ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_6
#12ቱ_የፍቅር_አይነቶች
እንደሚታወቀው ባለፉት ክፍሎቻችን ከ12ቱ 9ኙን ማየታችን ይታወሳል ። እነሆ ዛሬ ደሞ የቀሩትን 3ቱን እናያለን ።
#10ኛ_ሰልፊሽ_ላቭ (Selfish Love) ፦ ይሄኛው "ራስ ወዳድ ፍቅር " ይባላል ። እነዚህኞቹ ደግሞ ፍቅርን የሚጀምሩት የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ሲሉ ብቻ ነው ። ለምሳሌ ገንዘብ ቸግሯቸው ከሆነ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ሌላም ችግር ካለባቸው የገጠማቸውን ክፍተት ለመድፈን ሲሉ የሚጀምሩት የፍቅር አይነት ነው ። ይህ ፍቅር እራስን ከመውደድ የመነጨ ፍቅር አይደለም ። በውስጡ እውነተኛ ስሜትም ቅርበትም የለውም ።እነዚህ ሰዎች የሚፈልጉትን ካላገኙ ደግሞ ግንኙነቱን ለማቋረጥ ዐይናቸውን አያሹም
#11ኛ_ኮምፒኒየን_ላቭ (Companion Love ) ፦ ብዙ ጊዜ በዚህኛው ፍቅር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች እድሜያቸው ከትዳር ክልል ውጭ ወጣ ያለባቸው ሰዎች ናቸው ። እንዲህ አይነት ሰዎች በአብዛኛው ብቻቸውን በነበሩበት ዘመን የሌሎችን የትዳር ሕይወት እየተመለከቱ መቅናት ይጀምራሉ ። እናም ብዙ ነገር ያምራቸዋል ። በዚህ አምሮታቸው ውስጥ ትዳርን ይናፍቃሉ ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከእድሜያቸው ጋር እሩጫ ስለሚይዙ ሲያገቡ ለእነሱ የሚሆናቸውን መርጠው ፣ ባህርይን አጥንተው ፣ እረጋ ብለው አይደለም የሚያገቡት ። ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ብቻ ያገባሉ ። ምክንያቱም እነርሱ አሁን ፊታቸው ያለውን የትዳር አምሮት ፣ ልጅ ማሳደግ ፣ አብሮ መኖር ... ይሄ ብቻ ነው የሚታያቸው
#12ኛ_ኮንሲዮሜት_ላቭ (Consummate Love ) ፦ እውነተኛ ፍቅር ! ይህ እውነተኛ ፍቅር ነው ወይንም ደግሞ ዘለቄታው ያማረና የተስተካከለ ነው የሚያሰኘው #በ3 ነገሮች ላይ ሲዋቀር ነው ። እነሱም ቅርበት (Intimacy) ፣ ስሜት (Passion) ፣ ቁርጠኝነት (Commitment) ። በእነዚህ 3 ነገሮች ላይ የተዋቀረ ፍቅር አስተማማኝ፣ እውነተኛና ሕይወት ያለው የማይሞት ፍቅር ነው ። በዚህ ዓይነት ፍቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች መሰለቻቸት የሚባል ነገር አያውቃቸውም ። ፍቅራቸው ልዩና ጣዕም ያለው ፍቅር ነው ። በመካከላቸው #ስሜት አለ ። በስሜት ይጣጣማሉ ፣ ይግባባሉ ፣ በዚህም ተደስተው ይኖራሉ ። #ቁረጠኝነትም አለ ። እርሷ ከእርሱ ጋር እርሱም ከእርሷ ጋር አብሮ ለመኖር ቁርጠኞች ናቸው ። ይሄም ወደ ትዳር የሚያመራ ጥሩ መንገድ ነው ። በመቀጠልም #ቅርበት በመካከላቸው አለ ። ጥልቅ መቀራረብ በእነሱ መካከል ከመኖሩ የተነሳ ባህርይ ለባህርይ በደንብ ይተዋወቃሉ ። ከመተዋወቃቸውም የተነሳ በጣም ይዋደዳሉ ።ብዙ ጊዜ የባህርይ ለባህርይ መተዋወቅና በባህሪም የሚመሳሰሉ ባልና ሚስቶች በትዳራቸው ደስተኛም የሚሆኑት ከዚህ የተነሳ ነው ። #በ3ቱ ነገሮች ላይ የተዋቀረ ፍቅር ቀስ እያለ እስከመጨረሻው የሚያድግ እንጂ የሚከስም አይደለም ። በመከራ ሰዓትም ቢሆንም እንኳን አይበገርም።ፍፁም ቅርበት ስላላቸው አይለያዩም። ምንም ነገር ቢፈጠር እንኳን መከራ አራርቋቸው ከዓላማቸው ፈቀቅ አያደርጋቸውም ። ይሄኛው የፍቅር አይነት በጣም ጥሩ እና እውነተኛ ፍቅር ነው ። በዚህ ዓይነቱ የተያዘ በእውነተኛ ፍቅር እንደተያዘ እርግጠኛ መሆን ይችላል። 12ቱን የፍቅር አይነቶች ጨርሰናል ቀጣይ ደሞ #ቃልኪዳንን እናያለን ።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret