#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_9
#የተሳሳተ_የትዳር_ጓደኛ_አመራረጥ
በዓለማችን ላይ ለምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ውሳኔዎችን እንወስናለን ። #ጋብቻም የእኛን ውሳኔ ከሚጠይቁት ቁም ነገሮች አንዱ ነው ። በመንፈሳዊ መነጽር ስንመለከተው እግዚአብሔር ያዘጋጀውን በጋብቻ ልንረከብ /ልንቀበል/ እንደምንችል የታመነ ነው ። ለአዳም ሔዋንን የሰጠ እርሱ ነውና ። ሆኖም ግን ከመወለድ ፈጽሞ የተለየ ነው ። እኛ ስንወለድ አሁን አባት እናት ከሆኑን ወላጆቻችን ዘንድ መወለድ እንዳለብን ወስነን የገባንበት አይደለም ። ወይም የአሁኗ እናታችንና አባታችን እንዲሁም ወንድምና እህቶቻችንን የኛ ቤተሰብ እንዲሆኑልን ወስነን የገባንበት አይደለም ። #ጋብቻ ግን ከዚህ ይለያል ። ም/ቱም የትዳር ጓደኛችንን የምንቀበለው ትሆነኛለች ይሆነኛል ያልነውን ወስነን ነውና ። ከዚህ ጋር አያይዘንም ለምርጫችን አሳሳች የሆኑ ነገሮችን ማየትና መመርመር መርምሮም መገንዘብ ያስፈልጋል። ለዚሁም የሚከተሉትን በምሳሌነት ማየት ይቻላል።
#ሀ_ጥንቆላ
ጥንቆላ በቤተክርስቲያናችን የተወገዘ ተግባር ነው ። ሰዎች ዕውቀታቸው እና አእምሮአቸው ውሱን ስለሆነ ስለነገ ማወቅ አይችሉም ። በመሆኑም ስለተሰወረባቸው እውቀት ለማወቅ ጉጉዎች ናቸው ። ከዚህም በመነሳት የወደፊት የትዳር ጓደኛቸው ምን አይነት እንደሆነ ፣ ወደፊት ስለሚወልዱት ልጅ እንዲነግራቸው ጠንቋይ ጋር ይሄዳሉ ።
#ለ_አሳሳች_ሕልም
ሕልም ሁለት ወገን ነው ። #አንዱ የነፍስ ወገን ሆኖ ፍሬ ፣ ቁምነገርና ውጤት ያለው ትንቢት ወይም ራዕይ ይባላል። እነ ዮሴፍ እነ ዳንኤል ያዩት ህልም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው ። #ሁለተኛው ወገን ደሞ
ከሰይጣን የሚመጣ አሳሳች ነው ። መመንኮስ ያለበት ማግባት እንዳለበት ፤ ማግባት ያለበት ደሞ መመንኮስ እንዳለበት አድርጎ ሊያሳየው ይችላል። ስለዚህ በደፈናው እገሊትን እገሌን በህልሜ አይቻለው ብሎ ወደ ትዳር መግባት የቅዠት ትዳር ምስረታ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ።
#ሐ_ዕጣ_ማውጣት
ዕጣ ማውጣት በብሉይም በሀዲስም የነበረ አሁንም ያለ የሰው ልጆች የኑሮ ክፍል ነው ። ስለዚህ ሰዎች ለመወሰን የተቸገሩበትን ነገር ወይም ወስነው ይበልጥ ለማረጋገጥ የፈለጉትን ነገር አስመልክቶ ዕጣ ሲያወጡ ይታያል ። በመፅሐፍም ለምሳሌ በዮናስ ታሪክ ላይ ማዕበል በመነሳቱ በመርከብ ያሉትን ሰዎች በማን ሀጥያት መሆኑን ለማረጋገጥ ዕጣ ሲጥሉ በዮናስ ላይ ወጥቷል ። የእመቤታችን ጠባቂ እንዲሆን እግዚአብሔር በልዩ ልዩ ምልክት ጻድቁንና አረጋዊዉን ዮሴፍን ከመረጠው በሗላ ካህናቱ በዕጣ አረጋግጠዋል ። ዛሬም በሀገራችን በጎ ልማድ ተይዞ ሰዎች ሲታመሙ ጠበል ለመምረጥ ዕጣ ያወጣሉ ። ከዚህ በመነሳት ብዙ ሴት የወደደ ወንድ ፤ ወይም ብዙ ወንድ የወደደች ሴት ከእነዚህ አንዱ የኔ እንዲሆን ብላ ዕጣ ልታወጣ ታስብ ይሆናል ። ነገር ግን በዚህ መመራት ከባድ ነው ። ሁልጊዜ ዕጣ ማውጣት የእግዚአብሔር ፍቃድ መገለጫ ላይሆን ይችላል። መጓዝ ያለብንን ያህል ተጉዘን እንወስን እንጂ ከላይ ባየናቸው መንገዶች የትዳር አጋርን መምረጥ ስህተት ነው ። ቀጣይ ደሞ የጋብቻ አይነቶችን እናያለን።
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret

#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#ክፍል_2
#የንስሐ_አፈፃፀም_3_ደረጃዎች
#ሀ የንስሀ የመጀመሪያ ደረጃ ኃጢአትን መተው ብቻ ሳይሆን ንስሐ ለመግባት ማሰብ ወይም መፈለግ ነው። ይህ ኃጢአትን ከመተው የሚቀድም ነው ። ሰዎች ንስሐ ለመግባት ባልፈለጉና ባላሰቡ መጠን በኃጢአት እየተደሰቱ ኃጢአትን እየሰሩ ይኖራሉ። በእነርሱ አመለካከትም የያዙት የኃጢአት ኑሮአቸው መልካም ስለሚመስላቸው አይለወጡም ። ስለዚህ ንስሐ ለመግባት ማሰብና መፈለግ የንስሐ የመጀመሪያ ደረጃ ነው ።
#ለ ሁለተኛው ደረጃ ፦ በንስሐ ሂደት ሁለተኛው ደረጃ ኃጢአትን መተው ነው ። ኃጢአትን መተው ሲባልም ኃጢአትን ከኅሊናና ከልቡና ጨርሶ በፍፁም ማጥፋት ነው ። ይህም ኃጢአትን ከማሰብ መለየት ማለት ነው ። ፀፀቱ ወይም ንስሐው ልቡናው ከኃጢአት እስኪነፃ ድረስ መሆን አለበት ። ከዚህ አንፃር ኃጢአትን መተው የንስሐ ሁለተኛው ደረጃ ነው።
#ሐ ሶስተኛው ደረጃ ፦ የንስሐ የመጨረሻ ደረጃ ኃጢአትን መጥላት ነው ። ይህም ኃጢአትን በፍፁም ልብ መጥላት ፣ አለማሰብና ባሕርይን ለኃጢአት አለማስገዛት ማለት ነው ። ይህ ደግሞ የፍፁምነት ደረጃ ነው ። ሰው ኃጢአትን ከልቡ ከአስወገደና ፍፁም ካላሰባት ከፍጹምነት ደረጃ ደርሷልና ንፁህ ነው ይባላል። ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ውስጥ ከፍተኛውንና ዋነኛውን ኃጢአት ለመተው የሚችለው በክርስትና ሕይወቱ የዕለት ተዕለት ብስለት የሚገለጡለትን ረቂቃን ኃጢአቶች በመተው ነው።

#ክፍል_3
#የንስሐ_መሰናክሎች (እንቅፋቶች)
ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኀነት መንገዶች ውስጥ ንስሐን የሚያክል የለም። ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያቢሎስ የክርስቲያኖች ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበር በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው ። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ፣ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈጽሞ አያርፍም ። ከሚጠቀማቸው መሰናክሎች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ ።
#ሀ እንቅፋት መፍጠር ፦ እነዚህ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ። እነዚህ አጋጣሚዎች ወይም ፈተናዎች ተነሳሒው በድፍረት ወደ ንስሐ እንዳይመጣና ከኃጢአቱ እንዳይመለስ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ናቸው ።
#ለ ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የቀለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሐም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን ፤ #ቅድስና ግን ከኃጢአተኛ ሕይወት ሕይወት ጋር ሊነፃፀር አይገባም ። ኖኀ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቅዱስ እንደነበር ዮሴፍ፣ ሎጥና ሙሴም በኃጢአተኞች መካከል ቅዱሳን እንደነበሩ እኛም መቀደስ አለብን እንጂ እራሳችንን ማነፃፀር የለብንም ።
#ሐ ከሥጋ ድካም የተነሳ በአካባቢ ተፅእኖ መመራት ፦ ተነሳሒው ሰው በዓለም የማይታለል ጽኑ አቋም እንዲኖረው ያስፈልጋል ። ቅዱስ ጳውሎስ "ይህን ዓለም አትምሰሉ " እንዳለ ። (ሮሜ 12÷2) #ዓሣ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ። ክርስቲያንም እንዲህ ሊሆን ይገባዋል ። ደካማ ስጋን ቢለብስም ፈተናውን ተቋቁሞ ለንስሐ መብቃትና በመንፈሳዊ ሕይወት መኖር ይገባዋል ።
#መ መዘግየት ፦ ዲያቢሎስ ንስሐ እንዳንገባ የሚዋጋን በቀጥታ አይደለም ። ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችን እየደቀነ እንዳንገባ ያዘገየናል። #መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሐ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው ።
#ሠ ተስፋ መቁረጥ ፦ ይህ ንስሐ የማይቻልና ሊደረግ የማይሞከር እንደሆነ አድርጎ ማሰብ ነው። ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ እንድንሰራ ያደርገናል ፤ ከሰራነው ቡሃላ ደሞ የእግዚአብሔርን ፍርድና ጨካኝ እንደሆነ ያሳስበናል ። ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል ።
💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️

#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ )
#ክፍል_3
#ለንስሐ_የሚያበረታቱ_ሁኔታዎች
#1 ማንነትህን ካወቅህ ከኀጢአት በላይ ነህ ። ሰው እግዚአብሔር ምን ያህል እንዳከበረው ያወቀ እንደሆነ ራሱን በኃጢአት አያዋርድም ።ሰው ማነው ? አንተ አንቺ ማነህ ?
#ሀ አንተ እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ሰጥቶ የፈጠረህ ፍጥረት ነህ ። አንተ አፈር ብቻ አይደለህም ። ከ4ቱ ባህርያተ ስጋ ከ3ቱ ባህርያተ ነፍስ የተፈጠርክ ሕያው ሰው ነህ ። ሕያው በመሆንህም ለጊዜው በምድር የምትኖር ብትሆንም በክብር ወደ አምላክህ በመሄድ ሰማያዊ ሕይወትን ለመኖር የተፈጠርክ መሆንህን አስብ ። ስለዚህም በመንፈስ ኑር ። ከዓለም ከስጋዊ ስራም ተለይ ።
#ለ አንተ በመልኩና በምሳሌው የተፈጠርክ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ። በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠርክ ከሆንክ እንዴት ኃጢአትን ትሰራለህ ? በኃጢአት ወድቀህስ እንዴት የእግዚአብሔር ምሳሌ ልትባል ትችላለህ ? ስለዚህ ነገር ቅዱስ አትናቴዎስ "ሰው በበደለ ጊዜ የእግዚአብሔር ምሳሌ መሆኑ ይቀራል ። ቅድስናውን ያጣልና " በማለት ተናግሯል። ጌታችንም ሰው የሆነው ወደነበርንበት የቅድስና ሕይወት ሊመልሰን ነው ።የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያወቀ ሰው ኃጢአት አይሰራም ፤ ኃጢአትን ባለመስራትም አባቱን የሚመስል ይሆናልና ። አባቱን የማይመስል ልጅም ልጅ አይደለም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅነትህን ከኀጢአት በመለየት ልታረጋግጥ ይገባሀል። በዚህም አባትህን ትመስላለህና ። "የአብርሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር " እንደ ተባለ። የእግዚአብሔር ልጆች የኖሩትን የተቀደሰ ሕይወት ካልኖርን የእግዚአብሔር ልጆች አይደለንም ። በመሆኑም በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ልንል አንችልም ። "... ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደተወለደ ዕወቁ " (1ኛ ዮሐ 2÷29)
#ሐ አንተ የእግዚአብሔር ማደሪያ የመንፈስቅዱስ ቤተ መቅደስ ነህ ። "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ " (ምሳ 20÷26) ይህ አባባል የሰው ልብ የእግዚአብሔር ማደሪያ መሆኑን ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስም " የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ ፡ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? ማንም የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እሱን ያፈርሰዋል የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቅዱስ ነውና #ያውም-እናንተ ናችሁ። "(1ቆሮ 3÷16) ። #ዲያቢሎስ_በኃጢአት ሊፈትንህ ወደ አንተ በመጣ ጊዜ
✞ እኔ ለአንተ አይደለሁምና ከእኔ ወግድ በለው
✞ እኔ የእግዚአብሔር መቅደስና የመንፈስቅዱስ ማደሪያ ነኝ በለው
✞ እኔ የሥላሴ ባሪያ ነኝ በለው
✞ እኔ በእኔ ያድር ዘንድና ወደ ልቡናዬ ይገባ ዘንድ እግዚአብሔር ልቤን የሚያንኳኳ ነኝ በለው
✞ እኔ አብና ወልድ ማደሪያቸው ሊያደርጉኝ ወደ እኔ የሚመጡ ሰው ነኝ በለው

#ሕይወተ_ወራዙት
#የመጨረሻው_ክፍል
በቀሲስ ህብረት የሺጥላ
#በወር_አበባ_ወቅት_መከልከል_የሚገባው_ከምን_ከምን_ነው ?
#ሀ_ከሩካቤ ፦ የወር አበባን የምታይ ሴት ባለ ትዳር ከሆነች በደሟ ወቅት ምንም እንኳን ባሏም ቢሆን ሩካቤ መፈፀም በመንፈሳዊ ህግ አይፈቀድላትም ። የህክምና ባለሙያዎችም ቢሆኑ በደም ወራት የሚደረግ ሩካቤ በአብዛኛው ለአባላዘር ፣ ለልዩ ልዩ ተላላፊ በሽታዎችና ለኢንፌክሽን በቀላሉ ሊያጋልጥ እንደሚችል ይናገራሉ። መፅሐፍ እንዲህ ይላል "እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልፅ ዘንድ ሴት አትቅረብ " (ዘሌ 18÷19) ። ምንም እንኳን የወር አበባ በአዲስ ኪዳን መርገም ወይም ርኩሰት ስላልሆነ በዚህ ወቅት ሩካቤ የሚፈፅሙ ሰዎች እንደ ኦሪቱ በድንጋይ ተወግረው ባይሞቱም ተገቢው ቀኖና ግን ይሰጣቸዋል።
#ለ_ከመጠመቅ ፦ ሐዋርያው ጴጥሮስ "ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ... የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ። ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ " በማለት ተናግሯል ። ( 1ኛ ጴጥ 3÷21) ስለዚህ ጥምቀት ሥጋዊ እድፍ ማስወገጃ ስላልሆነ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው ከአፍአዊ እድፍ ከጠሩ በሁዋላ መጠመቅ ይገባል ። አንዳንድ ጊዜ በጠና የታመሙ ሴቶች በጠበል ለመፈወስ ክትትል ሲጀምሩ ልዩ ልዩ ፈተና ያጋጥማቸዋል ። ከፈተናዎቻቸውም ውስጥ አንዱና ዋነኛው ያለ ወሩ ያለ ማቋረጥ ወይም በተደጋጋሚ መከሰቱ ነው ። ይህን የመሰለ ነገር ሲከሰት ከሰይጣን ጋር እልህ መጋባትና ዝም ብዬ ብጠመቅ ምን አለበት ? ማለት ሞኝነት ነው ።
#ሐ_ከመቁረብ ፦ ምንም እንኳን ለቁርባን የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ቢሆኑም ሴቶች ከደመ ፅጌ ሳይነፁ #ሥጋና_ደሙን መቀበል አይችሉም ። ይህን ሥርዓት ተላልፎ ሴቶችን ከወር አበባ ሳይነፁ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡና ሥጋውን ደሙን እንዲቀበሉ ያደረገ ቢኖር ዲያቆን ሆነ ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሐ ነገስት እንዲህ ሲል ይደነግጋል ። "ከግዳጅዋ ያልነፃችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበላት ከመዓርጉ ይሻር " (ፍት.ነገ 6)
#መ_ቤተ_መቅደስ_ከመግባት ፦ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ሆና መማር መፀለይ ትችላለች መቅደስ መግባት ግን ክልክል ነው ።
እነሆ #ሕይወተ_ወራዙትን ጨረስን በቀጣይ ደሞ ሌላ ት/ት እንጀምራለን።
ለአስተያየት 👉ኢዮአታም ይጠቀሙ፡፡
👉ለመቀላቀል 👇👇👇

#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
#ክፍል_6
#4 አባትህንና_እናትህን_አክብር
🖊ለሰው ልጅ ከተሰጠ ህጉች የመጀመሪያው ህግ ነው። ዘፀ ፳፩÷፲፭
🖊ይህ ትዕዛዝ የፍቅረ ቢፅ መጀመሪያ ነው ። አባትና እናት ሲል የወለዱንን ብቻ ሳይሆን በአርአያ #ሥላሴ የተፈጠረ ሁሉ እንድናከብር ነው ። እነዚህም የሥጋ አባቶችና የመንፈስ አባት በማለት ለሁለት ይከፈላሉ። #1.የስጋ አባት የምንላቸው ፦
-ወላጆቻችን
-የቀለም አባቶች
-የሀገር መሪዎች
-ሽማግሌዎች
-የጡት አባት/እናት
-የእንጀራ አባት/እናት ፣
-አሳዳጊዎች
ምሳ፮÷፳ ዘፀ፳÷፳፪ ኤፌ፫÷፩-፫ ምሳ፳፫÷፳፭
#2.የመንፈስ_አባት ፦
-የንስሀ አባት
-ካህናት
-ሰባኪ ወንጌሎች
-የክርስትና እናትና አባት
-ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ናቸው። 🖊አክብር ማለት መውደድ ፣ መታዘዝ ፣ መርዳት ፣ አለማቃለል ማለት ነው ። በሁሉ ለወላጆቻችሁ ሲል በሁሉ የሚለው ቃል ብዙ ነገሮችን ያመለክታል። ይኸውም #ሀ ምክራቸውን በመስማት
#ለ በተቸገሩ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት
#ሐ በሌላቸው ጊዜ የሚረዱበትን መንገድ ማዘጋጀት
#መ በጠቅላላው ለወላጆች ብድራትን መመለስ ። ወላጆቻችንም ሆኑ ሌሎችን የሥጋና የመንፈስ አባቶችን ሲኖራቸውም ፣ሲያጡም ፣ ጤና ቢሆኑ ፣ ቢታመሙም ፣ባረጁ ጊዜ ልንረዳቸውና ልናከብራቸው ይገባል። ይሁንና ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣላና የሚያጋጭ ትዕዛዝ ቢያዙን ግን እንቢ ልንላቸው ይገባል።
ይቀጥላል.....
share👇share👇share
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret

#ክፍል_7
@zekidanemeheret
#5 አትግደል
🖊ይህ ትዕዛዝ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት አትግደል ማለት ነው።ይህም ማለት የሥላሴን መቅደስ አታጥፋ ማለት ነው።
🖊ኃጥያት በሦስት መንገድ ይሰራል
፩፦በመናገር
፪፦በተግባር
፫፦በማሰብ ናቸው።
🖊ሕይወት በአጋጣሚ ፣ በልማድና በእንዝሕላልነት የምትገኝ አይደለችም። ሕይወት ለራሱ ምክንያትና አስገኝ ከሌለው እግዚአብሔር የተገኘች ገንዘብ ነች። ሕይወትን ማንም ሊያዝባት እንደፈለገው ሊያደርጋት አይችልም። ለምን ? የእርሱ አይደለችምና ለዚህ ነው #አትግደል የተባለው ።
🖊መግደል ማለት በተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞ የሰው ሕይወት እንዲሞት ማድረግ ነው ።
🖊መግደል ከውስጥ ከሰው የሚወጡ ሰውንም የሚያረክሱ ብሎ ጌታችን ከዘረዘራቸው ክፉ ሥራዎች አንዱ ነው ። ማቴ፲፭:፲፱ ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ ላይ ከዘረዘራቸው ፲፮ የስጋ ስራዎች አንዱ መግደል ነው ።
🖊በሕይወት ላይ ስልጣን ያለው #እግዚአብሔር ብቻ ነው ። ሰውን ቢያድንም ቢገድልም ስልጣኑ የእርሱ ብቻ ነው ።
🖊መግደል ሲባል ፊት ለፊት ሄዶ የሰውን ሕይወት ማጥፋት ብቻ ሳይሆን ሰውን ለሞት የሚያበቁትን ነገሮች ሁሉ ነው ። ይኸውም፦
#ሀ በተለያዩ ሁኔታ (በቃላትና በመጠቆም) አጥፊውን መርዳት
#ለ የሰው ሕይወት ሊድን የሚችልበትን መረጃ በመከልከል #ሐ በሽታና ድካምን ሌላም ችግርን እያዩ ለሞት የሚያደርስ ስራ ማሰራት
#መ ለሞት የሚያደርስ ረሀብና ጥም አይተን አለመርዳት
#ሠ ሰውን በስጋ ብቻ ሳይሆን በነፍሱ መከራ የሚያመጣበትን መንገድ መፍጠር መግደል ነው ።
#ረ ዓለማውያንን በመንፈስ ባዶ ቀፎ ሆነው የተበላሹትን ወደ እናት ቤተክርስቲያን አለማምጣት ነፍስን መግደል ነው ።
🖊ወደ መግደል የሚያደርሱ ብዙ ነገሮች አሉ እነሱም ፦
#ቅንዓት
#ምቀኝነት
#ስድብ
#ጥላቻ
#ቁጣ ጥቂቶቹ ናቸው።
🖊 እራሳችንን በመግዛት እና ወንድማችንን በመውደድ ከዚ ድርጊት ልንቆጠብ ይገባናል። መሞት እንደማንፈልገው ሁሉ የሰው ነፍስ ማጥፋት የለብንም።
@zekidanemeheret
ይቀጥላል....
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት