✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
30.1K subscribers
91 photos
7 videos
50 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
ጥር 5/2016 #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (የለዉጥ በዐል)

👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ #የልደታቸዉ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጥር 5 በዚህች ዕለት #የአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ #የለውጥ_በዓል ነው ትውልድ ሀገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው

👉የአባታቸው ስም #ቅዱስ_ስምዖን እናታቸው ቅድስት #አቅሌስያ ይባላሉ ወላጆቻቸው #በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች

👉ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም #እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ የሚል ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ #መልከፀዴቅ ንጽሕናው እንደ #ነቢዩ_ኤልያስ እንደ መጥምቁ #ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ አሏት

👉ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡

👉ቅድስት #አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ ወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን አላት

👉ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ ዳግመኛም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ #ለአብ_ለወልድ_ለመንፈስ_ቅዱስ ምስጋና ይሁን አለ

👉 #የአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በዓለ ልደት ታህሳስ 29 #በጌታችን_ልደት ነው ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ #ቅዳሴ ይገባሉ

👉ስለዚህ #የአባታችን_አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ በዐል ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋልና በዓለ #ልደታቸው በዚህች ቀን ተከብሮ ይውላል

👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸዉ #ብርሐናተ_አለም_ቅዱስ_ጴጥሮስና_ጳዉሎስ ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​መጋቢት 29/2016 #በዐለ_ደብረ_ዘይት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የዘንድሮው #ዘመነ_ዮሐንስ መጋቢት 29 አምስት በአላት አንድ ላይ ዉለዋል

1ኛ ዕለተ ሰንበት
2ኛ ደብረ ዘይት ዕለተ ምፅዓት
3ኛ በዓለ ፅንሰት
4ኛ ዓለም የተፈጠረበት
5ኛ ጥንተ ትንሣኤ

👉ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን #ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም ማቴ፤24፣36)

👉 ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማንም አያውቅም ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣ዕለቱ ዕለተ እሑድ፣
ሰዓቱ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ቢታወቅም ብዙ ዘመነ ዮሐንስ፣ ብዙ ዕለተ እሑድ፣ብዙ መንፈቀ ሌሊት አለና ስለዚህ አይታወቅም የሰማይ #መላእክትም አያውቁትም

👉ልጅም አያውቀውም ማለቱ ልጅ ያለው ማንን ነው ከተባለ ፍጥረታትን ሁሉ ማለቱ ነው ኦሪት ዘልደት ሲል ኦሪት ዘፍጥረት ማለት እንደሆነ ሁሉ ልጅም ቢሆን አያውቅም የሚለው ቃል #መላእክትም ሌሎች ፍጥረታትም አያውቁም ማለት ነው

👉 #ከአብ በቀር የሚያውቃት የለም ማለቱ "በቀር" የሚለው ቃል ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም ይህን የመሰለ አገላለፅ 1ኛ ጢሞ፤1፣17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘለዓለም ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሁን አሜን የሚል ቃል አለ

👉በዚህ አገላለፅ "ብቻውን" ስላለ አምላክ "አብ" ብቻ ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ብቻውን የሚለው ከፍጥረታት ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ምክንያቱ #ሥላሴ በአብ፤ልብነት ያስባሉ በወልድ፤ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ፤እስትንፋስነት ለዘለዓለም ይኖራሉ

👉 #አጋዕዝተ_ዓለም_ሥላሴ ፤የአለምን መጨረሻ በአብ ልብነት ያውቃሉ፤ በወልድ ቃልነት የሚነገርበት ጊዜ ሲደርስ ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ጊዜው ሲደርስ ዓለምን ያሳልፋሉ ማለት ነው።

👉ሞት በሰዎች ትከሻ ላይ የተሰየመ ነውና ምጽዓተ ክርስቶስን ብቻ አንጠብቅ ሞት ለሰው ልጅ ዕለተ ምጽዓት ነው ምክንያቱም ከሞት በኋላ ጽድቅ ሥራ መሥራት፣መፆም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ ንስሐ መግባት፣ አይቻልምና ስለዚህ ሁል ጊዜ ከኃጢአት ርቀን ሕጉን ጠብቀን ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ለመኖር ጌታችን ይርዳን

👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት ለእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ #ገብርኤል የጌታን መፀነስ የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል

👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው

👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍፁም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና

👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #መጋቢት_ሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥