✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
28.3K subscribers
91 photos
7 videos
49 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
#እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡

ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

    ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
💚@Orthodox_tewahdo_nen
💛@Orthodox_tewahdo_nen
❤️@Orthodox_tewahdo_nen
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

✍️comment @tomi8019
ጥር 5/2016 #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (የለዉጥ በዐል)

👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ #የልደታቸዉ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጥር 5 በዚህች ዕለት #የአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ #የለውጥ_በዓል ነው ትውልድ ሀገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው

👉የአባታቸው ስም #ቅዱስ_ስምዖን እናታቸው ቅድስት #አቅሌስያ ይባላሉ ወላጆቻቸው #በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች

👉ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም #እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ የሚል ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ #መልከፀዴቅ ንጽሕናው እንደ #ነቢዩ_ኤልያስ እንደ መጥምቁ #ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ አሏት

👉ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡

👉ቅድስት #አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ ወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን አላት

👉ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ ዳግመኛም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ #ለአብ_ለወልድ_ለመንፈስ_ቅዱስ ምስጋና ይሁን አለ

👉 #የአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በዓለ ልደት ታህሳስ 29 #በጌታችን_ልደት ነው ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ #ቅዳሴ ይገባሉ

👉ስለዚህ #የአባታችን_አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ በዐል ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋልና በዓለ #ልደታቸው በዚህች ቀን ተከብሮ ይውላል

👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸዉ #ብርሐናተ_አለም_ቅዱስ_ጴጥሮስና_ጳዉሎስ ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ጥር 18/2016 #ዝርወተ_አፅሙ_ለቅዱስ_ጊዮርጊስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ እጅግ አሠቃቂ በሆኑ ብዙ መከራዎች እያሠቃየ ሦስት ጊዜም ቢገድለው ጌታችን ግን ቅዱስ #ጊዮርጊስን ከሞት እያስነሣው ከሃድያንን ያሳፍራቸው ነበር

👉ንጉሥ ዱድያኖስ የሚያደርገው ቢያጣ ጭፍሮቹን በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት ብሎ አዘዛቸው ጭፍሮቹም የቅዱስ #ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ #ጊዮርጊስ_ቅዱሱ_ለእግዚአብሔር ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል

👉አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን
ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና #ቆዩኝ_ጠብቁኝ አላቸው እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ
እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት #አምላኬ_ከሞት_አዳነኝ አላቸው

👉ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ‹‹ይቅር በለን›› ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት ቅዱስ #ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን
ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን #በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል

👉 #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ #በደብረ_ይድራስ_ተራራ ላይ የተበተነው በዚህች በጥር 18 ዕለት ነው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም
አገልጋይ ብርቱዉንም ደካማዉንም ፍጥረት ኹሉ ፈጥነህ የምትረዳ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሆይ እንደ እመቤትህ ቅድስት ድንግል ማርያም አንተም ከበቀልና ቂም የተለየህ ርኅሩኅ ልብና ለሰዎች ኹሉ የምታዝን ደግ ሰማዕት ነኽ

👉አማላጅነትህን በመታመን ለሚጠራህ ኹሉ ከነፋስ ዐውሎ ይልቅ ፈጥነህ የምትደርስ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ የርሕሩሕ አምላክ #እግዚአብሔር ርህራሄን ተጎናጽፈኻልና በዚህ ሰአት በጭንቅ ያሉ የወዳጆችህን ልመና ስማ

👉ኅዘንን የምታረጋጋ አባቴ ፍጡነ ረድኤት ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሆይ ለጠላት መሣቂያ ለጠላቶቻችን መዘባበቻ እናድንሆን በገዳም ያሉ የእናቶቻችንን የአባቶቻችንን የጩኸት ድምፅ ሰማ

👉ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ ሰባው ነገሥት ስለ #ክርስቶስ ሰለመሠከረ አካላቱ እየቆራረጡ በሥጋው የአሠቃዩት የልዑል #እግዚአብሔር ወታደር ፍጡነ ረድኤት ኃያል ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ እንሆ የተጋድሎ ዝናውን ስንሰማ ግርማ
ሞገስህ ከሰማዕታት ኹሉ ይበልጣል

👉ለሰባት ዓመታት ትእግሥትን በማዘወተር አስጨናቂዎች መከራዎችን ለተሸከመ ትከሻህ ሰላምታ የሚገባህ የአስጨናቂዎች የሥቃይ ሰባት ዓመታትን የታገሥህ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ የድል በተርህን ይዘህ ኹልጊዜ እደሚገሰግስ አርበኛ የኢትያጵያ ጠላቶች ትመታልን ዘንድ ፈጥነህ ገሥግሰህ ናልን

👉አቤቱ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ አምላክ እዘንልን ራራልን ይቅርም በለን የሰማእቱ ረድኤትና በረከት አይለየን ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
የካቲት 18/2016 #ፆመ_ነነዌ

👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆም እና በፀሎት ለምንማፀንበት ሀገር እና ህዝብ ከጥፋት ለዳኑበት ትንሽ ቀን ሆና በስራዋ ግን ታላቅ ታምር ለተፈፀመባት #ፆመ_ነነዌ እንኳን አደረሰን

👉ነነዌ ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ፆሙ ሶስት ( 3 ) ቀን ብቻ ነው ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ናቸው #የነነዌ_ፆም በመባቻ ሐሙስ( አቆጣጠር ) ከፍ እና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል ።

👉እናም የ2016 #ፆመ_ነነዌ የካቲት 18 ሰኞ ይጀምራል የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ፆም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በፆም ምክንያት #እግዚአብሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትንና ኃጢያትን ስላለ የነነዌ ሕዝብ ይቅር ያልክ አምላክ ዛሬን #ይቅር_በለን ለማለት ነው

👉የነነዌ ሰዎችም #እግዚአብሔርን አመኑ ለፆም አዋጅ ነገሩ ከትልቁም ጀምሮ እስከ ትንሾቹም ማቅ ለበሱ ወሬውም ለነነዌ ንጉስ ደረሰ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናፀፊያውን አውልቆ #ማቅንም_ለበሰ_አመድ ላይም ተቀመጠ አዋጅንም አስነገረ

👉በነነዌም ውስጥ የንጉሱንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ እንዲህም አለ #ሰዎችም_እንስሶችም አንዳችም እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ ሰዎችና እንስሳትም #በማቅ ይከደኑ ወደ #እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።

👉እኛ እንዳንጠፋ #እግዚአብሔር ተመልሶ ይፀፀት እንደሄነ ከፅኑ ቁጣውስ ይመለስ እንደሆነ ምን ይታወቃል በማለትም አሳሳበ #እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውም እንደተመለሱ በስራቸውም አየ #እግዚአብሔር_አምላክም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተፀፀቶ አላደረገውም ት;ዮናስ 3፤5-10

👉 #የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸሩ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንንም በምህረት አይኑ ይጎብኝልን ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙንም ለጥያቄያችን መልስ የምናገኝበት የበረከት ፆም ይሆንልን ዘንድ የአምላካችን #ቅዱስ_ፈቃድ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 6/2016 #ፆመ_ኢየሱስ_6ኛ_ሳምንት_ገብርሄር

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የአብይ ፆም 6ኛ ሳምንት #ገብርሔር :- ገብር ማለት አገልጋይ፣ሔር ማለት ቸር ማለት ነው

👉በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 25 እንደተገለጸው ቸሩ ፈጣሪ እራሱን እንደ ባለፀጋ ሰይሞ ለሶስት ሰዎች #መክሊት ፀጋና በረከት እንደሰጣቸውና አንድ መክሊት የተሰጠው አንተ ያልዘራኸውን የምታጭድ ጨካኝ መሆንህን ስለማውቅ ደብቄ ያቆየሁትን መክሊትህን እንካ አለው

👉የተሰጠንን ፀጋ በተለይ ካህናት አብዝተን ለጌታ መመለስ እንደሚገባን ሲያስተምረን አንተ በትንሽ ያልታመንክ እንደሌሎቹ አብዝተህ እንኳን ልትሰጠኝ ባትችል ለለዋጮች አደራ ሰጥተህ ልታተርፈው ትችል ነበር አለው  ስለዚህ #መክሊቱን ውሰዱበት  አስር መክሊትም ላለው ስጡት ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታልና

👉ምዕመናን ከዚህ ምን እንማራለን #እግዚአብሔር በሰጠን ፀጋ ጤንነትና እውቀት ተጠቅመን በዚህ ዐቢይ ፆም የሰራዊት ጌታ የሚወደውን መልካም በጎ ምግባር ብቻ አብዝተን በመስራት ፈጣሪን ማስደሰት እንደሚገባን ያስተምረናል

👉እርሱ የሚያተርፈው ይህን ጊዜ ብቻ ነው ሌላውማ ምን ቸግሮት ስለሆነም በአንቃድዎ ልቦናና በሰቂለ ህሊና ትኩረታችንን ወደ ጌታ መልሰንና በንስሐ ታጥበን ሁል ጊዜ ልንፀልይና ልንሰግድ ይገባናል  ቸሩ አንድ አምላክ ለሰው ዘር በሙሉ ምህረቱንና ረድኤቱን ይላክልን እኛም የተሰጠንን #መክሊት አትርፈንበት ታማኝ አገልጋይ ተብለን በጌታችን ታምነን የክብሩ ወራሾች እንድንሆን አምላካችን ይፍቀድልን "አሜን"

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 13/2016 #የፆመ_ኢየሱስ_7ኛ_ሳምንት_ኒቆዲሞስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለፆሙ 7ኛ ሳምንት #ለኒቆዲሞስ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

"ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል"

1ኛ.ኢትዮጵያዊ በተወለደበት መንደሩና አፉን በፈታበት ቋንቋው እየተፈረጀ አንተ ከየት ነህ እየተባለ በሚፈናቀልበትና በሚገደልበት ባለሥልጣን የሆናችሁት አለቆች

2ኛ.በሰው ሠራሽ ችግር ብዙ ወገን ትናንት ሰጪ ዛሬ ለማኝ በሆነባት፤ ወደ ሀብት ተጉዛችሁ ሳይሆን እሱ ራሱ ሀብት ድንገት ደርሶባችሁ በድንገቴ ሀብታም የሆናችሁ ባለፀጎች

3ኛ.ያለ ጥም ቆራጭ እውቀታችሁ ራሳችሁን አዋቂና ምሁር ስታደርጉበት ሕዝቡ ምሁራን እያለ የሚጠራችሁ የሀገሬ ምሁራን ሁላችሁ

👉በዛሬው ዕለተ #ሰንበት_ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል ወደ እሱ ባትመጡ እንኳን እስኪ እንደው አንድ ጊዜ ባላችሁበት ሁኑና ስሙት

👉እኔ ሦስት ነገሮች የተስማሙልኝ ሰው ነበርኩ ሀብት ሥልጣን ዕውቀት ይሁን እንጂ ጎዶሎ ነበርኩ

👉ጎዶሎዬም #እግዚአብሔር ነበር እሱን የምሞላበት ጊዜ ስፈልግ የራሴን ጊዜ የምተኛበትን እረፍተ ሥጋ የምወስድበትን ጊዜ አገኘሁ እናም ይኼንን ጊዜ ሰዋሁና በጨለማ በሌሊት ከጌታዬ እግር ሥር ቁጭ ብዬ ጎዶሎዬን ሞላሁት

👉ይገርማል ወደ #እግዚአብሔር ስንቀርብ ያለን ምድራዊ ሀብት ሥልጣንና ዕውቀት ሁሉ የሚወሰድብን ይመስለናል ግን እንደምናስበው አይደለም

👉እኔ ራሴ ሦስቱን ምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ይዤ መጥቼ ሦስት ዘላለማዊና ሰማያዊ ስጦታዎችን ነው ይዤ የተመለስኩት

1ኛ. ምድራዊ ሥልጣን ነበረኝ የሥላሴ ልጅ የመሆን ሥልጣን ገንዘብ አደረኩኝ፤ የጌታዬን ቅዱስ ሥጋ ለመገነዝም በቃሁ

2ኛ. ምድራዊ ሀብት ነበረኝ ሰማያዊዉን የፀጋ ልጅነት ሀብት ርስተ መንግሥተ ሰማያትን የማግኘት ሀብት የዘላለማዊ ሕይወት ሀብት አግኝቼ ተመለስኩ

3ኛ. ምድራዊ ዕውቀት ነበረኝ ያውም የብሉይ ኪዳን ወደ ጌታዬ ስመጣ ግን ምሁረ ሐዲስ ሆንኩኝ #ምሥጢረ_ሥላሴን ምሥጢረ ጥምቀትን ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን የማወቅ ፀጋ ተጨመረልኝ ይላችኋል

መልካም ዕለተ ሰንበት
❖ ኒቆዲሞስ ❖

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥