STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#AddisAbabaEducationBureau

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሰርተፍኬት ሲያስተምሩ የነበሩ 4 ሺህ የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራንን በዲፕሎማ ሊያሠለጥን መሆኑን አስታውቋል፡፡

የቅድመ አንደኛ ደረጃ (ሙዓለ ህፃናት) መምህራኑ ከሐምሌ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሦሥት ዓመታት በዲፕሎማ እንደሚሠለጥኑ ተገልጿል፡፡

ከግልና ከመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 2 ሺህ 500 መምህራንን በደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ እንዲሁም 1 ሺህ 500 መምህራን በአሰላ መምህራን ኮሌጅ የሚማሩ ይሆናል፡፡

ቢሮው ከደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ እና ከአሰላ መምህራን ኮሌጅ ጋር ለቀጣይ ሦሥት ዓመታት አብሮ ለመስራት ሰኔ 20/2014 ዓ.ም ስምምነት አድርጓል።

ለስልጠናው ከተመዘገቡ ከ5 ሺህ 600 በላይ መምህራን ኮሌጆቹ ያስቀመጡትን የመግቢያ ነጥብ ያሟሉት 4 ሺህ ብቻ በመሆናቸው ትምህርት ቢሮው ሁሉንም መምህራን ወደ ኮሌጆቹ ለማስገባት መወሰኑ ታውቋል፡፡

ትምህርቱ በክረምት እና በቅዳሜና እሁድ ለሦሦት ዓመታት የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ቢሮው ከ80 እስከ 90 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተገልጿል። #ሪፖርተር

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሊቋቋም ነው።

ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ኒውክሌርን ለኃይል ማመንጫነትና በተለያዩ ዘርፎች ለሚሠሩ ሥራዎች የማዋል ኃላፊነትን የሚወጣ ይሆናል።

ኢንስቲትዩቱን የሚመራ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት ሊቋቋም መሆኑም ተሰምቷል፡፡

በኒውክሌር ዘርፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚመራው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኢንስቲትዩቱንና ምክር ቤቱን የሚያቋቁሙ ሁለት ደንቦችን አዘጋጅቶ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን አሳውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ለ250 ባለሙያዎች ሥልጠና መስጠቱን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመርያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት መድረክ ላይ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም 11 ባለሙያዎች በኒውክሌር ሳይንስ ዘርፍ አንድ የሦሥተኛ ዲግሪ፣ አምስት የሁለተኛ ዲግሪ እና አምስት የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲማሩ ወደ ሩስያ እና ቻይና መላኩን አሳውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በኒውክሌር ሳይንስ ዘርፍ ተቋም የማቋቋም እና የአቅም ግንባታ እያደረገ ያለው ኢትዮጵያ እና ሩስያ ጥቅምት 2012 ዓ.ም በሩስያዋ ሱሺ ከተማ የተፈራረሙትን ስምምነት መነሻ በማድረግ መሆኑን የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተስፋዬ አለምነው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ኒውክሌርን በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ለማዋል በመጀመርያ ሊገነባ የታሰበው በጤና፣ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ሌሎች ዘርፎች ጥቅም ላይ የሚውል የኔውክሌር ሪሰርች ሪአክተር (ለካንሰር ሕክምና የሚውለውን ጨረር ጨምሮ) እንደነበር የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ም/ዋ/ዳይሬክተር መብራቱ ገብረማርያም (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡

የኒውክሌር ሪሰርች ሪአክተር ኒውትሮን የሚያመነጭ ሲሆን ቁሶች በውስጣቸው ምን እንደያዙ ለመለየት እንዲሁም ለሕክምናና ሌሎች ሳይንሳዊ ምርምሮች የሚያገለግሉ ሬድዮ አክቲቭ ቁሶችን ለማምረት ያገለግላል፡፡

ይሁንና አሁን ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫም (Nuclear Power Plants) ለመገንባት ማቀዷን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ሁለት ዕቅዶች የሚተገብረው በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ሊቋቋም የታሰበው የኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንደሚሆን የተናገሩት መብራቱ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ በኋላ የቁጥጥር ሥራ እንደሚሠራ አስረድተዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ለትግበራው ያዘጋጀው ሰነድ ለመንግሥት ውሳኔ ‹‹ወደ በላይ አካላት›› ተልኮ ውሳኔ እየጠበቀ እንደሆነ በስም ያልተጠቀሱ የሚኒስቴሩ ኃላፊ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የትግበራ ሥራ እንቅስቃሴው ቢጀመርም ‹‹በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል?›› የሚለውን በትክክል መናገር እንደማይቻል ኃላፊው ገልጸዋል። #ሪፖርተር


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው በጀት ዓመት ለመምህራን እና ሰራተኞቹ የመኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነው።

ዩኒቨርሲቲው የራሱን አፓርታማ ገንብቶ ገቢ እንዲያመነጭ በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ አራት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የተፈቀደለት መሆኑን የተቋሙ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና አስታውሰዋል።

የተቋሙ መምህራን እና ሰራተኞች በአነስተኛ የኪራይ ክፍያ የሚገለገሉበት ባለ 15 ፎቅ ህንፃ ለመገንባት መታቀዱን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከመኖሪያ ቤቶች ህንፃ በተጨማሪ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነባም ገልጸዋል።

ከሦሥት ዓመት በፊት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዩኒቨርሲቲው ከተፈቀደው 11.5 ሄክታር መሬት ውስጥ አራት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ብቻ ርክክብ መፈጸሙን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ቀሪውን ይዞታ የአካባቢው አርሶ አደሮች ባለመልቀቃቸው መረከብ አልተቻለም ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ለአርሶ አደሮቹ ተገቢውን ካሳ በመክፈል የተቀረውን ይዞታ ለዩኒቨርሲቲው እንደሚያስረክብ ቃል መግባቱን ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።

በዚህ ዓመት ለመጀመር የታቀደው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ዩኒቨርሲቲው ከአንድ ሺህ በላይ የአካዳሚክና ከአራት ሺህ በላይ የአስተዳደር ሰራተኞች አሉት። #ሪፖርተር


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት መምህራን አያስፈልጉም።"


የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተቋማቸውን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ለህ/ተ/ም/ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲ መምህራን በአማካይ በሴሚስተር አራት ኮርስ መያዝ ቢጠበቅባቸውም አብዛኞቹ መምህራን በሴሚስተር አንድ ኮርስ አስተምረው የሙሉ ጊዜ መምህራን ተብለው እንደሚጠሩ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ከበጀታቸው ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል የመምህራን ቁጥር በመያዝ በልካቸው ሊራመዱ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ከሌሎች የገንዘብ ምንጮች በሚያገኟቸው ገቢዎች ተወዳዳሪና ተመራጭ የትምህርት ተቋም የሚያደርጓቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ፤ ውድድርን መሰረት አድርገው ለመምህራኖቻቸው የተሻለ ደመወዝ ሊከፍሉ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

የተሻለ የደመወዝ ክፍያ መፈጸም ምንም ጥያቄ የሌለው ጉዳይ ቢሆንም አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሲቪል ሰርቪስ ህጉ እስከተገዙ ድረስ መንግስት ደመወዝ ልጨምር ቢል ለዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ተቋማት መሆን ስላለበት ይህ የማይቻል ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

አገሪቱ አሁን ካለችበት የጦርነት ድባብ ወጥታ የደመወዙ ጉዳይ በድጋሚ ሊታይ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከጥቂት ወራት በፊት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ባቋቋሟቸው ማኅበራት አማካይነት መንግስት የደመወዝ ጭማሪ እና የእርከን ዕድገት እንዲያደርግ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ #ሪፖርተር
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር መወሰኑ ተሠማ።

ይህ የተገለጸው የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ባለድርሻ አካላትን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰኞ ኅዳር 26/2015 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው የፐብሊክ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ ዘሪሁን አስፋው እንደተናገሩት፥ የመንግሥትን ሀብት በመመዝበር በተለዩ ስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ጭብጦችን የመለየት ሥራ በመከናወን ላይ ነው።

የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድባቸው የተለዩት ዩኒቨርሲቲዎችም ቡሌ ሆራ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልድያ፣ ሀዋሳ፣ መቱ፣ ደብረ ታቦር፣ ዲላ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል። #ሪፖርተር


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ

በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸወቀው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መምህራን የሚቀጠሩበትን መስፈርትን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን ያሻሽላል።

በትምህርት ሚኒስቴር እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘጋጀው አዲሱ ፖሊሲ፤ ለ28 ዓመታት ሲተገበር የቆየውን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የሚተካ ነው።

ፖሊሲው የመምህራን የሙያ ደረጃን፣ የተማሪዎችን የክፍል ዕርከኖችን፣ በሥርዓተ ትምህርት የሚካተቱ ቋንቋዎችን እንዲሁም በርካታ የትምህርት ሂደቶችንና አሰራሮችን የሚቀይር መሆኑ ተገልጿል።

ከተደረጉ በርካታ ማሻሻያዎች መካከል የመምህራን የትምህርት ዝግጁነትና ደረጃዎች አንደኛው ሲሆን የቅድመ-አንደኛ የትምህርት ደረጃ ተማሪዎችን ለማስተማር አነስተኛው የትምህርት ደረጃ "ሰርተፊኬት" እንዲሆን ያዛል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያሉትን ተማሪዎች ለማስተማር ደግሞ ዝቅተኛው የትምህርት ዝግጅት "ዲፕሎማ" እንደሚሆን ረቂቅ ፖሊሲው አስቀምጧል።

ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ለማስተማር አነስተኛው የመምህራን የትምህርት ዝግጅት የመጀመርያ ዲግሪ እንዲሆን በረቂቅ ፖሊሲው ተቀምጧል።

በተመሳሳይ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ አመራሮች ዝቅተኛው የትምህርት ዝግጅት የመጀመርያ ዲግሪ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው ይጠበቃል።

በተመሳሳይ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት አመራሮች ከቴክኒክ ክህሎት ባሻገር ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲኖራቸው ረቂቅ ፖሊሲው ያዛል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ | የትምህርት ዕርከኖች

ረቂቅ ፖሊሲው የትምህርት ዕርከኖችን ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ አንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ በማለት በአራት ይከፋፍለዋል።

የአንደኛ ደረጃ ዕርከን ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍልን ያጠቃልላል። መካከለኛ ደረጃ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍልን ያካትታል። ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ይይዛል።

የከፍተኛ ትምህርትን በሚመለከት የቅድመ ምረቃ በትንሹ አራት ዓመታትን እንደሚፈጅ፣ ሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ ሁለት ዓመታትን እንደሚፈጅ እና የሦሥተኛ ዶክትሬት ዲግሪ ደግሞ አራት ዓመታትን እንደሚፈጅ ፖሊሲው ይገልጻል።

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስምንት ደረጃዎች የሚኖሩት ሲሆን አሠልጣኞች ከመጀመርያ ዲግሪ እስከ ሦሥተኛ ዲግሪ ድረስ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው ይጠበቃል።

ለደረጃ አንድ እና ሁለት የመጀመርያ ዲግሪ፣ ከደረጃ ሦሥት እስከ ስድስት የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ለደረጃ ሰባት እና ስምንት ደግሞ ሦሥተኛ ዲግሪ እንደመስፈርት ተቀምጧል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት (እስከ ስምንተኛ ክፍል ያለው ትምህርት) በግዴታና በነፃ እንደሚሰጥ ረቂቅ ፖሊሲው አስቀምጧል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያቋቁመው ረቂቅ አዋጅ በርካታ አደረጃጀቶችን ይዞ መምጣቱ ጥያቄ አስነስቷል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ፤ ቻንስለር፣ የሥራ አመራር ቦርድ፣ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ሴኔት፣ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል፣ ማኔጂንግ ካውንስል እና ሌሎችም መዋቅሮችም እንደሚኖሩ ተብራርቷል፡፡

በትምህርት ተቋማቱ ይዋቀራሉ ተብለው የታሰቡት አደረጃጀቶች መብዛት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሥራ መጠላለፍና መደራረብ ይፈጥራል የሚል ስጋት እንዳለባቸው ምሁራን ገለጹ፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ ከዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የአደረጃጀቶች መብዛት የኃላፊነት መጣረስ እንዳያመጣ
እና ለውሳኔ አሰጣጥ ክፍተት እንዳይፈጥር ተሳታፊዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አደረጃጀቶቹ የተለያየ ኃላፊነት እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡

የቦርድ አወቃቀሩም ጠንካራ የሆኑና የዩኒቨርሲቲን ሥራ የሚያውቁ ሰዎች በያዘ መልኩ እንደሚደራጅ ጠቁመዋል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የመምህራኑ ጥያቄ ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን ማኅበር በሥሩ ከሚገኙት አባላት መካከል የ29,500 አባላቱ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታለት ከንቲባ አዳነች አቤቤን በደብዳቤ ጠይቋል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ለሪፖርተር ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር። በዚህ ቃለምልልስ ምን አሉ ?

- ማህበሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ለከንቲባዋ በጻፈው ደብዳቤ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ መምህራን የቤት ጥያቄ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡

- የመምህራን ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ ከንቲባዋ ከመምህራን ጋር በ2013 ዓ.ም. በነበራቸው ስብሳሰባ፣ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየ አይደለም።

- ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ለመምህራን የኑሮ ውድነትን የሚያረግቡ ድጎማዎች እንዲደረጉ፣ ከንቲባዋ በመድረክ ላይ የገቡት ቃል ወደ ታች ወርዶ እንዲፈጸምና በከተማ አስተዳደሩ በተጀመሩ ልማቶች የመምህራን ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ተጠይቋል።

- የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከተቻለ በልዩ ትኩረት በከተማው ደረጃ ውሳኔ ሰጥቶበት እንዲፈታ፣ ካልሆነም ደግሞ የሚመለከተው የፌዴራል ተቋም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እልባት መስጠት እንዲቻል እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

- የኑሮ ውድነት ማረጋጊያ ድጎማ 3,000 ብር የሚሰጥ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ከችግሩ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ቢያንስ በእጥፍ እንዲያድግ መምህራኑ ይፈልጋሉ።

በተጨማሪ ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ....

ለመምህራን ሁለተኛ መ/ ቤታቸው የሆነው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ፣ ግንቦት 2013 ዓ.ም. መምህራንን ባወያዩበት ወቅት መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ የተገለጸ ቢሆንም፣ ነገር ግን እስካሁን በተፈለገው ርቀት ወደ ሥራ አለመገባቱን ያትታል፡፡

በዚህ የተነሳ ባለፉት ወራት ምንም ዓይነት ለውጥ አለመኖሩ መምህራንን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ፣ ጉዳዩን በተቃራኒ በጥርጣሬ እንዲያዩት አነሳሽ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ተስፋ አስቆራጭነቱ እየሰፋ የመጣ ስለመሆኑ ይገልጻል።

ይህ ጉዳይ መምህራን ቃል የገቡልንን አልተገበሩልንም (አላስተገበሩልንም) የሚል ስሜት ፈጥሮ የመምህራንን ሞራል ያላሸቀ ፣ ቤት ባላቸውና በሌላቸው መምህራን መካከል የፍትሐዊነት ጥያቄ ያስነሳ መሆኑም በደብዳቤው ተመላክቷል፡፡

መምህራን የሚያገኙት የደመወዝ መጠንና በአሁኑ ወቅት ያለው ፦ የቤት ኪራይ ዋጋ፣ በተጨማሪም የኑሮ ውድነት መምህራንን ተረጋግተው እንዳያስተምሩ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ ከንቲባዋ ለመምህራኑ በገቡት ቃል መሠረት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ " አጥብቀን እንጠይቃለን " ብሏል።

በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መምህራኑ ከሚያገኙት ደመወዝና የኑሮ መደጎሚያ ጋር ተቋቁሞ መኖር ከባድ መሆኑን የሚያስረዳው ደብዳቤው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ባደረገው የኑሮ መደጎሚያ ላይ ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ ፦ https://telegra.ph/Reporter-04-23

#ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢንተርኔት አገልግሎት ላለፉት ሁለት ሳምንታት መቋረጡ በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን የቤት ሥራም ሆነ በግላቸው የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከየካቲት ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በአላማጣ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ሊደረግ ነው።

በኢትዮጵያ በቂ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ባለመኖራቸው፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሊያስተምሩ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን መምህራንን ጭምር የሚያሠለጥኑ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመድበው የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያስተምሩበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

"የእንግሊዝኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻቸው የሆኑ ሦስት ሺህ የሚሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በአገር ቤት ያሉ መምህራንንና ተማሪዎችን እንዲያስተምሩ በየትምህርት ቤቱ አንድ ለመመደብ አቅደናል" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ጥሪ መሠረት በውጭ አገር ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን ወደ አገር ቤት ልከው ትምህርት እንዲሰጡ ለማድረግ እንዲመዘገቡ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት በማድረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በነፃ የሚያገኝበት ማስተማሪያ ‹‹ፖርታል›› እንደተዘጋጀም ገልጸዋል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመሩበት የጽሑፍ ፖሊሲ የላቸውም ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ አምስቱም የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አሳውቋል፡፡

ኮሚሽኑ የጎንደር፣ ሐረማያ፣ ሐዋሳ፣ ጅማ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ያላቸውን ተደራሽነትና አካታችነት በተመለከተ በነሐሴ 2014 ዓ.ም. ያከናወነውን የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ኮሚሽኑ በተገለጹት ዩኒቨርሲቲዎች ባደረገው ምልከታ፤ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ አለመኖሩን፣ የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በዋና ዕቅድ ውስጥ ተካቶ አለመሠራቱን እንዲሁም የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ የኢሰመኮ የአካል ጉዳተኞችና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች አካታች የሴኔት ደንብ፣ ሕግና ሥርዓተ-ትምህርት መንደፍ እንዲሁም በረቂቅ ደረጃ የሚገኙትን አካታች ፖሊሲዎችን አጠናቅቀው ማፅደቅና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተደራሽ የሆኑ በቂ የመፀዳጃና የመታጠቢያ ክፍሎች፣ አሳንሰርና የተሽከርካሪ ወንበር መወጣጫ ያላቸው የመማሪያ ክፍሎች፣ ቢሮዎች፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ ካፍቴሪያዎችና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲያዘጋጁ ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል፡፡ #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የክብር ዶክትሬት ጉዳይ...

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ስለሚገኘው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አግባብነት፣ አሰጣጥ፣ ታሪካዊ አመጣጥና፣ ዓለም አቀፋዊ ባህሪ የሚያመላክትና መነሻ ሐሳብ ሊያመነጭ የሚችል ጥናት ሊያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አጠቃላይ ልምዱ ምን እንደሚመስልና በኢትዮጵያ ምንስ መምሰል አለበት የሚለውን ጥናት ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ተከተል ዮሐንስ (ፕ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጡ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የግለሰቦች ብቁ የመሆን ጉዳይ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አመራረጥ እና አሰጣጥ ላይ ጥያቄ ሲነሳቨ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም በጉዳዩ ላይ እንደ ገለልተኛ የፖሊሲ አማካሪና የጥናት ተቋም በመረጃ ላይ የተደገፈ ጥናት ለማድረግ መታሰቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ጥናቱን የሚያካሂዱ ሰዎችን መረጣ መጀመሩን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ጥናቱን ለማካሄድ የሚያግዘው ንድፈ ሐሳብ ዝግጅት ሲጠናቀቅ በመጭው ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ችግር ፈቺ ጥናቶች በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት የፖሊሲ ሐሳቦችን የሚያቀርብ ገለልተኛ ተቋም ነው፡፡

#ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች መግለጻቸውን የማኅበሩ አመራሮች ተናገሩ፡፡

ሰባት አባላትን የያዘ የማኅበሩ የሥራ አስፈጻሚ ቡድን ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመገኘት ለሰዓታት የፈጀ ውይይት አድርገዋል፡፡

የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ውጤታማ ይሆናል ብሎ እንደሚያስብ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት ጥያቄን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፣ ዕልባት እንዲያገኝ እየተሠራበት እንደሆነ ነው የተገለጸልን›› ሲሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላገኙት ምላሽ አስረድተዋል፡፡

የደመወዝ ጭማሪውን በሚመለከት፣ የኑሮ ውድነትን በአጠቃላይ የማቅለል ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹላቸው፣ ይህንንም ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ በውይይታቸው ላይ እንደተነሳ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የመምህራንን ሙያ፣ የትምህርት ቤቶች አቅምና ግብዓት በሚመለከት እንዲሁም ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠርንና ማኅበሩ ለማስገንባት ስላቀደው ሕንፃ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉ ተገልጿል፡፡
#ሪፖርተር


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot