ቴዎፍሎስ theophilus
216 subscribers
147 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ቄስ #ዶ/ር #ቶሎሳ #ጉዲና

" በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5:17)
#በእግዚአብሔር #ፊት #ፃዲቅ ክፍል 5 ነገ ይለቀቃል
እግዚአብሔር እኛን የወደደበትን ፍቅር በፍፁም አብራርተን ልንጨርሰዉ አንችልም። ምክንያቱም በዚህ ፍቅር ማንንም ወደን ስለማናዉቅ። በዚህ ፍቅር ልክ ማንም እርስ በእርስ ሲዋደድ ስላላየን። ከምንረዳዉ በላይ ጥልቅ ነዉ ከምናስበውና ከምንገምተው በላይ ትልቅ ነዉ።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
አንድ ሰዉ ስለ እግዚአብሔር ፀጋና፣ፅድቅ ተምሮ ታዲያ ሀጢአትን ብሰራ ምን ችግር አለዉ? ብሎ ካሰበ ትምህርቱ በፍፁም አልገባዉም። በክርስቶስ መፅደቃችን በገባን ልክ ራሳችንን ለፅድቅ ተገዢዎች አድርገን ለማቅረብ እንተጋለን።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ዶ/ር መለሰ ወጉ

ከ50 በላይ ቤተ ክርስቲያናትን ተክሏል!

ከ60 ዓመት በላይ ወንጌልን አገልግሏል!

ከ30 በላይ መጻሕፍት ጽፎአል!

ከ30 በላይ መለስተኛ መጻሕፍት ዐሳትሞአል!

ከ200 በላይ "የሕይወት መስታውት"
መጽሔት ጽሑፎች!(በመጽሔቶቹ የታተሙት ጽሑፎች ሁሉ የእርሱ ናቸው)::

ከ400 በላይ በካሴትና በሲዲ የተዘጋጁ ትምህርቶች አስተላልፎአል!

" በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5:17)
እግዚአብሔር መልካምን ነገር ያደርጋል
#ጴጥሮስ #ሲያምን #ተራመደ #ሲፈራ #ደግሞ #መስጠም #ጀመረ
ማመንም አለማመንም በህይወት ላይ የሚታይ ለዉጥን ያመጣል።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
#እንደ #ፀና #ቀረ በመጋቢና ዘማሪ #ተከስተ #ጌትነት ግለ ታሪክ የተፃፈ መፅሐፍ። በጣም የወደድኩት መፅሐፍ ነዉ። ዛሬ ልጀምረዉና ቀስ ብዬ እጨርሰዋለሁ ብዬ ማንበብ ጀምሬ ራሴን የመጨረሻዉ ገፅ ላይ አገኘሁት።
ተኬ በዚህ መፅሐፉ ከድካሙም ከብርታቱም እንድንማር በታማኝነት ዘግቦልናል። እንዲህ አይነት ግለ ታሪክ የያዘ መፅሐፍ በሀገራችን ብዙም አልተለመደም። በተለይም በእኛ በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ። ለብዙዎች ዓርአያ የሚሆን መፅሐፍ ነዉ ብዬ አስባለሁ።ተኬ ይህንን መፅሐፍ እንዲፅፍ መኖሪያዉን አሜሪካ ማድረጉ የጠቀመዉ ይመስለኛል። በዚህ መፅሐፍ የተኬን ቅንነት፥ታማኝነት፥ ትህትና፥የእግዚአብሔርን ዉለታ የማይረሳ አመስጋኝ እንደሆነ አስተዉያለሁ።#ተኬ የእግዚአብሔር ሞገስና እረዳትነት እንደ አርሞንዔም ጠል የረሰረሰ ሰዉ እንደሆነ ያሳብቅበታል።  እግዚአብሔርን ስለ አንተ እናመሰግነዋለን።
#እንደ #ፀና #ቀረን እንድታነቡት ግብዣዬ ነዉ።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:8)
በሞቱ ሞታችን ተሽሮ የዘላለምን ህይወት ተቀበልን
መልካም የፍሲካ በዓል
፦ሳምራዊቷን ሴት ስለ ዉሃ አዉርቷት እኔ የሕይወት ዉሃ ነኝ አላት።
፦ከ5ሺ የሚልቁትን ህዝብ በ2 አሳና በ5 እንጀራ በተአምራቱ ከመገባቸዉ በኃላ የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ አላቸዉ
፦የማርታና የማርያም ወንድም የሆነዉን አልአዛርን ከሞት ከማስነሳቱ በፊት ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ አለ።

፦ፈፅሞ ሊገባን የማይችለዉን ታላቁን የመለኮትን ጥበብ በሚገባን ቋንቋ የተናገረን እስኪገባን ድረስ ያስረዳን ኢየሱስ ይባረክ።


#ከፀደቀ #መንፈሰ
#ከሰለሞን #የሚበልጥ
ሁለት ሴቶች በንጉስ ሰለሞን ፊት ቀርበዉ መከራከር ይጀምራሉ ሁለቱም በአንድ ቤት ዉስጥ ነዉ የሚኖሩት። ሁለቱም በቅርቡ ነዉ የወለዱት። አንደኛዋ እናት ግን በልጇ ላይ ተኝታበት ገድላዉ ነበር። ደኅነኛውም ወስዳ ለራሷ አደረገችዉ የሞተዉን ደግሞ ከወሰደችበት የእናት እቅፍ ዉስጥ አኖረችዉ።እናትየዉም ስትነቃ የእርሷን አይደለም ያቀፈችዉ የኔ በህይወት ያለዉ እንጂ የሞተዉ አይደለም ይሄንንማ አልቀበልም ብላ ለመከራከር በንጉስ ሰለሞን ፊት ይዛት ቀረበች። ንጉስ ሰለሞንም ይህንን ታሪክ እንደሰማ ደኅነኛውን ሕፃን ለሁለት ከፍላችሁ ለአንዲቱ አንዱን ክፍል፥ ለሁለተኛይቱም ሁለተኛውን ክፍል ስጡ አለ።" በዚህም ጥበቡ በህይወት ያለዉ ህፃን የማን እንደሆነ አወቀ ለእናቱም ልጇን ሰጣት።
#ተወዳጆች #ኢየሱስ ከሰለሞን #ይበልጣል እርሱ ቢሆን የሞተዉ ህፃን የት አለ? ነበር የሚለዉ ምክንያቱም ህይወት መስጠት የሚችል ስለሆነ
#ኢየሱስ #ከሰለሞን #ይበልጣል

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ዛሬ በእድሜዉ ትንሽ ገፍ ያሉ ምናልባት ከ60ዎቹ ያለፉ አንድ አባት በአጋጣሚ አጊንቻቸዉ በጌታ እንደሆንኩኝ እንኳን ሳይጠይቁኝ፣ ስለ ጌታ ኢየሱስ መናገር ጀመሩ እኔም፣ የመስማት ፍላጎት እንዳለኝ፣ ገለፅኩላቸዉ ትኩረቴንና ጆሮዬን ሰጠዋቸዉ።በጌታ እንደሆንኩኝና እንደማገለግልም ነገርኳቸዉ። እሳቸዉም ስላገልግሎቴ ትንሽ ላጫዉት ምናልባት ለአንተ ሊጠቅምህ ይችላል አሉኝ። ለ40 አመታት ያህል የእግዚአብሔርን መንግስት በድካሜም በብትርታቴም አገልግያለሁ፣ነገር ግን እንዳገለገልኩት ዓመታትና፣ በዉስጤ እንዳለው አቅም ልክ ፍሬያማ ልሆን አልቻልኩኝም አሉኝ። ምክንያቱ ምን መሰለህ አሉኝ የአገልግሎት አብዛኛዉን እድሜዬን መለወጥ ከማልችለዉ ነገር ጋር ስታገል ነዉ ያሳለፍኩት ፣ያንን ነገር አሁን ላይ ሳስበዉ ይቆጨኛል፣መለወጥ የማልችለዉን ነገር ትቼ መስራት ወደምችላቸዉ ባተኩር በብዙ ፍሬያማ እሆን ነበር አሉኝ፣አሁን ላይ በህይወት ያሉትን ደግሞም ያለፉትን በምድሪቱ ላይ ታላላቅ በጎ ተፅዕኖ የፈጠሩትን የእግዚአብሔር ሰዎች ጠቀሱልኝና ፣ከእዚህ ከአብዛኛዎቹ ጋር አገልግሎት፣ በተመሳሳይ ጊዜ ነዉ የጀመርነዉ አሁን እነርሱ በአብዛኛው አማኝ ልብ ዉስጥ አሉ ምክንያቱም ለብዙዎች የመባረክና፥ የመታነፅ፥ ብሎም ለብዙ አገልጋዮች የመነሳት ምክንያት ስለሆኑ፣ ከኢትዮጵያ አልፈዉ በአለም ዙሪያ ዛሬም ቢሆን የእግዚአብሔርን ሀሳብ ያገለግላሉ እኔ ግን በዚያን ጊዜ ልለዉጠዉ ከማልችለዉ ነገር ጋር እታገል ነበር፣ በዙሪያዬ የነበሩ ሰዎች በአገልግሎቴ ብዙም ደስተኛ አልነበሩም፣ እነርሱን ለማስረዳት በአንድ ቤተክርስቲያን ቁጭ ብዬ 27 አመት ፈጀብኝ ከ27 በኃላ ነዉ ነገሩ እንደማይለወጥ የገባኝ፣ አስበከዋል የኔ ልጅ ከ27 አመት በኃላ ልክ እንዳልነበርክ ሲገባህ፣ ለካ ብዙ ስራ መስራት እችል ነበር አሉኝ። የጠቀስኩልህ በህይወት ያሉም የሌሉም አብረዉኝ አገልግሎት የጀመሩ አገልጋዮች በምድሪቱ ላይ ታላላቅ የሆነን ተፅዕኖን የፈጠሩት ሁሉም ሰዉ ስለተቀበላቸዉ አልነበረም ወደሚቀበሏቸዉ እየሄዱ እንጂ፣ በፅድቅና በእዉነት እያገለገሉ ብዙ ትችትና፥ ነቀፌታ፣ስድብ፣ድብደባም ጭምር ይደርስባቸዉ ነበር፣ እነርሱ ግን ጥሪያቸዉ ላይ ብቻ ነበር ትኩረት ያደርጉ የነበረዉ። ለዛ ነዉ ተፅእኖን መፍጠር የቻሉት። እኔ ግን ያልተቀበሉኝ እንዲቀበሉኝ ስታገልና፣ ሳስረዳ እድሜዬን አባከንኩ ወደሚሰሙኝ ብሄድ ብዙ እንደማተርፍ አሁን ገና ነዉ የገባኝ አሉኝ።የሳቸዉን ታሪክ በሀዘን ስሜት ሆኜ ብሰማዉም ደግሞ ካሳለፉት ህይወት ብዙ ነገር ተምሪያለሁ። ምናልባት ይሄ መልእክት አንድ ሰዉ ሊጠቅም ይችላል ብዬ ስላሰቡኩኝ ነዉ የፃፉኩት።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ብትሆንም በፅድቅና በታማኝነት ብታገለግልም ሁሉ ይቀበሉኛል ብለህ አታስብ። ሁሉ ይቀበለኝ ካልክ የማይቀበሉህ ሰዉ ሲገጥሙህ ልብህ ይጎዳል እነርሱ ደግሞ እንዲቀበሉህ ስታስረዳህ ለሚሰሙህ መልእክትህን ሳታሰማ ከጊዜህ ጋር ትተላለፍለህ። የምናመልከዉና የምንከተለዉስ ጌታ ሲያገለግል መቼ የሰሙት ሁሉ ተቀበሉት?

መለወጥ በማትችለዉ ጉዳይ ላይ እድሜህን እትጨርስ መስራት በምትችለዉ ጉዳይ ላይ አተኩር።አንተን የሚጠብቁ ብዙ ስራዎች ስላሉ።

በእየሱስ ስም ዘመናችሁ አይበላ አሜን።
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ሰይጣን እዉነተኛ የሆነዉን ነገር በተሳሳተ መንገድ መጠቀም ብቻ አይደለም አላማዉ እዉነተኛ የሆነዉን ነገር ሀሰተኛ ነዉ እስክልን ድረስ በብርቱ ይሰራል። ሀሰተኛ አገልጋዮችን የሚያበዛዉ እነርሱ ሀሰተኛ ናቸዉ እስክንል ብቻ አይደለም እዉነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮችን እንደ ሀሰተኛ አገልጋዮች እስክንቆጥራቸዉ ድረስ ነዉ ሰይጣን በረቀቀ መንገድ የሚሰራው። ማለትም እዉነተኞችን እንዳንሰማቸዉ፥ እንዳናከብራቸዉ፥ በአጠቃላይ ሁሉንም የእግዚአብሔር አገልጋዮቹን በሀሰተኛ መነፅር እንድናያቸዉ የሰይጣን ትልቁ የቤት ስራዉ ነዉ። ደግሜ እላለሁ እንዳለው ሐዋርያው ጳዉሎስ እኔም ደግሜ እላለሁ ሰይጣን እዉነተኛዉን ነገር በተሳሳተ መንገድ ተጠቅሞ እዉነተኛዉ ከሆነዉ ነገር ጋር ሊያለያየን ነዉ የሚፈልገዉ። እጣቢዉን ከነ ልጁ እንዳትደፍዉ ተጠንቀቅ። አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ያሉ አገልጋዮች እስኪመለኩ ድረስ የሚፈሩ አሉ። እነርሱ ሲመጡ ምዕመኑ ይንበረከካሉ አምልኮም ሲደረግለትም ያየሁት አለ ይህ ፈፅሞ ስህተት ነዉ። የዚህ ልኩ ግን እዉነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮችን መናቅና አለማክበር አይደለም። መፅሐፍ ቅዱስ እዉነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ልክ በሆነ መንገድ እንድናከብርራቸዉ ያዘናል " እንግዲህ በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፥ እርሱን የሚመስሉትንም አክብሩአቸው፤"
( ፊል2:29)" በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።"(1ኛ ጢሞ 5:17) ሀሰተኛ ነብያት አሉ የሚለዉ ድምዳሜህ እዉነተኞችን ባለመቀመል እንዳይንፀባረቅ። ምክንያቱም አንዳንድ ሰዉ ሀሰተኞችን ከመቃወም ብዛት ፈፅሞ እዉነተኞችን እስካለመቀበል የደረሱ ስላሉ።
የሰይጣንን ሀሳብ እንዳንስተዉ እግዚአብሔር በጥበብ መንፈስ ይሙላን አሜን።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
በአንዳንድ ቤተክርስቲያን በአገልግሎትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከተገኘዉ የዛን ቤተክርቲያን አገልጋዮችን በፍፁም ሳልጠይቅ የማላልፈዉ ጥያቄ አለ እርሱም የወንጌል ስርጭት ህብረትና Bible study team እዚ church ምን ይመስላል የሚል የተለመደ ጥያቄ አለኝ፣ከጠየኳቸዉም በኃላ በምላሻቸዉም ተመርኩዤ ሀሳቤን አንፀባርቃለሁ። ህብረቱ  ከሌለ ለመጀመር እንቅስቃሴዉን እንዲያደርጉ፣ ካለ ደግሞ ያላቸዉን experience እንዲያካፍሉኝ እጠይቃቸዋለሁ። እኔ በ bible study እና በወንጌል ስርጭት ህብረት በብዙ ስለተጠቀምኩ ፥ስለታነፅኩ፥ስለተሰራዉበት ማዉራት አይሰለቸኝም።
ምግብ ቤት ገብተን ጥሩ ምግብ ካገኘን ለጠየቁንም ላልጠየቁንም ስለዛ ምግብ ቤት ማዉራታችን አይቀርም። ጥሩ ነገር ለተጠቀምንበት ምላሽ እኛ ለጓደኞቻችን ወደ እዛ ቤት እንዲሄዱ የምንሰጠዉ ምስክርነት ነዉ። በእነዚህ ሁለቱ ህብረት በብዙ ተጠቅሜያለሁና እናንተም  ተጠቀሙ የሚለዉ ለተጠቀምኩበት የምሰጠዉ የዘወትር ምስክርነት ነዉ። በቤተክርስቲያናችሁ ካሉ የወንጌል ስርጭትና Bible study team join አድርጉ። እናንተም ነገ በብዙ ተጠቅማችሁ ምስክር እንደምትሆኑ አልጠራጠርም።
ብዙ ወዳጆቼን በወንጌል ስርጭት ህብረት ምክንያት አግንቻለሁ፣ ተግባብቺያለሁ፣ስለዚህም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
#ከፀደቀ #መንፈሰ