ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#መጋቢት_17

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው በአራተኛውም ቀን ከመቃብር ያስነሣው የከበረ #ጻድቅ_አልዓዛር አረፈ፣ አናጕንስጢስ #ቅዱሰ_ቴዎቅሪጦስ በሰማዕትነት አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው #ጻድቅ_አቡነ_ዮናስ የበዓለ ዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አልዓዛር_ሐዋርያ

መጋቢት ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው በአራተኛውም ቀን ከመቃብር ያስነሣው የከበረ ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህም ጻድቅ ሰው ከእስራኤል ልጆች ውስጥ ነው ማርያና ማርታ የተባሉ ሁለት እኅቶች አሉት። ማርያም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሸቱ የቀባችው ናት።

እነርሱም ለጌታ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው ስለ ምግባራቸውም ጌታችን ይወዳቸዋል ሁሉም ያላገቡ ድናግል ናቸው። በሰው ወገን ሁሉ ላይ የተቆረጠና የተወሰነው ሰዎችም ሊጠጡት ያላቸው የሞት ጻዋን የሚጠጣበትና እጁን ለሞት የሚሰጥበት ለዚህ ጻድቅ ጊዜው ሲደርስ እርሱም እጁን በመስጠት አረፈ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ግን የሚሠራውን ያውቃልና መጀመርያ ከሞት አላዳነውም ጠርቶ እስከሚአሥነሣው ድረስ ሙቶ በመቃብር አራት ቀን እንዲኖር በዚህ በአራት ቀንም የጻድቃንን ማደሪያዎችንና የኃጥአንን የሥቃይ ቦታዎች እንዲያይ ተወው እንጂ አላዳነውም ያን ጊዜም ታላቅ ምልክት ትሆናለች።

ከአራት ቀኖችም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ አልዓዛር አልዓዛር ና ውጣ ብሎ ከመቃብር ውስጥ ጠራው ያን ጊዜ አጆቹና እግሮቹ እንደታሠሩ ሙታኖችንም እንደሚጠቀልሏቸው በሰበን ፊቱ ተጠቅልሎ ወጣ።

እጆቹና እግሮቹ እንደ ተጠቀለሉና እንደ ታሠሩ ከመቃብር የመውጣቱ ምክንያት ሰዎች ሁሉ መሞቱን እንዲረዱ ሌሎችም ይህ በመካከላቸው በስምምነት የሆነ ነው ብለው እንዳያሰቡ። ስለዚህም እንደ ገነዙት ሁኖ እንዲወጣ ጌታችን አዘዘው ይችም ምልክት እንድትሆን።

ከሀዲዎችም በመቃብር ውስጥ ሕያው እንደ ነበር ቢያስቡም እጆቹና እግሮቹ ፊቱም እንደ ተጠቀለሉ እንዴት ይወጣ ነበር እኛ የክርስቲያን ወገኖች ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአራት ቀኖች በኋላ አልዓዛርን ያስነሣው እርሱ እንደሆነ እናምናለን። እንታመናለንም እርሱ በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ አለውና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎቅሪጦስ_አናጉንስጢስ

በዚችም ዕለት አናጕንስጢስ ቴዎቅሪጦስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የሮሜ አገር ሰው ነው። ዐላውያንም ለጣዖት እንዲሠዉ ክርስቲያኖችን ይዘው በአስገደዷቸው ጊዜ እርሱንም ከእነርሱ ጋር ያዙት ወደ ንጉሥም አቀረቡት ያንጊዜ የዐሥራ አምስት ዓመት ልጅ ነበር።

ንጉሡም በማመጣብህ ሥቃይ ትፈተናለህን ወይስ ለአማልክት ትሠዋለህ አለው። ቴዎቅሪጦስም እኔስ ለክብር ባለቤት ለጌታዬ ለፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እሠዋለሁ አለው።ንጉሡም ቴዎቅሪጦስ ሆይ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ አለው።

እርሱም ንጉሥ ሆይ መሥዋዕቴን እንድታይ ና አለው ንጉሡም ወደ ጣዒቱ ቤት እንዲወስዱትና በዚያ እንዲሠዋ አዘዘና እርሱም በበር ቆመ። ቅዱሱም በጸለየ ጊዜ ንውጸውጽታ ሁኖ አጽቀላጽዮስ የሚሉት አምላካቸው ወድቆ ተሰበረ ።

ንጉሡም እንደ ዘበተበት አይቶ አፍንጫውን ቆረጠው አሥረው በወህኒ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ። በማግሥቱም አውጥተው በብረት ምጣዶች ውስጥ ጨመሩት ደግመው ጥልቅ ግድጓድ ቆፈሩ በውስጡም እንጨት ረብርበው ሥጋው ከመለያያው እስቲቦጫጨቅና ቅልጥሙም ከአጥንቶቹ እስቲፈስ ድረስ ወረወሩት ። በዚህም ሊአጠቁት አለቻሉም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከእርሱ ጋር አለና።

ከዚህ በኋላ አማልክቶቻቸው የሚበቀሉት መስሏቸው ከአማልክቶቻቸው ቤት አስገብተው በዚያ ዘጉበት ። ቴዎቅሪጦስ ግን ከጣዖታቱ ላይ ያለውን ወርቅ ቀጥቅጦ በሥውር ይዞ እየወጣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች መጸወተው። ተመልሶ ሲገባም ደጃፉ እንደ ቀድሞው ራሱ ይዘጋል።

በስምንተኛውም ቀን ንጉሡ መጣ ከደጃፍም ሁኖ አየ አማልክቶቹም ተጥለው ተሰባብረው የከበረ ቴዎቅሪጦስም ሲዘብትባቸው አገኛቸው። ዕውነተኛ ቴዎቅሪጦስንም የሆድ ዕቃው እስቲታይ እንዲሰነጣጥቁት አዘዘ። ደግመው ወደ ጨዋታ ቦታ እንዲአስገቡትና በላዩ አንበሶችን እንዲአስገቡአቸው አዘዘ። አንበሶችም ቁስሎቹን ላሱለት።

ዳግመኛም ሕዋሳቱ እስቲነጣጠል ከሚአጣብቅ ቦታ እንዲአስገቡት መላ አካላቱም ታጥፎ እስቲቆለመም እንዲአሠቃዩት አዘዘ። በዚህም ተሸብሮ አላሸነፉትም ንጉሡም ብርታቱን አይቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።

የከበረ ኤጲስቆጶስ ኤሞሬዎስና ህዝብ ሁሉ በጸሎት እየተራዱት ቅዱስ ቴዎቅሪጦስን ተከተሉት በቅዱሳን ሰላምታም ተሳልመውት ተሰናበቱት ባለወግ ወታደርም ሰይፉን አንስቶ አንገቱን ቆረጠው ምስክርነቱንም ፈጸመ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_አቡነ_ዮናስ

በዚኽች ዕለት አቡነ ዮናስ የበዓለ ዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ አቡነ ዮናስ አባታቸው ንዋየ እግዚእ እናታቸው ኂሩተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በኅዳር 17 ቀን 1357 ዓ.ም በሀገረ ቡር (ሀገረ መስቀል) ሚባል ተወለዱ፡፡ አቡነ ዮናስ በሕፃንነታቸው በጎች እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም መዝሙረ ዳዊት ኣስተማራቸው፡፡ እርሳቸውም ይህን ዓለም ንቀው ከመነኮሱ በኋላ 150 መዝሙረ ዳዊት በአንድ ጊዜ እየጸለዩ 3 ሺህ ስግደት ይሰግዱ ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ሲጸልዩም "ጠላቂት" በሚባል ሐይቅ ውስጥ እየገቡ እስከ አንገታቸው ድረው በሐይቁ ውስጥ ገብተው ይጸልዩ ነበር፡፡ ከተሰጧቸውም ጸጋዎች ውስጥ አንዱ 10 ጣቶቻቸው ወደ ሐይቁ ሲገቡ ይበሩ ነበር፡፡ አቡነ ዮናስ በየቀኑ ከ5 ፍሬ "ዳዕሮ" ወይም "ዓየ" በቀር ሌላ ምግብ አይመገቡም ነበር፡፡

ከዚኽም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ኀብስተ ኣኩቴትን ጽዋ በረከት ከሰማይ አውርዶላቸዋል፡፡ ጻድቁ እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ወደተለያዩ ቦታዎች እየዞሩ የተለያዩ ተኣምራት በማድረግ ሕሙማንን በመፈወስ ሙታን በማስነሣት ብዙዎችን ከክህደት ወደ እምነት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከጣኦት ኣምልኮ ወደ እግዚአብሔር ኣምልኮ መልሰዋል፡፡

ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ‹‹ከመቃብርህ ጸበል የተቀባ የጠጣ ከኃጥያቱ ይነጻል›› የሚል ቃልኪዳን አስቀድሞ የሰጣቸው ሲሆን በዚህ ድንቅ ቃልኪዳን መሠረት ዛሬም ድረስ ከመካነ መቃብራቸው ላይ ፈዋሽ የሆነ ቅብዓ ቅዱስ ይፈልቃል፡፡ ይህንንም በ2011 ዓ.ም ለአንድ ወር በአክሱምና ኤርትራ የዞር ጉዞ ባደረግንበት ወቅት ወደዚህ ታላቅ ገዳም ሔደን የጻድቁን ገዳም ተሳልመን ቅብዓ ቅዱሱን በዐይናችን አይተን በአባቶች ተቀብተን በረከታቸውን አግኝተናል፡፡ ቅብዓ ቅዱሱ በተለይም ጆሮውንና ዐይኑን ለሚያመው ሰው መድኃኒት ነው፡፡

አቡነ ዮናስ ይይዙት በነበረው መቋሚያ በውኃ እየታጠበ ውኃው በጣም ለታመሙ ሰዎች እየተሰጠ በቶሎ ከበሽታቸው ይድኑበታል፣ የማይድኑም ከሆነ ቶሎ በሞት ያርፋሉ፡፡ የሚታጠቡበት ሁሉ ለድኅነት ከሆናቸው በአጭር ጊዜ ይድናሉ ወይም ለዕረፍት ከሆናቸው ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ያሰናብታቸዋል፡፡ አቡ ዮናስ በቁርባን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም በሠረገላ መንፈስ ደርሰው ያስቀድሱ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡
#መጋቢት_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ሃያ በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #ጻድቅ_አልዓዛር ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ ላስነሳበት መታሰቢያ ነው፣ የእስክንድርያ ሃምሳ ሰባተኛ ሊቃነ ጳጳሳት የሆነ #ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ሚካኤል አረፈ፣የተመሰገነችና የከበረች ተጋዳይም የሆነች #ቅድስት_አስጠራጦኒቃ ስለ ክርስቶስ ምስክር ሁና ሞተች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አልዓዛር_ጻድቅ_ሐዋርያ

መጋቢት ሃያ በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ ሰው አልዓዛርን ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነስቶት ነበርና ስለዚች ምልክት ገናናነት ብዙዎች አመኑበት።

ይህም ጻድቅ ሰው ከእስራኤል ልጆች ውስጥ ነው ማርያና ማርታ የተባሉ ሁለት እኅቶች አሉት። ማርያም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሸቱ የቀባችው ናት። እነርሱም ለጌታ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው ስለ ምግባራቸውም ጌታችን ይወዳቸዋል ሁሉም ያላገቡ ድናግል ናቸው። በሰው ወገን ሁሉ ላይ የተቆረጠና የተወሰነው ሰዎችም ሊጠጡት ያላቸው የሞት ጻዋን የሚጠጣበትና እጁን ለሞት የሚሰጥበት ለዚህ ጻድቅ ጊዜው ሲደርስ እርሱም እጁን በመስጠት አረፈ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ግን የሚሠራውን ያውቃልና መጀመርያ ከሞት አላዳነውም ጠርቶ እስከሚአሥነሣው ድረስ ሙቶ በመቃብር አራት ቀን እንዲኖር በዚህ በአራት ቀንም የጻድቃንን ማደሪያዎችንና የኃጥአንን የሥቃይ ቦታዎች እንዲያይ ተወው እንጂ አላዳነውም ያን ጊዜም ታላቅ ምልክት ትሆናለች።

ከአራት ቀኖችም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ አልዓዛር አልዓዛር ና ውጣ ብሎ ከመቃብር ውስጥ ጠራው ያን ጊዜ አጆቹና እግሮቹ እንደታሠሩ ሙታኖችንም እንደሚጠቀልሏቸው በሰበን ፊቱ ተጠቅልሎ ወጣ።

እጆቹና እግሮቹ እንደ ተጠቀለሉና እንደ ታሠሩ ከመቃብር የመውጣቱ ምክንያት ሰዎች ሁሉ መሞቱን እንዲረዱ ሌሎችም ይህ በመካከላቸው በስምምነት የሆነ ነው ብለው እንዳያሰቡ። ስለዚህም እንደ ገነዙት ሁኖ እንዲወጣ ጌታችን አዘዘው ይችም ምልክት እንድትሆን።

ከሀዲዎችም በመቃብር ውስጥ ሕያው እንደ ነበር ቢያስቡም እጆቹና እግሮቹ ፊቱም እንደ ተጠቀለሉ እንዴት ይወጣ ነበር እኛ የክርስቲያን ወገኖች ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአራት ቀኖች በኋላ አልዓዛርን ያስነሣው እርሱ እንደሆነ እናምናለን። እንታመናለንም እርሱ በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ አለውና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሚካኤል_ሊቀ_ዻዻሳት

በዚህች ቀን በእስክንድርያ ከተሾሙ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ ሰባተኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል አረፈ።

ይህም አባት በሹመቱ ወራት ብዙ ኀዘንና መከራ ደረሰበት ጎሕ በሚባል አገር የተሾመ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ክብር የሚወድ አንድ ክፉ ኤጲስቆጶስ ነበረ። በሀገረ ስብከቱም ውስጥ ደነውስር በሚባል አገር ያሉ ምእመናን የቤተ ክርስቲያናቸውን ሕንፃዋን አደሱ ሊአከብሩዋትም በፈለጉ ጊዜ የአገር ታላላቆች ከእርሳቸው ሊባረኩ ወደው ሊቀ ጳጳሳቱና በአገሩ ዙሪያ ያሉትን ኤጲስቆጶሳት ልኮ እንዲአስመጣቸው ይህን ክፉ ኤጲስቆጶስ ለመኑት እርሱ ግን እምቢ አላቸው ልመናቸውን መቀበል አልወደደም።

እነርሱም በራሳቸው ፈቃድ ይህ ክፉ ኤጲስቆጶስ ሳይፈቅድ ሊቀ ጳጳሳቱንና ኤጲስቆጶሳቱን ሁሉ ልከው አስመጡአቸው። ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልና ኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ በመጡ ጊዜ ምሳ አዘጋጅላቸዋለሁ ብሎ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትቶአቸው ሔደ። ማርታ ማርታ ብዙ በማዘጋጀት ብዙ ትደክሚያለሽ ግን ጥቂቱ ይበቃል ያለውን የጌታችንን ቃል አላሰበም።

የቍርባን ጊዜ ሊያልፍ ስለሆነ ሊቃውንቱና ኤጲስቆጶሳቱ የቅዳሴውን ሥርዓት ይጀምር ዘንድ ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት ግድ ባሉትም ጊዜ በሊቀ ጵጵስና ማዕረግና ክብር ተሠይሞ ተነሣ እርሱ ለሁሉ አባት የሆነ ሥልጣኑም ከሥልጣናቸው በላይ ነውና የቅዳሴውንም ሥርዓት ጀመረ።

ያ ክፉ ኤጲስቆጶስም በሰማ ጊዜ በልቡ ሰይጣን አደረበትና ተቆጥቶ መጣ። መሥዋዕቱንም ከመቅደስ ገብቶ ከጻሕሉ ውስጥ ነጥቆ ወደ ምድር ወረወረው ሊቀ ጳጳሳቱም ሌላ መሥዋዕት አምጡ ብሎ አዘዘ አምጥተውለትም ቀድሶ ለሕዝቡ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸውና አሰናበታቸውም።

በማግሥቱም ይህ አባት አባ ሚካኤል ሕዝቡን ሰበሰበ ከእርሱ ጋራ ያሉትንም ኤጲስቆጶሳት ካህናቱንና የምእመናንን አንድነት ሰብስቦ ይህን ክፉ ኤጲስቆጶስ ከሹመቱ ሽረው በእርሱ ፈንታ ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ።

ይህም ለአስቆሮቱ ሰው ለይሁዳ ሁለተኛው የሆነ የምስርን አገር ወደ ሚገዛ ስሙ አሕመድ ወልደ በጥሎን ወደተባለው ሹም ሔደ ይህን አባት አባ ሚካኤልን እንዲህ ሲል ነገር ሠራበት። በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ብዙ የወርቅና የብር ገንዘብ እንዳለ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት የወርቅና የብር ንዋየ ቅድሳትን የተመሉ እንደሆኑ መኰንን ሆይ ዕወቅ አለው።

መኰንኑም ይህን አባት ወደርሱ አስቀርቦ ንዋየ ቅድሳቱን እንዲሰጠው ፈለገ እርሱም ሥጋዬን እንደፈለግህ አድርግ ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር እጅ ናት በሎ ከለከለው። እጆቹንና እግሮቹን አሥረው በእሥር ቤት እንዲጥሉት አዘዘ በእሥር ቤትም ከአንድ ዓመት በላይ ኖረ በእሥር ቤት ውስጥ በኖረበት መጠን ከለምለም እንጀራና ከጨው ከበሰለ አተር በቀር ሳይበላ ሁል ጊዜ ይጾም ነበር።

ከዚህም በኋላ አንድ ጸሐፊ ምእመን ዮሐንስ የሚባል መጥቶ ለዚህ ለከበረ አባት አባ ሚካኤል ዋስ ሆነው ለመኰንኑ አባ ሚካኤል ሃያ ሽህ የወርቅ ዲናር እንዲሰጠው ሁኖ ከወህኒ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሔደ ጥቂት ቀን ተቀመጠ ታላላቆች ምእመናንና የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት ዐሥር ሽህ የወርቅ ዲናር ሰበሰቡ ደግሞ የእስክንድርያ አገር ሰዎች ከምድራቸው አንዱን ለዐሥር ሽህ ዲናር ሸጡ ሃያ ሽህ እስከሚሞላ ሰበሰቡ።

ሊቀ ጳጳሳቱም ለመኰንኑ ይህን ሃያ ሽህ የወርቅ ዲናር ሰጠው መኰንኑም ዐሥር ዐሥር ሽህ የወርቅ ዲናር እንደ ግብር ሁኖ በየዓመቱ እንዲከፈል ጽፎ አስፈረመው።

ጊዜውም ሲቀርብ ይህ አባት አባ ሚካኤል ከምእመናን ሊለምን ተነሥቶ ወጣ በልበይስ ወደተባለም አገር ደርሶ አንዲት ቀን ዋለ ወደርሱም አንድ ምስኪን ድኃ መነኰሴ ገባ። ከሊቀ ጳጳሳቱም ቡራኬ ተቀብሎ ተመልሶ በበር አጠገብ ከረድኡ ጐን ቆሞ አትዘን በልብህም አትተክዝ ከዛሬዪቱ ዕለት እስከ አርባ ቀኖች ትድናለህ በላይህ ያለውን የዕዳ ደብዳቤ ትቀበላለህና ለመኰንኑ ምንም አትሰጠውም ብለህ ለአባት ሊቀ ጳጳሳት ንገረው አለው ያ ረድኡም እንዳለው ነገረው ድኃውን መነኲሴ ፈለጉት ግን አላገኙትም።

አርባ ቀኖችም ሳይፈጸሙ ያ መኰንን በክፉ አሟሟት ሞተ በእርሱ ፈንታም ልጁ ተሾመ ለዚህም አባት ያንን የዕዳ ደብዳቤ መለሰለት ይህም አባት ድኃው መነኰስ ትንቢት እንደ ተናገረ ደብዳቤውን ተቀብሎ ቀደደው ከዕዳም ዳነ። ይህም አባት በታላቅ መከራና በኀዘን በሹመቱ ዘመን ሃያ ዘጠኝ ዓመት ከኖረ በኋላ በፍቅር በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስትና_ሰማዕት_አስጠራጦኒቃ

በዚህችም ዕለት የተመሰገነችና የከበረች ተጋዳይም የሆነች አስጠራጦኒቃ ስለ ክርስቶስ ምስክር ሁና ሞተች። የዚች ቅድስት አባቷ ጣዖት አምላኪ ነው እርሷ ግን በክብር ባለቤት በክርስቶስ የምታምን ናት ሥጋዋም እስቲከሣና እስቲደርቅ መልኳም እስቲለወጥ ድረስ በሥውር ትጾማለች ትጸልያለችም።
#መጋቢት_28

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

#ጻድቅ_ንጉስ_ቈስጠንጢኖስ

መጋቢት ሃያ ስምንት በዚች ቀን ጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አረፈ። የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ቍንስጣ የእናቱ ስም ዕሌኒ ነው ቊንስጣም በራንጥያ ለሚባል አገር ንጉሥ ነው መክስምያኖስም በሮሜ በአንጾኪያና በግብጽ ላይ ነግሦ ነበር።

ይህም ቍስጣ አረማዊ ነበር ግን በጎ ሥራ ያለው እውነትን የሚወድ በልቡናውም ይቅርታና ርኃራኄን የተመላ ክፋት የሌለበት ነው። ወደ ሮሐ ከተማ በሔደ ጊዜ ዕሌኒን አይቶ ሚስት ልትሆነው አገባት እርሷም ክርስቲያናዊት ናት። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስንም ፀንሳ ወለደችው ስሙንም ቈስጠንጢኖስ ብላ ጠራቸው ይህም ዝንጉርጒር ማለት ነው።

ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቊንስጣ ዕሌኒን በዚያው ትቷት ወደ በራንጥያ ከተማ ተመለሰ። እርሷም ልጇን እያሳደገች በዚያው ኖረች የክርስትናን ትምህርት አስተማረችው ይቅርታንና ርኅራኄን በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው ትዘራበት ነበር። እርሷ ክርስቲያን ስትሆን የክርስትና ጥምቀትን ታጠምቀው ዘንድ አልደፈረችም መንፈሳዊ ዕውቀትን ሁሉ በማስተማር አሳደገችው ዳግመኛም ለመንግሥት ልጆች የሚገባውንም ሁሉ።

ከዚያም በኋላ ወደ አባቱ ሰደደችው አባቱም በአየው ጊዜ ደስ ተሰኘበት ዕውቀትን የተመላ ሁኖ ፈረስ በመጋለብም ብርቱና የጸና ሆኖ አግኝቶታልና በበታቹም መስፍን አድርጎ ሹሞ በመንግሥቱ ሥራ ላይ ሁሉ ሥልጣን ሰጠው።

ከሁለት ዓመትም በኋላ አባቱ አረፈ ቈስጠንጢኖስም መንግሥቱን ሁሉ ተረከበ የቀና ፍርድንም የሚፈርድ ሆነ ከእርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ ከሰዎች ላይ አስወገደ። አሕዛብም ሁሉ ታዘዙለት ወደዱትም የአገዛዙ ቅንነትና የፍርዱ ትክክለኛነት በአገሮች ሁሉ እስቲሰማ ተገዙለት።

የሮሜ ሰዎች ታላላቆች መልእክትን ወደርሱ ላኩ ከከሀዲ መክስምያኖስ ጽኑ አገዛዝ እንዲያድናቸው እየለመኑ እርሱ አሠቃይቷቸው ነበርና። ነመልእክታቸውንም በአነበቡ ጊዜ ስለ ደረሰባቸው መከራ እጅግ አዘነ ያድናቸውም ዘንድ ምን እደሚያደርግ በዐደባባይ ተቀምጦ እያሰበ ሲያዝን እነሆ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በቀትር ጊዜ ኅብሩ እንደ ከዋክብት የሆነ መስቀል ታየው በላዩም በዮናኒ ቋንቋ ኒኮስጣጣን የሚል ጹሑፍ አለ ትርጓሜውም በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ ማለት ነው።

የመስቀሉም ብርሃን የፀሐይን ብርሃን ሲሸፍነው በአየ ጊዜ አደነቀ። በላዩ ስለተጻፈውም አስቦ ለጭፍሮቹ አለቆችና ለመንግሥቱ ታላላቅ ባለሥልጣኖች አሳያቸው። እነርሱም ቢሆኑ ይህ መስቀል ስለምን እንደተገለጠ አላወቁም።

በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ለቈስጠንጢኖስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው በቀኑ እኩሌታ በቀትር በአየኸው በዚያ መስቀል አምሳል ላንተ ምልክት አድርግ በርሱም ጠላትህን ድል ታደርጋለህ አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ልቡ ጸና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት ዘውድ ላይ አደረገው መኳንንቱንና ወታደሮቹን ጭፍሮቹን ሁሉ መስቀል ሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም እንዳዘዛቸው አደረጉ።

ይህም የሆነው በበራንጥያ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ ነው። የሮሜን ሰዎች ከሥቃያቸው ሊያድናቸው ሠራዊቱን ሰብስቦ ተነሥቶ ወጣ። መክስምያኖስም ሰምቶ በታላቅ ወንዝ ላይም ታላቅ ድልድይ ሠርቶ ወደ ቈስጠንጢኖስም ተሻግሮ ከእርሱ ጋራ ተዋጋ።

የመስቀሉም ምልክት ቀድሞ በታየ ጊዜ የመክስምያኖስ ሠራዊት ድል ይሆኑ ነበር የቈስጠንጢኖስም ሠራዊት ከመክስምያኖስ ሰራዊት ብዙ ሰው ገደሉ። የቀሩትም ሸሽተው ሲሔዱ ከመክስምያኖስ ጋር ሊሻገሩና ወደ ሮሜ ሊገቡ ድልድይ ላይ ወጡ ድልድዩም ፈርሶ ፈርዖን ከሠራዊቱ ጋራ እንደ ሠጠመ እንዲሁ መክስምያኖስ ከሠራዊቱ ጋራ ሠጠመ።

ቈስጠንጢኖስም ወደ ሮሜ ከተማ ሲገባ የሮሜ ሰዎች ከካህናት ጋራ መብራቶች ይዘው በእንቍ የተሸለሙ አክሊሎችን ደፍተው እምቢልታ እየነፉ ተቀበሉት የተማሩ ሊቃውንትም የከበረ መስቀልን ሲያመሰግኑት የሀገራችን መዳኛ ይሉት ነበር ለከበረ መስቀልም ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።

ቈስጠንጢኖስም ዳግመኛ በሮሜ ነገሠ ከሀዲዎች የሆኑ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ስለ ክብር ባለቤት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ያሠሩአቸውን እሥረኞች ሁሉንም ፈታቸው ደግሞ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ ብሎ ዓዋጅ አስነገረ።

ዳግመኛም ክርስቲያኖችን እንዲአከብሩአቸው እንጂ እንዳያዋርዱአቸው የጣዖታቱንም ገንዘብና ምድራቸውን ለካህናት እንዲሰጧቸው አዘዘ ክርስቲያኖች በአረማውያን ላይ እንዲሾሙ አደረገ። ዳግመኛም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ ማንም ሰው በሰሙነ ሕማማት ሥራ እንዳይሠራ አዘዘ።

በነገሠ በሥስራ አንድ ዓመት በሮሜ ሊቀ ጳጳሳት በሶል ጴጥሮስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። ሠራዊቱም ሁሉ። ይህም የከበረ መስቀል ከተገለጠለት በኋላ በአራት ዓመት ነው።

ከዚህ በኋላም በእርሱ ርዳታና ድል ያገኘበትን የሚያድን ስለ ሆነ ስለ ጌታችን መስቀል ትመረምር ዘንድ እናቱ ዕሌኒን ወደ ኢየሩሳሌም ላካት። እርሷም ዐመፀኞች አይሁድ ቀብረው ከደፈኑት ቦታ አወጣችው።

በዘመኑ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ጳጳሳት የአንድነት ስብሰባ በኒቅያ ስለ አርዮስ ተደረገ። ለክርስቲያኖች መመሪያ በበጎ አሠራር ክርስቲያናዊት ሥርዓት ተሰራች።

ከዚህም በኋላ በበራንጥያ ታላቅ ከተማ ሊሠራ አሰበ እንደ አሰበውም ታላቅ ከተማ ሠርቶ በስሙ ቍስጥንጥንያ ብሎ ጠራት። በውስጧም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአግያና በሶፍያም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሠራ መንፈሳዊ በሆነ በመልካም ጌጥ ሁሉ አስጌጣት። በውስጥዋ ከሐዋርያት የብዙዎቹን ዓፅም ከሰማዕታትና ከቅዱሳን ጻድቃን ሥጋቸውን ስለሚሰበስብ።

የክብር ባለቤት ጌታችንን ደስ አሰኝቶ መልካም ተጋድሎውን ከፈጸመ በኋላ በኒቆምድያ ከተማ ጥቂት ታሞ አረፈ። ገንዘውም በወርቅ ሣጥን አድርገው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ አደረሱት የጳጳሳት አለቆችና ካህናቱ ከሁሉ ሕዝብ ጋር ወጥተው ተቀበሉት በብዙ ጸሎት በመዘመርና በማኅሌት በምስጋና ወደ ከበሩ ሐዋርያት ቤተ መቅደስ አስገብተው በክብር አኖሩት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
#ደግ እና #ጻድቅ #ንጉሥ አፄ #ዘርዓያዕቆብ ካረፉ ዛሬ (ጳጉሜን 3) 554ዓመት ሞላቸው፡፡

✞ ሃይማኖታቸው የቀናው ንጉሥና የእመቤቴ ወዳጅ ከ1426 - 1460 በቆየ መሪነታቸው፡-

✿ለቤተ ክርስቲያንና ለሃገር ብዙ ሆነዋል፡፡
✿ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ልዕልናዋ መልሰዋል ፡፡
✿ሃይማኖት ይቀናና ይሠፋ ዘንድ ተግተዋል፡፡
✿ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ (መጽሐፈ ብርሃንን ፡ ምዕላድን ፡ መልክዐ ማርያምን ፡ መልክዐ ጊዮርጊስን ጨምሮ)
✿ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ ቋንቋ አስተርጉመዋል፡፡
✿የሃይማኖት ጉባኤያትንም አድርገዋል ፡፡

✞ በዚህ ሁሉ መሐል ግን ስለሃገርና ቤተ ክርስቲያን ልዕልና ሲሉ የወሰዷቸውን መንግስታዊ ርምጃዎችን እየጠቀሱ ሊያቃልሏቸው የሚሞክሩ ዘመን የወለዳቸው ጸሐፍት አሉ፡፡

✞ ስለእነዚህ ሰዎች የምለው የለኝም ፡፡ "አቤቱ ፍረድልን" ከማለት በቀር፡፡

✞ ትልቁ ችግር ግን ሁሉን ነገር በሥጋዊ ልቦና ለመመርመር መሞከሩ ይመስለኛል፡፡

✞ ቤተ ክርስቲያን ግን ክብራቸውን፡-
✿በገድለ #ተክለሃይማኖት
✿በገድለ አቡነ #ተክለሐዋርያት
✿በገድለ አቡነ #ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን
✿በገድለ አቡነ #መብዓጽዮን
✿በድርሳነ #ኪዳነምሕረት እና
✿በመጽሐፈ #ስንክሳር . . . ትመሰክራለች፡፡

✞ የበለጠውን ምስክርነት የሚሻና ፡ ቅን ልቡና ያለው ሰው ካለ ደግሞ ወደ #ጻድቃኔማርያም ሔዶ እውነቱን ሊረዳ ይቻለዋል፡፡
"#የዘርዓያዕቆብ #እመቤት" ሲሏት #እመብርሃን ትሰማለችና፡፡

አምላከ #ቅዱሳን ከጻድቁ ንጉሥ በረከት ያሳትፈን፡፡

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
"" እንኳን አደረሳችሁ ""

☞ለ450 ዓመታት በኢየሩሳሌም፡ ግብጽ፡ ኢትዮጵያ (በጸገሮ፡ ኤጎራ፡ ጎንድ . . .): ፀሐይ ላይ የተጋደሉት ታላቁ #ጻድቅ #እጨጌ #አባ #ዮሐንስ የተወለዱት በዚህች ዕለት (ኅዳር 28፡ በ1110) ነው፡፡

=>ጸጋ በረከታቸው ይደርብን፡፡
#ደግ እና #ጻድቅ #ንጉሥ አፄ #ዘርዓያዕቆብ ካረፉ ዛሬ (ጳጒሜን 3) 555ዓመት ሞላቸው፡፡

✞ ሃይማኖታቸው የቀናው ንጉሥና የእመቤቴ ወዳጅ ከ1426 - 1460 በቆየ መሪነታቸው፡-

✿ለቤተ ክርስቲያንና ለሃገር ብዙ ሆነዋል፡፡
✿ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ልዕልናዋ መልሰዋል ፡፡
✿ሃይማኖት ይቀናና ይሠፋ ዘንድ ተግተዋል፡፡
✿ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ (መጽሐፈ ብርሃንን ፡ ምዕላድን ፡ መልክዐ ማርያምን ፡ መልክዐ ጊዮርጊስን ጨምሮ)
✿ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ ቋንቋ አስተርጉመዋል፡፡
✿የሃይማኖት ጉባኤያትንም አድርገዋል ፡፡

✞ በዚህ ሁሉ መሐል ግን ስለሃገርና ቤተ ክርስቲያን ልዕልና ሲሉ የወሰዷቸውን መንግስታዊ ርምጃዎችን እየጠቀሱ ሊያቃልሏቸው የሚሞክሩ ዘመን የወለዳቸው ጸሐፍት አሉ፡፡

✞ ስለእነዚህ ሰዎች የምለው የለኝም ፡፡ "አቤቱ ፍረድልን" ከማለት በቀር፡፡

✞ ትልቁ ችግር ግን ሁሉን ነገር በሥጋዊ ልቦና ለመመርመር መሞከሩ ይመስለኛል፡፡

✞ ቤተ ክርስቲያን ግን ክብራቸውን፡-
✿በገድለ #ተክለሃይማኖት
✿በገድለ አቡነ #ተክለሐዋርያት
✿በገድለ አቡነ #ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን
✿በገድለ አቡነ #መብዓጽዮን
✿በድርሳነ #ኪዳነምሕረት እና
✿በመጽሐፈ #ስንክሳር . . . ትመሰክራለች፡፡

✞ የበለጠውን ምስክርነት የሚሻና ፡ ቅን ልቡና ያለው ሰው ካለ ደግሞ ወደ #ጻድቃኔማርያም ሔዶ እውነቱን ሊረዳ ይቻለዋል፡፡
"#የዘርዓያዕቆብ #እመቤት" ሲሏት #እመብርሃን ትሰማለችና፡፡

አምላከ #ቅዱሳን ከጻድቁ ንጉሥ በረከት ያሳትፈን፡፡
#ቅድስት #ደብረ #ቢዘን (ኤርትራ)

#እመቤታችን በስደቷ ጊዜ ያረፈችበት፡፡
#በመካከለኛው_ዘመን እጅጉን ታዋቂ የነበረና የታላላቁ #ቅዱሳን #አባ_ፊልጶስ ፡  #አባ_ዮሐንስ እና #አባ_ናርዶስ ገዳም ነው፡፡

ዛሬ ደግሞ የታላቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓላቸው ነው፡፡

ከቅዱሱ ገዳምና ከሐዋርያዊው #ጻድቅ በረከት ይክፈለን፡፡
Forwarded from ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ (🕊Dawit🕊)
"" እንኳን አደረሳችሁ ""

☞ለ450 ዓመታት በኢየሩሳሌም፡ ግብጽ፡ ኢትዮጵያ (በጸገሮ፡ ኤጎራ፡ ጎንድ . . .): ፀሐይ ላይ የተጋደሉት ታላቁ #ጻድቅ #እጨጌ #አባ #ዮሐንስ የተወለዱት በዚህች ዕለት (ኅዳር 28፡ በ1110) ነው፡፡

=>ጸጋ በረከታቸው ይደርብን፡፡
ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት) ሕዝቡና ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት የሚመለክበት ነበር::ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል ገብተው ነበር::

ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር::

በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው:: እርሱም "እሺ" ብሎ ታዝዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ ተቀበለ:: ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል: ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር አደረገ::

በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ:-
1.ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
2.ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
3.ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን የጣለ ነቢይ ይባላል::

መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን ጣዖት አስመለኩት::

ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሐሰት ምስክር ደሙን አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም: አልለውጥም" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::

ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም::

በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: 900ው ሲታረዱ አንድ መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል (ለበአል) ሰገደ::

ይህን ጊዜ ግን ቅዱስ ኤልያስ እንዲህ አለ:-
"ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ከለከለ:: ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር : ጠል ለመከር ከመስጠት ተከለከለ::

ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ::

ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት:: ቀጥሎም 7 ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ ቀምሰዋል::

ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታለታለችና ሕዝቡ 850ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል::

ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ! ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው::

ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ (ሚካኤል) ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውኃ በመንቀል አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ3ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና እስክትጠግብ ብላ" አለው::

ኤልያስም ለ40 ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ በኋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም:: እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው በኋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ 2 ጊዜ እሳትን አዝንሟል::

የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን "የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን" አለው:: ሦስት ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ በኋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት::

ዛሬ ቅዱስ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሄኖክ ጋር ያርፋል:: (ራዕይ) ለተጨማሪ ንባብ ( ከ1ነገ. 17-2ነገ. 2 / እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ:: )

††† ነቢዩ ኤልያስ በእውነት ታላቅ ነው!

††† አምላከ ኤልያስ ለሃገራችንና ለሕዝቧ ርሕራሔውን ይላክልን::

††† #ጻድቅ_ኖኅ †††

††† የዚህን ታላቅ ቅዱስ ሰው ክብር የሚያውቅና የሚያከብረው ሁሉ ንዑድ ነው:: አባታችን ኖኅ ዛሬ በዓለም የሚመላለሰው ሰው ሁሉ አባት ነው:: ደግ ጻድቅና ነቢይ ሰው ነው::

ከአባታችን አዳም 10ኛው ጻድቅ ሲሆን ከ15ቱ አበው ነቢያትም አንዱ ነው:: ከአባቱ ከላሜሕ ተወልዶ: በደብር ቅዱስ አድጐ: ንጽሐ መላእክትን ገንዘብ አድርጐ: ለ500 ዓመታት በድንግልና ኑሯል::

በእነዚህ ጊዜያትም አጽመ አዳምን እየጠበቀና መስዋዕትን ለልዑል አምላክ እየሰዋ ያመልክ ነበር:: የሴት ልጆች ከቃየን ልጆች ጋር ተባብረው ዓለም በረከሰች ጊዜም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ተገኝቷል:: ከሚስቱ (እናታችን) ሐይከል (አምዛራ) ጋር 3 ጊዜ አብሮ አድሮ ሴም: ካምና ያፌትን ወልዷል::

የጥፋት ውኃ በመጣ ጊዜም የእመቤታችን ምሳሌ በሆነች መርከብ ድኗል:: ከመርከብ ወጥቶም ከጌታ ጋር በቀስተ ደመና ምስክርነት ቃል ኪዳን ተጋብቷል:: ከዚያም ዓለምን ለ3 ልጆቹ አካፍሎ ለ350 ዓመታት በበጐ አምልኮ ኑሯል:: በዚህች ቀንም ዕድሜን ጠግቦ በ950 ዓመቱ ዐርፏል::

††† የአባታችን በረከት ይደርብን።

††† ጥር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት


1.በዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ
2.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
3.ቅዱስ ኖኅ ጻድቅ
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
5.አባ ሙሴ ገዳማዊ
6.አባ ወርክያኖስ

††† ወርሐዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
4.ቅድስት ሰሎሜ
5.አባ አርከ ሥሉስ
6.አባ ጽጌ ድንግል
7.ቅድስት አርሴማ ድንግል

††† "እውነት እውነት እላቹሃለሁ:: በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል:: ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል::" †††
(ዮሐ. ፲፬፥፲፪)

††† "ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝኩትን: የባሪያየን የሙሴን ሕግ አስቡ:: እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላቹሃለሁ:: መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች: የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል::"  ††† (ሚል. ፬፥፬)

††† "እግዚአብሔርም:- 'የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ:: ከሰው እስከ እንስሳ: እስከ ተንቀሳቃሽም: እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና' አለ:: ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ::
የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው:: ኖኅም በትውልዱ
ጻድቅ: ፍጹምም ሰው ነበር:: ኖኅ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ::" †††
(ዘፍ. ፮፥፯)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
Forwarded from 🕊ኢዮአታም🕊
የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወዳጅ፡ የእግዚአብሔር ሰው፡ ኢትዮጵያዊው #ጻድቅ_አቡነ_እንድርያስ  የካቲት1 ዕረፍታቸው ነው።

"" ከበረከቱ ይክፈለን! ""


✞✞✞Abune Endrias (Andrew) the Ethiopian✞✞✞
✞Also on this day (Yekatit 1 – February 8) is commemorated the departure of the man of God, Abune Endrias the Ethiopian, the companion of Abune Ewostatewos (Eustathius) at the age of 126 years.
መጋቢት 5

††† እንኳን ለጻድቅ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

†††
#ጻድቅ_አፄ_ገብረ_መስቀል †††

††† የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ነገሮቿ የታደለች ናት:: ከእነዚህም መካከል በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ነገሥቶቿ (መሪዎቿ) ቅዱሳን (ጻድቃን) ናቸው:: ለአንዲት ሃገር የመሪዎቿ ጥሩ ክርስቲያን መሆን እጅግ ወሳኝ ነው::

ባለፉት 40 ዓመታት እንኩዋ የደረሰብንን የመንፈስ ዝለትና የሞራል ዝቅጠት ስንመለከት አንድም ችግሩ ከመሪዎቻችን እንደ ሆነ እናስተውላለን:: የሃገራችንን ታሪክ ስንመለከት ግን በእሳትና በጦርነት መካከል ሆነው ለፈጣሪ የተገዙ ብዙ ነገሥታትን እናገኛለን::

††† እንደ ምሳሌም:-
*ንግሥተ ሳባ
*ቀዳማዊ ምኒልክ
*አብርሐ ወአጽብሐ
*ካሌብ
*ገብረ መስቀል
*ለሐርቤ
*ላሊበላ
*ይምርሐ
*ነአኩቶ ለአብ
*ዳዊት
*ቴዎድሮስ ቀዳማዊ
*ዘርዓ ያዕቆብ
*በእደ ማርያም
*ናዖድ
*ልብነ ድንግል
*ገላውዴዎስ
*ዮሐንስ
*ኢያሱ ቀዳማዊና
*ተክለ ሃይማኖት መናኔ መንግሥትን እናገኛለን::

††† ከእነዚህ መሪዎቻችን መካከል እኩሉ መንግስታቸውን ትተው በርሃ የገቡ ሲሆኑ እኩሉ ደግሞ በዙፋናቸው ላይ ሳሉ በጐ ሠርተው የተገኙ ናቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ በጥፋታቸው ተጸጽተው ንስሃ የገቡ ናቸው::

ከነገሥት ጻድቃን መካከልም ይህች ዕለት የአፄ ገብረ መስቀል መታሰቢያ ናት:: ጻድቁ ንጉሥ የአፄ ቅዱስ ካሌብ ልጅ ሲሆን በኢትዮዽያ የነገሠው በ515 ዓ/ም ነው:: ሲነግሥም እጅግ ወጣት ነበረ:: ምክንያቱም አባቱ ካሌብ ከናግራን ጦርነት መልስ በመመነኑ በዙፋኑ የተቀመጠ ልጁ እርሱ ነበርና::

ከዚህ ቅዱስ የመጀመሪያ የምናደንቀው ስሙን ነው:: የዛሬ 1,500 ዓመት እንኩዋ በመስቀል የሚመኩ: ለመስቀል የሚገዙ መሪዎች መኖራቸው በዘመኑ የነበረውን የክርስትና ደረጃ ያሳያል:: "ገብረ መስቀል" ማለት "የመስቀል አገልጋይ (ባሪያ)" ማለት ነውና::

አፄ ገብረ መስቀል በጐ ንጉሥ እንዲሆን የቅዱስ አባቱ ማንነት የረዳው ይመስላል:: ያ ኃያል: ብርቱና ዓለም የፈራው አባቱ ሲጀመር በፍቅረ ክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር የተያዘ ደግ ሰው መሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስቱን እንደ ጨርቅ ትቶ ሲሔድ መመልከቱ እርሱንም ያው አድርጐታል::

እርሱም ከአባቱ እንዳየው በአክሱም ላይ በነገሠባቸው ዓመታት በጾምና በጸሎት: ፍትሕ ርትዕ ሳያጓድል: ድሃም ሳይበድል ይኖር ዘንድ ጥረት አድርጉዋል::

††† አፄ መስቀል †††

††† ይህ ጻድቅ ንጉሥ ለእኛ ከተወልን ትሩፋቶቹ አንዱ በዓለ መስቀልን በአደባባይ ማስከበሩ ቅድሚያውን ይይዛል:: በዓሉ መስከረም አካባቢ የሚደረግ ሲሆን "አፄ መስቀል" ይባላል::

ሕዝቡ: ካህናቱና መሣፍንቱ አድዬ አበባ እየዘነጠፉ ወደ ንጉሡ አደባባይ ይተማሉ:: በዚያም በያሬድ ዝማሬ ለቅዱስ መስቀሉ ታላቅ በዓል ይከበራል:: ይህ በዓል ይኼው ዛሬ በUNESCO ተመዝግቧል::

††† ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ †††

††† ሃገራችን ታላቁን ሰማያዊ ዜማ ያገኘችው በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው:: ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ያገኘውን ማኅሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በአክሱም ጽዮን:-

"ሃሌ ሉያ! ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ: ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ" ብሎ ከ3ቱ ጸዋትወ ዜማ በአንዱ በአራራይ ሲያዜም ንጉሡ በዜማው ተመስጦ እየሮጠ ወደ ጽዮን ደርሷል::

ከዜማው ጥፍጥና (ጣዕም) የተነሳ ሁሉም ተደመሙ:: ንጉሡም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከቅዱስ ያሬድ የማይለይ ሆነ:: ስብሐተ እግዚአብሔርንም ለብዙ ጊዜ ከቅዱሱ ሊቅ በጥዑም ዜማ ተቀምሞለት ተመገበ::

እንዲያውም አንዴ ሊቁ ሲያዜምለት ጻድቁ አፄ ገብረ መስቀል የቅዱስ ያሬድ እግር ላይ በትረ መንግስቱን ተክሎበታል:: ሁለቱም ከተመስጧቸው ሲነቁ ግን ንጉሡ ደንግጦ "ምን ልካስህ?" ቢለው "ወደ በርሃ አሰናብተኝ" አለው::

አፄ ገብረ መስቀልም እያዘነ ፈቅዶለታል:: ቅዱስ ያሬድም ከመሬት ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፎ: የመሰናበቻ ምስጋናን:-
"ውዳሴ ወግናይ: ለእመ አዶናይ: ቅድስት ወብጽዕት . . ."
ብሎ አንቀጸ ብርሃንን: በሚጣፍጥ ዜማ ሰተት አድርጐ አደረሰ:: ይህንን ሲሰማ ንጉሡ ፈጽሞ አለቀሰ::

እስከ መንገድ ድረስ ከሕዝቡና ሠራዊቱ ጋር ከሸኘው በሁዋላም ቅዱስ ያሬድ ጸለምት ላይ ሲደርስ በዜማ አሰምቶ "ሰላም ለኩልክሙ" አለ:: አፄ ገብረ መስቀልና ሕዝቡም "ምስለ መንፈስከ" ብለውት ቀና ሲሉ ከዓይናቸው ተሰወረ:: ንጉሡም በዘመኑ ማኅሌተ ሰማይ እንዲስፋፋ ብዙ ጥሯል::

††† ንጉሡና 9ኙ ቅዱሳን †††

ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ወንጌልን እንዲሰብኩ: መጻሕፍትን እንዲተረጉሙና ገዳማዊ ሕይወትን እንዲያስፋፉ አፄ ገብረ መስቀል ትልቅ ጥረት አድርጉዋል::

በተለይ ከአባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል ጋር ልዩ ቅርበት ነበረው:: ዘወትርም ከእነርሱ ይባረክ ነበር:: አቡነ አረጋዊንም በየጊዜው ይጐበኛቸው እንደ ነበር ይነገራል::

††† ንጉሡና ታቦት †††

ልክ እንደ ቅዱስ መስቀሉ ሁሉ ታቦተ እግዚአብሔር በዑደት እንዲከበር ያደረገ ይህ ንጉሥ ነው ይባላል:: መነሻው ደግሞ የደብረ ዳሕሞ መታነጽ ነው:: አንድ ቀን አቡነ አረጋዊን ምን እንደሚሹ ቢጠይቃቸው "የድንግል እመቤታችን ማርያምን መቅደስ አንጽልኝ" አሉት::

በደስታ አንቆጥቁጦ አነጻት:: የምርቃቱ ዕለትም ንጉሡ: ጻድቁና ሊቁ (ማለትም ገብረ መስቀል: አረጋዊና ያሬድ) ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ተገኙ:: በጊዜውም ታቦቱ ሲነግሥ ቅዱስ ያሬድ ባቀረበው ማኅሌታዊ ዜማና አበው ባደረጉት ዝማሬ: ታቦቱ እየዞረ ታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ሆነ::

ደብረ ዳሞ ያኔ መወጣጫ ደረጃ ነበረው:: ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ ከበዓል ሲመለሱ በአቡነ አረጋዊ ጥያቄ መወጣጫው ተደርምሷል::

ጻድቁ "ዳሕምሞ (ደርምሰው)" ስላሉት ቦታው ዳሕሞ (ዳሞ) ተብሎ ቀርቷል:: ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

††† አምላከ ነገሥት ጻድቃን ቅኑን መሪ በሁሉም ሥፍራ ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::

††† "አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል::
በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::
የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም::
በበጐ በረከት ደርሰህለታልና::
ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ::
ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም::
ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ::
በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" †††
(መዝ. 20፥1-5)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር†††