The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#NewsAlert
#ኑ_ጸሎትን_ወደ_ስፍራው_እንመልስ ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በትላንትናው እለት እሑድ ሐምሌ 7 ቀን፥ 2011 ዓ.ም. በአዲስ ጌታቸው የተጻፈውንና "ኑ ጸሎትን ወደ ስፍራው እንመልስ" የተሰኘውን ላይ ውይይት ተደረገ።

በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት (EGST) መሰብሰቢያ አዳራሽ በ9 ሰዓት በተካሄደው ውይይት ለውይይት መነሻ ጽሑፍ አቶ ሳሙኤል ኅይሉ አቅርበዋል። በሰኔ ወር የመጽሀፍ ውይይት "እርካብና መንበር" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት መደረጉ የሚታወስ ነው።
#ሼር #Share
#NewsAlert

#በአረብ_አገር_ለቤተክርስቲያን_የማምለኪያ_ፍቃድ_ተሰጠ

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት በአቡዳቢ ከተማ 19 የሙስሊም ያልሆኑ የአምልኮ ቤቶችን ፍቃድ ሰጠ። ከ19ኙ መካከል 17ቱ የክርስቲያን የአምልኮ ስፍራዎች ናቸው።

የሃገሪቱ መንግስት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የካቶሊኩ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳስ ፍራንሲስ የአረቧን ሃገር ከጎበኙ በኋላ ነው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከ1 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች የሚኖሩ ሲሆን፣ ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ዜግነት አጊኝተው የሚኖሩት።

የእምነት ቤቶቹ ፈቃድ መስጠት ሌላ የሚያካትተው ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጡ ሰዎች ህጋዊ ስርዓት ጠብቀው ነው ክርስቲያን የሚሆኑት።

አሁንም ግን እምነትን መስደብ ያስቀጣል የሚሉ ህጎች እንደጸኑ ናቸው። የአደባባይ እና ጎላ ያለ ሰበካም የተከለከለ ነው።

#ሼር #Share
#NewsAlert

#የእግዚያብሄር_ጀነራሎች_ቁጥር_ሁለት_ተመረቀ
“የእግዚያብሄር ጀነራሎች የሪቫይቫል አቀጣጣዮች” የተሰኘው ቁጥር ሁለት የሮበርትስ ሊያርደን መጽሀፍ በወንድም ዳንኤል ነጋሽ ተተርጉሞ ባሳለፍነው ሳምንት በቤተል ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተመርቆ ለንባብ በቃ።

መጽሀፉ በ10 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በአጠቃላይ 507 ገጾች አሉት በውስጡም የ9 ሰዎችን ትሪክ ይዟል።

የመጽሀፉ ተርጓሚ ወንድም ዳንኤል ነጋሽ በ2009 ዓ.ም የመጀመሪያ እትም የሆነውን “የእግዚአብሔር ጀነራሎች የስኬታቸው ሚስጥርና የአንዳንዶቹም የውድቀታቸው ምክንያት” የተሰኘ ርዕስ ያለው ባለ 386 ገጽ እና የ12 ሰዎች ታሪክን የያዘ ቁጥር አንድ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወስ ነው።

#ሼር #Share
#NewsAlert

በኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘንድ ሠላም እንዲሰፍን የሃይማኖት ተቋማት የኅብረትና የፍቅር ትምህርት እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።
በኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ሠላምና ትብብር እንዲፈጠር የተቋቋመው ኮሚቴ የ52ቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን በተገኙበት የመጀመሪያ ጉባዔውን ዛሬ በአዲስ አበባ አካሂዷል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት ቡራኬ “የሃይማኖት ተቋማት የሠላም ምንጮች ናቸው” ብለዋል።

በህዝቦች ዘንድ ሠላም እንዲሰፍን፤ ፍቅር፣ አንድነትና ትብብር እንዲጎለብት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት እንዲሰብኩም ጠይቀዋል።

ሠላምን ማስፈን የሁሉም ምዕመን ድርሻ ቢሆንም የቤተክርስቲያን አባቶችና መምህራን ቅድሚያ መስራት “ይጠበቅብናል” ነው ያሉት።

“ፀሎታችን ብዙ ነው፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልደረሰም ወይስ ምን ሆነ ዛሬም ችግር ውስጥ የሆንነው?” ያሉት ፓትሪያርኩ “አሁንም ህሊናችንን ሰብሰብ አድርገን ወደራሳችን መመለስ ይገባናል” ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማት አባቶችም በተሰማሩባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ምዕመናንን ማህበራዊና መንፈሳዊ እሴት ማጎልበት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አቡነ ማትያስ “ስለ ሠላም እየተሰበከ ሠላም የጠፋው ከመልካም የህሊና ዳኝነት ይልቅ መጥፎውን በመከተላችን የመጣ ነው” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ሠላም፣ ልማት፣ ዕድገትና ትብብር እንዲጎለብት ሁሉም በፀሎትና በትጋት ለሠላም ዘብ እንዲቆምም አሳስበዋል።
#NewsAlert

#መልካም_ወጣት_2011_2ኛው_ዙር

የመልካም ወጣት 2011 ስልጠና "መልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት" የ2ኛው ዙር ፕሮግራም የመጀመሪያ ቀን ስልጠና ተጀምሯል።

የዘንድሮ ዓመት ፈተናው በበዛበት ጊዜ ነው በዛው ልክ በርካቶች ለለውጥ ቆርጠው የተነሱበት ዓመት ነው።

እግዚያብሄር ግን ሁሌም ከመልካሞች አጠገብ ነው።