SOA COMMUNITY GEjA 2 CAMPUS
1.11K subscribers
851 photos
40 videos
398 files
90 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ 👉👉👉 @SOA2C
Download Telegram
Chat GPT driven
Addis Ababa Grade 8 Social Study 100 Q with A
Forwarded from Girum Tesfa (גירום טספה וורקנה)
4_5866247988518590697.doc
73.5 KB
Forwarded from SOA
ከአፀደ ህፃናት እሰከ 8ኛ ክፍል የትምህርት ቤታችን ምስጉን ተማሪ የነበረው አሁን ደግሞ በአዲስአበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርስቲ AASTU የ2ኛ አመት ተማሪ  አማኑኤል ዱታሞ ባጋጠመው ድንገተኛ ህልፈት ህይወት መሪር ሀዘናችን እየገለፅን ለወላጆቹ እንዲሁም ለመላው ቤተሰቦቹ መፅናናትን አንመኛለን።
Forwarded from SOA
Forwarded from AASTU-ECSF
ሰላም ቤተሰቦች 

የህብረታችን አባል እና በናታኒም ያገለግል የነበረው የ2ኛ አመት የElectrical Engineering ተማሪ የሆነው አማኑኤል ዶታሞ (ኑኤል) ወደ ጌታ መሄዱን ዛሬ ሰምተናል።

ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ወንድማችንን ላጣነው ለኛም ለሁላችንም እግዚአብሔር መፅናናቱን ይስጠን።

የቀብር ስርአቱ ነገ 9:00 ላይ ሲሆን ከዛ በፊት ግን 7:00 ላይ በልደታ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሽኝት ይደረጋል። በSmall Group ፣ በናታኒም አብራችሁ ያገለገላችሁ እንዲሁም ሌሎቻችሁም ወንድማችንን የምታውቁ እና ቀብር ላይ የምትገኙ እና ቤተሰቡንም ማፅናናት የምትፈልጉ ሁሉ ነገ (ማክሰኞ) 5:30 በቱሉ ዲምቱ በር ባስ ስለሚመጣ እንድትወጡ እና አብረን እንድንሄድ ይሁን።

የወንድማችንን ኑኤል ቤተሰቦች እንዲሁም ጓደኞቹን እና የቅርብ ወዳጆቹን ሁሉ አፅናኝ የሆነው እግዚአብሔር እንዲያፅናናቸው በጸሎት ከጎናቸው እንድንሆን አደራ እንላለን።

#AASTU_ECSF
Telegram | YouTube | Instagram | TikTok
Free IT Summer Camp for primary students by INSA ,register now!!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ

#CyberTalentChallengeSummerCampProgram2025

" የ11 አመት እድሜ ካላቸው ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን "- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ላለፉት ሶስት አመታት ያከናወነው የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ፕሮግራም ስልጠና መርሃግብር የ2017 ዓ/ም ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

ለአራተኛ ጊዜ የሚከናወነው የባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ እና ወጣቶች የሳይበር ሥልጠና የክረምት መርሃ ግብር ሥልጠና ምዝገባ እስከ ግንቦት 24/2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚሰጠው ይህ ስልጠና ፦
- በሳይበር ደህንነት፤
- በሳይበር ዴቨሎፕመንት፤
- በኢምቤድድ ሲስተም
- በኤሮስፔስ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ችሎታ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ቢመዘገቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተቋሙ አሳውቋል።

በዘንድሮው ስልጠና ለመሳተፍ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ቀደም ብለው የወሰዱ ተመዝጋቢዎች የተሻለ እድል እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

ተያያዥ የሆነ ሰርተፍኬት ያላቸው ተመዝጋቢዎችም በምዝገባው ወቅት በማስገባት ስልጠናውን ለመሳተፍ የተሻለ እድል ይኖራቸዋል።

የተቋሙ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ " ሰልጣኞች ከስልጠና በኋላ በቀጥታ ወደ ኢንሳ ፣ሌሎች የግል ተቋማት ወይም የመንግስት ቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ቦታዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ " ከ11 አመት ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን " ያሉ ሲሆን " ምዝገባው እንዳበቃ ለቦታው ፍላጎት ያላቸው እና በቂ የሚባል ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል " ነው ያሉት።

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በሚከናወነውን ሥልጠና ተካፋይ ለመሆን ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በ https://talent.insa.gov.et ላይ በመግባት እስከ ግንቦት 24/2017 ዓም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ማሳሰቢያ:- ለተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች/
ከዚህ በላይ በተቀመጠው ሊንክ መሠረት እድሜያቸው ከ11 ዓመት ጀምሮ ያሉ በሙሉ ከዛሬ ማለትም ከ21/09/2017 ዓ.ም ጀምሮ በመመዝገብ ወደ ስልጠና እንዲገቡ እያሳሰብን ስልጠናው ሲያጠናቅቁ ዓለምዓቀፍ የእውቅና ሰርተፍኬት የሚሰጣቸው ይሆናል። ስልጠናው በኮምፒውተር ወይም በስልክ እቤታቸው ባሉበት (online) መውሰድ ይችላሉ።
🌟ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።

አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።

ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::

ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።

በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

መጭው ጊዜ የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች #ሸር በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር 🤲🤲🤲🤲

መልካም ፈተና

🔠🔠🔠🅰️  🔠🔠🔠
🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤
🔤🔤🔤🅰️ 🔤🔤🔤

ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇
❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/dam76