STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአራት ቀን የሚቆይ ውይይት በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ውይይቱ በዛሬው እለት በ77 ክላስተሮች 63,470 መምህራን እና የትምህርት አመራሮችን ተሳታፊ በማድረግ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸው በውይይቱ 1,368 ቡድኖች ከመደራጀታቸው ባሻገር 2,736 አወያዮች መመደባቸውን አስታውቀዋል።

ውይይቱ በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶችና በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሰረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ዶክተር ዘላለም ገልጸው ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት መምህራንም ሆኑ የትምህርት አመራሮች የአንበሳውን ድርሻ እንደመውሰዳቸው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነምግባር ለማሻሻል ውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት መሆኑንም አስረድተዋል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በክላስተር ደረጃ ተካሂዶ እሁድ እለት ከየትምህርት ቤቱ ከተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በየክፍለከተማው ተመሳሳይ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር እሁድ 500 የሚሆኑ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ታላላቅ የልማት ስራዎችን የሚጎበኙበት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ኃላፊው ጠቁመው ሰኞ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት 5,000 ከሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#ማሳሰቢያ

ለሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት !
በ2015 ዓ.ም ከሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exite Exame) የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻችሁን መረጃ በተላከላችሁ የመረጃ መላኪያ ቅጽ መሠረት እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንድታቀርቡ እያሳሰብን እስከ ተጠቀሰው ቀን መረጃውን የማያቀርብ ተቋም ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoH

ጤና ሚኒስቴር በግንቦት 2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምዝገባው እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ብቻ ይከናወናል።

የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት በኦንላይን እንድትመዘገቡ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ከተጠቀሰው ጊዜ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የግል ትምህርት ተቋማት አዲስ ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በማረጋገጥ ስማችሁን ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

ማንኛውም ተመዛኝ ምዝገባ ሲያደርግ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር የያዘ ወረቀት (ስሊፕ) print አድርጎ መያዝ ይጠበቅበታል። #ጤና_ሚኒስቴር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትምህርት ቤቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሳደግ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው
-----------------------------
ሚያዚያ 20,2015ዓ.ም ( የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከክልልና ከተማ መስተዳደር ለተውጣጡ የትምህርት ባለሙዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኔስኮ-ሁዋዊ (UNESCO - Huawei) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ነው የተሰጠው።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የዩኔስኮ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ሪታ ቢሶናዝ (ዶ/ር) ስልጠናው ለትምህርት ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ክፍተት ለመሙላት አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።

በትምህርት ቴክኖሎጂ በቂ እውቀት ያላቸውን የትምህርት ባለሙያዎችን በማፍራት እና ት/ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ርብርብ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ከድር ኡርጂ በበኩላቸው የትምህርት ስርአቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በተጠናከረ መልኩ ለመደገፍ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያከናወናቸው ካሉ የለውጥ ስራዎች መካከል አንዱ ዲጂታላይዜሽን ሲሆን በዘርፉም በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢንተርኔት አገልግሎት ላለፉት ሁለት ሳምንታት መቋረጡ በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን የቤት ሥራም ሆነ በግላቸው የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከየካቲት ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በአላማጣ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
🤔 ለትምህርት ቤቶች አስተዳደር ሠራተኞች የተላለ መልዕክት ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ #tikvah

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ አንድ ተቋም እና 18 ኮሌጆች የተሟላ መረጃ መላካቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) #ETA

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን አዲስ አዋጅ ፀደቀ‼️

የተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት አዋጅ አፀደቀ‼️

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን አዲስ አዋጅ አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ መንግስት አዘጋጅቶ ያቀረበውን የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ኖህ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ መከላከያ ሰራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ሃይል አባል የሚሆኑ ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠብቁላቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡

በመንግስት ተዘጋጅቶ የቀረበው የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የተጣለበትን ሀገርን የመጠበቅ ተልክኮ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመወጣት እንዲችል ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በመንግስት የተሻሻለውና ከትናንት በስቲያ በምክር ቤቱ የፀደቀው ይህው አዋጅ የሰራዊቱ አባላት የጡረታ መውጫ የእድሜ ጣሪያ አወሳሰን እንዲሁም የአገር ህልውና ከባድ አደጋ ላይ በሚወድቅ ጊዜ ከሰራዊቱ የተገለሉ አባላት መቀጠር የሚችሉበትን ሁኔታ ሁሉ አካቶ መያዙም ተገልጿል፡፡

አዲስ አድማስ


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው::

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ተወካዮች በቀጣይ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ከ22ኛው ሳምንት ጀምሮ የሚያስተናግደውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለአራተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ረፋድ ላይ ተመልክተዋል።

ቀደም ባሉ ምልከታዎቻቸው የሊጉ የበላይ አካል በሜዳውና ከሜዳው ውጪ ያሉ መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ መሆናቸውን ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ሊጉ በቀጣይ ሀዋሳ ላይ እንደሚደረግ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ፕሪምየር ሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታውን በአዳማ ከጀመረ በኋላ ከመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ እስከ 27ኛው ሳምንት ድረስ ሀዋሳ የሊጉን ውድድር ታስተናግዳለች::

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
መምህራን ትውልድን የመቅረፅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቁ

መምህራን በሀገር ግንባታና ትውልድን የመቅረፅ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቁ፡፡

በከተማ ደረጃ የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ የትምህርት ጥራትን እናገጋግጥ በሚል መሪ ከመምህራን ጋር ሲካሄድ የቆየው ውይይት የማጠቃለያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላትን (ዶ/ር) ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው አመራሮችና መምህራን ተገኝተዋል።

በመርኃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላት (ዶ/ር) ባለፉት 3 ቀናት በ77 ክላስተር እንዲሁም ከ63 ሺሕ በላይ መምህራን ጋር በተደረገ ውይይት የጋራ መግባባት የተፈጠረበትና በርካታ ልምዶች የተወሰዱበት እንደነበር ገልጸዋል።

መምህራን በሀገር ግንባታና ትውልድን የመቅረፅ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ኃላፊው የትምህርት ደህንነትን ማስጠበቅ፣ ተወዳዳሪ የትምህርት አመራር እና ማህበረሰብን መፍጠር የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ተገኙት መምህራን ጋር ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የትብብርጥሪ በትግራይ ክልል ለአመታት ከትምህርት ውጪ ሆነው የነበሩ ተማሪዎችን ለማገዝ የማህበራዊ ሚድያ ርብርብ ተጀምሯል።

እኔም ይህን በመቀላቀል ይህ ከታች ያለው መልዕክት ለብዙዎች እንዲደርስ በማሰብ ፌስቡክ ላይ ሼር በተደረገው መጠን (10,000 ግዜ ሼር ከተደረገ 10,000 ብር... ወዘተ) በግሌ የማግዝ ይሆናል። Link:
https://facebook.com/100044173462677/posts/pfbid032CP45Ls2BoUNBtettj1KweTYC3qL4tFBKc89zG9f3zgsBxx5yUSvppEGudLfhRLDl/

ይህንን ዘመቻ ለመደገፍ ይህን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት መጠቀም ይቻላል: 1000541451203 

Biru Tsegaye
Mohammed Dula Mohammed
Melesse Engida
Bini Berhe

ዘመቻውን ላስተባበራችሁ ሁሉ ታላቅ ምስጋና 🙏

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot