ቴዎፍሎስ theophilus
214 subscribers
147 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ይህ በገብረ ክርስቶስ ደስታ የተሳለዉ የክርስቶስ ምስል ድንቅ መልእክት አለዉ መልካም የፍሲካ በዓል
ከፀደቀ
#የመፅሐፍ #ግብዣዬ

በሀገራችን ብዙ ፀሐፍቶች የተለያዩ መፅሐፍ ይፅፋሉ፣ ነገር ግን ትክክለኛ የመፅሐፍ ይዘትና አካሄዱን ተከትለዉ የሚፅፉ ፀሐፊዎች ጥቂቶች ናቸዉ። ምክንያቱም መፅሐፍ እንዴት ይፃፍል? የሚለዉን የሚጠቁሙ መፅሐፍ በሀገራችን በጣም ጥቂት ስለሆኑ። እኔ ያገኘሁት ይህ ሆህያተ ጥበብ የተሰኘዉን #የዶ/ር #ተስፍዬ #ሮበሌ መፅሐፍ ነዉ። በጣም ጥቂት ናቸዉ ያልኩት የማዉቀዉ ይህን ብቻ ቢሆንም ምናልባት ሌላ ሊኖር ይችላል ብዬ ነዉ። ያገኛችሁት ካለ ብትጠቁሙኝ ደስ ይለኛል። ጥቂት መፅሐፍቶችን ከመዉጣታቸዉ በፊት ለመገምገም አድሉን አግንቼ ነበር፣ አብዛኛዉን ትኩረት የማደርገዉ ከሀሳብ ፍሰትና ከቃላት አጠቃቀም አንፃር ነዉ። ይህን መፅሐፍ ካነበብኩ በኃላ መፅሐፍ በተለያየ አይነት መንገድ መገምገም እንዳለበት ተረዳሁ። እጅግ በጣም የጠቀመኝ መፅሐፍ ነዉ። በተለይም መፅሐፍ የመፃፍ ሀሳብ ያላችሁ ወይም የጀመራችሁ ካላችሁ ይህንን #ሆህያተ #ጥበብ የተሰኘዉን የዶ/ር ተስፍዬ ሮበሌን መፅሐፍ ብታነቡ በብዙ ትጠቀማላችሁ።

#ፀደቀ #መንፈሰ
ርዕስ ሞርሞን

ይህ ሀይማኖት ለበርካታ ክርስቲያኖች እንግዳ ሲሆን አይቻለሁ።
በሀገራችን ቀስ በቀስ እያደገ ያለ እምነት ነዉ ካደመጣችሁ በኃላ ለሌላዉ ማጋራት እንዳይረሱ። ቅድመ ግንዛቤን እንፍጠር።
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 13 08 2015
የነገረ መለኮት መፅሐፍ ማንበብ ለምትፈልጉ ይህንን መፅሐፍ ካለበት አፈላልጋችሁና አሳዳችሁ ገዝታችሁ አንብቡት። በቀላሉ በመፅሐፍ መደብር አታገኙትም ምክንያቱም ቆየት ያለና ተፈላጊ መፅሐፍ ስለሆነ። እኔም ይህን መፅሐፍ ያገኘሁት በብዙ ድካም ነዉ።
ለአንድ መፅሐፍ መደብር ባለቤት ይህን መፅሐፍ እንዲያመጣልኝ ከአደራ ጋር አዝዤዉ ነበር። በተደጋጋሚም መጣ እንዴ? ብዬ ለመጠየቅ ወደ እዛ መፅሐፍ መደብር እሄድ ነበር። በመጨረሻ የመጣ ቀን ያልከኝ መፅሐፍ መጥቷል ሲለኝ እንደ ቶማስ ካልነካዉ አላምን ብዬ ነበር። እጄ ከገባ በኃላ ነዉ ያመንኩት።😊

ምን ለማለት ነዉ ይህንን መፅሐፍ ካገኛችሁት በፍፁም እንዳታልፉት

#ፀደቀ ነኝ
የህይወት ምስክርነት ከአንደበት ስብከት የበለጠ ለትዉልድ ይሰማል።
ጌታ ሆይ🙏 የኖርነዉን እንድንሰብክ
የሰብክዉን እንድንኖር ፀጋህን አብዛልን
አሜን

#ከፀደቀ
በህብረት ወንጌል ስርጭት ወጥታችሁ እንዲህ አይነት የመጫወት አድልን ካገኛችሁ እንደእኛ ባታልፉት መልካም ነዉ😊
ድንቅ ትዝታ ይሆናችኃልና
በ2011ዓ.ም ትዉስታ ቡታጀራ
ርዕስ እግዚአብሔር በአንድም በሌላ ይናገራል

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ርዕስ ስብከት ክፍል 22
ከስብከት በኃላ ምን ላድርግ?🤔

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 24 08 2015
መሪነት ክፍል 3
የእዉነተኛ መሪ መገለጫዉ ምንድነዉ?🤔
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ድንቅ ትምህርት
ቀን 25 08 2015
እምነት ከድል በፊት ማመስገን ነዉ
ጌታ ሆይ ተመስገን
ርዕስ theology (ስነ መለኮት)

theology መማር ለምትፈልጉና አጠቃላይ ስለትምህርቱ ይዘት ማወቅ ለምትፈልጉ የተዘጋጀ

theology መማር የእዉነት እንደሚባለው ያደርቃል?

Theology መማር ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ አጋሯቸዉ
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 29 08 2015
ከለሊቱ ሰባት ሰዓት እየተኛክ የለሊት ፀሎት እንዳልፀልይ ሰይጣን በድካም እየተዋጋኝ ነዉ አትበል ታዲያ በዚህ ሰዓት እየተኛክ በለሊት እንዴት ልትነሳ ነዉ

#ከፀደቀ #መንፈሰ
እግዚአብሔር ሆይ አንተ የማትጠረጠር መታመኛ ፥ የማታሰጋ እረፍት ፥የማትሰጋ ፅኑ ፥ የማትዝል ብርቱ ፥ የማይጨልምብህ ብርሃን፥ የማይጎድልህ ባለፀጋ ፥የማትቀደም ፊተኛ ፥የማትነፃፀር ብቸኛ ፥የማትታረም ትክክል .................... ነህ

#ፀደቀ ነኝ የእርሱ ጥገኛ
" እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን" 1ቆሮ 1:23

ለሞተልን ኖረን የሞተልንን እንድንሰብክ እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልን። አሜን
ወንድማዊ ምክሬ ነዉ

የማይፀልዩትን ለመኮነን አትፀልይ ከእግዚአብሔር ጋር ለማዉራት ፀልይ


አጠገብህ ያሉት ካንተ በላይ ቃሉን እንደማያዉቁ ለማሳወቅ ብለህ አታንብብ እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማወቅና መንፈሳዊ ህይወትህን ለማሳደግ አንብብ

#ከፀደቀ
ምን እንደምትፈልግ ሳታዉቅ መፈለግ አትጀምር በመጀመሪያ ፍላጎትህን እወቅ በመቀጠል መፈለግ ጀምር
#ከፀደቀ #መንፈሰ
እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ የሰዉ ልጅ ባይሆን እኛ የሰዉ ልጅ የእግዚአብሔር ልጆች መሆን አንችልም ነበር