ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
872 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
ለመንፈሳዊ ልምምድ ጠቃሚ ምክሮች
++++++++++++++++++++++

በመጀመሪያ ምን ያህል አዋቂዎች ብንሆን ማወቃችን ብቻ ሊያስደስትን እና ሊያረካን አይገባም፡፡ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ያወቅነውን በስራ ለምንተረጉምበትና ትእዛዛትን መፈፀም ለምንችልበት ሕይወት ነው፡፡
ጌታችን የተራራው ስብከቱን ሲያጠቃልል የተናገረው ቃል ይህን ነው፡፡ ‹‹ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በአለት ላይ የሰራ ልባም ሰው ይመስላል፣ ይህንንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሰራ ሰነፍን ሰው ይመስላል፡፡›› (ማቴ 7፣24-26) ስለዚህ እንደሰማን ለመስራት ለምግባራችን ትልቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥልን ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› ብሏል ካህኑም በጸሎተ ቅዳሴ (ቅድመ ወንጌል) ወንጌልን ለመስማት፣ እንደሰማንም ለመስራት በቅዱሳን ጸሎት የበቃን አድርገን›› እያለ የሚጸልየው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ ትእዛዙ ለመኖር እና ቃለ ወንጌሉን ለመፈፀም ራሳችንን እናለማምድ፡፡
መንፈሳዊ ልምምድ አንድ ሰው ለነፍሱ ድኅነት ያለውን ተስፋ ያመለክታል፡፡ ስሕተቶቹን፣ ድክመቶቹን ሁሉ ለይቶ አውቆ ለማስወገድ እየጣረ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ አንተም ወንድሜ ስህተቶችህን ሌሎች
አይተው እስከሚነግሩህ ድረስ መጠበቅ ሳይኖርብህ በራስህ ለይተህ እወቃቸው፡፡ምክንያቱም ያለብህን ችግር ሳታውቀው ለመንፈሳዊ ልምምድ መነሳት ስለማትችል ነው፡፡ ‹‹በሽታውን የደበቀ መድሃኒት አይገኝለትም›› ይባል የለ፡፡ ‹‹ህምምተኞች እንጂ ባለጤናዎች ባለመድሃኒት አያስፈልጋቸውም›› (ማቴ 9፤12)

ባንተ ያለውን ችግር ሌሎች ማወቃቸውም ቢሆን አያበሳጭህ፡፡ ይልቁንም በየትኛው መንፈሳዊ
መስክ ልምምድ ማድረግ እንደሚገባህ አድርገህ ተቀበለው፡፡
በእግዚአብሔር ሕግ ብርሃንነት ራስህን እየመረመርክ ድክመቶችህን ፈልግ፡፡ ትንንሽ ድክመቶች እንኳ ቢሆኑ አትናቃቸው፤ምክንያቱም
ያድጋሉና፡፡ ‹‹ወይናችን አብቧል ኑ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ፡፡››(መኃ 2፣15)

#ራስህን ከማፅደቅ ተቆጠብ ለስህተቶችህም ማስተባበያ አትፈልግ ራሱን የሚያፀድቅ ሰው ዘወትር ባለበት መሔድ እንጂ የሚያሻሽለው አንድም ነገር የለምና፡፡ ምክንያቱም በዓይኑ ፊት ከእርሱ በላይ ሰው የለም ለራሱ እንከን የለሽ ነው፡፡ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ይህን ያደረኩት በዚህ ምክንያት ነው እያለ ሲያስተባብል ወድቆ ይቀራል፡፡ለራሱ ትክክለኛ ግምት ያለው የማይመፃደቅ ሰው ግን ድክመቱን መናዘዝ ብሎም ማስወገጃውን መንገድ መለማመድ ይችላል፡፡ ችግሮችህ ስር ሰደው ሰዎች ሊገልጡብህ የሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ የሚሰማህ መሸማቀቅ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ቀደምብለህ እራስህ ገልጠሀቸው ለመፍትሔው ልምምድ ብታደርግ ይህ ሁሉ ነገር ባንተ ላይ አይከሰትም፡፡

#ሁሌም ራስህን ሁነህ ተገኝ፡፡በሕይወትህ ቅንነት የሚነበብብህ ሰው ሁን፡፡ መጽሐፍትን ስታነብም ሆነ ስብከት ስታዳምጥ ጉድለቶችህን እየፈለክ ይሁን፡፡ ሰምተህ ለማድረግም ተነሳሳ፡፡

#የኃጢያት ስሩ አንድ ነው፡፡ ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም እርስ በራሳቸው የተያያዙ መሆናቸውንም እርግጠኛ ሁን፡፡ አንድ የተወሰነ የሀጢያት አይነትን ለመቅረፍ ስትነሳ ሳታውቀው
ሌሎችንም እየበጣጠስክ መሆኑን እወቅ፡፡እንዲሁም አንድ በጎ ሥነ ምግባርን ለማዳበር ስትለማመድም ቢሆን ሌሎች ብዙ ሥነ ምግባራትን እያተረፍክ መሆኑን ልብ በል፡፡ ሥነ ምግባራቱም በአንድ ሠንሰለት የተያያዙ ናቸው።

#ሼር

https://t.me/zekidanemeheret
ከኢንሳ የመጣ አዲስ መረጃ…!

"…ዘመዴ እንደምንም ብለህ ይሄን መረጃ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና ለሕዝቡ አድርስ። መንግሥት በቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እና በአንተ ላይ ዶክመንተሪ እንዲሠራ አዟል። በአባቶች ላይ የውሸት ድምጽ ማስመሰል ሊሠራ ያቀደ ሲሆን ሲሠራም 2 ዋና ዋና ነገሮችን አስቦ ነው።

1ኛ፥ ለማኅበረሰቡ በውሸት እነዚህ አባቶች የፖለቲካ ንክኪ አጀንዳ እንዳሏቸው ለማስረዳት፥

2፥ የኦሮሞን ህዝብ እንደሰው እንደማይቆጥሩት የሚያሳይ ድምጽ ለማውጣት ነው።

"…በዚህም የታሰበው በማኅበረሰቡ ብቻ ሳይሆን የሲኖዶሱ አባቶች እርስ በእርሳቸው መተማመን እንዲያጡ ለማድረግ የታሰበ ነው። እናም ስልክ ደግሞ 100% በኢትዮቴሌኮም የፎቶጋለሪ ሳይቀር መመልከት  ይችላሉ። እንዲህ መጠቀም ከጀመሩ 1 አመት አልፏቸዋል።

"…የInsa cyber security specialist ከሰለሞን ሶካ የ insa director encrypted መልዕክት ተልኳል። ይህም የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት አባቶች እንዲሁም የሃይማኖት ተቆርቋሪዎች accounts check እንዲያደረጉ፣ እንቅስቃሴያቸው እንዲጠና፣ እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂዎች ጭምር እንዲበረበር፣ ከዚያውስጥ ደግሞ ዘመዴ ላይ Documentary ለመሥራት Vulnerability እየፈለጉ ነው። በቅርቡም በአቡነ ማቲያስና በአቡነ አብርሃም ላይ የተሠራ voice over ለማኅበረሰቡ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው።

"…በቀደም ዕለት በእነ አካለወልድ የተሰጠው መግለጫ ተመልክቶ ከመግለጫው በፊት እነ ሽመልስ አብዲሳ የነገሯቸው ነገር "እኛ ውስጥ ውስጡን እንጨርሰዋለን እናንተ ግን ግፉበት። ወደ ኋላ የሚል በህይወቱ ላይ እንደፈረደ ይቁጠር። አንዴ ገብተንበታል ዳር ሳናደርስ አንመለስም። የብልፅግናን ፈጥረን ወደ አራት ኪሎ የመጣነው በዚሁ መንገድ ነው። አዲሲቱን ኦሮሚያ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ላይ የእናንተ ድርሻ ቀላል አይደለም። በርቱ ነበር ያላቸው። ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መኖር ካልተቻለ ዐማራን ለትግሬና ለሱዳን ሰጥተን፣ ሱማሌ ወደ ፈለገበት እንዲሄድ አድርገን፣ ደቡብን ከእኛ ጋር ቀላቅለን በኃይ ግማሽ ደቡብ ወሎን እና አዲስ አበባን ጨምሮ ይዘን መገንጠል ነው።" ይሄ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው። ማንም አያስቆመንም። ምንም አትስጉ ነው ያላቸው። መነኩሴዎቹ አሁን ታግተው ነው ያሉት።

"…ዘመዴ Voice over ን በተመለከተ እንደምንም ብለህ ለቅዱስ ሲኖዶሱም ለኅበረተሰቡም ቀድመህ ማድረስ አለብህ። መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶሱን ከህዝቡ ለመነጠል እንደ ዋነኛ መንገድ ነው ሊጠቀመው ያሰበው። ይህም ስል የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶች በኩራት እንዳይቃወሙት አንገት ማስደፊያ ነው። መረጃው ቀድሞ ከወጣ የጨጓራ በሽተኞች ከመሆን በዘለለ ምንም አባታቸው አያመጡም። የሚገርምህ እኔ ሃይማኖቴ አይደለም። ነገር ግን ሰዎቹ ሊፈጥሩ ያሰቡት ምስቅልቅል ስላሳሰበኝ ነው። በአሁን ወቅት ደግሞ በጣም የምት ሰማው እና ታማኝ የመረጃ ምንጭ ስለሆንክ ብዬ ነው ወዳንተ መምጣቴ።

"…በአጠቃላይ ስለዚህ ሥራ የሚያውቁ ሰዎች 3 የኮምፒዩተር ስፔሻሊስቶች፣ አንድ ስሙን ከሰሞኑ ስሙን የምነግርህ አርቲስት የድምጽ የአባቶችን ድምፅ የማስመሰሉን ሥራ እንዲሠራ ተመርጧል። አርቲስቱን በፎቶ እሰጥሃለሁ። አርቲስቱ ያስመሰለውን የአባቶች ድምጽ ወደ ኮምፒዩተራቸው አስገብተው ነው በስልክ እንደተነጋገሩ የሚያስመስሉት። ንግግሩ ኦሮሞን የሚያንቋሽሽ አድርገው እንዲሠራ ነው የታዘዘው። ድምፁ ከተሠራ በኋላ አርቲስቱ ይገደላል ወይ መርፌ ወግተው ያጀዝቡታልም ተብሏል። አዛዡ ሰለሞን ሶካ እና ከሱ በላይ ያሉ ሰዎች ናቸው።

"…አንተን በተመለከተ ኢንተርኔት ላይ ባለህ እንቅስቃሴ የተውካቸውን ኮቴዎች ተከተለው አካውንት መጥለፍ ሲሆን፣ በዚያም ሳታውቅባቸው የሚችሉትን ያህል መረጃ መውሰድ ነው። ካልቻሉ ደግሞ ሶሻል enginering የሚባለውም ቴክኒክ በመጠቀም ነው ሊመጡብህ ያሰቡት። በዚህም ወዳጅ መስለዉ መረጃው መመዝበር ነው። ከዛ በራስህ መረጃ documentary ሠርተው ያንተ ተከታዮች ላይ conspiracy መፍጠር። ይሄን ካሳካን ቢያንስ እንደ ጉድ ከሚከተሉህ ሰዎች ከብዙ ሚልዮኖቹ ቢያንስ ግማሽ የሚሆነው ሰው ከአንተ መራቅ ነው የፈለጉት።

"…ያንተከትሎ ከዚያ በኋላ በዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን ሚዲያዎች የሠሩትን documentary አንተን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አሸባሪ ማሳየት ነው የፈለጉት። በዚህም ዋና ዓላማው አንተን በወንጀለኛ፣ በዘር አጥፊነት ለመፈረጅ ነው። ጭቅጭቅ ነበረባቸው። ልጁ ለዚህ ፍረጃ አይመችም የሚል ነገር ተነሥቶም ነበር። ነገርግን አቶ ሰሎሞን ሶካ ይገባናል ነገርግን ሌላ የተሻለ ምርጫ የለንም ስለዚህ በዚሁ ግፉበት የሚል መመሪያ ሰጥቷቸዋል።

"…ዛሬ voice over እንዲሰሩ ከታዙት መካከል ከinsa ፕሮጀክቶች በሙሉ ወደ እኛ ወደ ኦሮምያ ደኅንነት ቢሮ እንዲመጡ ተደርጓል። በኦሮሚያ ደህንነት ቢሮ እንዲሠራ የተፈለገው አቶ ተመስገን በሚሠራው የደኅንነት ቢሮ መተማመን በማጣታቸውና ዐማሮቹ እንደ ፓርቲም፣ እንደ ክልልም ለእኛ ለኦሮሚያ ብልጽግና የሚያሳዩት እንቅስቃሴ እጅግ መተማመን ስለጠፋበት ነው። አቶ ደመቀ ከእነ አቢይ ያፈነገጠ ይመስለኛል። አቶ ተመስገንም በጎጃሜዎቹ የተጠለፈ ነው ብለው አያምኑትም። በመከላከያውም ስንጥቃት አለ። የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ በአባቶች ጥበብ አለፈ እንጂ ከህዝቡ ይልቅ ጦሩ ነበር የሚፋጀው። 

"…በኦሮሚያ ደኅንነት ቢሮ የሚሠሩት ከቱርክ ተምረው የመጡ እንዲሁም የቀድሞ insa ላይ የነበሩ ሰዎች ናቸው። አንተ አሁን መረጃውን ለማኅበረሰቡ እና ለቅዱስ ሲኖዶሱ አሳውቅ። ዘመዴ ፍጠን ትናንት ምሳ ሰዓት ላይ ሙሉ ለሙሉ ፕሮጀክቶቹን በአጠቃላይ ወደ እኛ ኦሮሚያ ደህንነት ቢሮ መጥቷል። ሁሉም ያነቡሃል። ግትርነትህን፣ ሃቅህን ይወዱታል፣ እልህህ ደስስ ይላቸዋል። የሚጠሉት ሴራቸውን ስለምታፈራርሰው ነው። በፊት በፊት ጓደኛህ ስለሆነ ዳንኤል ክብረት ነው መረጃ የሚሰጠው ብለው ይሟገቱ ነበር። አሁን አሁን ግን በተለይ ዳንኤል ላይ ከጻፍክ በኋላ ስለ ዳንኤል እንደ አዲስ መረጃ ካንተ ስላገኙ በአንተ ላይ ክትትልና የመረጃ ምንጮችህን ለማወቅ እንቅልፍ አጥተዋል። ነገር ግን ምንም ዱካ ሊያገኙ አልቻሉም። የአንስ ልዩ ነው። በርታ ዘመዴ። ህዝቡ አስቀድሞ ተጠንቅቆ እንዲጠብቅ አንተ ይሄን ቀድመህ አውጣሁ።

"…ስላለኝ አውጥቼዋለሁ። እኔን በተመለከተ ግን በ email የምጻጻፈው ከጀርመን መንግሥት ለሥራ ጉዳዮች ብቻ ነው። ለማንም በኢሜል መልስ ሰጥቼ አላውቅም። ሲበረብሩ ውለው ቢያድሩ የሚጣሉት ከጀርመን መንግሥት ጋር ነው። በተረፈ በስልኬ ላይ የሚቀመጥ ምንም የተለየ ነገር የለኝም። የማገኛቸውን መረጃዎች ሃገር የሚያፈርሱትን በመደበቅ ነው በስሱ እንዲደነግጡ፣ ንስሀም እንዲገቡ የምለቅላቸው። የብዙዎቹን ነውር ሁላ ደብቄያለሁ። እነሱ አሸባሪ ሲሉኝ እኔ ደግሞ እየቀፈፈኝ ገመድ ፈልገው ይታነቁ ዘንድ የሚያደርጋቸው መረጃዎችንም እለቃለሁ። 

#ሼር_በማድረግ_አድርሱ
•••

ምንጭ፡ (ዘመዴ)

የቴሌግራም ገፅን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/zekidanemeheret
ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ስለ ሃይማኖታቸው ጠንቅቀው ያውቁ ዘንድ በፍኖተ መንግሥተ ሰማያት ዩቲዩብ ቻናል ተከታታይ ትምህርት /Course/ ሊጀመር ነው።

በዚህም መሠረት በቅድምያ ትምህርተ ሃይማኖት መግቢያን ከዛሬ ጀምሮ ወደእናንተ ማድረስ እንጀምራለን። በትምህርተ ሃይማኖት መግቢያ ት/ት ሃይማኖት ምን ማለት ነው ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ ብዙ ክፍል እንዳስስበታለን።

አንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ነኝ የሚል ምእመን ስለ ትምህርተ ሃይማኖት ሊያውቅ ሊረዳም ይገባዋል።

ትምህርቱን ስትከታተሉ እስኪርብቶ እና ወረቀት ይዛቹ ዋና ዋና ሃሳብ መዝግባቹ ብትይዙ ወደፊት ይጠቅማል።

የተመረጡትን ርዕሶች እንደ ጨረስን ፈተና የሚኖር ሲሆን ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ እንድትፈተኑ ይጠበቃል።

#ትምህርቱን ከታች ባስቀመጥነው #YouTube Link በመግባት ሰብስክራይብ በማድረግ ትምህርቱን በዕለቱ ይከታተሉ።

https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw

መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልን ምሥጢር ሰማያዊን ቸሩ አምላክ ይግለጽልን


#ሼር
💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️
💕 #ኒቆዲሞስ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌📌 #ኒቆዲሞስ  :-ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን የሚያመለክት ሲሆን በቤተክርስቲያን ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ነው። ትርጓሜው የአይሁድ መምህር ወይም ደሞ የጌታችን ደቀ መዝሙር የሌሊቱ ተማሪ ማለት ነው።

👉🏾 ኒቆዲሞስ #ፈሪሳዊ ነው።ዮሐ 3:1
👉🏾 ኒቆዲሞስ #የአይሁድ_አለቃ ነው።ዮሐ 3: 1
👉🏾 ኒቆዲሞስ #መምህረ_እስራኤል ነው።ዮሐ 3:10
👉🏾 ኒቆዲሞስ #ምሁረ_ኦሪት ነው።የሐ 7:51
👉🏾 ኒቆዲሞስ በኢየሩሳሌም በሀብት በእውቀት በዝና በስልጣን የታወቀ ነው። ኒቆዲሞስ በትንሹ ስለ ሦስት ነገር ሌሊት ሌሊት እየሄደ ከጌታ እግር ስር ይማር ነበር።

1. አይሁድን ፈርቶ:- በዛን ሰዓት በአይሁድ ሕግ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሀብት ንብረቱ ስለ ሚቀማ ከነሱ ለመሸሽ ሌሊትን መረጠ።
2. ውዳሴ ከንቱን ሽቶ:- በወቅቱ የነበረ እውቅ ሊቅ ነበርና እንዴት ከመምህር ስር ይማራል እንዳይሉት።
3 ልቡናው እንዲሰበሰብ:- ከቀን ይልቅ ሌሊት የአዕምሮ እረፍት ስላላት እሱን ሽቶ ነው።

📌 #ኒቆዲሞስ ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ ስለ ምስጢረ ጥምቀትና ዳግመኛ ልጅነት የፅድቅ ስራ በሰፊው ተምሮአል።ዮሐ ም 3፡ 1-12

🛑 እባካችሁ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ መልዕክቱን እናድርስ።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

https://t.me/zekidanemeheret
#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምታስገኝ ሐዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባሕርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው እኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳዕና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በኃጥያት የመረረውን ሕይወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪይ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪይ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንተ ባህሪይ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ኃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ሕይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ጊዜ የወይራ ዘይት ለመሥዋዕትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡

#ሼር

👉ለመቀላቀል 👇👇👇@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ቃላት_እና_ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነው፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡ "ኪርያላይሶን" የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው "ዬ" ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ" ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፣ ማረን" ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው፡፡ "እብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣ አምላክ" ማለት ነው፡፡ "ታኦስ ናይናን" ማለትም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲሕ" ማለት ነው፡፡ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነው

#ትስቡጣ
"ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።

#አምንስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚአ ኵሉ በውስተ መንግሥትከ የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡

#ሼር

https://t.me/zekidanemeheret
ይድረስልኝ

ፍቅር ይዞኛል ለምትሉ ሁሉ
..........................................................
     አንተ ፍቅር ይዞኛል የምትለው፤ አዎ አንተ በፍቅሯ አብጃለው፣ ስነሳም ስተኛም ስለእርሷ ነው የማስበው የምትለው! በዓይኗ ሰረቅ አድርጋ ድንገት ስታየኝ ልቤ ቀጥ ይልብኛል የምትለው፤ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አያድርገውና በመጀመሪያ ያየሃት ቀን ያፈዘዘህ ዓይኗ ቢፈስ፣ ቀልብህን ስቦ ያስደነገጠክ መልኳ ቢጠቁር እና ቢጠፋ፣ እስከ ወገቧ  የረዘመው ፀጉሯ ቢቆረጥ፣ አቅርበሃት ጓደኛህ ካደረካት በኋላ የወደድክላት ፀባዩዋ እና ሥርዓቷ ተለውጦ ክፉ እና ደረቅ ብትሆንብህ፣ አንጀትህን ያርሰው የነበረው አረማመዷና ቅልጥፍናዋ በበሽታ ተቀምቶ አልጋ ላይ ሆና ብታቃስት አሁንም ከእርሷ ጋር ትሆናለህ? እንደ ድሮ ከእርሷ ጋር ለመሆን ትሽቀዳደማለህ? ሁሌ እንደምታፈቅራትና እንደምትሳሳላት መንገርህን ትቀጥላለህ? ለእርሷ የምታሳየው ትህትናና ክብር ይቀንስብሃል? አንቺስ ብትሆኚ? መጀመሪያ ያየሽው ዕለት ደስ ያለሽ መልኩና ቁመናው እንዳልነበረ ቢሆን፣ ሁሌ አንቺን ለማስደሰት ብሎ አንቺን በመጋበዝ እና በማዝናናት ያጠፋው የነበረው  ገንዘብና ሀብት ጠፍቶ ፍጹም ደሃ ቢሆን፣ መጀመሪያ የተዋወቃችሁ ሰሞን ሲያሳይሽ የነበረው ፍጹም ትህትና እና አክብሮት ተለውጦ በትዕቢት አንቺን መማታት ቢጀምር፣ ጤንነቱን አጥቶ በበሽታ ቢንከራተት፣ በመጀመሪያ ወደ እርሱ ስቦ ያመጣሽ ነገሮቹ ሁሉ ቢጠፉ አሁንም ከእርሱ ጋር ትሆኚያለሽ? አሁንም እርሱ ጋር ስልክ መደወልሽን ትቀጥያለሽ? እህቴ ሆይ እስቲ ንገሪኝ፤ ፍቅርሽ ከአፍሽ ነው ወይስ ከልብሽ? ወንድሜ ሆይ ልጠይቅህ፤ ፍቅርህ በመናገር ነው ወይስ በተግባር?

     መልሳችሁ " ይህ ቢፈጠር አብሬ አልቀጥልም" ከሆነ ከመጀመሪያውም ፍቅር እንዳልያዛችሁ ላርዳችሁ እወዳለሁ፡፡ ስትተያዩ እወድሃለሁ፣ እወድሻለሁ ከምትባባሉ ባየሁሽ/ ባየሁህ ቁጥር በውስጤ ያሉት ንጥረ ነገሮች (hormones) ይንተከተካሉ ብትባባሉ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ትርጉም  ይህ አይደለምና፡፡

     ፍቅርማ ምን እንደሆነ ራሱ ፍቅር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገባ አስተምሮናል፡፡ እርሱ ከምድር አፈር ካበጃጀን በኋላ የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ ካለብን በኋላ ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ያኔ አምሮብን፣ ተከብረን ሳለ ወዶናል፡፡ እፀ በለስን በልተን ያበራ የነበረው የጸጋ ልብሳችን ተገፎ ራቁታችንን ስንሆን፣ ደዌ የማያውቀው ሥጋችን በከንቱ ፍትወታት ሲታመምም በፍጹም ፍቅሩ አፍቅሮናል፡፡ ይተወንም ዘንድ ስላልቻለ ፍቅርን ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ስለእኛ እስከ ሞት አደረሰው፡፡ ታመን በኃጢአት አልጋ ተኝተን ሳለ ከጎናችን ሳይለይ ያሳታመመን አምላካችን ነው፡፡ እስከመጨረሻው ድረስ በኃጢአት የከረፋነውን ሳይጸየፈን ተጠግቶን ቁስላችንን በቁስሉ ያከመን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሊያክመን መጥቶ እንኳን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ቁስላችንን ሳይጸየፍ የቀረበንን ፈጣሪያችንን መታነው፡፡ ኑ ላድናችሁ ሲለን በመስቀል ላይ ሰቀልነው፡፡ ሐኪሙን የሚሳደብና የሚማታ በሽተኛ እንደምን ያለ ነው? የበሽተኛውን ስድብ እና ድብደባ ታግሶስ በትጋት የሚያክም ሐኪም እንደምን ያለ ነው? ለዚህስ አንክሮ ይገባል!!

     ወዳጄ ሆይ ፍቅር በደስታ ጊዜ ኖሮ በኃዘን ጊዜ የሚጸና፣ በጤናው ጊዜ አብቦ በደዌ ጊዜ የሚፈካ፣ በሰላም ጊዜ ተኮትኩቶ በጭንቅ ጊዜ የሚበቅል ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ታድያ ወዳጄ ሆይ በፍቅርሽ ተይዣለሁ ያልካት ሚስትህን ያማረው መልኳ በድንገት ቢጠፋስ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ እንዴት እወዳታለሁ ልትል ትችላለህ? ጤናዋን አጥታ አልጋ ላይ ብትተኛ ጥለሃት ለመሄድ የምታስብ ከሆነ እንዴት እወድሻለሁ ልትላት ትችላለህ? አንቺስ ብትሆኚ፤ ፀባዩ እንዳለ ተለውጦ ቢንቅሽና ቢያቃልልሽ ትተሽው ለመሄድ የምታስቢ ከሆነ እንዴት ዓይኑን እያየሽ እወድሃለሁ ትይዋለሽ? ቢመታሽም እንኳን እንደ አምላክ ምቱን ታግሰሽ እርሱን ለማከም ካልፈቀድሽ እንዴት አፈቅርሃለሁ ትይዋለሽ?

      " ፍቅር ያስታግሳልና"(1ኛ ቆሮ 13÷4) የማትታገሱ ከሆነ እንዴት ፍቅር ይዞኛል ትላላችሁ? አምላክ ያሳየንን ፍቅር ለሌሎች በመስጠት ክርስቶስን ልንመስለው ይገባናል፡፡ እህቴ ሆይ ወዳጅሽ በክፉ ሱስ ተጠምዶ፣ በትዕቢትና በንቀት ልቡ ተነድፎ ገብቶ ቢያንቋሽሽሽ ለእርሱ የምትሰጪው ፍቅር እንዲጎድል አትፍቀጂ፡፡ የፈለገ ተለውጦ የማታውቂው ሰው ቢሆንብሽም ለእርሱ የምትሰጪውን እንክብካቤ በትጋት ፈጽሚ፡፡ ያለንግግር ፍቅርሽን የሚነግሩትን ዓይኖችሽን ከዓይኖቹ አታንሺ፡፡ ወንድሜ ሆይ የሚስትህን የምትወድላት ፀባዩዋን ረስታ ደረቅና የምታውክ ብትሆንብህ እንኳን በስስት የምታያትን የፍቅር መመልከት አትንፈጋት፡፡ አምላክስ በሕመማችን ጊዜ ዓይኑን ከእኛ ድንገት ቢያነሳ ኑሮ ወድቀን እንደምንቀር ሁሉ አንተም ዓይንህን ከሚስትህ ላይ አታንሳ፡፡ ጌታ በፍጹም ፍቅር ወዶናልና እርስ በርሳችሁ በሚያስታግሰው እውነተኛው ፍቅር ተዋደዱ፡፡ በፍቅርም ቃል ተነጋገሩ እንጂ አትቆጡ፡፡

     ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ የአፍ ብቻ ሳይሆን የልቡና፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የምንገልጠው እውነተኛውን ፍቅር ይስጠን፡፡

                ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

🕊#ሼር_ይደረግ!
መዝሙር ዘኖላዊ ከታኅሣሥ ፳፩  - ፳፰

የዕለቱ ምስባክ፦

ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ፤
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ፤
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ። መዝ ፸፱፥፩

ትርጕም፦

ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ የእስራኤል ጠባቂ አድምጥ፤
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ።

ምሥጢር፦

የዮሴፍ በጎች እንዲጠበቁ እስራኤል ዘነፍስን የምትጠብቅ ሆይ ጸሎታችንን አድምጥ ስማ።
በዘባነ ኪሩቤል ተቀምጠህ በአንድነት በሦስትነት የምትመሰገን አቤቱ በሥጋ ማርያም ተገለጥ አንድም በመምህርነት ተገለጥ።

የወንጌሉ አጠቃላይ መልእክት፦

፩. በበሩ የማይገባ በሌላ የሚገባ ሌባ ነው።

ዛሬም በበሩ የማይገቡና በትክክለኛው በር መግባትን የሚከለክሉ በሰፊው መንገድ የሚሄዱና የሚወስዱ ብዙ ናቸው። እኛን የሚጠቅመን ግን በጠበበው ደጅ መግባቱ ነው እሱ ወደዘለዓለም ሕይወት ያደርሰናልና።

፪. በጎቹ የእረኛቸውን ድምጽ ሰምተው ለይተው ያውቃሉ።

የቤተ ክርስቲያን ድምጽ የሚመስሉ ግን ያልሆኑ ብዙ ድምጾች አሉ እውነተኛውን ድምጽ መስማትና እውነተኛውን እረኛ መከተል ለሕይወታችን ይጠቅመናል።

፫. ከእውነተኛው እረኛ በፊት የመጡ ሌቦች ነበሩ።

በግብረ ሐዋርያት ፭ እንደተገለጠው ይሁዳ ዘገሊላና ቴዎዳስ ዘግብጽ ክርስቶስ ነን ብለው ተነሥተው ነበር እነሱም ጠፉ የተከተሏቸውም ጠፍተዋል።
የምንከተላቸው የሚያድኑን እንጂ የሚያጠፉን መሆን የለባቸውም። እንዴት እናውቃቸዋለን ብለን እንዳንጨነቅ አምላካችን ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ብሎናል።

፬. በበሩ የሚገባ መውጣት መግባት ይችላል መሰማሪያም ያገኛል።

ይህ የሚያሳየን በአባታችን ቤት ያለንን ነጻነትና የዘለዓለም ዕረፍት ነው። የልጅነት መብትና መንፈስ ስላለን የአባታችንን መንግሥት የመውረስ ሥልጣን አለን።

፭. ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ሲመጣ እውነተኛው እረኛ ግን ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲበዛልን መጣ።

ነፍሳችንን የሚሰርቁ ለዘለዓማዊ ሞት በሚዳርግ በኑፋቄ በክህደት ሊያጠፉን የሚተጉ አሉና ከእነዚህ እንራቅ።

፮. በጎቹ የእሱ ያልሆኑ ምንደኛ ወይም ሙያተኛ ተኵላ ሲመጣ በጎቹን ትቶ ይሸሻል።

በዘመናችን በተኵላዊ ግብር ውስጥ ሆነው የእረኝነት ሥራ የሠሩ እየመሰሉ ትቶ መሸሽ ብቻ ሳይሆን አስመስለው በያዙት የእረኝነት ሥልጣን በጎችን ቆመው የሚያስበሉና ለዚህ ዓላማ እየሠሩ ያሉ ብዙዎች እየሆኑ ስለመጡ ማነው እረኛችን የሚለውን ጠይቆ ምላሽ ማግኘት አስፈላጊ ነው።

፯. እረኛው አንድ ነው መንጋውም አንድ ነው።

በመጽሐፍ ያለው እውነት ይህ ሆኖ እያለ በተለያየ ምክንያት በልዩነት መንገድ እየሄድን አለመስማማትን መጨቃጨቅን መካሰስን ስም መጠፋፋትን መለያችን ወደማድረግ ከፍ እያልን መጥናተናል አይጠቅመንምና ከእንዲህ ዐይነቱ አካሄድ ራሳችንን በቃሉ ልጓምነት ልንገታ ግድ ነው።

#ሼር

https://t.me/sinkisar_gisawe_z_tewahedo

ከወደዱት በreaction ያሳዩን!
‼️የቤተመቅደሱ ዘፋኞች‼️

ሰላም ተወዳጆች! እንዴት አላችሁ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

ተወዳጆች እስቲ ለዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ጥያቄውን አይታችሁ ግር ልትሰኙ ብትችሉም አካሄዳችሁ ልክ ስላልሆነ ወደ ጥያቄው ልለፍ።

የእግዚአብሔር ወልድ ደም በነጠበባት፤ ሰማያውያን እና ምድራውያን በሚያስቀድሱባት፤ የአምላክ ወልደ አምላክ ሥጋወደሙ በሚፈተትባት በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ መዝፈን፤ መደነስ ይቻላል

በአርባ በሰማንያ ቀናችን ተጠምቀን ክርስቶስን በለበስንባት፤ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለመሆን በታተምንባት፤ ሥጋወደሙን ተቀብለን ሕያው በሆንባት፤ በእኛ ክርስቶስ እንዲኖር እኛ በእርሱ እንድንኖር በሆንባት በዚች ቅድስት ቤተክርስቲያን መዝፈን ይቻላል? ቤተመቅደስ ውስጥ የሆነ ሰው ሲዘፍን፤ ሲደንስ ብታዩ ምን ይሰማችሁ ይሆን(ዮሐ 6÷54-56)

እንዲህ ነው ብላችሁ መመለስ ከምትችሉት በላይ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።

አምላከ አምላክት አባታችሁ የሆነ፤ እግዚአ አጋዕዝት ጌታችሁ የሆነ፤ የንጉሠ ነገሥት ልጆች የሆናችሁ እናንተስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችሁን አታውቁምን?

ሥጋወደሙ በሚፈተትበት መዝፈን መደንስ ካልተቻለ ሥጋወደሙን በተቀበለ መቅደስ በሆነ አካላችን መዝፈን መደንስ ይገባል

ቤተመቅደስ ውስጥ የሆነ ሰው ሲዘፍን፤ ሲደንስ ብታዩ ምን ይሰማችሁ ይሆን ብዬ ስጠይቃችሁ የተሰማችሁ ስሜት ትዝ አላችሁ

ቤተመቅደስ ውስጥ የምትዘፍኑት የምትደንሱት እናንተ ስትሆኑስ? እውነት ያ ቀድሞ በሌላ ሰው ያሰባችሁት ስሜት አብሯችሁ አለ

ተወዳጆች ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ሥጋችን ምን እንደሆነና በሥጋችን ምን ማድረግ እንዳለብን ሲናገር እንዲህ ይላል፦

"ሥጋችኹ የክርስቶስ አካል እንደ ኾነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን አካል ወስዳችሁ የአመንዝራ አካል ታደርጉታላችሁን አይገ፟ባ፟ም።

.....ሥጋችኹ ከእግዚአብሔር ለተቀበላችኹት በእናንተ አድሮ ላለ ለመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ኾነ አታውቁምን? ለራሳችኹም አይደላችኹም። በዋጋ ተገዝታችኋልና፤
ስለዚህም እግዚአብሔርን በሥጋችኹ
አክብሩ።" 1ኛ ቆሮ 6÷15-20

ከንባቡ እንደምንረዳው፦
ሥጋችን የክርስቶስ አካል ነው።
ሥጋችን ከእግዚአብሔር የተቀበልነው የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነው። በሥጋችን ደግሞ እግዚአብሔርን ልናከብረው ይገባናል።

እስኪ ንገሩኝ በሥጋችን እግዚአብሔርን የምናከብረው እንዴት ነው

ሀ. አጋንንትን በመምሰል ነው

"አጋንንት ይዘፍናሉ" እንዲል ኢሳ 13÷21

አንድ ሰው ዘፈን ሲዘፍን ሲደንስ አጋንንት ወደ እርሱ ቀርበው ከእርሱ ጋር አብረው ይዘፍናሉ ይደንሳሉ አንድ አባት እንዳየው!

ለ. ቅዱስ ጳውሎስን በመምሰል ነው

"እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" እንዳለው  1ኛ ቆሮ 11÷1

ደግሞም 1ኛ ቆሮ 11÷20 እንዲህ ይላል "በዋጋ ተገዝታችዃልና  ለራሳችኹ አይደላችኹም"

"በዋጋ ከተገዛን እኛ ራሳችን የራሳችን አይደለንም ማለት ነው። እንዲህ ተብሎ በማይነገር፤ ወርቅ ብር በማይመዝነው ቅዱስ ደም የተገዛን የክቡር ጌታ ክቡር ልጆች ነን።"

ክቡር ልጅ እንዴት ክብሩን ጥሎ ክብሩን በሚያሳጣው ቦታ ይገኛል

እንዴት የቅዱሱ ልጅ ርኩስ ከሆኑ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ይዋደዳል

እንዴት የንጉሥ ልጅ ከሥልጣኑ ወርዶ ለአጋንንት እራሱን ባርያ ያደርጋል

ተወዳጆች እንዴት የክርስቶስን አካል ለአጋንንት መጠቀሚያ ታደርጋላችሁ

እንዴት መቅደስ በሆነ ሰውነታችሁ ዘፋኞች ትሆናላችሁ

እንዴት ከተዋረዳችሁበት ከፍ ለማድረግ አምላካችሁ ከበረት እስከ ሞት የከፈለላችሁን ትረሳላችሁ

ተወዳጆች በልባችሁ እንዲህ ብላችሁ ሰይጣንን ተቃወሙት፦ በልደቱ እራሱን በትህትና ለገለጸው ራሴን አዋርጄ ፣ በንስሐ ወደእርሱ ቀርቤ፣ እርሱን በመቅደሴ አመልካለሁ እንጂ ኮንሰርት ብዬ የመቅደሱ ዘፋኝ አልሆንም። ዘፈን ልዝፈን ብዬ የቤተመቅደሱ ዘፋኝ አልሆንም!!!

ምክንያተ ጽሕፈት፦ አብዛኛው የኦርቶዶክስ አማኝ የልደቱን ቀን ከባለልደቱ ጋር፤ ባለልደቱ (አማኑኤል) እንደሚወደው ሳይሆን
ልደቱን ከሚጠላው፤ ሰይጣን በሚወደው መልኩ ከእርሱ ጋር ሰዎች በማክበራቸው ነው።

የእንመለስ ደወል ነው!!!

ጸሐፊ፦ ዳዊት ፍቅሬ

ታኅሣሥ 26 2016 ዓ.ም


#ሼር_ይደረግ!