ቴዎ ፍሎስ theophilus
219 subscribers
144 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ሰላም ለእናንተ ተወዳጆች
ነገ በደረስንበት በሚል ርዕስ አዲስ ትምህርትን እንማራለን። ይጠብቁ
ሰይጣን ሰዉን ሀጢያት እንዲሰራ ይገፍፍና ሀጢአት ካሰራ በኃላ ደግሞ ለምን ሰራህ ብሎ ይከሳል።

ከፀደቀ መንፈሰ
ሁለት አመት የሞላዉ ይመስለኛል በአንድ እስር ቤት ዉስጥ ባለ አማኞች በሚሰበሰቡበት አዳራሽ የመስበክ እድል አጊንቼ ነበር: ስብከቴንም እንደጨረስኩ እድሜዉ በግምት ወደ 50 የሚጠጋ ተለቅ ያለ ሰዉ ፊቱ ላይ በሚነበብ ድንቅ በሆነ ፈገግታዉ አጥብቆ ሰላም አለኝ አጠገቡም ወዳለ ወንበር በመጠቆም ቁጭ እንድል ጋበዘኝ እኔም አንዳች ለእኔ ሊነግረኝ የፈለገዉ ነገር እንዳለ ስለገባኝ በደስታ ተቀመጥኩኝ።እርሱም ቀበል አድርጎ ትንሽ ደቂቃ ብትሰጠኝ እግዚአብሔር በህይወቴ የሰራዉን ስራ ላወራህ ፈልጌህ ነበር አለኝ እኔም በደስታ እንደምሰማው ገለፅኩለት:ያሳለፈዉ ህይወት ፊልም ወይም መፅሐፍ ሊሆን የሚችል ሚደንቅ ታሪክ ነዉ። እስር ቤት ከመግባቱ በፊት በጣም ሀብታም ነበር: የተለያዮ ድርጅቶችና መኪኖችም ነበሩት ሀብቱን ያጣበትንና እስር ቤት የገባበትን ምክንያት አጫወተኝ። በተስመጨረሻ ያለኝ ነገር ልቤ ዉስጥ ቀረ: ያለኝን ሀብት በአብዛኛዉ ከእጄ ላይ ተወስዶ ለእስር ተዳረኩ: እዚህ እስር ቤት ግን ኢየሱስ አገኘሁት: እርሱንም አወኩት እርሱ ደግሞ ትላንት በእጄ ላይ ካለዉ ሀብት እጅግ በለጠብኝ አሁን ገና ባለጠጋ ሆንኩኝ: ጳዉሎስን በደማስቆ ያገኘ ጌታ እኔን ደግሞ በእዚህ በእስር ቤት አገኘኝ። በኢየሱስ ያገኘሁት ነፃነትና ሰላም እስር ቤት ከመግባቴ በፊት ካለኝ ነፃነትና ሰላም በእጅጉን ይበልጣል። በእዚህ እስር ቤት ቃሉን እለት እለት አነባለሁ ሰፊ ሰዓትም እፀልያለሁ: አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ከዚህ እስር ቤት ለመዉጣት ጥቂት ቀናቶች ነዉ የቀሩኝ ከዚህም በኃላ ባለኝ እድሜና ጉልበት ሁሉ የእግዚአብሔርንም መንግስት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ አለኝ።ሲናገር ፊቱ ላይ የሚንፀባረቀዉ ደስታ ዋዉ.😮 የሚገርም ነዉ መዝናኛ እንጂ እስር ቤት ያለ አይመስልም: ንግግሩንም ሳይጨርስ የመዉጫ ሰዓታችን ስለደረሰ ለማቋረጥ ተገደድንና ተሰናበትኩት። ከዚህ ሰዉ ህይወት እግዚአብሔር ብዙ ነገር አስተማረኝ: ስለ እርሱም እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ተመለስኩ።

ተወዳጆች በኢየሱስ ያገኘነዉ ነፃነት በምንም ዋጋ የማናገኘዉ ማንም ደግሞ የማይሰጠን ትልቁ ሀብታችን ነዉ።

ኢየሱስ ማግኘት ምድር ላይ ካለ የትኛዉንም ሀብት ከማግኘት ይበልጣል።

ኢየሱስ በእዉነት ከሁሉ በላይ ነዉ።
ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም
የጌታ ፀጋ አላነሰንም
ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ በእጥፍ
አይተኛም እኛን ሚጠብቅ

ዘማሪ #ደረጀ #ከበደ
ርዕስ #በእግዚአብሔር #ፊት #ጻዲቅ ክፍል 1

የእግዚአብሔር ፅድቅ ክርስቶስ አጸደቀን

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 24_06_2016
ርዕስ #በእግዚአብሔር #ፊት #ጻዲቅ ክፍል 2

የእኛ ፅድቅ በእግዚአብሔር ፊት
#ለመፅደቅ #ፅድቅን #ያዋጣ #የለም
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 28_06_2016
በስራዬ ነዉ መፅደቅ የምፈልገዉ የሚሉ ሰዎች እግዚአብሔር የሚፈልገዉን የፅድቅ ልክ ቢያዉቁ ያለ ማንገራገር የእግዚአብሔር ፅድቅ የሆነዉን ክርስቶስን ይቀበሉ ነበር።
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ርዕስ #በእግዚአብሔር #ፊት #ጻዲቅ ክፍል 3

#ፅድቃችን #በእግዚአብሔር #ፊት

እግዚአብሔር #ጻዲቅ ነዉ
ማነዉ በፊቱ #የሚቆመዉ?
ቀን 2_07_2016
አራት መነኩሴዎች ከሚኖሩበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ ጉዞን ይጀምራሉ፣ አርፍደዉ ስለተነሱ የፈለጉበት ቦታ በጊዜ ስላልደረሱ፣ እዛዉ በደረሱበት ቦታ አረፍ ብለዉ ለመሄድ ይወስናሉ፡ ሰዓቱም ስለመሸ ምሽቱንም ባሉበት ቦታ ድንኳን ይዘዉ ስለነበር ድንኳናቸዉ ዘረጉ። ከመተኛታቸዉ በፊት ለመፀለይ ይስማማሉ ከመፀለያችን በፊት አንድ ህግ እናዉጣ አለ አንደኛው መነኩሴ ይህም ህግ ሁላችንም የምንፀልየዉ በዉስጣችን ነዉ ምን አይነት ነገር ቢፈጠር ማዉራት አይፈቀድም አለ፣ የቀሩት ሁሉም በወጣዉ ህግ ተስማምተዉ በዉስጣቸዉ ድምፅ ሳያሰሙ መፀለይ ይጀምራሉ። በጣም ስለጨለመ በድንኳናቸዉ ዉስጥ ሻማ ለኩሰዉ ነበር የሚፀልዮት። ትንሽ እንደቆዮም ከዉጪ በመጣ ንፍስ እየበራ የነበረዉ ሻማ ያጠፍዋዉ።
አንደኛዉ መነኩሴ ከመካከላቸዉ ወይኔ ሻማዉ እኮ ጠፍ አለ፣ ሁለኛዉ መነኩሴ ቀበል አድርጎ በፀጥታ ነዉ መፀለይ ያለብን አለ፣ሶስተኛዉ ደግሞ እባካችሁ ዝም እንበል ያወጣነዉን ህግ እየጣሳችሁ እኮ ነዉ አለ፣ አራተኛዉ መነኩሴ በመጀመሪያ ፈገግ ብሎ እኔ ብቻ ነኝ ያላወራሁት አለ።
ይህንን ታሪክ ያነሳሁት አንድ መልእክት ለማስተላለፍ ነዉ።
በዚህን ጊዜ የአገልጋዮችን ስህተት ወደ social media ይዞ መጥቶ መተቸት የተለመደ ነዉ፣ በአስተምህሮ ወይም በልምምድ ስህተት ዉስጥ ያለን ሰዉ እንድንቃመዉ መፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ያስተምረናል 👉ፊል 3:2 ማቴ 16፡12 ገላ 5:5_11_12 1ዮሐ 2:22...... መፅሐፍ ቅዱስ ስህተትን እንድንቃወም ብቻ ሳይሆን የሚያስተምረን ስህተትን ስንቃወም አስቀድመን ማወቅ ስላለብን ነገር እንደ መመሪያ ያስተምረናል። ነገሩ ስህተት መሆኑን ብቻ ማወቅ ሳይሆን ያንን ስህተት የምናቀናበትን መንገድ አስቀድመን ማወቅ መቻል አለብን። ምክንያቱም በአሁን ሰዓት ስህተት የሆነን ነገር ለመቃወም በተሳሳተ መንገድ እየተቃወሙ ያሉ እየበዙ ስለመጡ። በቤተክርስቲያን ዉስጥ በአስተምህሮም ሆነ በልምምድ በስህተት መንገድ ያሉ አገልጋዮች ከመፅሐፍ ቅዱስ መምሪያ ዉጪ ስለሆኑ ነዉ። ከመመሪያው ዉጪ ሆነዉ የተሳሳቱትን የምንመልሳቸዉ በመመሪያዉ ነዉ። ስለዚህ የሳቱትን ለመመለስ የመፅሐፍ ቅዱስ መመሪያን ልንከተል ይገባል። ለእኛ ሲባል የሚሻር የመፅሐፍ ቅዱስ መመሪያም ሆነ ህግ የለም። ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ " ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር" ይላል(1ኛ ጴጥ4:11) ይህ ለሁሉም ሰዉ የሚሰራ መመሪያ ነዉ። የተሳሳተን ሰዉ በመሳደብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመናገር ነዉ ልናቀናዉ የምንችለዉ። እኛ ስንሳደብ የእኛ ስድብ ልክ ስለማይሆን።" ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።" ይላል መፅሐፍ ቅዱስ።እግዚአብሔር የአንደበታችንን ቃል ብቻ ሳይሆን የልባችንን motive (ምክንያት) የሚያይ አምላክ ነዉ የተሳሳተን ሰዉ ስንቃወም እርሱን ለመመለስና ገንዘብ ለማድረግ እንዲሁም በእዛ ስህተት መንገድ የሚሄዱትን ምዕመናንን ለማቅናት እንጂ የተሳሳቱትን ፈፅሞ ለመስበርና ለማጥፍት መሆን የለበትም " እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን? "( ኤር 8:4) ይላል የሳቱት ቢመለሱ እኛ ለእነርሱ የሚመለስ ልብ እንዳለን እናረጋግጥ። ተሳስታችኋል የተባሉ ከስህተታቸዉ የተመለሱ እዉነተኛዉን አስተምህሮ የሚያስተምራቸዉ አጥተዉ ግራ በመጋባት ዉስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች አሉ።😔 ስህተትን መናገር ብቻ ሳይሆን ከስህተቱ ለተመለሰ ሰዉ በፍቅር የሚያቅፍ እጅ ሊኖረን ይገባል።ለዚህ ደግሞ እዉነትን በፍቅር ልንይዘዉ ይገባል " ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን"(ኤፌ4:15) ስህተቱን ለመናገር እንደረበታነዉ ሁሉ እዉነተኛዉን አስተምህሮ ለማስተማር መትጋት አለብን። " እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። "(ዮሐ8:32) በስህተት የተያዘን ሰዉ ነፃ የምናወጣዉ በእዉነት ነዉ። 1+1 ሶስት አይደለም ፥4ትም አይደለም፥10ም አይደለም እያልክ ያልሆነዉን ከምትነግረኝ የሆነዉን 2 ብትነግረኝ ያልሆነዉን እኔ በቀላሉ እለያለሁ። አማኞች ስህተት የሆነዉ ነገር እንዲለዩ እዉነተኛዉን የእግዚአብሔርን ቃል እናስተምራቸዉ።
ይህ ከላይ የገለፅኩላችሁ ስህተትን ስንቃወም መፅሐፍ ቅዱስ ከሚሰጠን መመሪያዎች በጥቂቱ ናቸዉ።
መጀመሪያ ወዳነሳሁላችሁ ታሪክ ልመላሳችሁ፣ አራቱም መነኩሴዎች ያወጡትን ህግ ሽረዋል። አራቱም የሻሩት ልክ በሚመስል ምክንያት ነዉ፣ አንደኛዉ የሻማ መጥፍቱን እንዲያዉቁ ተናገረ ፥ሁለተኛው ደግሞ የወጣዉን ህግ ለተናገረዉ ሰዉ ለማስታወስ ተናገረ፥ሶስተኛዉ ደግሞ ሁለቱም ፀጥ እንዲሉ እንዳይናገሩ ተናገራቸዉ፥አራተኛዉ በስተመጨረሻ እኔ ብቻ አልተናገርኩም ብሎ አለመናገሩን ተናገረና ህጉን አፈረሰ።

ተወዳጆች የእግዚአብሔር ቃል የሁላችንም መመሪያ ነዉ። አንድ አገልጋይ ከተሳሳተ ልንመልሰዉ የሚገባ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ አሳማኝ በሚመስል ምክንያት ግን ስህተት በሆነ መንገድ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ህግ በመሻር መሆን የለበትም።
ጌታ ኢየሱስ ታልፎ በሚሰጥበት ምሽት
ይሁዳ ጭፍሮችንና ከካህናት አለቆች ከፈሪሳውያንም ከሎሌዎችን ጋር በችቦና በፋና በጋሻ ጦር ሆኖ ወደ ኢየሱስ መጣ
ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና ማንን ትፈልጋላችሁ አላቸው። የናዝሬቱን ኢየሱስን ብለው መለሱለት። ኢየሱስ። እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር።እንግዲህ። እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ።ደግሞም። ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም። የናዝሬቱን ኢየሱስን አሉት።
ኢየሱስ መልሶ። እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው አለ፤ይህም። ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን ስንኳ አላጠፋሁም ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥ የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባርያውም ስም ማልኮስ ነበረ።ኢየሱስም ጴጥሮስን። ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣትምን? አለው።
(ዮሐ 18_1_11) ጴጥሮስ የማልኮስን ጆሮ ለመቁረጥ በቂ ምክንያት ነዉ ያለዉ። ግን ልክ አልለበረም። ኢየሱስ ጎበዝ ብሎ አላበረታታዉም ወዲያዉኑ ሰይፍህን ወደ ሰገባዉ ክተት ነዉ ያለዉ። ተወዳጆች ከእኛ ልክ ካልሆነ አሳማኝ ከሚመስል ምክንያት ይልቅ የእግዚአብሔር ቃል መመሪያ ሁሌም ልክ ነዉ።
ክፍል 2 ይቀጥላል ..

#ከፀደቀ #መንፈሰ