#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_4
#ማስተማር_የማን_ተግባር_ነው ?
ዛሬ በፕሮቴስታንት ሐይማኖት ውስጥ የሴት ምህራን ወይም ሰባኪያን እያየን ነው ። ግን ማስተማር #የሐዋርያት ተግባር ነበር ። ከዚያም የእነርሱ ደቀመዛሙርት ለሆኑ ፣ ጳጳሳት ዲያቆናት ተግባር ሆነ ነገር ግን ምእመናን አስተምረው አያውቁም ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንኑ ሲያረጋግጥልን "እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዝኀችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ #እያስተማሯችኀቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ። ( ማቴ 28:19) እንደገናም "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ #ስበኩ ። (ማር 16:15) ብሏል ። ጌታችን #ማስተማርን ለሐዋርያት ሥራ አድርጎ ሰጠ እንጂ ይህንን ሥልጣን ለማንም አልሰጠም ። ሐዋርያት ቃሉን ሊሰብኩ ሊያስተምሩ ፣ ሊያገለግሉና እምነቱን ለሌሎች ሊያስተምሩ ተመርጠው ነበር ። ሰባቱን ዲያቆናት በካኑበት ጊዜ ሐዋርያው "እኛ ግን ለጸሎትና #ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን " ብሏል ። ስለ ጌታም ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ "በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን አሁን ግን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቷል ። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ #ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም #አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት ወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋት ወደ ብርሃን አውጥቷል ። (2ኛ ጢሞ 11) በመሆኑም ሐዋርያት ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት እያስተማሩና እየሰበኩ ኖሩ ።
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የማስተማርና የስበከት ተግባር ለደቀመዛሙርቱ አደራ ሲሰጥ ለጢሞቲዎስ " #ቃሉን ስበክ በጊዜውም አለጊዜውም ፅና ፈፅመህ እየታገስህና እያስተማርህ ዝለፍና ገስፅ ምከርም " (2ጢሞ ዠ4:2) አለው ።
በተጨማሪም ለደቀ መዝሙሩ ለቲቶም "ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገስጽም ማንም አይናቅህ " (ቲቶ 2:15) አለው ። ካህናት በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ስለሚያስተምሩ ወይም ስለሚቀድሱ ብቻ አይደለም ። ነገር ግን በንስሐና በመሳሰሉት ሁሉ መንፈሳዊ እንደራሴዎች ስለሆኑ ጭምር መምህራን ሊሆኑ ይገባቸዋል ። ምዕመናን ደግሞ ሁልጊዜ በተማሪዎች ቦታ ሆነው ሊማሩ ይገባል። እምነት ፣ ሥርዓትና ትውፊት በመንፈስቅዱስ የሚተረጎሙ የቤተክርስቲያን ሕይወት ናቸው ። ሰባኪያን በእምነትና በባህል ሃይማኖት ሽፋን የራሳቸውን አመለካከት ሊያስተምሩ አይገባም ። በመሆኑም ካሁን ቡሃላ በተከታታይ በእኛ እና በፕሮቴስታንት መካከል ስላለው ልዩነት በሰፊው እናያለን።
#ሼር
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret