STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
A message by JIGJIGA UNIVERSITY about GERD
#Itismydam
#GERD
#Ethiopia

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ሰበር ዜና

#Ethiopia : አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት ኢ/ር ታከለ ኡማን በመተካት ወ/ሮ አዳነች አበቤ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ በመሆን ከሰአት በኃላ በአዲስ አበባ ምክር ቤት ይሾማሉ

©natnael mekonen

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Ethiopia : ከአዲስ አበባና ባህር ዳር ባለ ቀይ መለዮ ለባሽ ኮማንዶዎችን የያዙ ሂሊኮፕተርና አንቶኖቭ አውሮፕላን መቀሌ አርፈዋል::

#SHARE #FORWARD

@NATIONALEXAMSRESULT
Update

#Ethiopia : ሰራዊቱ መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎችን ያዘ!

የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ።

የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ ለመከላከያ ሰራዊት ወገንተኝነቱን አሳይቷል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲቀየህ፣ ማይመሳኖን እና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ሃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አድርጓል። የህወሃት ጁንታ በሰላም እጁን እንዲሰጥ መንግስት የሰጠውን የ72 ሰዓታት ጊዜ ሊጠቀም ባለመቻሉ ከትናንት ጀምሮ የህግ ማስከበር ስራው ቀጥሏል።

በመከላከያ ሰራዊት ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ የህግ ማስከበር ሂደት በውጤታማነት ቀጥሎ ተጨማሪ የትግራይ ክልል ከተሞችን ከጁንታው ታጣቂ ነፃ ማድረግ ተችሏል። በዚህም በአድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሰራዊት ሃውዜን፣ አብርሃ ወአፅበሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ ሲሆን አጉላን በግማሽ ቀን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በመቀሌ አቅራቢያ ወደሚገኘው መሰቦ ተራራ እየገሰገሰ ሲሆን ይህም መቀሌን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ጠቁመዋል። በሁለተኛው ግንባርም በአዲግራት በኩል ሳንቀጣ እና አልነጃሺን በመቆጣጠር ውቅሮ ገብቷል። በሶስተኛው የራያ ግንባር ደግሞ አዲቀይህን የተቆጣጠረ ሲሆን ሄዋናና በመቆጣጠር ሁሉንም ምሽጎች ሰባብሮ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የመከላከያ ሰራዊቱ የራያ ግንባር ሒዋነ ከተማን ከጁንታው እጅ ማስለቀቁን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡

#Ethiopia : ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ የጁንታው ቡድን ወደ ዐዲ ጉደም መሸሹን ተናግረዋል፡፡
ሰራዊቱ አካባቢውን በተቆጣጠረበት ወቅት የጥፋት ሃይሉ ይጠቀምባቸው የነበሩ 6 ታንክ እና ሁለት ዙ23ን ጨምሮ በርካታ መሳሪያዎች መደምሰሳቸውንም ነው የተናገሩት፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ አስቸጋሪ መልክዓ ምድሩን በብቃት በማለፍ የጁንታውን ቡድን መደምሰሱንም አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሰራዊቱ የጥፋት ሃይሉ ሲሸሽ ያወደማቸውን ድልድዮችና መሰረተ ልማቶች እየጠገነ በጁንታው ቡድን ላይ ድል ማስመዝገቡንም አውስተዋል፡፡ አሁን ላይ ሰራዊቱም ወደ መቐለ የሚያደርገውን ግስጋሴ መቀጠሉን ጠቅሰው ሰራዊቱ ከተማዋን በአጭር ጊዜ እንደሚቆጣጠርም ገልጸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Good news

#Ethiopia : በትግራይ ክልል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች በትግራይ ክልል በቀጣይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መክረዋል።ለናሙናነት በተካሄዱ የመስክ ምልከታዎች እንደተረጋገጠው በክልሉ የሚገኙ የትምህርት መሠረተ-ልማትና ግብዓቶች በህወሃት የጥፋት ቡድን ጉዳት እንደደረሰባቸውና እንደተዘረፉ ለመመልከት መቻሉን ሚንስቴር መስሪያቤቱ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።የመማር-ማስተማር ሥራው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የክልሉ መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ አረጋግጠዋል።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ዶክተርም ፓይለትም በመሆን የመጀመሪያዋ ሴት ኢትዮጵያዊት❗️

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት በህክምና ዶክተር ሆና የተመረቀችው መቅደስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን አካዳሚ ደግሞ የአብራሪነት ስልጠና ተከታትላ የፓይለትነት ፈቃድ ተቀብላለች። አሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ረዳት አብራሪ ሆና እየሰራች ነው።

Meet #Dr_Mekdes_Berhanu ,the first woman to be both Medical Doctor and Pilot in #Ethiopia .

#Dr_Mekdes studied medicine at Addis Ababa University ,School of Medicine .

She then studied her Commercial Pilot License (CPL) at Ethiopian Aviation Academy, Pilot Training School (PTS).

She is now serving as a First Officer( a.k.a Copilot) at Ethiopian Airlines.She is the first Female in Ethiopia to be both Medical Doctor and Commercial pilot!

Dr. Mekdes could be a good role model for other women in the world that nothing is unachievable.

©World Press

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ
@NATIONALEXAMSRESULT
#Ethiopia : ማይጨው የሚገኘው የራያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ግቢውን ለቀው በአማራ ክልል ራያ ከተማ አላማጣ አድርገው ወልዲያ ገብተዋል::

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
#News_alert

#Ethiopia
አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ለፓርላማ)

1. አዲስ አበባ ከተማ
- ብልጽግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል
- አንዷን መቀመጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ አሸንፈዋል

2. አፋር ክልል
- 8 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው 6 መቀመጫዎችን በሙሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

3. አማራ ክልል
- ምርጫ ከተካሄደባቸው 125 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና በ114ቱ አሸንፏል
- አብን 5 መቀመጫዎችን አሸንፏል

4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- 9 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- በሶስት የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ 14 ምርጫ ተከናውኗል
- ሶስቱንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

5. ድሬዳዋ
- 2 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ብልጽግና ፓርቲ አንዱን መቀመጫ አሸንፏል

6. ጋምቤላ ክልል
- 3 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ሶስቱንም ምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

7. ኦሮሚያ ክልል
- 178 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ምርጫ ከተካሄደባቸው 170 መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና 167ቱን መቀመጫ አሸንፏል
- ቀሪ 3 መቀመጫዎችን 3 የግል ዕጩዎች አሸንፈዋል

8. ሲዳማ ክልል
- 19 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- 19ኙንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

9. ደቡብ ክልል
- 104 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ምርጫ ከተከናወነባቸው 85 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ በ75ቱ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
- ኢዜማ 4 መቀመጫዎችን አሸንፏል
- የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 መቀመጫዎችን አሸንፏል

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
#Ethiopia

ባለፉት ቀናት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት #ቴሌግራም እና #ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ትላንት ፈተናው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@NATIONALEXAMSRESULT
#Ethiopia : በአንድ ነጥብ አንድ (1.15) ቢሊዮን ብር በላይ በጀትና በ19ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነባው የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ጠብቆ የተገነባ፣ በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ የመጀመሪያዎቹ አስር ቤተ-መጽሐፍት አንዱ ሆኗል። በውስጡ በ4 ወለሎች 1.5 ኪሜ እርዝመት ያለውና በውስጡ 1.4 ሚሊዮን መፃህፍትን መደርደር የሚችል መጽሐፍት መደርደሪያ ያለው፣ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የወረቅት አልባ መጽሐፍትና 300 ሺህ ጥናታዊ ፅሁፎችን የያዘ፣ ለአጥቢ እናቶችና የህፃናት ማንበቢያ ስፍራን ያመቻቸ፣ አለማቀፍ ማየት ለተሳነቸው ወገኖቻችን የብሬይል መጽሐፍትን አቅርቦት ያለው፣ ዘመናዊ የካፊቴሪያና የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ ስምንት የመፅሃፍትና ተጓዳኝ አገልግሎት ሱቆችን፣ አምፊ ትያትርና መጫወቻ ቦታዎችን እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ መኪናዎችን በአንዴ 115 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ ስፍራን የያዘ ነው። ይህ ፕሮጀክት በተቀመጠለት ጊዜና በጀት ሳያልፍ የተጠናቀቀና የመንግስትን የመፈፀም አቅም በድጋሚ ያረጋገጠ ውጤት ነው።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
1,000,000 ብር አበርክተዋል

#Ethiopia ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ ባለሀብቶች ያሰባሰቡትን 1,000,000 ብር ለአጨብጭቡለት ፊልም በጦርነቱ ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ማቋቋሚያ አላማ እንዲውል አበርክተዋል::

የፊልሙም አባላት አላማቸውን ደግፈው ላበረከቱላቸው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

ተወዳጅነትን ያገኝው "አጨብጭቡለት" ፊልም በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች በእይታ ላይ ይገኛል::

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
" ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ከኤምባሲያችን ጋር ተመካከሩ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

#Ethiopia : በዩክሬይን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በርሊን፣ ጀርመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል።

በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዩክሬይን ውስጥ በትምህርት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በገጠማችሁ ችግር ምክንያት ከመንቀሣቀሣችሁ በፊት ለዜጎቻችንን ደህንነት በማንኛውም ጊዜ በሞባይል ስልክ ቁጥር +491767269094 እና በemail berlin.embassy@mfa.gov.et ከኢምባሲያችን ጋር እንድትመካከሩ በአደራ ጭምር እናሣስባለን " ብሏል።

ትላንት በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ መግለፃቸውና የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው መማፀናቸው አይዘነጋም።

ለከፍተኛ ትምህርት ዩክሬን የሚገኙ በርካታ የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከ400 እስከ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ይገመታል።

    ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በባህላችን የተመረቀ ሰው ለበጎ የተጠራ ነው። እያንዳንዱ ተመራቂ የተጠራለት ተግባር ለሀገሩ ዕድገት ምሦሶ መሆን ነው። ፈጠራን ለማቀላጠፍ፣ ለማኅበረሰብ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን ለማግኘት እና ለብዙዎች የተስፋ ብርሃን ለመሆን።

As many graduate from their studies this season, the task each graduate is called upon is to be pillars of #Ethiopia’s development. To innovate, to find solutions to societal challenges and become beacons of hope for many.

[Abiy Ahmed Ali]

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ዛሬ በእነዚህ አካባቢዎች መብራት ይጠፋል

#Ethiopia | አርብ፣ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመካከለኛ የኤሌትሪክ ሃይል ተሸካሚ ላይ የማሻሻያ ሥራ ስለሚከናወን በሚከተሉት አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለሰዓታት የሚቋረጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ

👉🏻 በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣
👉🏻 በሲ ኤሚ ሲ ልዩ ቤቶች፣
👉🏻 በተባበሩት፣
👉🏻 በሲኤሚሲ ሚካኤል እና አካባቢዎች

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ

👉🏻 በአያት 49 ማዞርያ፣
👉🏻 በአየር መንገድ ቤቶች፣
👉🏻 በአያት 2፣ 3፣ 4 ኮንደሚኒየም፣
👉🏻 በቦሌ አራብሳ እና አካባቢዎቻቸው

በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ ተብሏል፡፡

መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ETHIOPIA

ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው ተልዕኮ ውጪ ለሆነ #የፖለቲ_ሥራ እንደሚውል በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠና ጥናት ላይ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ኮሚሽኑ ጥናቱን ያከናወነው በፌዴራል ደረጃ በሚገኙ የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የጥናቱ ትኩረት ሙስናና ብልሹ አሠራር በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርሰውን የሙስና ሥጋት ለመለየት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከምንጮቼ አገኘሁት ያለውና ኮሚሽኑ በተመረጡ 61 ተቋማት ላይ ያደረገው የጥናት ሪፖርት እንደሚያሳየው ፦

- በተቋማቱ፤ ከመምህራን ልማት እና ከአሠልጣኞች ምልመላ ጋር በተገናኘ፣ የዘመድና የፓርቲ አሠራር፣ እንዲሁም አድልኦና ጉቦ የመቀበል አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል።

- በመምህራንና ሠራተኞች አስተዳደር ክፍል ሕገወጥ ቅጥርና ዝውውር መኖር፣ መምህራን ተማሪዎችን ለይቶ ለመጥቀም የሚደረግ ዝንባሌ መኖር፣ ለመምህራን ቅጥር ውድድር ተፈልጎ እኩል ውጤት ሲመጣ፣ አንዱን በትውውቅ ብቻ የመምረጥ አሠራር እንደሚስተዋል ተገልጿል፡፡

- ከሐሰተኛ የትምህርት ሰነድ ጋር በተያያዘ የብቃት ማረጋገጥና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ መሥፈርት ሳያሟሉ፣ ለተቋማት ፈቃድ መስጠት እና የፈቃድ ዕድሳት እንደሚከናወን ተግልጿል።

- መምህራንና በትምህርት አስተዳደር አመራር ላይ ያሉ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች እንደተገኘባቸው ፤ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት ሲሞከር ደግሞ ሠራተኞች ከሥራ ቀድመው የመልቀቅ እንቅስቃሴ እንዳለ ተገልጿል።

- በግል ኮሌጆች የሲኦሲ ምዘና ሳያልፉና ትምህርት አጠናቀው ሳይጨርሱ፣ እንዲሁም ፈጽሞ ያልተማሩ ሰዎች የትምህርት ማስረጃ አትሞ መስጠትና በኮሌጆች ሽያጭ የመፈጸም ድርጊት መኖሩን ሪፖርቱ ገልጿል።

- በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች ሬጅስትራሮች ውስጥ የተማሪዎችን ውጤት የማሳሳትና የማጭበርበር ድርጊት እንዳለ ተጠቅሷሳ።

- በግል ትምህርት ተቋማት ውሳኔዎች የሚተላለፉት ለተቋማቸው መልካም ስም ቅድሚያ በመስጠት እንደሆነ፣ በመንግሥት ተቋማት ደግሞ ሰነድ ማዘጋጀት እንጂ ትግበራ ላይ እምብዛም እንደሌሉበት ተገልጿል።

- በተደረገው ጥናት በተቋማቸው ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ ወይ ተብለው ከተጠየቁት ውስጥ 65 በመቶ የሚሆኑት " አዎ " የሚል መልስ መስጠታቸውን፣ 35 በመቶ የሚሆኑት " የለም " የሚል መልስ ሲሰጡ፣ በተመሳሳይ የሙስና ችግሮች መኖራቸውን 66 በመቶ መናገራቸውና 47 በመቶ ደግሞ ለሚቀርቡ ጥቆማዎች ከተቋማቱ መልስ እንደማይሰጥ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

- በትምህርት ተቋማቱ የመምህራን በተደጋጋሚ ወደ ክፍል አለመግባት፣ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መስጠት፣ በአመራር የሚከናወን ስርቆት፣ ሕገወጥ ዝውውርና የደረጃ ዕድገት፣ ሕግና ደንብን ተከትሎ የማይከናወን ግዥ፣ የመረጃና ማስረጃ ማጭበርበር፣ ግልጽነት የሌለው አሠራር መብዛት፣ በሬጅስትራር የሚፈጸም ብልሹ አሠራር ተቋማቱን ለከባድ ሙስና አደጋ ጥሏቸዋል፡፡

- በግዥ ወቅት ለተቋም የማያስፈልግ ንብረት እንዲገዛ ተጨማሪ በጀት ማስያዝ፣ በጨረታ ወቅት የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ እንዲጋብዝ አድርጎ ሰነድ ማዘጋጀት፣ ወቅቱንና ጥራቱን ያልጠበቀ ግንባታ እንዲከናወን ማድረግ፣ በሕንፃ ርክክብ ጥራቱን ያልጠበቀ ሕንፃ እንዲገነባ ማድረግና ያልተጠናቀቀ ሕንፃ መረከብ ተቋማቱን ለከባድ ሙስና እንዳጋለጣቸው ሪፖርቱ ያሳያል።

እንደ ምክንያት የተጠቀሱት ችግሮች ምንድናቸው ?

• የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ፣
• የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖር፣
• የሞራል መላሸቅ፣
• የተጠያቂነት ማነስ፣
• የላላ የአመራር ቁጥጥርና ከፍተኛ የሆነ የበጀት ምደባ የሚሉት ይገኙበታል።

ጥናቱ በሚደረግበት ወቅት ምን ችግሮች አጋጠሙ ?

➤ የተቋማት አመራሮች በቦታው ላይ አለመገኘት፣
➤ ተቋማት መረጃ ለመሥጠት ፈቃደኛ አለመሆን፣
➤ የተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች መረጃዎችን በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመሥርቶ አለመስጠት ... መሰል ዓይነት ችግሮች ነበሩ።

ሪፖርተር 👇
https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-09-25

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከነገ ህዳር 3: 2015 ጀምሮ በፓርኩ አገልግሎት ለማግኘት ከስር የተቀመጠውን የጥቅል ዋጋ ይመልከቱ::
የቅድሚያ ምዝገባን በተመለከተ በቅርቡ እናሳውቃልን::

#park #kidsplayground #sports #weddinggarden #AddisAbaba #Ethiopia

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Ethiopia

ከጥቂት ቀናት በፊት አገልግሎታቸው እንዲገደብ የተደረጉት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዛሬም አገልግሎታቸው ወደ ቦታው እንዳልተመለሰ ለመረዳት ታችሏል።

#ቴሌግራም ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎታቸው እንዲገደብ ከተደረገ ቀናት ያለፉ ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ ያብራራ/ያሳወቀ የለም።

የአገልግሎት ገደቡ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች (ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ) ተፈፃሚ እየሆነ ይገኛል።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ያለ አንዳች ገደብ እየሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ አገልግሎት የመገደብ እርምጃ ከምን በመነሳት እንደተወሰደ እና እስከመቼ ድረስስ እንደሚቆይ ያብራራ አካል የለም።

ምንም እንኳን አገልግሎቶች ላይ ገደብ ቢደረግም የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች በ #VPN ገደቡን በማለፈ አገልግሎት እየተጠቀሙ ይገኘሉ።

መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Ethiopia

'' መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የውትድርና ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ይችላል " - ዲማ ኖጎ ( ዶ/ር)

መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች  በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ እንደሚችል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ሰብሳቢው ይህንን ያሳወቁት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል  የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ  ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ዲማ  ናጎ ምን አሉ ?

" ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕድሜያቸው 15 ዓመት የሞላቸው እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል።

ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አባላት የሚሆኑ ከሆነ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ያደርጋል። "

የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ የተጣለበትን ሀገር የመጠበቅ ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የተሻለ ሠራዊት ለመገንባት ማነቆ የሆኑ ሕግ ማዕቀፎችን እና ተቋማዊ አስተሳሰቦችን በመፈተሽ ለሀገር እና ሕዝብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነው የተገለፀው።

ምክር ቤቱ በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1286/2015 አድርጎ   በስድስት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

Via HoPR
@NATIONALEXAMSRESULT