ቴዎፍሎስ theophilus
216 subscribers
147 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ወንድማዊ ምክሬ ነዉ
አንዳንድ ክርስቲያኖች ለምንድነዉ ወደ ቤተክርስቲያን የማትሄዱት ሲባሉ እዚህ #ቸርች እንዲህ ችግር ስላለበት :እዚያ ደግሞ እንደዚያ እያሉ ቸርች የማይሄዱበትን ምክንያት ይዘረዝራሉ
አንተም ከእነዚህ ወገን ነህ? #church ለመሄድ ፍፁም የሆነች ቤተክርስቲያንን እየፈለክ ነዉ? ብዙም አትልፍ እንከን የሌለባትና #ፍፁም የሆነችን #ቤተክርስቲያን አታገኝም።ፍፁም የሆነች #church ብታገኝም እንኳን ወደ እዛ #church እንዳትሄድ አንተ #ፍፁም ስላልሆንክ የእነርሱን ፍፁምነታቸዉን እንዳታሳጣቸዉ። በአጭሩ ምን ልልህ መሰለህ ፍፁም የሆነን ነገር የትም #አታገኝም። ስለዚህ ነገሮች ፍፁም እንዲሆኑልክ አትጠብቅ። ይልቁንስ ህብረት ልታደርግ ያሰብክበት ወይም እያደረክ ያለበት #church መፅሐፍ ቅዱሳዊና ጤናማ አስተምሮን እንደሚከተሉ እርግጠኛ ሁን።ይህንን የሚከተሉ ከሆነ በዛን ካሉ ቅዱሳን ጋር ህብረት አድርግ።


#ከፀደቀ #መንፈሰ