The Christian News
5.15K subscribers
3.04K photos
25 videos
714 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የሕብረት መሪዎች
ወቅታዊ ምላሽ ምን ይሁን?
-------------------
#የኮሮና_ቫይረስ ስርጭት ለመግታት መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እየተከታተልን ነው። የእግዚአብሔር ምህረት እንዲበዛ፤ በፀሎት #የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ ጀምረናል። እሱ ይራራልን!

ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ባይዘጉም እንቅስቃሴዎችና ስብሰባዎች ተገተዋል።

ኢቫሱ፣ የሚያስተባብራቸው የተማሪ ሕብረቶች ምላሽ ምን መሆን እንዳለበት በደብዳቤ ለሁሉም ሕብረቶች እንዲያውቁት ተደርጓል፡፡ በዋናነት የተማሪ ሕብረት አገልግሎት #ሣይቋረጥ ነገር ግን #የስልት ለውጥ በማድረግ መቀጠልን የሚያበረታታ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

በዚህ ወቅት በሕብረት ውስጥ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፍ #የመሪነት_ድርሻ ያላችሁ ተማሪዎች ትልቅ ኃላፊነት ወድቆባችኋል።

* የተማሪ ሕብረት አገልግሎቱን በእንዴት ያለ ሁኔታ እናስቀጥለው?

* በዚህ ወቅት የአገልግሎት ትኩረታችን ምን መሆን አለበት?

* አማራጭ የአገልግሎት መንገዶች ምን ምን ናቸው?

* ስርጭቱን ለመግታት የሕብረት አባላት ድርሻቸው ምንድነው?

* በዚህ ወሳኝ ጊዜ የሕብረት ልዩ ልዩ መሪዎች [#ዋና እና #የዘርፍ አገልግሎት መሪዎች፣ የፀሎትና የወንጌል #ሞብላይዘርስ፣ የንዑስ ቡድን እና የባች #አስተባባሪዎች፣…ወዘተ] የሚጫወቱት ሚና ምን መምሰል አለበት?

* የዚህ ወቅት የሕበረቱ የአገልግሎት ተግዳሮቶች ምንድናቸው? እንዴት እንፍታቸው?

* በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የሕብረት #አባላት ቢኖሩ ምላሻችን ምን ዐይነት ይሁን?

* በቫይረሱ የተጠቁ #አማኝ_ያልሆኑ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላትን በተመለከተ አተያያችንና ምላሾቻችን ምን መሆን ይኖርበታል?

እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮችን በጥልቅተ በመመልከት መልስ መስጠት አለባችሁ። ጉዳዩ፣ የእግዚአብሔርን #ምሪት መከተል፣#ፀሎትና #ምክክር ይፈልጋል።
---------
በፀሎትና በምክር አብረናችሁ ነን!
ለበረከት ሁኑ!
-----
ኢቫሱን ይቀላቀሉ
@EvaSUE58

@TCNEW