ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
827 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_6
#የ40ቀንና_የ80ቀን_ጥምቀት
አብዛኛውን ጊዜ በፕሮቴስታንቶች በኩል ጥምቀት ላይ የሚያነሷቸው ሁለት ነገሮች ናቸው ። #አንደኛ ፦ ሕፃናት መጠመቅ የለባቸውም የሚል ሲሆን #ሁለተኛው ደሞ እምነት እንጂ ጥምቀት አያድንም የሚል ነው ። በማር 16:16 ላይ ያለውን በመጥቀስ አንድ ሰው አምኖ መጠመቅ አለበት እንጂ ሳያምን ፣ ሳያውቅ ቢጠመቅ ምን ይረባዋል ? ይላሉ ። በመሰረቱ " ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል "የሚለው ይህ ቃል ላመኑት ሳይሆን ላላመኑት የተነገረ ነው ። በተለይም ወደ ዓለም በሚሄዱበት ሰዓት ሐዋርያት አገልግሎታቸው የቀና ይሆን ዘንድ ያላመኑት ማመን ስለሚያስፈልጋቸው ነው ። ለቃሉ መነሻ የሆነው ጥቅስ እንዲህ ይነበባል "... ተነስቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውን የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ " (ማር 16:16) አለማመናቸውን ለመንቀፍ ጌታ የተናገረውን ቃል ሕፃናትን መጠመቅ የለባቸውም ብሎ ከሚያምን ቤተሰብ የተገኙትን ህፃናት ላይ እንዳይጠመቁ መፍረድ ክፋ ሀጥያት ነው ። እንደውም መፅሐፍ ቅዱስ ጥምቀተ ሕፃናትን አይቃወምም እንደውም ይደግፈዋል። ለዚህም ማረጋገጫችን ጌታችን " ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው " ብሏል ። /ማቴ19:14/ ታዲያ ይህን እውነት ይዘን ስንጓዝ ወደ ብሉይ ኪዳን መለስ ብለን እናስተውለዋለን ። ይህም በዘሌ 12 ላይ ከቁ 1 - 8 ስናነብ ይህንኑ የወንድ ልጅና የሴት ልጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ የሚገባቸውን ጊዜ እንዲህ በማለት ገልፆታል ። "ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት። በስምንተኛው ቀን ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ ከደምዋም እስክትነፃ 33 ቀን ትቀመጥ ይላል ። 7 እና 33 ስንደምራቸው #40 ቀን ይሆናል ። #ለወንድ ልጅ ይህንን ብሏል ። #ለሴት ልጅ ደሞ 2 ሳምንት ያህል የረከሰች ናት ከደምዋም እስክትነፃ ድረስ 66 ቀን ትቀመጥ ይላል ።14 እና 66 ስንደምራቸው #80 ቀን ይሆናል ። በመፅሐፈ ኩፋሌ 4:9 ላይ ደሞ "እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረው በ40 ቀኑ ሔዋንን በፈጠራት በ80 ቀኗ መላዕክት ዕፁብ ዕፁብ እያሉ ገነት እንዳስገቧቸው ይናገራል ። ቤተክርስቲያን ይሄን ምክንያት በማድረግ ወንድ በ40 ቀን ሴት በ80 ቀን ታጠምቃለች ። ነገር ከ40 ቀን በተለያየ ችግር ምክንያት ቢያልፍ መጠመቅ አይችልም ማለት አይደለም ። ከዛ በፊትም የከፋ ለሞት የሚያደርስ ህመም ቢያጋጥመው እንዲጠመቅ ፍትሐ ነገስት ያዛል ።
#የአጠማመቅ_ሥርዓታችንና_ፍቺው
ዲያቆኑ ሕፃኑን ይዞ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ እክህደከ ሰይጣን በማለት 3 ጊዜ ይናገራል ። ይህም ሰይጣንን እክደዋለው ማለት ነው ።
እንደገና ፊቱን ወደ ምስራቅ ሕፃኑን እንደያዘ ይመልስና አአምን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ በማለት 3 ጊዜ ከተናገረ በኀላ ወደማጥመቂያው ያቀርበዋል። ይህም በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አምናለው ማለት ነው ። "በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጥምቁ " ብሎ እንዳዘዘው ነው ። (ማቴ 28:19)
ምንጭ ። ኰኲሕ ሐይማኖት



ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
ኢዮአታም
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_6
#12ቱ_የፍቅር_አይነቶች
እንደሚታወቀው ባለፉት ክፍሎቻችን ከ12ቱ 9ኙን ማየታችን ይታወሳል ። እነሆ ዛሬ ደሞ የቀሩትን 3ቱን እናያለን ።
#10ኛ_ሰልፊሽ_ላቭ (Selfish Love) ፦ ይሄኛው "ራስ ወዳድ ፍቅር " ይባላል ። እነዚህኞቹ ደግሞ ፍቅርን የሚጀምሩት የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ሲሉ ብቻ ነው ። ለምሳሌ ገንዘብ ቸግሯቸው ከሆነ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ሌላም ችግር ካለባቸው የገጠማቸውን ክፍተት ለመድፈን ሲሉ የሚጀምሩት የፍቅር አይነት ነው ። ይህ ፍቅር እራስን ከመውደድ የመነጨ ፍቅር አይደለም ። በውስጡ እውነተኛ ስሜትም ቅርበትም የለውም ።እነዚህ ሰዎች የሚፈልጉትን ካላገኙ ደግሞ ግንኙነቱን ለማቋረጥ ዐይናቸውን አያሹም
#11ኛ_ኮምፒኒየን_ላቭ (Companion Love ) ፦ ብዙ ጊዜ በዚህኛው ፍቅር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች እድሜያቸው ከትዳር ክልል ውጭ ወጣ ያለባቸው ሰዎች ናቸው ። እንዲህ አይነት ሰዎች በአብዛኛው ብቻቸውን በነበሩበት ዘመን የሌሎችን የትዳር ሕይወት እየተመለከቱ መቅናት ይጀምራሉ ። እናም ብዙ ነገር ያምራቸዋል ። በዚህ አምሮታቸው ውስጥ ትዳርን ይናፍቃሉ ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከእድሜያቸው ጋር እሩጫ ስለሚይዙ ሲያገቡ ለእነሱ የሚሆናቸውን መርጠው ፣ ባህርይን አጥንተው ፣ እረጋ ብለው አይደለም የሚያገቡት ። ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ብቻ ያገባሉ ። ምክንያቱም እነርሱ አሁን ፊታቸው ያለውን የትዳር አምሮት ፣ ልጅ ማሳደግ ፣ አብሮ መኖር ... ይሄ ብቻ ነው የሚታያቸው
#12ኛ_ኮንሲዮሜት_ላቭ (Consummate Love ) ፦ እውነተኛ ፍቅር ! ይህ እውነተኛ ፍቅር ነው ወይንም ደግሞ ዘለቄታው ያማረና የተስተካከለ ነው የሚያሰኘው #በ3 ነገሮች ላይ ሲዋቀር ነው ። እነሱም ቅርበት (Intimacy) ፣ ስሜት (Passion) ፣ ቁርጠኝነት (Commitment) ። በእነዚህ 3 ነገሮች ላይ የተዋቀረ ፍቅር አስተማማኝ፣ እውነተኛና ሕይወት ያለው የማይሞት ፍቅር ነው ። በዚህ ዓይነት ፍቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች መሰለቻቸት የሚባል ነገር አያውቃቸውም ። ፍቅራቸው ልዩና ጣዕም ያለው ፍቅር ነው ። በመካከላቸው #ስሜት አለ ። በስሜት ይጣጣማሉ ፣ ይግባባሉ ፣ በዚህም ተደስተው ይኖራሉ ። #ቁረጠኝነትም አለ ። እርሷ ከእርሱ ጋር እርሱም ከእርሷ ጋር አብሮ ለመኖር ቁርጠኞች ናቸው ። ይሄም ወደ ትዳር የሚያመራ ጥሩ መንገድ ነው ። በመቀጠልም #ቅርበት በመካከላቸው አለ ። ጥልቅ መቀራረብ በእነሱ መካከል ከመኖሩ የተነሳ ባህርይ ለባህርይ በደንብ ይተዋወቃሉ ። ከመተዋወቃቸውም የተነሳ በጣም ይዋደዳሉ ።ብዙ ጊዜ የባህርይ ለባህርይ መተዋወቅና በባህሪም የሚመሳሰሉ ባልና ሚስቶች በትዳራቸው ደስተኛም የሚሆኑት ከዚህ የተነሳ ነው ። #በ3ቱ ነገሮች ላይ የተዋቀረ ፍቅር ቀስ እያለ እስከመጨረሻው የሚያድግ እንጂ የሚከስም አይደለም ። በመከራ ሰዓትም ቢሆንም እንኳን አይበገርም።ፍፁም ቅርበት ስላላቸው አይለያዩም። ምንም ነገር ቢፈጠር እንኳን መከራ አራርቋቸው ከዓላማቸው ፈቀቅ አያደርጋቸውም ። ይሄኛው የፍቅር አይነት በጣም ጥሩ እና እውነተኛ ፍቅር ነው ። በዚህ ዓይነቱ የተያዘ በእውነተኛ ፍቅር እንደተያዘ እርግጠኛ መሆን ይችላል። 12ቱን የፍቅር አይነቶች ጨርሰናል ቀጣይ ደሞ #ቃልኪዳንን እናያለን ።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
#ክፍል_6

#4 አባትህንና_እናትህን_አክብር
🖊ለሰው ልጅ ከተሰጠ ህጉች የመጀመሪያው ህግ ነው። ዘፀ ፳፩÷፲፭
🖊ይህ ትዕዛዝ የፍቅረ ቢፅ መጀመሪያ ነው ። አባትና እናት ሲል የወለዱንን ብቻ ሳይሆን በአርአያ #ሥላሴ የተፈጠረ ሁሉ እንድናከብር ነው ። እነዚህም የሥጋ አባቶችና የመንፈስ አባት በማለት ለሁለት ይከፈላሉ። #1.የስጋ አባት የምንላቸው ፦
-ወላጆቻችን
-የቀለም አባቶች
-የሀገር መሪዎች
-ሽማግሌዎች
-የጡት አባት/እናት
-የእንጀራ አባት/እናት ፣
-አሳዳጊዎች
ምሳ፮÷፳ ዘፀ፳÷፳፪ ኤፌ፫÷፩-፫ ምሳ፳፫÷፳፭
#2.የመንፈስ_አባት ፦
-የንስሀ አባት
-ካህናት
-ሰባኪ ወንጌሎች
-የክርስትና እናትና አባት
-ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ናቸው። 🖊አክብር ማለት መውደድ ፣ መታዘዝ ፣ መርዳት ፣ አለማቃለል ማለት ነው ። በሁሉ ለወላጆቻችሁ ሲል በሁሉ የሚለው ቃል ብዙ ነገሮችን ያመለክታል። ይኸውም #ሀ ምክራቸውን በመስማት
#ለ በተቸገሩ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት
#ሐ በሌላቸው ጊዜ የሚረዱበትን መንገድ ማዘጋጀት
#መ በጠቅላላው ለወላጆች ብድራትን መመለስ ። ወላጆቻችንም ሆኑ ሌሎችን የሥጋና የመንፈስ አባቶችን ሲኖራቸውም ፣ሲያጡም ፣ ጤና ቢሆኑ ፣ ቢታመሙም ፣ባረጁ ጊዜ ልንረዳቸውና ልናከብራቸው ይገባል። ይሁንና ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣላና የሚያጋጭ ትዕዛዝ ቢያዙን ግን እንቢ ልንላቸው ይገባል።


ይቀጥላል.....

share👇share👇share
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!