናም__እህትዬ!

በዬሶሽያል ሚድያው ትዳር አይገኝም
ቢገኝም አይጥምም
እወቂው እ'ት ዓለም

#እናም!
እህት አለም እኔ ሳስታውስሽ
ጌታሽን ተማጸኝ በጧትም በማታም
በሱጁድ ተደፍተሽ

እሱን ብጠይቂው ብዙን ይሰጥሻል
አንች ከለመንሽው እንኳን ትዳርና
ሌላ እንደሚሰጥ ቃልም ገብቶልሻል

#ዱዓና_ሶብር_ለስኬት_ያደርሳልና

እህቶቼ ሆይ ለህይወታችሁና ለትዳር አጋራችሁ አስቡበት።በዱዓና በሶብር ታግዛችሁ ትዳር ፈልጉ።
አላህ መልካም ያድርጋችሁና መልካም የትዳር አጋርም ይስጣችሁ።አሚን🤲🤲

💌:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
🚫:::::::::እህቴ__ሆይ::::::::::::🚫

📌📌#በሶሻል_ሚድያ ያመጣሽው ትዳር ላያዛልቅሽ
ገብተሽ ከማልቀስ ከአሁኑ ታቅበሽ
መኖሩ ይሻላል በቤትሽ ተከብረሽ

#እናም__እህትዬ!

🚫በዬሶሽያል ሚድያው #ትዳር አይገኝም☜☜☜
ቢገኝም አይጥምም
እወቂው እህት ዓለም ምክሬ ላንችዉ ነዉ።
📌እናም እህት አለም እኔ ሳስታውስሽ
ጌታሽን ተማጸኝ በጧትም በማታም
በሱጁድ ተደፍተሽ

እሱን ብጠይቂው ብዙን ይሰጥሻል
አንች ከለመንሽው እንኳን ትዳርና
ሌላ እንደሚሰጥ ቃልም ገብቶልሻል
#ዱዓና_ሶብር_ለስኬት_ያደርሳልና
እህቶቼ ሆይ ለህይወታችሁና ለትዳር አጋራችሁ አስቡበት።በዱዓና በሶብር ታግዛችሁ ትዳር ፈልጉ።

አላህ መልካም ያድርጋችሁና መልካም የትዳር አጋርም ይስጣችሁ አሚን 🤲🤲🌹ከስቀየምኳቹ አፉ በሉኝ እህቶቼ ። ሁሌም የእህቶቼ ችግር ያሳሰበኛል

💍:::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
❥::::::::::እህቴ__ሆይ:::::::::::::❥

በሶሻል ሚድያ ያመጣሽው ትዳር ላያዛልቅሽ
ገብተሽ ከማልቀስ ከአሁኑ ታቅበሽ
መኖሩ ይሻላል በቤትሽ ተከብረሽ

#እናም__እህትዬ!

በዬሶሽያል ሚድያው ትዳር አይገኝም
ቢገኝም አይጥምም
እወቂው እ'ት ዓለም

#እናም!
እህት አለም እኔ ሳስታውስሽ
ጌታሽን ተማጸኝ በጧትም በማታም
በሱጁድ ተደፍተሽ

እሱን ብጠይቂው ብዙን ይሰጥሻል
አንች ከለመንሽው እንኳን ትዳርና
ሌላ እንደሚሰጥ ቃልም ገብቶልሻል

#ዱዓና_ሶብር_ለስኬት_ያደርሳልና

እህቶቼ ሆይ ለህይወታችሁና ለትዳር አጋራችሁ አስቡበት።በዱዓና በሶብር ታግዛችሁ ትዳር ፈልጉ።
አላህ መልካም ያድርጋችሁና መልካም የትዳር አጋርም ይስጣችሁ።አሚን🤲🤲

💍:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::💍

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam