ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_8
#የእጮኝነት_ጊዜ
መሰረቱ ጠንካራ የሆነ ህንፃ አስተማማኝ ኩራት ነው ። መሰረቱ የተስተካከለና ጠንካራ የሆነ የፍቅር ጅማሬም እንደዚያው ነው ። ትዳር ከእጮኝነት ጊዜ መሠረቱ ጥሩ ካልሆነ መልካም ጎኑ ደምቆ አይታይም ። እና ይህ ጊዜ በጣም ጥንቃቄን ይፈልጋል። አስበን አውጥተን ፣ አውርደን ፣ በተለይም እግዚአብሔር ለሚወድልን ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ትርፍና ኪሳራውን አመዛዝነን ፣ የምንጀምረው የፍቅር ውጥን ነው ። መተጫጨት በራሱ ለነገው ሕይወታችን የዛሬ መሰረት ነው ። ከሁሉ በፊት ግን ፍቃድን ለእግዚአብሔር መስጠት ያስፈልጋል ። #የክርስትና_ሕይወት ማለት ከራስ ፍቃድና ጥበብ ውጪ ሆኖ #በእግዚአብሔር_ፈቃድ ውስጥ መኖር ማለት ነው ። ጥበብ ፣ ፍልስፍና ፣ ሊቅነትና ሰፊ የእውቀት አድማስ እንኳን በውስጣችን ስፍራ ቢኖራቸውም በእግዚአብሔር ፍቃድ ውስጥ ካልዋሉና በመንፈስቅዱስ ኃይል ካልታገዙ በራስ መደገፍ ብቻውን ትርጉም አይኖረውም ። ሰለሞን ለዚህ ነው "በራስህ ማስተዋል አትደገፍ" ያለው ምሳ 3÷5
#ከማጨት_በፊት_ምን_ያስፈልጋል_?
#1ኛ #አካላዊ_ብቃት (Physical Maturity) ፦ አንድ ሰው ከማጨቱ በፊት ማሰብ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል ለአካላዊ ብቃት መድረሱን ነው ።ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ "ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ..." ብሎ ለፍቅር ሕይወት የእድሜን ወሳኝነት የነገረን ። (1ኛ ቆሮ7÷36) ሠሎሞንም "ለመውደድም ጊዜ አለው "ያለው ቃል ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክርልን
#2ኛ #መንፈሳዊ_ብስለት (Spritual Maturitey )
በመንፈሳዊ ሕይወት መብሰል ለምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ስኬት ውበት ነው ። በመንፈሳዊው ነገር የበሰለ ሰው ቤቱን በዓለት ላይ የሠራን ሰው ይመስላል ። ከማጨት አስቀድሞ ራስን ማየት ያስፈልጋል ። ያልበሰለ ሰው ያየው ሁሉ ያምረዋል ። ዐይኖቹ ላረፈበት ነገር ሁሉ ቶሎ ይሸነፋል ። እንደ ዮሴፍ በሩን ሰብሮ መውጣት ቢያቅተው እንኳን ቢያንስ እንደ ትዕማር "ይህ በእስራኤል ዘንድ ኃጢአት ነው " (2ሳሙ 13÷12)እንኳን አይልም ።
#3ኛ #የኢኮኖሚ_ብቃት (Economical Maturation ) ፦የፍቅር ሕይወት አላማ #ጋብቻ ነው ። በጋብቻ ሕይወት ለመኖር ደግሞ ኢኮኖሚ አንዱ ነገር ነው ። ለትዳር ጣራ የነካ ኢኮኖሚ ባያስፈልግም የተወሰነ የኢኮኖሚ አቅም ግን ያስፈልጋል ። በቀጣይ ደሞ የተሳሳቱ የማጫ (የፍቅር ጓደኛን) መምረጫ መንገዶችን እናያለን ይቆየን

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_9
#የተሳሳተ_የትዳር_ጓደኛ_አመራረጥ
በዓለማችን ላይ ለምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ውሳኔዎችን እንወስናለን ። #ጋብቻም የእኛን ውሳኔ ከሚጠይቁት ቁም ነገሮች አንዱ ነው ። በመንፈሳዊ መነጽር ስንመለከተው እግዚአብሔር ያዘጋጀውን በጋብቻ ልንረከብ /ልንቀበል/ እንደምንችል የታመነ ነው ። ለአዳም ሔዋንን የሰጠ እርሱ ነውና ። ሆኖም ግን ከመወለድ ፈጽሞ የተለየ ነው ። እኛ ስንወለድ አሁን አባት እናት ከሆኑን ወላጆቻችን ዘንድ መወለድ እንዳለብን ወስነን የገባንበት አይደለም ። ወይም የአሁኗ እናታችንና አባታችን እንዲሁም ወንድምና እህቶቻችንን የኛ ቤተሰብ እንዲሆኑልን ወስነን የገባንበት አይደለም ። #ጋብቻ ግን ከዚህ ይለያል ። ም/ቱም የትዳር ጓደኛችንን የምንቀበለው ትሆነኛለች ይሆነኛል ያልነውን ወስነን ነውና ። ከዚህ ጋር አያይዘንም ለምርጫችን አሳሳች የሆኑ ነገሮችን ማየትና መመርመር መርምሮም መገንዘብ ያስፈልጋል። ለዚሁም የሚከተሉትን በምሳሌነት ማየት ይቻላል።
#ሀ_ጥንቆላ
ጥንቆላ በቤተክርስቲያናችን የተወገዘ ተግባር ነው ። ሰዎች ዕውቀታቸው እና አእምሮአቸው ውሱን ስለሆነ ስለነገ ማወቅ አይችሉም ። በመሆኑም ስለተሰወረባቸው እውቀት ለማወቅ ጉጉዎች ናቸው ። ከዚህም በመነሳት የወደፊት የትዳር ጓደኛቸው ምን አይነት እንደሆነ ፣ ወደፊት ስለሚወልዱት ልጅ እንዲነግራቸው ጠንቋይ ጋር ይሄዳሉ ።
#ለ_አሳሳች_ሕልም
ሕልም ሁለት ወገን ነው ። #አንዱ የነፍስ ወገን ሆኖ ፍሬ ፣ ቁምነገርና ውጤት ያለው ትንቢት ወይም ራዕይ ይባላል። እነ ዮሴፍ እነ ዳንኤል ያዩት ህልም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው ። #ሁለተኛው ወገን ደሞ
ከሰይጣን የሚመጣ አሳሳች ነው ። መመንኮስ ያለበት ማግባት እንዳለበት ፤ ማግባት ያለበት ደሞ መመንኮስ እንዳለበት አድርጎ ሊያሳየው ይችላል። ስለዚህ በደፈናው እገሊትን እገሌን በህልሜ አይቻለው ብሎ ወደ ትዳር መግባት የቅዠት ትዳር ምስረታ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ።
#ሐ_ዕጣ_ማውጣት
ዕጣ ማውጣት በብሉይም በሀዲስም የነበረ አሁንም ያለ የሰው ልጆች የኑሮ ክፍል ነው ። ስለዚህ ሰዎች ለመወሰን የተቸገሩበትን ነገር ወይም ወስነው ይበልጥ ለማረጋገጥ የፈለጉትን ነገር አስመልክቶ ዕጣ ሲያወጡ ይታያል ። በመፅሐፍም ለምሳሌ በዮናስ ታሪክ ላይ ማዕበል በመነሳቱ በመርከብ ያሉትን ሰዎች በማን ሀጥያት መሆኑን ለማረጋገጥ ዕጣ ሲጥሉ በዮናስ ላይ ወጥቷል ። የእመቤታችን ጠባቂ እንዲሆን እግዚአብሔር በልዩ ልዩ ምልክት ጻድቁንና አረጋዊዉን ዮሴፍን ከመረጠው በሗላ ካህናቱ በዕጣ አረጋግጠዋል ። ዛሬም በሀገራችን በጎ ልማድ ተይዞ ሰዎች ሲታመሙ ጠበል ለመምረጥ ዕጣ ያወጣሉ ። ከዚህ በመነሳት ብዙ ሴት የወደደ ወንድ ፤ ወይም ብዙ ወንድ የወደደች ሴት ከእነዚህ አንዱ የኔ እንዲሆን ብላ ዕጣ ልታወጣ ታስብ ይሆናል ። ነገር ግን በዚህ መመራት ከባድ ነው ። ሁልጊዜ ዕጣ ማውጣት የእግዚአብሔር ፍቃድ መገለጫ ላይሆን ይችላል። መጓዝ ያለብንን ያህል ተጉዘን እንወስን እንጂ ከላይ ባየናቸው መንገዶች የትዳር አጋርን መምረጥ ስህተት ነው ። ቀጣይ ደሞ የጋብቻ አይነቶችን እናያለን።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_8
@zekidanemeheret
#6 አታመንዝር
🖊ይህ ህግ የተሰጠበት አላማ በንፅህና በቅድስና እንዲኖር ሲል ነው።
🖊አመንዝራነት በሦስት ይከፈላል
#፩ ፦ አመንዝራ ማለት ባልና ሚስት ኖሯቸው ትተው ወደ ሌላ ሲሄዱ አመንዝራ ይባላል።
🖊እግዚአብሔርን ትቶ ወደ ጣኦት አምልኮ መሄድ አመንዝራ ይባላል
#፪ ፦ሴሰኝነት ማለት ስስታም ማለት ነው
#፫ ፦ጋለሞታ ማለት ሰውነትን ለገንዘብ አሳልፎ መስጠት ናቸው።
@zekidanemeheret
🖊ለአቅመ አዳምና አቅመ ሔዋን የደረሱት ወንድና ሴት ከጋብቻ በፊትም ሆነ በኀላ ሕግ ከሚፈቅድላቸው የጋብቻ ግንኙነት ውጭ የሚፈፅሙት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሁሉ #አመንዝራነት ወይም #ዝሙት ይባላል። ይህም አድራጎት በ፯ኛው ትዕዛዝ የተከለከለ ነው ።
🖊 አመንዝራነት በገነነበት ሀገር ሕጋዊ ጋብቻ ይናቃል ። #ጋብቻ ከሌለ ጤናማ ቤተሰብ አይኖርም ። ጤናማ ቤተሰብ ከሌለ ደግሞ ጠንካራ ኀብረተሰብና ጥሩ ዜጎችን ማግኘት አይቻልም። እንዲያውም ከሐዲና ዘማዊ ትውልድ ይፈጠራል። ይህም የሀገርን ውድቀት ያስከትላል። የእግዚአብሔርን እርግማን ያመጣል። ስለዚህ በልዩ ልዩ በደልና ክፋት የተያዙትን በተለይም በዓመፅ ስራና በዝሙት ኀጢአት ብዛት ከገፀ ምድር የጠፉትን የኖኀ ዘመን ሰዎችን በአብርሃም ዘመን የነበሩትን ሰዶምና ገሞራን እያሰብን ከዝሙት ራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል።
🖊ቤተክርስቲያን በዝሙት እንዳንወድቅ የምትሰጠው መፍትሄ አለ። ይኸውም ፦
# ራሳችንን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጣጠር
# በተዓቅቦ መኖር ፡
# አንድ ወንድ በአንዲት ሴት አንዲት ሴት በአንድ ወንድ መፅናት
🖊 እንዲሁም መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግ ነው።
🖊 የዝሙት የርኩሰት ሥራ ሁሉ እንስሳዊ ባህርያችንን ስለሚያጎላም በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረችውን ነፍሳችንን በጣም ይጎዳታል።
🖊የዝሙት ኀጢአት በድርጊት ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን (በሀልዩ) በሐሳብ ፣በምኞት ጭምር የሚፈፀም ነው። ጌታችን በወንጌል "አታመንዝር እንደተባለ ሰምታቹሀል ። እኔ ግን እላቹሀለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሯል ። /ማቴ፭÷፳፯/ እንግዲህ ይህ ድርጊት አልባ የሆነው የዝሙት ምኞትና ሐሳብ ቆይቶ ወደ ድርጊት ስለሚያመራ በቅድሚያ እሱን መቆጣጠር የመጀመሪያው ሥራችን መሆን ይገባዋል።
🖊የዝሙትና የሐጢአት ሁሉ መነሻቸውና ምንጫቸው ምኞት መሆኑን ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ነግሮናል። "እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ ቡሃላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ፣ ኃጢአትም ካደገች ቡሃላ ሞትን ትወልዳለች " (ያዕ፩:፲፬)
🖊በርግጥ በአሁን ሰአት ወጣቶችን የሚያማልል የዝሙትን ነገር የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ፊልሞች ይታያሉ። እንደዚህ ዓይነቱ የዝሙት ሐሳብን የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ሥዕሎች ፣ ልብ ወለድ ድርሰቶችና የመሳሰሉት በየሱቁና በየቦታው ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነው በመገናኛ ብዙሀንም ይኽን የመሰለ ነገር በየጊዜው በመታየቱ ነው። ጤናማውን የሞራል የቤተሰብንና የማኀበራዊ ኑሮን የሚመርዙት ፊልሞችና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች ቀርተው በምትኩ የትምህርትና የሥራ ጉዳዮች ፣ የልማትና የምርት ስራዎች ፣ የጤናና የማህበራዊ ኑሮን የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ሰፋ ያለ ጊዜ ተሰጥቷቸው በመገናኛ ብዙሀን ቢታዩና ቢሰሙ ለሀገርና ለወገን ይጠቅማል ። መዝናኛም ከተፈለገ የሀገሩን ባሕል ፣ የሕዝቡን ሃይማኖትና ሞራል በመጠበቅ በወጉና በአግባቡ ሊደረግ ይችላል። ራስን በመግዛት በንፅህና በመመላለስ ከዝሙት መራቅ ይገባናል።
🖊የአመንዝራነት መንስዔ
# ከመጠን በላይ መብላትና መጠጣት
# አለባበስ
# ምኞት
# ፌልም ማየት
# መላፋት ፤ የአላግባብ መተቃቀፍ ፤ መሳሳም ወዘተ ናቸው። { በዘፈኗ እንዳታስትህ ከዘፋኝ ሴት ጋር አትጫወት} ሲራክ ፱÷፬
🖊የአመዝራነት ፍፃሜው
# የሞራል ድቀት {መሞት}
# በመንፈሳዊ ሞት
@zekidanemeheret

ይቀጥላል...

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret