ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_8
@zekidanemeheret
#6 አታመንዝር
🖊ይህ ህግ የተሰጠበት አላማ በንፅህና በቅድስና እንዲኖር ሲል ነው።
🖊አመንዝራነት በሦስት ይከፈላል
#፩ ፦ አመንዝራ ማለት ባልና ሚስት ኖሯቸው ትተው ወደ ሌላ ሲሄዱ አመንዝራ ይባላል።
🖊እግዚአብሔርን ትቶ ወደ ጣኦት አምልኮ መሄድ አመንዝራ ይባላል
#፪ ፦ሴሰኝነት ማለት ስስታም ማለት ነው
#፫ ፦ጋለሞታ ማለት ሰውነትን ለገንዘብ አሳልፎ መስጠት ናቸው።
@zekidanemeheret
🖊ለአቅመ አዳምና አቅመ ሔዋን የደረሱት ወንድና ሴት ከጋብቻ በፊትም ሆነ በኀላ ሕግ ከሚፈቅድላቸው የጋብቻ ግንኙነት ውጭ የሚፈፅሙት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሁሉ #አመንዝራነት ወይም #ዝሙት ይባላል። ይህም አድራጎት በ፯ኛው ትዕዛዝ የተከለከለ ነው ።
🖊 አመንዝራነት በገነነበት ሀገር ሕጋዊ ጋብቻ ይናቃል ። #ጋብቻ ከሌለ ጤናማ ቤተሰብ አይኖርም ። ጤናማ ቤተሰብ ከሌለ ደግሞ ጠንካራ ኀብረተሰብና ጥሩ ዜጎችን ማግኘት አይቻልም። እንዲያውም ከሐዲና ዘማዊ ትውልድ ይፈጠራል። ይህም የሀገርን ውድቀት ያስከትላል። የእግዚአብሔርን እርግማን ያመጣል። ስለዚህ በልዩ ልዩ በደልና ክፋት የተያዙትን በተለይም በዓመፅ ስራና በዝሙት ኀጢአት ብዛት ከገፀ ምድር የጠፉትን የኖኀ ዘመን ሰዎችን በአብርሃም ዘመን የነበሩትን ሰዶምና ገሞራን እያሰብን ከዝሙት ራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል።
🖊ቤተክርስቲያን በዝሙት እንዳንወድቅ የምትሰጠው መፍትሄ አለ። ይኸውም ፦
# ራሳችንን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጣጠር
# በተዓቅቦ መኖር ፡
# አንድ ወንድ በአንዲት ሴት አንዲት ሴት በአንድ ወንድ መፅናት
🖊 እንዲሁም መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግ ነው።
🖊 የዝሙት የርኩሰት ሥራ ሁሉ እንስሳዊ ባህርያችንን ስለሚያጎላም በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረችውን ነፍሳችንን በጣም ይጎዳታል።
🖊የዝሙት ኀጢአት በድርጊት ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን (በሀልዩ) በሐሳብ ፣በምኞት ጭምር የሚፈፀም ነው። ጌታችን በወንጌል "አታመንዝር እንደተባለ ሰምታቹሀል ። እኔ ግን እላቹሀለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሯል ። /ማቴ፭÷፳፯/ እንግዲህ ይህ ድርጊት አልባ የሆነው የዝሙት ምኞትና ሐሳብ ቆይቶ ወደ ድርጊት ስለሚያመራ በቅድሚያ እሱን መቆጣጠር የመጀመሪያው ሥራችን መሆን ይገባዋል።
🖊የዝሙትና የሐጢአት ሁሉ መነሻቸውና ምንጫቸው ምኞት መሆኑን ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ ነግሮናል። "እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ ቡሃላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ፣ ኃጢአትም ካደገች ቡሃላ ሞትን ትወልዳለች " (ያዕ፩:፲፬)
🖊በርግጥ በአሁን ሰአት ወጣቶችን የሚያማልል የዝሙትን ነገር የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ፊልሞች ይታያሉ። እንደዚህ ዓይነቱ የዝሙት ሐሳብን የሚያንፀባርቁ ማስታወቂያዎችና ሥዕሎች ፣ ልብ ወለድ ድርሰቶችና የመሳሰሉት በየሱቁና በየቦታው ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነው በመገናኛ ብዙሀንም ይኽን የመሰለ ነገር በየጊዜው በመታየቱ ነው። ጤናማውን የሞራል የቤተሰብንና የማኀበራዊ ኑሮን የሚመርዙት ፊልሞችና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች ቀርተው በምትኩ የትምህርትና የሥራ ጉዳዮች ፣ የልማትና የምርት ስራዎች ፣ የጤናና የማህበራዊ ኑሮን የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ሰፋ ያለ ጊዜ ተሰጥቷቸው በመገናኛ ብዙሀን ቢታዩና ቢሰሙ ለሀገርና ለወገን ይጠቅማል ። መዝናኛም ከተፈለገ የሀገሩን ባሕል ፣ የሕዝቡን ሃይማኖትና ሞራል በመጠበቅ በወጉና በአግባቡ ሊደረግ ይችላል። ራስን በመግዛት በንፅህና በመመላለስ ከዝሙት መራቅ ይገባናል።
🖊የአመንዝራነት መንስዔ
# ከመጠን በላይ መብላትና መጠጣት
# አለባበስ
# ምኞት
# ፌልም ማየት
# መላፋት ፤ የአላግባብ መተቃቀፍ ፤ መሳሳም ወዘተ ናቸው። { በዘፈኗ እንዳታስትህ ከዘፋኝ ሴት ጋር አትጫወት} ሲራክ ፱÷፬
🖊የአመዝራነት ፍፃሜው
# የሞራል ድቀት {መሞት}
# በመንፈሳዊ ሞት
@zekidanemeheret

ይቀጥላል...

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_9
@zekidanemeheret
#7 አትስረቅ
🖊መስረቅ ማለት የሌላውን ገንዘብና ንብረት መውሰድ ሲሆን አወሳሰዱም ባለቤቱ ሳያውቅ ወይም በማታለል ወይም በኀይል ይፈፀማል።
🖊ጉቦኝነትም ሰዎች በሥልጣናቸው አማካኝነት የሌላውን ገንዘብ የሚወስዱበት ወይም ጥቅም የሚያገኙበት መንገድ እስከሆነ ድረስ ስውር ስርቆት ነው ማለት ይቻላል። 🖊ሚዛንም ስርቆት ነው ። "ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው ፡ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም " ተብሎ ተፅፏል ። ( ምሳ፳÷፳፫) 🖊የሰውን ገንዘብ ከመውሰድ የከፋ ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት መስረቅ ነው ። ም/ቱም ይህንን ያደረገው ሰው ከስርቆት ወንጀል ሌላ የእግዚአብሔርን ስም አቃሏል ፤ ሃይማኖቱንም ክዷል ማለት ይቻላል። ስለዚህ አድራጎቱ የበደል በደል ነው ። እንደዚህ አይነት ሰው ባልንጀራውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው የበደለው። 🖊ሌሎችም እንደስርቆት የሚቆጠሩ ነገሮች አሉ ። በምቀኝነትም ይሁን በተንኮል ወይም በግፍ የሰውን ገንዘብና ንብረት ማስቀረት ወይም መቀነስ ወይም ማቆየት ነው ። 🖊የሰራተኞችን ደመወዝ ማስቀረት ወይም አለአግባብ ደመወዛቸውን መቁረጥ አሰሪዎችን በደለኞች ያደርጋቸዋል። ቅዱስ ያዕቆብ "እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮሀል ፡ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባኦት ጆሮ ገብቷል ። " (ያዕ፭÷፬)
🖊ሌላው የአደራ ገንዘብን መብላትና የተዋሱትን የተበደሩትን ገንዘብ አለመመለስም እንደ ስርቆት ይቆጠራል። የተሳሉትን ስዕለት ፣ የገቡትን ብፅዓት አለመፈፀም እግዚአብሔርን መበደል ነው ። ልንፈፅመው የማንችለውን ነገር ቃል አለመግባት ይሻላል። አስራት በኩራትን ማስቀረት እግዚአብሔርን መስረቅ ነው {ት-ሚል፫÷፰}።
🖊ሰውን ወደ መስረቅ ምን ያደርሰዋል
# ድህነት
# በተንኮል
# በምቀኝነት
# በልማድ{በልምድ} ፤
# ምኞት
# በሰይጣን ግፌት ፤
# አለማመን {እግዚአብሔርን አለማወቅ } ወዘተ ናቸው።
🖊 ከመስረቅ እንዴት እንቆጠባለን
# በማመን
# ይበቃኛል ማለት ፤
# በፃም
# በፀሎት
# በስግደት እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ መፅሐፍት ማንበብ ናቸው።
🖊ሰዎች ሁሉ እንኳን የሌላውን ገንዘብ መስረቅ ቀርቶ የራሳቸውንም እንዲያካፍሉ ታዘዋል ። ስለዚህ የቀማን መልሰን የበደልን ክሰን ያለንን አካፍለን ከስርቆት ተቆጥበን ልንኖር ይገባል።
@zekidanemeheret

ይቀጥላል....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
👉 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_10
#8 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
@zekidanemeheret
🖊ይህ ቃል የሚሰራው በሐሰት ለሚመሰክር ብቻ አይደለም ሐሰትንም ለሚቀበል ነው። ማቴ ፰÷፵፩
ምሳ ፲፪÷፳፪ ፤ ፩ነገ ፳÷፲፫ ፤ መሳፍ ፲፱÷፭
🇪🇹ምስክርነት ምን ማለት ነው ? በሐሰት መመስከርስ እንዴት ነው ?
🖊 #ምስክርነት ማለት በዳኛ ፊት ወይም በባለሥልጣን ፊት ወይም በአስታራቂ ሽማግሌዎች ወይም ስለ ሥነ ስርዓት ጉዳይ በተሰየመ ጉባኤ ፊት የቀረበውን ሙግትና ክርክር በትክክል ለመፍረድና ለመወሰን የሚረዳ የቃል ማረጋገጫና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያመለክት ነው ። በእውነት የሚቀርበው ምስክርነት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስመሰግናል። ነገር ግን ሰዎች በልዩ ልዩ ጥቅም ተገዝተው ወይም ባልንጀራን አለአግባብ ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል እውነቱን ነገር በመሸሸግ ሐሰት ነገር በመፍጠር ያልተነገረውን ተነገረ ያልተደረገውን ተደረገ በማለት በመሐላም ሆነ ያለ መሐላ የሚቀርበው የውሸት ማስረጃ ሁሉ የሐሰት ምስክርነት ይባላል። በኀብረተሰቡ ውስጥ እውነትና ሐቅ ጠፍቶ ፍርድ ጎድሎ ድሀ ተበድሎ ሰዎች ሁሉ ጊዜያቸውንና ኃይላቸውን ገንዘባቸውንም በክርክርና በጠብ እንዳያጠፋና ሰላማቸውን እንዳያጡ በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ በማሰብ እግዚአብሔር "በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር" የሚለውን ትእዛዝ እንድንጠብቀው ሰጥቶናል።
🖊ይህን ትዕዛዝ መተላለፍ ትልቅ በደል ነው ።
#በመጀመሪያ መስካሪው እውነት እመሰክራለው ብሎ የገባውን ቃል ኪዳን ወይም መሐላ አፍርሶ ውሸት በመናገሩ ፣
#2ኛ ዳኛውን በማሳሳት የሐሰት ፍርድ በማስፈረዱ ፣
#3ኛ የተፈረደበትን ሰው ሳያጠፋ በማስቀጣቱ በደሉ ብዙ ነው።
🖊ይህ ትዕዛዝ ቀጥታ ምስክሮችን ብቻ የሚመለከት አይደለም ። ልዩ ልዩ የሐሰት መረጃዎችን በማዘጋጀት ፡ ሰነዶችንና መዝገቦችን በማጭበርበርና በማዘዋወር አስመስሎ በመፈረምና በተሰረቁ ማኀተሞች በመጠቀም እንደዚሁም ሌሎች ይኽን የመሰሉ በተንኮል የተቀናበሩትን ሁኔታዎች በማመቻቸት የሚያስፈርዱትንና የሚፈርዱትንም ሁሉ ይመለከታል።
🖊ስለዚህ ምስክርነታችን ሁሉ #በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ።
@zekidanemeheret

ይቀጥላል.....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል-11
#9 የባልንጀራህን _ሚስት{ቤት} _ንብረት_አትመኝ አትግደል ፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ ፣በሐሰት አትመስክር በማለት
ክፉ አድራጎትን ወይም የጥፋት ሥራዎችን የሐሰት ንግግሮችን ይከለክላል።
🖊 #አትመኝ በማለቱ ደግሞ ክፉ ምኞትንና መጥፎ ሐሳብን ይከለክላል። በውጭ በተግባር የሚደረጉት ከውስጥ በልቡናችን ከሚፈፀሙት ጋር ማለት ከምኞትና ከሐሳብ ጋር እንደሚታየው እንደ ግንዱ የተያያዙ ናቸው ። ሥሩ ደኀና ከሆነ ግንዱም ደኀና ይሆናል ። አንድ ነገር በድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ነገሩ የሚጠነሰሰውና የሚጀመረው በምኞትና በሐሳብ ውስጥ ውስጡን ነው ። ክፉ ሰው ከልቡ ክፉ ነገርን ያወጣል ፤ ደግ ሰው ግን ከልቡ ደጋግ ነገሮችን ያወጣል።
🖊 #መመኘት ማለት የሌላውን ሰው ሚስት / ባልና ሀብት ለራስ እንዲሆን መፈለግና ማሰብ ስለሆነ አንድ ነገርን የተመኘ ሰው ጊዜና ቦታ ባይገድበውና ሁኔታዎች ቢመቻቹለት በልቡ የፈለገውን በሐሳብ ያቀደውን ፣ በስሜቱ የፈቀደውን ከማድረግ አይመለስም።
🖊 ስለዚህ የኀጢአት ምንጩ የወንጀል አባቱ በልቡና የሚገኘው ክፉ #ምኞት ነው ። ስለዚህ የሰውን ንብረት ከመመኘት መታቀብ አለብን ።
🖊ይህንንም ለማጥፋት እና ኀሊናን ለማፅዳት መትጋት አለብን ። የሕግ ሁሉ ፍፃሜና ማጠቃለያ #ፍቅር ነው ። ሁሉም ትዕዛዞች በፍቅር ይጠቃለላሉ። 🖊ባልንጀራውንም አምላኩንም የሚወድ ህግን ይጠብቃል።
ዘፍ፫ ፤ ማር፯÷፳፩-፳፫ ፤ ሮሜ፩÷፳፱ ኢያ፯÷፮-፳፮ ፤ ፪ኛሳሙ፲፩÷፲፬-፲፯/፲፪÷፲፭ ፤ መክ ፪÷፲/፩÷፯-፲ ፤ ዘፍ ፳፭÷፳፱-፴ ፤ ዘኁ ፲፩÷፬-፭ /፲፩÷፬ ፤ መዝ ፵፰/፵፱/፲፪÷፲፯ ፤ ሉቃ ፲፪÷፲፭ ፤ ፩ጢሞ ፮÷፱ ፤ ኤፌ ፭÷፭ ፤ ፩ኛቆሮ፲፪÷፩ /፲፬÷፩ ፤ ገላ፭÷፲፯
@zekidanemeheret

ይቀጥላል....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ-ሥነምግባር
ክፍል-14
@zekidanemeheret
#2.ወደ ሴት አትመልከት በልብህም አታመንዝር
🖊ወደ ሴት በመመልክት በልቡና የሚያድርገው ፍትወተ ሥጋ ኃጢአት መሆኑን የሚያመለክት ነው። ሴትን ማየት ሳይሆን ባዩአት ጊዜ ለፈቃደ ሥጋ መመኘትን ነው እግዚአብሔር የማይፈቅደው።
ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜም በልብ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል በማለት የተነገረው። አይቶ የሚያስናክል ዓይን የተባለውን ፍትወተ ተራክቦን አውጥቶ መጣልና መንግሥተ ሰማይን ገንዘብ ማድረግ በማየት የሚመጣ ምኞትን በመፈፀም በገሃነም ከመጣል ይሻላል ይበልጣልም። ማቴ 5 ÷ 28
🖊ዓይን ሁሉን ይመለከታል ወደልቡና መዝገብ የሚልከው ግን ቀልቡ ያረፈበትን ነው።
🖊ሴትን በክፉ የኃጢአት ምኞት መመልከት አይገባም በልቦናም ለዝሙትና ለተራክቦ ማሰብ ታላቅ በደል ነው። የሃሳብ መድረሻ ተግባር ነውና እነርሱም ዝሙት። ስለዚህ በማየት መዘዝ ከሚመጣ ውድቀት ለመዳን ይህን ሕገ ወንጌል በሚገባ መረዳትና ዓይነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ዓይነ ልቡናንም መቆጣጠር ያስፈልጋል።
#3.ሚስትህን ያለዝሙት ምክንያት በሌላ ነውር አትፈታት
@zekidanemeheret
🖊ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው አባትንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።
ሰው ሚስቱን ለመፍታት አንዳች ምክንያት የለውም። በሥነ-ፍጥረትም ቢሆን ለአንድ አዳም አንዲት ሔዋን ለአንዲት ሔዋን አንድ አዳም ብቻ የተፈቀደ መሆኑን ስንመለከት የምናስተውለው ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ የሚደረግ አንድነት መሆኑንና በቀላሉና በሰው ፍላጎት እንዳይፈርስ ሰማያዊና አምላካዊ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን ነው።
🖊ይህን የከበረ አንድነት ማፍረስ በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ በደልና ኃጢአት ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር አንድ የሆኑ ባልና ሚስት አንድነታቸውን አክብረው ሊጠብቁትና ከተቀደሰ ጋብቻ የሚለቀመውን መልካም ፍሬ በረከት ገንዘብ ለማድረግ መትጋት ይኖርባቸዋል።
🖊ፈጣሪአችን እግዚአብሔር ኃጢአት በሆነ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ጋብቻ እንዳይፈርስ አዝዟል። መፋታት በተረጋገጠ የዝሙት ኃጢአት ምክንያት ካልሆነ በቀር የተወገዘ ነው። ምክንያቱም ፍች ቤተሰብን ከመበተን አልፎ ከዚያ ጋብቻ የተገኙትን ሕፃናት የሚያጎሳቁል ተስፋ ቢስ ሰላምና በማኀበራዊ ፍቅርም የሌላቸው በመጨረሻም ወደ ኃጢአት ሥራ እንዲያዘነብሉና በነፍሳቸውም እንዲጎዱ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ነው። 🖊በዚህ የተነሳ ተስማምተው የተጋቡ ባልና ሚስት መፋታትም ሆነ መለያየት እንደማይገባቸው ዐውቀው በጋብቻቸው መጽናት አለባቸው።
ይቀጥላል......

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret