الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.5K subscribers
359 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️እሷን ፍታት እና ከእኔ ጋር እንጋባ❗️

➻አንዳንድ እህቶች ለሌላዋ እህታቸው ብቻ ሳይሆን ለራሳቸውም አያዝኑም።❗️

እንዴት ብትሉ........❗️
የያዝካትን ሚስት ፍታትና እኔ ጋር እንጋባ ማለታቸው ለራስም ካለማሰብ የመነጨ ነው ለማለት ፈልጌ ነው። ምናልባት ይሄን የምትፈፅም ሴት በእህቷ ላይ የፈፀመችው ግፍ በራሷ ላይ ዞሮ እንደሚመጣባት ባለማስተዋሏ ሊሆን ይችላል። እውነታው ግን እህቷን በድላ ያገባች ሴት ቢዘገይም በሌላዋ እህት ተገፍታ መውጣቷ አይቀሬ ነው። ሌላዋን አስፈትታ በሀራም የመሠረተችውም ትዳር ለእሷ የተባረከና ፍሬያማ ሳይሆን አቃጣይ እሳት እንድሁም  ፍሬውም መራራ ሊሆንባት ይችላል። ምክንያቱም አላህ ፍትሃዊ ጌታ ስለሆነ የተበደለችውን እህት ብሶት ከንቱ አያደርገውም።
እንደአባባልም  "በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም" ሲባል አልሰማችሁም? አዎ "አልጀዛኡ ሚን ጂንሲ አል ዐመል" ነው።

ስለዚህ ሁለተኛ አግብታው መኖር እየቻለች ከእሷ እኔ እሻልሃለሁ ብላ በማታለል ወይም ባል የመጀመሪያዋን በምን ምክንያት እንደጠላት ስላወቀች ብቻ የእሷን ግድፈቶች እንደምትሞላለት በመግለፅ አታልላ ማስፈታቷ
#ሀራም ነው።

ኢብኑ ሂባን በዘገቡት እና አልባኒ ትክክለኛ ባሉት ሀዲስ  "አንድት ሴት (በዲን) እህቷ እቃዎች ልትጠቀም  የእህቷን ፍች መጠየቅ  አይፈቀድላትም ማለታቸው የራሷን
#ትዳር ለመመስረት በማሰብ ሌላዋን ማስፈታት ሀራም መሆኑን በግልፅ ጠቋሚ ነው። ከዚህም በተጨማሪ " የአንድትን እህት ባል ልቦና በማስኮቦለል የእህቷን ትዳር ማናጋት ለአላህ እርግማን ያጋልጣል።
ማንም እንደሚያውቀው ይሄ አይነት በደል ከምንም በላይ  ከምቀኝነት የመነጨ ነው። ምቀኝነት ደግሞ ቦታው ጀሃነም ነው

ስለዚህ እህቶች ትዳርን በዚህ መልኩ ለመመስረት አትሞክሩ። ነፍ ለሆነ ባል በዚህ ፀያፍ ድርጊት አትሳተፊ🚫
#ሼር_ያድርጉ👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
!!!!!!!! ጥቆማ !!!!!!!!!!

#ዛሬ ከመሸ የዙል-ሒጃህ ጨረቃ  ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ሲሆን እሁድ ሰኔ 9 ደሞ የዒደ-ል-አዽሓህ በዓል ይሆናል።

☞ከዚህ ሰ
ዐት ጀምሮ የወርቃማዎቹ የዱንያ ንጉስ እና ቅዱስ ቀናቶች ነፋስ መንፈስ ጀምሯል።

☞በእውነቱ ለዚህ ዐይነታ ፀጋ መወፈቅ በራሱ ትልቅ የሆነ መመረጥ ነውና አላህን እናመስግን።

☞አደራ ትኩረታችን በአጠቃላይ አላህ
ወደሚወዳቸው ዒባዳዎች ላይ ይሁን።

💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን
#ሼር!👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
☀️ከሴቶች ከሚያስጠሉኝ ዉስጥ  ሰዉ ሰራሽ ዉበት ይዘዉ  የሚኩራሩ  ከነሱ በላይ ቆንጆ የሌለ የሚመስላቸዉ በቃ የሌለ  የሚከመሩ ናቸዉ።  በዉሀ  ለሚለቅ ዉበት ባትኮፈሱ  ጥሩ ነዉ እሺ።


ጀግና ሴት ጌታዋ በሰጣት ዉበት የምትብቃቃ ለዘመኑ አርትፊሻል ኮተት ቦታ የማትሰጥ ነች።
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
☀️ቤቷ ውስጥ ባለው ምንጣፍ ላይ ተቀምጣ በጥሞና ቁርዓንን ታነባለች። ፊቷ ከምታነባቸው የቁርዓን አንቀፆች ጋር እንደሁኔታው ይቀያየራሉ። ስለ ጀነት የሚናገሩ አንቀፆችን ስታነብ ፊቷ በደስታ ያበራል። ስለ አሳማሚው የጀሃነም ቅጣት የሚናገሩ አንቀፆች ላይ ስትደርስ ደስታዋ ብንን ብሎ ይጠፋና እንባ ከዓይኖቿ ኩልል ኩልል እያሉ ይፈሳሉ። ባሏ ይህን ትዕይንት ከቅርብ ርቀት ሆኖ እየተከታተለ መሆኑን አላስተዋለችም ነበር። ድንገት ቀና ስትል ዓይን በዓይን ተጋጩ። ንባቧን አቋርጣ በፈገግታ... አቤት ሆዴ! ምን ፈልገህ ነው? ምን ልታዘዝ አለችው።

ዓይኖቹ በደስታ እያነቡ አዎ የሆነ ነገር ፈልጌ ነው አላት። ተነስታ አጠገቡ በመምጣት እሺ ምን ፈለክ ውዴ! አለቸው። እቅፉ ውስጥ አስገብቷት "ውዴ በጀነት ውስጥም አብረን እንድንሆን ፈለኩ ቃል ትገቢልኛለሽ?" አላት። ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው... አዎ፤ አዎ፤ አዎ ውዴ!
ቃል እገባለሁ እያለች ጥምጥም አለችበት።


ያ አላህ! ጅማሬው ዱንያ ላይ ሆኖ መቋጫውን 
አኺራ ያደረገ ምንኛ የማረ ፍቅር ነው።
ያ ረብ! እንደዚህ አይነቱን ሙሃባ ወፍቀን!

#𝙘𝙤𝙥𝙮..
☀️ትፍዘዢ  ንቂ  አትልፊ በከንቱ
መጫወቻ አያርግሽ  ማርኪያ ለስሜቱ
ከወደደሽ  ያግባሽ  ሰዉ ይላክ ላባትሽ
ነገ ዛሬ  እያለ  ቀጠሮ  አያብዛብሽ
ነቃ በይ  እንስቷ  ከወዲሁ ንቂ
ኋላ  እንዳታለቅሽ  ክብርሽን ጠብቂ


ጊዜሽን  በጅንጀና  አትፍጂ  እህቴ ቁም ነገር ይኑርሽ  አግቢ  የሚመሥልሽን  ካላገኘሽ  ደግሞ  ተሰተሪ  አትዝረክረኪ

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
💥ወንድሜ ሆይ ትዳር እፈልጋለው አጋቡኝ እያልክ በየግሩፑ የምትናገረውና የምታሳውቀው ለምንድነው????? ትዳርን የመሠለ ውድ ነገር በርካሽ መልኩ አትፈልገው።ሱብሀነላህ ያውምኮ ተቂያህ(አላህን ፈሪ)የሆነችን ሴት ነው ምጠይቀው።ተቂያህ የሆነች ሴት ማንኛውም ቦታ አይደለም የምትገኘው።አላህን ምትፈራ ሴት ኦን ላይን የምትሆነው ለዲኗ ብቻ ነው።በየሚድያው እየገባህ አላህን ምትፈራ ሴት ፈልጉልኝ አትበል።    ይልቅ ሁሉን ትተህ ሱጁድህ ውስጥ፣ሶላትህ፣ዱዐህ ውስጥፈልጋት።



☀️አሉ ደግሞ አንዳንዶች 👉[የማጋባት ስራ በትሰሩ የሚሉ] አሏሁ ሙስተዐን  እንዴት አላህ ያልሰጠኸህን ሪዝቅ የሰው ልጅ ሊሰጥህ ይችላል ያኣኺ? ?????ላንተ ያለው የትም አይሄድብህም አንተ የዘገየ ቢመስልህም!!ተቂያህ ሴትን እፈልጋለው ስላልክ እኔ አላህን እፈራለው ብላ አትመጣልህም።ሙእሚናህ የሆነች ሴተሰ ጊዜዋን በምን መልኩ መጠቀም እንዳለባት ጠንቅቀቃ ምታውቅ ነች።አንተ ስለጮህክ መቼም አትመጣልህም።እንዲህ በማለትህ ደግሞ ርክሰትን እንጂ ክብርን አታገኝም።ያኣኺ ጠንቀቅ በል።አንተ ብቻ አላህ ያዘዘህን በቻልከው መልኩ ታዘዝ።የከለከለህን ግን ሙሉ ለሙሉ በመከልከል ወደሱ ተቃረብ።እንጂ በየሚድያው ስለጮህክአይሳካልህም። የዚህን ጊዜ አላህ ጥሎ አይጥልህም። ነገር ግን ኒያህን አስተካክለህ መሆን አለበት።
ነቃ በል!!!!!!!!!

#Tg
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
📌ስለ ሂጃብ አጠር ያለች ፅሁፍ ተዘጋጅቷል ለማንበብ ዝግጁ ናቹ?
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
📌ስለ ሂጃብ አጠር ያለች ፅሁፍ ተዘጋጅቷል ለማንበብ ዝግጁ ናቹ?
🌷አል ሂጃብ🌹
"ሒጃብ" ማለት ትርጉሙ የቅርብ ዘመዶቿ ካልሆኑ ወንዶች ሰውነቷን መሸፈን ማለት ነው።አሏህ እንዲህ ይላል፦
ولا ييدين زينتهن إلا ما ظهر منها وليضربن بخمرهن على جيوبهن ولا يبدين زينتهن إلا لبعولتهن أو ءابائهن أو ءاباء بعولتهن أو أبناء بعولتهن أو إخوانهن))النور ٣١
"...ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ።ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው  ላይ ያጣፉ።(የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው።"(አን-ኑር:31)

በሌላ የቁርኣን አንቀፅ አሏህ እንዲህ ይላል፦
((وإذاسألتموهن متعا فسآلوهن من وراء حجاب))الأحزاب:٥٣
"ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጨይቋቸው።"(አል-አህዛብ:53)
ሂጃብ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ የሚፈለግበት ሴትን ልጅ የሚሸፍን እንደ አጥር ወይም መዝጊያ ወይም ልብስ ማለት ነው።የቁርኣን አንቀፁ የወረደው በነብዩ ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም ባለቤቶች ቢሆንም መመሪያነቱ ግን ለአጠቃላይ አማኝ ሴቶች ነው።ለምን ቢባል?አሏህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ምክንያቱን እንዲህ ሲል ይገልፃል፦
((ذالكم آطهر لقولبكم وقولبهن))الأحزاب:٥٣
"ይህ ለልቦቻችሁ፤ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው።"(አል-አሕዛብ:53)

ምክንያቱ ሁሉንም ሴቶች የሚያካትት መሆኑ መመሪያነቱ(ህጉ) ለሁሉም ለመሆኑ ማስረጃ ነው።አሏህ እንዲህ ይላል፦
((يأيها النبي قل لأزاجك وبناتك ونساء المؤمنين يدنين عليهن من جلابيبهن))الأحزاب:٥٩
"አንተ ነቢዩ ሆይ!ለሚስቶችህ፤ለሴት ልጆችህም፣ለምእመናን ሚስቶችም መከናነቢያዎቻቸውን በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው።"(አል አህዛብ:59)

💥ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ መጅሙዑል ፈታዋ 22ኛው ጥራዝ ገፅ 110-111 ላይ እንዲህ ይላሉ፦"ጅልባብ ማለት መከናነቢያ ሲሆን ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ እና ሌሎችም ኩታ እያሉ ሲጠሩት ተራው ሰው ሽርጥ ይለዋል።ይህም እራስን እና ሌላውን ሰውነት የሚሸፍን ትልቅ ሽርጥ ነው።ከአቡ ኡበይዳ እና ከሌሎችም እንደተወራው ከራሷ በላይ ወደ ታች የምትለቀው ሆኖ ሁለት አንኖቿን ብቻ ግልፅ የምሸታደርግበት ነው፤ኒቃብም የእሱው አካል ነው።"
💥ሴት ልጅ የቅርብ ዘመዶች ካልሆኑ ወንዶች ፊቷን መሸፈኗ እና ዋጂብ ስለመሆኑ ከሃዲስ ካሉት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ የአዒሻ ሐዲሥ ነው። ኣዒሻ አሏህ ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ትላለች፦

وكان الركبان يمرون بنا ونحن مع رسول الله صلى الله عليه وسلم محرمات،فإذا حاذوا بنا سدلت إحدانا جلبها من رأسها على وجهها،فإذا جاوزنا كشفناة>>
"ከአሏህ መልዕክተኛ ጋር ሐጅ ላይ ሁነን ሳለን ጋላቢዎች ባጠገባችን ሲያልፉ ከመካከላችን አንዷ ጅልባቧን ከራሷ በፊቷ ላይ ትለቃለች፤ሲያልፉን እንገልጸዋለን።(አቡዳዉድ:አሕመድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።)
💥ሴት ልጅ የቅርብ ዘመዶቿ ካልሆኑ ወንዶች ፊቷን መሸፈን ግዴታ መሆኑን የሚያመላክቱ ከቁርኣን እና ከሱና ብዙ ነው።በዚህ ዙሪያ ላይ የሚከተሉትን ኪታቦች እጠቁምሻለሁ፦
☀️"ሪሳለት አል-ሒጃብ ወሊባስ ፊ ሰላህ" የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ
☀️"ሪሳለቱል- ሒጃብ"የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ዐብደሏህ ኢብኑ ባዝ
☀️"ሪሳለቱ አሷሪም አል መሽሁር ዐለል መፍቱኒነ ቢሱፉር"የሸይኽ ሐሙድ ኢብኑ ዐብደሏህ አት-ቱወይጅሪ
☀️"ሪሳለቱል-ሒጃብ" የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን
እነዚህ መጣጥፎች በቂ የሆነ ማስረጃ ይዘዋሉ።
💥አንቺ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ!ያንቺን ፊት መግለጥ የፈቀዱልሽ ዑለሞች አባባላቸው ሚዛን የተደፋበት ከመሆኑም ጋር እነሱም ቢሆን ፈተና አለመኖሩ የሚታመንበት ከሆነ ይላሉ።ፈተና ደግሞ የሚታመን አይደለም በተለይ በዚህ ዘመን የዲን መካሪ የሆኑ ወንዶች  እና ሴቶች ባሉበት፣ሃያዕ (እፍረት) ባነሰበት፣ወደ ፊትና የሚጣሩ በበዙበት፣ሴቶችም የተለያዩ የመዋቢያ አይነቶችን ፊቶቻቸው ላይ መጠቀም የተካኑ መሆናቸው ወደ ፊትና ከሚጣሩ ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው።
💥አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ!ከመገላለጥ ተጠንቀቂ! (በአሏህ ፍቃድ) ከፈተና ጠባቂሽ የሆነውን ሂጃብሽን ያዥ።በንግግራቸው ግምት ከሚሰጣቸው የጥንትም ይሁን የአሁን ዐሊሞች ለእነዚህ ተፈታኝ ለሆኑ ሴቶች የወደቁበትን የፈቀደ የለም።
💥አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ሂጃብ የሰው ውሻ ከሆኑ እና የልብ በሽታ ካለባቸው ሰዎች ከሚያመነጩት መርዛማ እይታ ይጠብቅሻል ሒጃብሽን በፅናት ከያዝሽው የተቃጠለ ስሜትን ካንቺ ይነቅልልሻል።ሂጃብን ለምትዋጋ ወይም የሂጃብን ጉዳይ ቀለል አድርጋ ለምታይ ዓላማ አዘል ተጣሪ ቦታ አትስጪ።እሷ ላንቺ የምትመኝልሽ ሸር ነው።አሏህም እንዲህ ይላል፦
((ويريد الذين يتلعون الشهوات أن تميلو ميلا عظيما))النساء:٣٧
"እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ።"(አን-ኒሳእ:27)

#Tg
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
☀️በቲክቶክ ወጥቶ መጨፈር ጀግንነት ሳይሆን ጅልነት ነዉ እህቴ ይቅርብሽ ጭፈራ አያዋጣሺም የዛሬ አድናቂሽ አጨብጫቢሽ ነገ አሏህ ፊት አይጠቅምሽም  ተመለሽ እህቴዋ ወደ ጌታሽ ተመለሺ ይብቃ መጃጃሉ!
💥الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد.
💥ብዙ ሴቶች ሂጃብ አስተካክላችሁ ልበሱ! ፎቶም ሆነ ቪዲዮ ሚዲያ ላይ አትልቀቁ ሲባሉ

ቀንታችሁ ነው ይላሉ አሏሁ ሙስተዓን አሁን ወደ ጀሀነም የምትሮጥ ሴት ምኗ ያስቀናል  አሁን የረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እርግማን ውስጥ የገባች ሴት ምኗ ያስቀናል !!

ሀቂቋ የሚያስቀኑትስ አሏህ ባዘዛቸው ቀጥ ያሉ እንስቶች

የኔ ሙተነቂብ እመሪበት  
በኒቃቡ
💥እህቴ ሆይ!
መጠንቀቅን ተጠንቀቂ በስልክ መጀናጀን ሚባለውን ነገር ያ ወጣት ሴት እና ወንዶች የተፈተኑበት የሆነው።ሀይልም ይሁን ዘዴ የለም በአሏህ ቢሆን እንጂ። ተጠንቀቂ ከሰው ተኩላዎች እነዚያ ማራማ በሆኑ ጣፋጭ ንግግራቸው የሚያታልሉሽን  ለምሳሌ ምን ይልሻል፦እወድሻለው የኔ በላጭ፣ልቤን ወሰድሽው፣ቀንና ለሊት አንቺን ነው ማስበው፣መተኛት አልቻልኩም፣ካየሁዋቸው ሴቶች ሁሉ ቆንጆ አንቺ ነሽ፣ሌላም ሌላም
እሱ በጣም ውሸታምና ኩራተኛ ነው።ካንቺ ውጪ ብዙ አይነት ሴቶችን ያውቃል ላንቺ ያለሽን ለነሱም ይላቸዋል።ነገር ግን ሀጃውን ማሳካት ስለሚፈልግ  በቀላሉ እግሩ ስር ይቀብርሻል፣እንደፈለገ አድርጎ ሚጫወትብሽ አሻንጉሊት ያደርግሻል።
ስሜቱን ካረካ በዉሀላ የማያውቅሽ አድርጎ ከኋላው ይወረውርሻል።እንደዛ ለሊቱን አልተኛሁም እንዳላለሽ፣አገባሻለው ብሎ እንዳልቀጠረሽ።በድንገት ግን ጨዋና የተከበረች የላቀች እንስትን ማግባቱን ትሰሚያለሽ።እሱ እንደሆነ ከጅምሩም ወዶሽ ስላልመጣ ምንም አይመስለውም አንቺ ግን ከሱ ውጪ ወንድ እንደሌለ አድርገሽ አስበሽ ስለ ነበር በጣሙን ትጎጃለሽ ትፀፀቺያለሽ።ክብርሽ ግን ላይመለስ አሸልቧል።እድሜ ልክሽን እያለቀስሽ ተኖርያለሽ። አስተውይ ውዷ እህቴ ይህ ፊትና ከመከሰቱ በፊት!
አሁን አሁንማ ሱብሀነሏህ! በዲን ስም ቀርበዋት ህይወቷን አመሠቃቅለው መውጣት ጀምረዋል።አኺ ግን ምን ብትበድልህ ነው እንዲህ ምትጨክንባት እህትህ ላይ ቢሆን ይህ እነዲደርስ ትፈልጋለህ???አትፈልግም ሀቂቃ እቺም እኮ ያንተ እህት ባትሆንም የሌላ ሠው እህት ናት።አሏህን ፈርተህ ክብሯንና ማንነቷን ጠብቅላት።የእምባዋ የመከፊያዋ ሰበብ አትሁን።ከየት በኩል መጣ ሳትል ያንተንም ህይወት የሚያመሰቃቅል ሙሲባ  ሊከሰትብህ ይችላል እናም ረቡናን ፈርተህ  ከእንደነዚህ ስራዎች  ታቀብ።።

☀️እህቴ አንቺም ወደ አሏህ ተመለሺ ተስፋም እነዳትቆርጪ የአሏህ ራህመት ሁሌም ክፍት ነው።ሰው ሆኖ ማይሳሳት የለም።ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም አደል ሚባል?ሰለዚህ ወደ አሏህ ሽሺ ጥሩ ጓደኞችንም ተጎዳኚ የሸይጧን እና የነፍሲያ በሮችን ዘጋጊ።
📌አሏህ ሽርክን እንጂ ሌሎችን እንደሚምር በቃሉ ተናግሯል።ሽርክንም ከቶበቱ ይቅር የሚል ጌታ ነው።ስለዚህ ጊዜ አለሽ ቶሎ ወደ አላህ ተመለሺ።
አኺ ላንተም ጊዜ አለህ ወደ አሏህ   ተመለስ ዱዐም  አድርግ !!!
ወንጀሉ ላሳሰበው ሰው ትልቅ ብስራት

«የአረፋ ቀን ፆም የሁለት አመት ወንጀል ያብሳል።»

ትንሽ ሰርቶ ብዙ ማትረፍ ማለት ይህ ነው።

ከአቡቀታዳህ ተይዞ እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦ {ያለፈውንም የወደፊቱንም (የሁለት) አመት ወንጀል ያብሳል}።
ሙስሊም ዘግቦታል።

ይህ ሀቂቃ ለተጠቀመበት ሰው ትልቅ እድል ነው።

√√የአረፋ ቀን ማለት፦

⸕ሰዎች ከጀሀነም ነፃ የሚወጡበት
⸕ወንጀሎቻቸው በብዛት የሚማርበት
⸕ዱአቸው ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት
⸕አረፋ ተራራ ላይ በቆሙት ባሮቹ አላህ የሚፎክርበት
⸕የሀጅ ዋና ሩክን የሆነው አረፋ ተራራ ላይ የሚቆምበት
⸕አላህ እዝነቱ ለባሮቹ የሚቸርበት የአመቱ ምርጥ ቀን ነው።

⁌ይህንን ወሳኝ ቀን፦
☞ቀኑን በመፃም
☞ዱአ በማብዛት
☞ቁርአን በመቅራት
☞ዚክር በመዘከር
☞ሶደቃ በመስጠት
☞ተክቢራ በማብዛትና
👉በሌሎችም መልካም ስራ ላይ ሆነን ልናሳልፈው ይገባል።

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
እንኳን ለ1445ኛው ለዒድ አል-አድሓ ለዐረፋ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኝላችኋለን።
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
            عيدكم مبارك!!
أعاده الله علينا وعليكم وأنتم في صحة وعافية وإيمان

ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሐል-አዕማል

عيد مبارك
ዒድ- ሙባረክ🌷🌷🌷


            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam