ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
803 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ ሰሞኑን በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚወጡትን ነገሮች እና ጽሁፎች
ለምሳሌ ፦ከ 5G ጋር የተገናኙ ፣እውነተኛ ሳይሆን በ 666 አባላት የተፈበረከ የአለምን ህዝብ ለመቀነስ እና ከአምላኩ ጋር ያለውን መንፈሳዊ ግንኙነት ማጥፋት የተሰራ ቫይረስ ነው የሚሉ ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ትክክል የሆኑ መላ ምቶችን ባለፈው ልኬላችሁ ነበር አሁን ደግሞ በተጨማሪ ሌላ channel ላይ ባሉ ወንድሞቻችን የተሰራ ስላለ ከነሱ ላይ ወስደን ልናቀርብላችሁ ስላሰብን ዛሬ ማታ ላይ ይዘን እንቀርባለን፡፡

#ሼር ይደረግ፡፡

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret
@zekidanemeheret @zekidanemeheret
ፖርኖግራፊ ምንድነው
ክፍል 5
በኤርሚያስ ኪሮስ
ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጫ መንገዶች

1.እግዚአብሔር እንደሚወዳችሁ አውቃችሁ ንስሐ ግቡ፦

በዚህ ሱስ ውስጥ የገቡ ሰዎች እግዚአብሔር እንደሚጠላቸውና እንደሚፀየፋቸው ያስባሉ ። እንዲህ አይነቱ ሃሳብ ሰዎችን የሱሱ ባሪያ አድርጎ ለማኖር ሰይጣን ይጠቀምበታል ። በፖርኖግራፊ ሀጢአት መውደቅን ተከትሎ ሰይጣን ሁልጊዜ እዛው ተብትቦ ሊያስቀረን ይጥራል ። ይህም ራሳችንን እንድንጠላ ፣ እግዚአብሔር ለእኛ ግድ እንደማይለውና ሩቅ እንደሆነ እንድናስብ እና ተስፋ ቢስነት እንዲሰማን ሀሳባችንን በመያዝ ይተጋል ። ሁሌም ቢሆን ውድቀትን ተከትሎ ዋና ጠላታችን ማን እንደሆነ ማወቁ ተገቢ ነው ። በጥፋታችን ማዘናችን ተገቢ ቢሆንም እንደ ይሁዳ ወደ ከፋ እርምጃ የሚወሰድ መሆን የለበትም (ማቴ 27:4) ራሳችንን በመጥላት ውስጥ ዋዥቀን ራሳችንን የመቅጣት አዝማሚያው ቢኖረንም መውሰድ ያለብን እርምጃ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ዳዊት በንስሃ መደፋት ነው ። (መዝ 51:1) በእኛና በኃጢአታችን መካከል ልዩነት አለ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል ፤ ኃጢአተኛውን ግን ይወዳል እናት የልጅዋ ልብስ ቢቆሽሽ ለልጅዋ ያላት ፍቅር እንደማይቀየር እግዚአብሔርም ለእኛ ያለው ፍቅር አይቀየርም "የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃል " (1ዮሐ 1:7) የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለ ዓለም ሁሉ ስለፈሰሰ በእግዚአብሔር ፊት ይቅር የማይባል ኃጢያት የለም። ንስሐ ግቡ!

2.አምናችሁ ጸልዩ

የሰው ልጅ በራሱ ጥረት ከኃጢአት መውጣት አይችልም ። የእግዚአብሔር ፀጋ ሲያግዘው ግን የማይቻለውን ችሎ በቅድስና አሸብርቆ መኖር ይችላል ። እስከ ዛሬ በግል ጥረታችሁ ከዚህ ሱስ መውጣት ስላልቻላችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ሊሆን ይችላል ። ጸጋው ግን ጣልቃ ገብቶ አዲስ ህይወት ሊሰጣችሁ ይችላል ። ይህ ደግሞ የሚሆነው "እኔ ደካማ ስለሆንኩ የሚረዳኝ ጸጋ ይሰጠኝ " ብሎ በጸሎት እግዚአብሔርን በመለመን ነው ። በፀሎት ትጉ (ኤፌ 6:18) መውጣት እንደሚቻል አለማመን በራሱ ሰንሰለት ነው ።፡የእግዚአብሔር ፀጋ ታሪክን እንደሚቀይር ከዚህ ህይወት መውጣት እንደሚቻል እመኑ ። ምክንያቱም ከኀጢአት አውጥቶ ቅዱስ የሚያደርግ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጧልና ። (ቲቶ2:11)

.... ይቀጥላል
#ሼር ይደረግ

🕊👉 @zekidanemeheret

https://t.me/zekidanemeheret
ይድረስልኝ

ፍቅር ይዞኛል ለምትሉ ሁሉ
..........................................................
     አንተ ፍቅር ይዞኛል የምትለው፤ አዎ አንተ በፍቅሯ አብጃለው፣ ስነሳም ስተኛም ስለእርሷ ነው የማስበው የምትለው! በዓይኗ ሰረቅ አድርጋ ድንገት ስታየኝ ልቤ ቀጥ ይልብኛል የምትለው፤ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አያድርገውና በመጀመሪያ ያየሃት ቀን ያፈዘዘህ ዓይኗ ቢፈስ፣ ቀልብህን ስቦ ያስደነገጠክ መልኳ ቢጠቁር እና ቢጠፋ፣ እስከ ወገቧ  የረዘመው ፀጉሯ ቢቆረጥ፣ አቅርበሃት ጓደኛህ ካደረካት በኋላ የወደድክላት ፀባዩዋ እና ሥርዓቷ ተለውጦ ክፉ እና ደረቅ ብትሆንብህ፣ አንጀትህን ያርሰው የነበረው አረማመዷና ቅልጥፍናዋ በበሽታ ተቀምቶ አልጋ ላይ ሆና ብታቃስት አሁንም ከእርሷ ጋር ትሆናለህ? እንደ ድሮ ከእርሷ ጋር ለመሆን ትሽቀዳደማለህ? ሁሌ እንደምታፈቅራትና እንደምትሳሳላት መንገርህን ትቀጥላለህ? ለእርሷ የምታሳየው ትህትናና ክብር ይቀንስብሃል? አንቺስ ብትሆኚ? መጀመሪያ ያየሽው ዕለት ደስ ያለሽ መልኩና ቁመናው እንዳልነበረ ቢሆን፣ ሁሌ አንቺን ለማስደሰት ብሎ አንቺን በመጋበዝ እና በማዝናናት ያጠፋው የነበረው  ገንዘብና ሀብት ጠፍቶ ፍጹም ደሃ ቢሆን፣ መጀመሪያ የተዋወቃችሁ ሰሞን ሲያሳይሽ የነበረው ፍጹም ትህትና እና አክብሮት ተለውጦ በትዕቢት አንቺን መማታት ቢጀምር፣ ጤንነቱን አጥቶ በበሽታ ቢንከራተት፣ በመጀመሪያ ወደ እርሱ ስቦ ያመጣሽ ነገሮቹ ሁሉ ቢጠፉ አሁንም ከእርሱ ጋር ትሆኚያለሽ? አሁንም እርሱ ጋር ስልክ መደወልሽን ትቀጥያለሽ? እህቴ ሆይ እስቲ ንገሪኝ፤ ፍቅርሽ ከአፍሽ ነው ወይስ ከልብሽ? ወንድሜ ሆይ ልጠይቅህ፤ ፍቅርህ በመናገር ነው ወይስ በተግባር?

     መልሳችሁ " ይህ ቢፈጠር አብሬ አልቀጥልም" ከሆነ ከመጀመሪያውም ፍቅር እንዳልያዛችሁ ላርዳችሁ እወዳለሁ፡፡ ስትተያዩ እወድሃለሁ፣ እወድሻለሁ ከምትባባሉ ባየሁሽ/ ባየሁህ ቁጥር በውስጤ ያሉት ንጥረ ነገሮች (hormones) ይንተከተካሉ ብትባባሉ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ትርጉም  ይህ አይደለምና፡፡

     ፍቅርማ ምን እንደሆነ ራሱ ፍቅር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገባ አስተምሮናል፡፡ እርሱ ከምድር አፈር ካበጃጀን በኋላ የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ ካለብን በኋላ ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ያኔ አምሮብን፣ ተከብረን ሳለ ወዶናል፡፡ እፀ በለስን በልተን ያበራ የነበረው የጸጋ ልብሳችን ተገፎ ራቁታችንን ስንሆን፣ ደዌ የማያውቀው ሥጋችን በከንቱ ፍትወታት ሲታመምም በፍጹም ፍቅሩ አፍቅሮናል፡፡ ይተወንም ዘንድ ስላልቻለ ፍቅርን ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ስለእኛ እስከ ሞት አደረሰው፡፡ ታመን በኃጢአት አልጋ ተኝተን ሳለ ከጎናችን ሳይለይ ያሳታመመን አምላካችን ነው፡፡ እስከመጨረሻው ድረስ በኃጢአት የከረፋነውን ሳይጸየፈን ተጠግቶን ቁስላችንን በቁስሉ ያከመን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሊያክመን መጥቶ እንኳን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ቁስላችንን ሳይጸየፍ የቀረበንን ፈጣሪያችንን መታነው፡፡ ኑ ላድናችሁ ሲለን በመስቀል ላይ ሰቀልነው፡፡ ሐኪሙን የሚሳደብና የሚማታ በሽተኛ እንደምን ያለ ነው? የበሽተኛውን ስድብ እና ድብደባ ታግሶስ በትጋት የሚያክም ሐኪም እንደምን ያለ ነው? ለዚህስ አንክሮ ይገባል!!

     ወዳጄ ሆይ ፍቅር በደስታ ጊዜ ኖሮ በኃዘን ጊዜ የሚጸና፣ በጤናው ጊዜ አብቦ በደዌ ጊዜ የሚፈካ፣ በሰላም ጊዜ ተኮትኩቶ በጭንቅ ጊዜ የሚበቅል ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ታድያ ወዳጄ ሆይ በፍቅርሽ ተይዣለሁ ያልካት ሚስትህን ያማረው መልኳ በድንገት ቢጠፋስ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ እንዴት እወዳታለሁ ልትል ትችላለህ? ጤናዋን አጥታ አልጋ ላይ ብትተኛ ጥለሃት ለመሄድ የምታስብ ከሆነ እንዴት እወድሻለሁ ልትላት ትችላለህ? አንቺስ ብትሆኚ፤ ፀባዩ እንዳለ ተለውጦ ቢንቅሽና ቢያቃልልሽ ትተሽው ለመሄድ የምታስቢ ከሆነ እንዴት ዓይኑን እያየሽ እወድሃለሁ ትይዋለሽ? ቢመታሽም እንኳን እንደ አምላክ ምቱን ታግሰሽ እርሱን ለማከም ካልፈቀድሽ እንዴት አፈቅርሃለሁ ትይዋለሽ?

      " ፍቅር ያስታግሳልና"(1ኛ ቆሮ 13÷4) የማትታገሱ ከሆነ እንዴት ፍቅር ይዞኛል ትላላችሁ? አምላክ ያሳየንን ፍቅር ለሌሎች በመስጠት ክርስቶስን ልንመስለው ይገባናል፡፡ እህቴ ሆይ ወዳጅሽ በክፉ ሱስ ተጠምዶ፣ በትዕቢትና በንቀት ልቡ ተነድፎ ገብቶ ቢያንቋሽሽሽ ለእርሱ የምትሰጪው ፍቅር እንዲጎድል አትፍቀጂ፡፡ የፈለገ ተለውጦ የማታውቂው ሰው ቢሆንብሽም ለእርሱ የምትሰጪውን እንክብካቤ በትጋት ፈጽሚ፡፡ ያለንግግር ፍቅርሽን የሚነግሩትን ዓይኖችሽን ከዓይኖቹ አታንሺ፡፡ ወንድሜ ሆይ የሚስትህን የምትወድላት ፀባዩዋን ረስታ ደረቅና የምታውክ ብትሆንብህ እንኳን በስስት የምታያትን የፍቅር መመልከት አትንፈጋት፡፡ አምላክስ በሕመማችን ጊዜ ዓይኑን ከእኛ ድንገት ቢያነሳ ኑሮ ወድቀን እንደምንቀር ሁሉ አንተም ዓይንህን ከሚስትህ ላይ አታንሳ፡፡ ጌታ በፍጹም ፍቅር ወዶናልና እርስ በርሳችሁ በሚያስታግሰው እውነተኛው ፍቅር ተዋደዱ፡፡ በፍቅርም ቃል ተነጋገሩ እንጂ አትቆጡ፡፡

     ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ የአፍ ብቻ ሳይሆን የልቡና፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የምንገልጠው እውነተኛውን ፍቅር ይስጠን፡፡

                ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

🕊#ሼር_ይደረግ!
‼️የቤተመቅደሱ ዘፋኞች‼️

ሰላም ተወዳጆች! እንዴት አላችሁ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

ተወዳጆች እስቲ ለዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ጥያቄውን አይታችሁ ግር ልትሰኙ ብትችሉም አካሄዳችሁ ልክ ስላልሆነ ወደ ጥያቄው ልለፍ።

የእግዚአብሔር ወልድ ደም በነጠበባት፤ ሰማያውያን እና ምድራውያን በሚያስቀድሱባት፤ የአምላክ ወልደ አምላክ ሥጋወደሙ በሚፈተትባት በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ መዝፈን፤ መደነስ ይቻላል

በአርባ በሰማንያ ቀናችን ተጠምቀን ክርስቶስን በለበስንባት፤ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለመሆን በታተምንባት፤ ሥጋወደሙን ተቀብለን ሕያው በሆንባት፤ በእኛ ክርስቶስ እንዲኖር እኛ በእርሱ እንድንኖር በሆንባት በዚች ቅድስት ቤተክርስቲያን መዝፈን ይቻላል? ቤተመቅደስ ውስጥ የሆነ ሰው ሲዘፍን፤ ሲደንስ ብታዩ ምን ይሰማችሁ ይሆን(ዮሐ 6÷54-56)

እንዲህ ነው ብላችሁ መመለስ ከምትችሉት በላይ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።

አምላከ አምላክት አባታችሁ የሆነ፤ እግዚአ አጋዕዝት ጌታችሁ የሆነ፤ የንጉሠ ነገሥት ልጆች የሆናችሁ እናንተስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችሁን አታውቁምን?

ሥጋወደሙ በሚፈተትበት መዝፈን መደንስ ካልተቻለ ሥጋወደሙን በተቀበለ መቅደስ በሆነ አካላችን መዝፈን መደንስ ይገባል

ቤተመቅደስ ውስጥ የሆነ ሰው ሲዘፍን፤ ሲደንስ ብታዩ ምን ይሰማችሁ ይሆን ብዬ ስጠይቃችሁ የተሰማችሁ ስሜት ትዝ አላችሁ

ቤተመቅደስ ውስጥ የምትዘፍኑት የምትደንሱት እናንተ ስትሆኑስ? እውነት ያ ቀድሞ በሌላ ሰው ያሰባችሁት ስሜት አብሯችሁ አለ

ተወዳጆች ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ሥጋችን ምን እንደሆነና በሥጋችን ምን ማድረግ እንዳለብን ሲናገር እንዲህ ይላል፦

"ሥጋችኹ የክርስቶስ አካል እንደ ኾነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን አካል ወስዳችሁ የአመንዝራ አካል ታደርጉታላችሁን አይገ፟ባ፟ም።

.....ሥጋችኹ ከእግዚአብሔር ለተቀበላችኹት በእናንተ አድሮ ላለ ለመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ኾነ አታውቁምን? ለራሳችኹም አይደላችኹም። በዋጋ ተገዝታችኋልና፤
ስለዚህም እግዚአብሔርን በሥጋችኹ
አክብሩ።" 1ኛ ቆሮ 6÷15-20

ከንባቡ እንደምንረዳው፦
ሥጋችን የክርስቶስ አካል ነው።
ሥጋችን ከእግዚአብሔር የተቀበልነው የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነው። በሥጋችን ደግሞ እግዚአብሔርን ልናከብረው ይገባናል።

እስኪ ንገሩኝ በሥጋችን እግዚአብሔርን የምናከብረው እንዴት ነው

ሀ. አጋንንትን በመምሰል ነው

"አጋንንት ይዘፍናሉ" እንዲል ኢሳ 13÷21

አንድ ሰው ዘፈን ሲዘፍን ሲደንስ አጋንንት ወደ እርሱ ቀርበው ከእርሱ ጋር አብረው ይዘፍናሉ ይደንሳሉ አንድ አባት እንዳየው!

ለ. ቅዱስ ጳውሎስን በመምሰል ነው

"እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" እንዳለው  1ኛ ቆሮ 11÷1

ደግሞም 1ኛ ቆሮ 11÷20 እንዲህ ይላል "በዋጋ ተገዝታችዃልና  ለራሳችኹ አይደላችኹም"

"በዋጋ ከተገዛን እኛ ራሳችን የራሳችን አይደለንም ማለት ነው። እንዲህ ተብሎ በማይነገር፤ ወርቅ ብር በማይመዝነው ቅዱስ ደም የተገዛን የክቡር ጌታ ክቡር ልጆች ነን።"

ክቡር ልጅ እንዴት ክብሩን ጥሎ ክብሩን በሚያሳጣው ቦታ ይገኛል

እንዴት የቅዱሱ ልጅ ርኩስ ከሆኑ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ይዋደዳል

እንዴት የንጉሥ ልጅ ከሥልጣኑ ወርዶ ለአጋንንት እራሱን ባርያ ያደርጋል

ተወዳጆች እንዴት የክርስቶስን አካል ለአጋንንት መጠቀሚያ ታደርጋላችሁ

እንዴት መቅደስ በሆነ ሰውነታችሁ ዘፋኞች ትሆናላችሁ

እንዴት ከተዋረዳችሁበት ከፍ ለማድረግ አምላካችሁ ከበረት እስከ ሞት የከፈለላችሁን ትረሳላችሁ

ተወዳጆች በልባችሁ እንዲህ ብላችሁ ሰይጣንን ተቃወሙት፦ በልደቱ እራሱን በትህትና ለገለጸው ራሴን አዋርጄ ፣ በንስሐ ወደእርሱ ቀርቤ፣ እርሱን በመቅደሴ አመልካለሁ እንጂ ኮንሰርት ብዬ የመቅደሱ ዘፋኝ አልሆንም። ዘፈን ልዝፈን ብዬ የቤተመቅደሱ ዘፋኝ አልሆንም!!!

ምክንያተ ጽሕፈት፦ አብዛኛው የኦርቶዶክስ አማኝ የልደቱን ቀን ከባለልደቱ ጋር፤ ባለልደቱ (አማኑኤል) እንደሚወደው ሳይሆን
ልደቱን ከሚጠላው፤ ሰይጣን በሚወደው መልኩ ከእርሱ ጋር ሰዎች በማክበራቸው ነው።

የእንመለስ ደወል ነው!!!

ጸሐፊ፦ ዳዊት ፍቅሬ

ታኅሣሥ 26 2016 ዓ.ም


#ሼር_ይደረግ!