#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_4
#ማስተማር_የማን_ተግባር_ነው ?
ዛሬ በፕሮቴስታንት ሐይማኖት ውስጥ የሴት ምህራን ወይም ሰባኪያን እያየን ነው ። ግን ማስተማር #የሐዋርያት ተግባር ነበር ። ከዚያም የእነርሱ ደቀመዛሙርት ለሆኑ ፣ ጳጳሳት ዲያቆናት ተግባር ሆነ ነገር ግን ምእመናን አስተምረው አያውቁም ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንኑ ሲያረጋግጥልን "እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዝኀችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ #እያስተማሯችኀቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ። ( ማቴ 28:19) እንደገናም "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ #ስበኩ ። (ማር 16:15) ብሏል ። ጌታችን #ማስተማርን ለሐዋርያት ሥራ አድርጎ ሰጠ እንጂ ይህንን ሥልጣን ለማንም አልሰጠም ። ሐዋርያት ቃሉን ሊሰብኩ ሊያስተምሩ ፣ ሊያገለግሉና እምነቱን ለሌሎች ሊያስተምሩ ተመርጠው ነበር ። ሰባቱን ዲያቆናት በካኑበት ጊዜ ሐዋርያው "እኛ ግን ለጸሎትና #ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን " ብሏል ። ስለ ጌታም ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ "በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን አሁን ግን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቷል ። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ #ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም #አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት ወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋት ወደ ብርሃን አውጥቷል ። (2ኛ ጢሞ 11) በመሆኑም ሐዋርያት ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት እያስተማሩና እየሰበኩ ኖሩ ።
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የማስተማርና የስበከት ተግባር ለደቀመዛሙርቱ አደራ ሲሰጥ ለጢሞቲዎስ " #ቃሉን ስበክ በጊዜውም አለጊዜውም ፅና ፈፅመህ እየታገስህና እያስተማርህ ዝለፍና ገስፅ ምከርም " (2ጢሞ ዠ4:2) አለው ።
በተጨማሪም ለደቀ መዝሙሩ ለቲቶም "ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገስጽም ማንም አይናቅህ " (ቲቶ 2:15) አለው ። ካህናት በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ስለሚያስተምሩ ወይም ስለሚቀድሱ ብቻ አይደለም ። ነገር ግን በንስሐና በመሳሰሉት ሁሉ መንፈሳዊ እንደራሴዎች ስለሆኑ ጭምር መምህራን ሊሆኑ ይገባቸዋል ። ምዕመናን ደግሞ ሁልጊዜ በተማሪዎች ቦታ ሆነው ሊማሩ ይገባል። እምነት ፣ ሥርዓትና ትውፊት በመንፈስቅዱስ የሚተረጎሙ የቤተክርስቲያን ሕይወት ናቸው ። ሰባኪያን በእምነትና በባህል ሃይማኖት ሽፋን የራሳቸውን አመለካከት ሊያስተምሩ አይገባም ። በመሆኑም ካሁን ቡሃላ በተከታታይ በእኛ እና በፕሮቴስታንት መካከል ስላለው ልዩነት በሰፊው እናያለን።
#ሼር
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret

♻️♻️ምስክርነት♻️♻️
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
ክፍል ፯
እማማ የተናገሩት ነገር ገርሞኛል። የሰውየው ሚስት ለመሆኑ ከአሁን በኋላ ምን አስበሻል? አለችኝ ምንም አላሰብኩም ወደዚህ ቤትም የመጣሁት እግሬ ወደ መራኝ በመሄድ ላይ ሳለሁ ባለቤትሽን መንገድ ላይ ስላገኘሁት ለአንድ ቀን አዳር ለምኜ ነው እንጂ ወደ ግሸን ማርያም ለመሄድ የመሸብኝ እንግዳ አይደለሁም። የሚገርማችሁ የግሸን ማርያም መንገድ መሆኑንም ሥላሴ ቤተክርስቲያን ነው የሰማሁት። እማማ መልሰው ከተማ የለመደ አሁን ገጠር ይመቸዋል ብለሽ ነው? አሉኝ እኔም ከዚህ በፊት ለመሞት ወስኜ መርዝ( በረኪና) ልጠጣ ነበር ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ ሁሉም ጮሁብኝ። ሰውየው ምነው አንቺ ፊደልም አልቆጠርሽ? እንዴት እንዴት እንደዚህ ትናገሪያለሽ አለኝ።
ሚስቱ ሁለት እጆቿን በጡቷ ላይ ለጥፋ ልክ አይደለሽም አለሽኝ። ወዲያው አንድ አባባል ትዝ አለኝ "ንጹሕ ስለተለበስ ንጹህ አይታሰብም" "ያደፈ ስለተለበሰም ክፉ አይታሰብም" አልኩ እማማ ለመሆኑ መርዙን ምን አደረግሽው? አሉኝ። እማማ መርዙን ገዛሁት እንጂ ለመጠጣት አልደፈርኩም። ድፍረቱን አጣሁና መርዙን ደፋሁት። እንደገና በገመድ ታንቄ ለመሞት አሰብኩ ግን አልተቻለኝም አልኳቸው። እማማ ለመሆኑ ጤነኛ ነሽ አሉኝ። ለአንቺ ሚያስፈልግሽ ፀበል ነው። ወድያው ሚስትየውም ሆነች እማማ ተራ በተራ ሰውየውን ቀስ እያሉ እያዩት ነበር ለትንሽ ደቂቃ በቤት ውስጥ ዝምታ ሰፈነ ።
ትንሽ ቆይቶ ባልየው ለስለስ እና ባለ ረጋ ባለ አገላለጽ አንቺ ከተመቸሽ እና ሥራው ካልደከመሽ ከዛሬ ጀምሮ የቤቱ አባል ሁኚ ብሎ ፈቀደልኝ። እንደገና የተወልድኩ ያህል ተሰማኝ ። ያለምንም መሳቀቅ የሚሠሩትን እየሰራው የሚበሉትን እየበላሁ የሚጠጡትን እየጠጣሁ በእውነተኛ ቤተሰባዊ ፍቅር ተዋደን ያለምንም መለያየት ሁላችንም በአንድነት ተስማምተን መኖር ጀመርን። ነገሮችን እንዳውቅና በእምነቴ እንድጠነክርና ስተኛሽስነስ ፀሎት ማድረግ እንደሚገባኝ ሁሉ አስረዱኝ።
ከእማማ ጋር የእናትና የልጅ ያህል ተቀራረብን ስለ እግዚአብሓር ፈጣሪነት መሐርነትና አዳኝነት የቻሉትን ያህል አሳውቀውኛል። በተለይ በመንፈሳዊ ህይወቴ በጣም ደካማ ስለነበርኩ የማላውቃቸውን ነገሮች እንዳውቅ በእምነቱ እንድጠነከር አደረጉኝ።
የሥላሴ ቤተክርስቲያን እኛ ከምንኖርበት ቤት ቢርቅም ዓመታዊ በዓል ሲሆን በጥር ሰባት (ሕንጻ ሰኖኦር በነፋስ ኃይል የፈረሰበት ዘፍ ፲፩፣፩-፲) እንዲሁም በሐምሌ ፯ ታቦት ይወጣል። ከደረስን አስቀድሰን ካልደረስን ግቢው ውስጥ አረፍ ብለን ቤተክርስቲያኑን ተሳልመን እና ፀሎይ አድርሰን እንመለሳለን። አንድ ቀን ተሳልመን ከግቢው ስንወጣ "መዝገበ ፀሎት" የሚባል መጽሃፍ በሩ ላይ ሲሸጥ አይቻ ገዛው እማማም ደስ አላቸው። ታድያ ማታ ማታ ይሄንን የጸሎት መጽሐፍ ሳነብላቸው ሁሉም በተመስጦ ያደምጡኝ ነበር። እኔም ብዙ ትምህርት አገኘሁበት ። በመሸ ቁጥር ሁሌም አነብላቸዋለሁ ከልብ ያደምጡኛል። አንብቤ ስንጨርስ ፀልየን ነበር ምንተኛው።
ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከእማማ ጋር ስሄድ እሳቀቃለሁ። ምክንያቱም ስለምሸታቸው እየዞሩ ሁሉ ያዩኛል ይሰድቡኛል። ታድያ አንድ ቀን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተሳልመን ከእማማ ጋር ቁጭ ብለን ሳለ ጀርባዬን የሆነ ነገር ሲመታኝ ተሰማኝ ዞር ስል አንድ ጎረምሳ እግሩን ፍርክክ አድርጎ ከኋላችን ቁጭ ብሏልም አይቼ እንዳላየ ዝም አልኩት። በድጋሜ ድንጋይ ወርውሮ ሊመታኝ ሲል ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን ወድያው ምን አጠፋሁ? ለምን ትመታኛለህ አልኩት። ዘብነን ብሎ ለምን ሰውነትሽን አትታጠቢም አንቺን የመሰለች ሴት እንዴት እንደዚህ ትገማለች አለኝ ደነገጥኩ።
ይቀጥላል።
👉 📩 @zetaodokos
#አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁት_SHARE_በማድረግ_አግዙን።
#አብሮነታችሁ_ያበረታናል።
👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret

ክፍል ፰
እማማ ከአጠገቤ በፍጥነት ብድግ ብለው የሚመረኮዙበትን መቋሚያ ጭብጥ አድርገው በመያዝ ግንባሩን ሊፈጠርቁት ሲሰነዝሩ ርጦ አመለጠ። ወዲያው እማማ ምን አባቱ ይላል ይሔ መናጢ ሰው የላትም ብሎ ነው እንዲህ መናገሩ ብለው አባረሩት። ከዚህ በኋላ እማማ ከእግዚአብሔር ዘን የተሰጡኝሽልዩ ስጦታዬ ናቸው ብዬ አመንኩ። እግዚአብሔርን አመሰገንኩት።
ወደዚህ ቤት ከመምጣቴ በፊት የሆቴሏ ባለቤት የነገረችኝን ለእማማ ነግርኳቸው። መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ሰሚ ነው ሒጂና በፀበሉ ተጠመቂ። ዑራኤል ተዓምረኛ ታቦት ነው አልኳቸው። ይህ ቤተክርስቲያን የት ነው የሚገኘው? እና የሚውልበት ቀንስ መች ነው ስላቸው በ ፳፪ እንደሚውል በጥር 22 እና ሐምሌ 22 ደግሞ ዓመታዊ በዓሉ እንደሆነ አውቃለሁ የት እንዳለ ግን አላውቅም። ልጄን ጠይቄ እነግርሻለሁ አሉኝ።
አንድ ቀን ማታ ቤት ውስጥ ሁላችንም ተሰብስበን የባቄላ አሹቅ እየበላን እሳት በመሞቅ ላይ ሳለን የእማማ ልጅ የቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ውስጥ መገናኛ ወይንም 22 ማዞርያ የሚባል ሰፈር ስትደርሺ ማንም ሰው ብትጠይቂ ያሳይሻል አለኝ። በጣም አመስግኜ ጸሎታችንን አድርሰን ተኛን። ሌሊቱን ሙሉ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን እንዴት እንደምሄድ ሳወጣና ሳወርድ አደርኩ። ሲነጋ በሉ እማማ ቤተክርስትያኑን ፈልጌ ተጠምቄ እመጣለሁ ስላቸው በይ ለእኔም ጸበል እምጪልኝ ብለው ፭ሊትር ጄርካን ሰጡኝ። ሚስትየውም በይ ለእኔም እምነት አምጪልኝ አለሽ። ባልየው ደግሞ ይህ መሳፈርያ ይሁንሽ ብሎ 50 ብር ሰጠኝ ላለመቀበል ብግደረደርም እማማና ሚስቱ ተቆጡኝ በእርግጥ ብሩም ያስፈልገኝ ነበር ገንዘቤ አልቆ 20 ብር ብቻ ነው የቀረኝ። ይህ ሰውዬ እንዴት ብሩን እንደሚያመጣው አውቃለሁ በዚህ ቤትም ውስጥ ይህ ብር ብዙ ነገር ይሰራል። ይህን ብር ሲሰጠኝ ከሕጻን ጉሮሮ ነጥቆ ለእኔ እንደማጉረስ ያህል ቆጠርኩት። አመስግኜ ተቀበልኩ።
ዕለቱ ጥር 22 ቅዱስ ዑራኤል ለበር በጥዋት ከቤት ወጥቼ መንገድ ጀመርኩ። አውቶብስ ተራ ገብቼ የአዲስ አበባን መንገድ በሎንችና ጀመርኩት።
ይቀጥላል
#አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁት_SHARE_በማድረግ_አግዙን።
#አብሮነታችሁ_ያበረታናል።
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret

የመጨረሻ ክፍል
ጌታዬ ሆይ በፊትህ መቅረቤን እንደ ዋጋ አድርገህ ተቀበልልኝ ከኔትህ በረከትን ተቀበልልኝ ከቤትህ በረከትን ጠግቤ ነቀፈታዬ ተወገደልኝ ብዬ ስለተደረገልኝ ነገር እንድመሰክር ስላበቃኸኝ በእናትህ በድንግል ማርያም ፣ በታዛዥህና በአገልጋይህ በመልዐኩ በቅዱስ ዑራኤል ልመናና ጸሎት ዘወትር ለአፍታ ያለአንተ መኖር እንደማልችል አውቄዋለሁና ከአሁን በኋላ ካንተ ጋር ለመኖር ለራሴ ቃል ገባሁ። እኔስ ከሚዘገንነው በሽታ በድንቅ ጥበብህ ፈወስከኝ "እኔ በእግዚአብሔር አዳኝነት እተማመናለሁ" መዝ ፲፩፣፩
አንተ ስትምረኝ ቤተሰቦቼ እጃቸውን ዘርግተው ተቀበሉኝ "አንተ ስላዳንካቸው የሚወዱህ ሁሉ ዘወትር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ይበሉ" መዝ ፵፣፲፮። የሰው ልጅ በሥጋዊ ህይወቱ ሲኖር ሥራ ያስፈልገዋልና ከምወደው መ/ቤት አፍሬ ብጠፋም ደፍሬ እንድገባ ያደረከኝ ጌታ የጠፋ ፍቅራቸውን መልሰው እንዲቀበሉኝ አድርገኸኛልና አምላኬ ሆይ አመሰግናለሁ።
የሰው ልጅ በህይወቱ ሲኖር ብዙ ነገሮች ያስፈልጉታል። አንዱ ይጎልበት እና እግዚአብሔርን እንዲሰጠው ይጠይቃል። እግዚአብሔርም ሰው አፍቃሪ ይልቁንም የጎደልንን አውቆ ሳንለምነው የሚሞላልን የሚያስፈልገንን ገና ሳንጠይቀው የሚያዘጋጅልን አምላል ስለሆነ ከጠይቅነውና ካሰብነው በላይ መስጠት የባህርይው ነውና ለእኔም የብዙ ጊዜ ህመሜን በአንድ ቀን ንይቅሎ ጥሎ ጤናማ አደረገኝ። ሥራ አጥቼ የሰው እጅ እንዳላይ ከነበረኝ ደመወዝ ላይ ተጨምሮልኝ ያልሠራሁበት ተከፍሎኝ በነበርኩበት መ/ቤት እንድሠራ ያደረገ ጌታ እግዚአብሔር ነው። ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል።
በቅዱስ ዑራኤል ቤተ/ን ምስክርነቴን ተናግሬ እንደጨረስኩ የቅዱስ ዑራኤልን ሥዕል ከጽጌረዳ ጋር ሆነን ፈልገን ገዛን። በቀጥታ ወደቤት ሄድን በሳሎን በር አንኳኩተን ወደ ውስጥ ልንገባ ስንል በአንድ ድምጽ ሁሉም ጮኸው ከተቀመጡበት ተነስተው ግር ብለው ወደኛ ሮጡ በየተራ አቅፈው ሳሙኝ።
ለቤተሰቦቼ የበፊት መ/ቤቴ ነገ ሥራ እንደምጀምት ስነግራቸው ሁሉም ደስተኞች ቢሆኑም አባቴ ግን ትንሽ እረፍት ብታደርጊ ጥሩ ነበር ሰውነትሽ ተጎድቷል አለኝ። እኔን እንድሰራ የፈቀደ እግዚአብሔር ነው ነገሮችን አስተካክሎ የጠበቀኝ እርሱ ስለሆነ ካሁን በኋላ እንደራሴ ሃሳብ ሳይሆብ እንደእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃድ መመላለስን መርጫለሁ አልኩት። አባቴም እውነትሽን ነው ብሎ አቅፎኝ እያለቀሰ ከአሁን በኋላ አልበድልሽም አለኝ እኔም አባበልኩት። የደስታችን ተካፍይ ለመሆን ከመጡት ጎረቤቶቻችንና ዘመዶቻችን መሃል እናቴ ተቀምጣ ለልጄ መጥፋት እኔ ነኝ ተጠያቂ እያለች እራሷን ትወቅሳለሽ። እንዲሁም ታቦታትን እየጠራች ምስጋና ታቀርባለች።
እኔና ጽጌረዳ ወደ እኔ መኝታ ቤት ገባን ጸሎት አድርገን እንደጨረስን ጋደም አልን። ፅጌረዳ አንድ አዲስ ነገር ለመንገር እንደፈለገችና ለመናገር ግን ድፍረት እንዳጣች ደጋግማ ነገረችኝ ።
ይሄን ሳልነግርሽ በመቆየቴ መቼም አትቀየሚኝም ደግሞ መንገር ስላለብኝ ነው። አሳመነች ትዝ አለች አለችሽ አለችኝ እኔም ትንሽ አሰብ አደረኩና አዎ ትዝ አለችኝ አልኩ በርግጥም አሳመነች በአንድ መ/ቤት የምንሠራ ብንሆንም ለእና ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም ጥሩ ያልሆነ ስሜት ነበራት። እኔ ባለሁበት ቦታ መምጣትም መገኘትም አትፈልግም ብዙ ጊዜ ለምን እንደማትወደኝ ለማወቅ ሞክሬ ነበር። ጽጌረዳም ንግግሯን በመቀጠል አሳመነች አንቺን ለመጥላት የነበራት ምክንያት ተልካሻ ነበር እጮኛዋ ሳምሶንን በአንቺ ትጠረጥረው ነበር። እርሱ አንቺን ያከብርሻል ያደንቅሻል ለእሷ ይሄ በውስጧ ሌላ ነገር ፈጥሮባታል ስለዚህ ሁሌ ላንቺ ጥሩ አመለካከት አልነበራትም ። ሰዎች ሲያመሰግኑሽ ስትሰማ እበጂ እበጂ ይላት እንደነበር ትነግረኝ ነበር። ግን ቦታ አልሰጠውም ነበር አንቺ ስራውን ትተሽ ከጠፋሽ በኅላ እርሷም በጣም ታማ ነበር ከመሥሪያ ቤት ስዎች ጋር ተሰብስበን ለመጠየቅ ቤቷ ስንሔድ እሷ አትመስልም እንዴት ገርጥታለች መሰለሽ።ፀጉሯ ጭብርር ብሎ ከንፈሯ ከብት መስሎ ብቻዋን ትለፈልፉለች።ያንን ዓይኗን እያጉረጠረጠች ትሳደባለች። ሰገራውን እንዳታነሺው ደግሞ የአንቺን ስም እያነሳች አንቺ ግን አንሺው እያለች ትጮህ ነበር ግን የሚገርመው ረዥም ጊዜ ታማ ተሰቃይታ ሞተች ብላ አረዳችኝ።
በነጋታው አረፋፍደን ቢት ገባን እንደድሮ ዘው ብሎ ገብቶ ወንበር ላይ መቀመጥ ቀረ አማትቤ ጸልዬ እንጂ። ማታ ላይ ደብረብርሃን ስለገጠመኝ ነገር ለቤተሰቦቼ ተናግሬ ደብረብርሃን እንደምንሄድ ነገርኳቸው። በነጋታውም ጉዞ ጀመርን። ከሩቅ እማማን አየኋቸው በጣም ደስ አለኝ ሮጬ ተጠመጠምኩባቸው እኔ መሆኔን ሲያውቁ አቅፈው ሳሙኝ አቶ ደመርና ባለቤቱ ውብዓለምም ወጥተው ተቀበሉኝ ሁሉንም ሳምኳቸው ከቤተሰቦቼ ጋር አስተዋወቋቸው። አቶ ደመረ ጠቦት አርዶልን በልተን ጠጥተን እንደለመድነው ጸሎት አድርሰን ክቡር
። በነጋታው ለእማማና ለውባለም ያመጣሁላቸውን ጸበልና እምነት ሰጠኋቸው። አቶ ደመረ የነበረኝ ገንዘብ አልቆ ምንም ባልነበረኝ ጊዜ መሳፈርያ ትሁንሽ ብለህ የሰጠኸኝ 50 ብር እነሆ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብዬ ስመልስለት አልቀበልም አለኝ ። በግድ ተለማምጬና ተቶጥቼ ሰጠሁት። በመቀጠል ቤተሰቦቼ የእነማምን ቤተሰብ እንዲመርቅ ጋበዝኳቸው ። አባዬ እማዬ ወንድሜና እህቴ መርቀው ከጨረሱ በኋላ እኔም የድርሻዬን እንዲህ አልኩ ። በቅድሚያ አቶ ደመረን ምክንያቱን በመንገዱ ላይ ተገናኝተን ማደርያ ስጠይቅ ያለምንም ማቅማማትና ማንገራገር ቤት የእግዚአብሔር ነው ብሎ ወደ ቤቱ አምጥቶ እንድኖር ስለፈቀደልኝ። በመቀጠል ውብዓለም አንድም ቀን ሳታስከፋኝ ተፈቃቅረን ተዋደን እንድንኖር ስለፈቀድሽልኝ ከልቤ አመሰግንሻለሁ እግዚአብሔር ያሰብሽውን ሁሉ ይፈጽምልሽ ። በመጨረሻ እማማ ለእኔ በዚህ ቤት ከገባሁ ጀምሮ ከእግዚአብሔር የተሰጡኝ ስጦታዬ ኖት አሁንም ፈጣሪ ረዥም እድሜ ይስጥልኝ ። በዚህ ቤት ያገኘሁት ፍቅር በገንዘብ ሚተመን አይደለም። ቢሆንም ግን በዚህ ቤት የነበርኩበት ዓመታት ሥራ እንደሰራው ተደርጎ የ 2 ዓመት ከ 6 ወር ደመወዝ ታስቦ 30,000 ብር ተሰጥቶኛል ይህ ብር እንዲከፈለኝ ያደረገ እግዚአብሔር መሆኑን አውቃለሁ። ይህ ብር የተሰጠኝ ሥራዬን ሰርቼ ሳይሆን በዚህ ቤት ሆኜ ነውና ይህ ብር ሚገባው ለናንተ ነው ስለሆነም አቶ ደመረ ብሩን ከአባቴ እጅ እንዲረከቡ በትህትና እጠይቃለሁ አልኩ።ሁሉም እንግዳ ሆኖባቸው ግር ብሏቸዋል ። አባቴ ብሩን ሲያስረክብ ሁላችንም እግዚአብሔር ይመስገን የሚለውን መዝሙር ዘመርን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
#አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁት_SHARE_በማድረግ_አግዙን።
#አብሮነታችሁ_አይለየን።
👇👇👇
ምስክርነት
ዲያቆን ጌትነት ፍቅሩ
ታህሳስ 2004 ዓ.ም ተጻፈ።