STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
እንኳን ለዓለም-አቀፍ የላብ አደሮች ቀን አደረሳችሁ!

አለም የቆመችዉ በላብ አደሮች ነዉ ፣ ለላብ አደሮች ግን ተገቢዉን  ክፍያ ከፍላ አታዉቅም ...🥹

ክብርና ምስጋና ሃገራችሁን በትጋት ለምታገለግሉ ሁሉ👷‍♀👷‍♂

መልካም  የላብ አደሮች  ቀን 🙏

Team : @NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
🔝

ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለትም በቀን #21/08/2015 ከጥዋቱ 1፡50 ላይ በእንጅባራ ዩንቨርሲቲ በተምዶ ኪዳነምህረት መግቢያ በመባል በሚታወቀው በር በኩል የዩንቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ኤደን ገብሩ ከቤተክርስቲያን መልስ የግቢ መታወቂያ ( ID Card ) አለመያዟን ተከትሎ ከዩንቨርሲቲው ተረኛ የጥበቃ ሠራተኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በደረሰባት አካላዊ ጥቃት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ተማሪዋ ከባድ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በርካታ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቆማ አድርሰውናል።

ይህንን ጥቆማ በመቀበል ጉዳዩን ለማረጋገጥ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ጋር እንዲሁም የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረትን አናግረናል።


<ተማሪ ኤደን ገብሩ ጋር በደወልንበት ጊዜ ተማሪዋ በስልክ ለማውራት አቅም ስላጠራት አጠገቧ ከነበሩት ጓደኞቿ ነው መረጃውን ያገኘነው>

ጉዳት በደረሰባት ተማሪ የእጅ ስልክ ደውለን ያገኘነውን መረጃ በአጭሩ ለመግለፅ👇

[ተማሪዋ ወደ ቤተክርስትያን ስትሄድ የግቢ መታወቂያ ትረሳለች። ወደ ግቢ ስትመለስ የግቢ መታወቂያ እንዳልያዘች በመንገር በመመገቢያ ካርድ ያስገቧት ዘንድ የጥበቃ ሠራተኞችን ስትጠይቅ አንዱ ጥበቃ ይገፈትራታል። አትገፍትረኝ ብላ እጁን ለማስለቀቅ ስትሞክር በጥፊ ይመታታል። ለምን በጥፊ ትመታኛለህ ስትለው በድጋሚ ገፍትሮ ጥሎ ጭኗ አካባቢ ይረግጣታል። ጭኗ አካባቢ የረገጣት ህመም ሲበረታባት ሌሌች ጥበቃዎች ጣልቃ ገብተው ወደ ግቢ እንድትገባ ይፈቅዱላታል። ዶርም ገብታ መታወቂያዋን ይዛ ክስ ለመመስረት ዲሲፕሊን ቢሮ ሄዳ ሰኞ ትመለስ ዘንድ ነግረዋት ከቢሮ ስትወጣ ራሷን ሳተች።አሁን ላይ ማህፀኗ አካባቢ የተቋጠረ ደም እንዳለ እንደተነገራትና ህመሙ ምናልባትም ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል በእጅ ስልኳ መረጃ የሰጡን ከጎኗ ያሉ ጓደኞቿ ነግረውናል። ጓደኞቿ በተጨማሪ እንደነገሩን ከሆነ ተማሪዋ ሽንት ለመሽናትና ለመንቀሳቀስ እጅጉን እየተቸገረች እንደሆነ ገልፀው ዩንቨርሲቲው ጉዳዩን አለባብሶ ለማለፍ እንዳይሞክር ድምፅ እንሆንላት ዘንድ ጠይቀዋል።]


ይህን ጉዳይ በተመለከተ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት የሰጠን ምላሽ 👇

ዩንቨርሲቲው መረጃው የደረሰው ቢሆንም ጉዳዩ በመጣራት ሂደት ላይ እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ነግረውናል።አሁን ላይ ተማሪዋ የህክምና እርዳታ እያገኘች እንዳለ ገልፀው የህመሟን ምክንያት ማለትም ተማሪዋ ያቀረበችውን ምክንያት በተጨማሪም ራሷን ስታ በምትወድቅበት ጊዜ የመታት ነገር መኖር አለመኖሩን የባለሙያ ማረጋገጫ እንደሚያስፈልግና እንደ ፀጥታም መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች በመኖራቸው ጉዳዩን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያጣሩ እንደሚገኙና በሚናፈሱ ወሬዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ የግል አስተያየት መስጠት እንደማይገባ ገልፀውልናል።


፨የተማሪ ኤደን ገብሩን ጉዳይ በተመለከተ የሚኖሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሁዋዌ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የአይሲቲ ስልጠና ማዕከሉን አስጀመረ።

ማዕከሉ ተማሪዎች በኢንስቲትዩቱ ከሚሰጣቸው መደበኛ ስልጠና በተጨማሪ ክህሎት የሚጨብጡበት ይሆናል ተብሏል።

የስልጠና አሰጣጡ የገጽለገጽ እና የonline አማራጮች እንዳሉት ተገልጿል።

በኢንስቲትዩቱ የ HUAWEI ICT Academy የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አስተባባሪ
ቤተልሔም መስፍን፥ በማዕከሉ የሚሰጥ ስልጠና በአገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ ያሉ የሙያተኞች ፍላጎት ለመሙላት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።

ሁዋዌ በኢትዮጵያ ከ43 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየሠራ የሚገኝ ሲሆን የሚሰጠውን ስልጠና በብቃት ለሚያጠናቅቁ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ይሰጣል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ትግራይ

በትግራይ ክልል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ።

ላለፉት ዓመታት በትግራይ ክልል አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት ዛሬ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ትምህርት የሚጀመረው ሁሉ ነገር ተሟልቶ ፤ ችግሮች ሁሉ ተፈተው ሳይሆን ትውልድን ለማስቀጠል ሲባል መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቆ ነበር።

ዛሬ ትምህርት ከተጀመረባቸው ት/ቤቶች መካከል የኤርትራ ጦር ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት የተነገረው " ማይመኸደን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በእንደርታ ወረዳ የሚገኘው ሓሬና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ይጠቀሳሉ።

ምንም እንኳን በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም በተማሪዎች ሆነ በወላጆች ዘንድ ትምህርት መጀመሩ ደስታን እና ተስፋን ፈጥሯል።

በትግራይ 85 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ባለው ነገር ትምህርት ቢጀምሩም አሁንም የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተፈናቃይ ዜጎችን አስጠልለው ይገኛሉ።

ፎቶ ፦ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት

#BringTigrayChildrenBacktoSchool

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Reminder

ጤና ሚኒስቴር በግንቦት 2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ብቻ ይጠናቀቃል።

የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት በኦንላይን መመዝገብ ትችላላችሁ።

ከተጠቀሰው ጊዜ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ  የዩኒቨርሲቲዎች አምሳለ ችሎት ውድድር አሸነፈ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ  እና በፌደራል ፍትህ እና ህግ ኢንስቲትዩት ትብብር ሲካሄድ የቆየው 7ኛው አገር አቀፍ የኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች  የምስለ-ችሎት  ውድድር በጎንደር ዩኒቨርስቲ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በፍጻሜ ውድድሩ አዘጋጁ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲ 2ኛ እንዲሁም ድሬደዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የዋንጫና የሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል።

ጎንደር ዩኒቨርስቲን ወክለው የተወዳደሩት የ5ኛ አመት የህግ ተማሪ የሆኑት ሰላማዊት አሰፋ፣  ኢያሱ ጨቅሉ እና  መክሊት ጌጡ ሲሆኑ አሰልጣኛቸው ደግሞ የህግ መምህር የሆነው አቶ ሃይለማርያም በላይ ናቸው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ስለ ውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች‼️
° ከእስያና ከአውሮፓ ሀገራት ጋር የስምምነት ሥራዎችን ተጀምረዋል።

° የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ጭምር በማሰልጠን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነወ።

° ዜጎች ስራው ካልተመቻቸው መጥፋት ሳያስፈልጋቸው ይቀየርልን የሚሉበትን አሰራር ተዘርግቷል።

° ዜጎች ለፓስፖርት፣ ለጤና ምርመራ ለአሻራ ከሚከፍሉት ውጪ የሚያወጡት ወጪ የለም።

° ባለፉው ዘጠኝ ወራት ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በሥራ ፈላጊነት ተመዝግበዋል።

° ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ከሚኒስቴሩ ድረ-ገጽ መመልከት ይቻላል።

° በውጪ ሃገር የሥራ እድል ላይ መመዝገብ የሚቻለው በዲጂታል አማራጭ ብቻ ነው

ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለሶሰተኛ ሚስትነት ተማሪዋን ከትምህርት ቤት የጠለፉት በቁጥጥር ስር ዋሉ!

ከሰንበቴ ከተማ የተጠለፈቸው ወጣት በባቲ ከተማ አስ/ር ፖሊስና ሚሊሻ 3 ጠላፊዎችን ጨምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተማሪ ሀምዲያ አህመድ ወሌ ትባላለች ሠንበቴ 04 ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን በቀን 20/8/2015 ዓ/ም  1ኛ.አልይ አመድ ሙሴ፣ 2ኛ.አህመድ አደም፣ 3ኛ.አልይ አሜ መሀመድ የተባሉት ግለሠቦች በተራ ቁጥር 1 ለተጠቀሰው ግለሠብ ለአቶ አልይ አመድ ሙሴ 3ኛ ሚስት ለማድረግ በማሰብ ልጅቷን ከትምህርት ቤት በባጃጅ በመጥለፍ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አ.አ B23937 በሆነ መኪና በአዴሌላ ገዋኔ አዋሽ ሰባት ከደረሱ በሗላ ተመልሰው በሚሌ ባቲ ሲሄዱ የባቲ ከተማ  አስ/ር ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በጋራ በመሆን ልጅቷንና 3 ጠላፊ ግለሠቦችን ከነመኪናው በቁጥጥር ስር በማዋል ከሰንበቴ ከተማ አስ/ር ፖሊስ  ማስረከብ ተችሏል ሲል ከባቲ ከተማ አስ/ር ፖሊስ ኮሚኒኬሺንና ሚዲያ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#አቸኳይ_መልዕክት ♨️

በ2015 ዓ/ም ከጥቅምት 15 ጀምሮ አዳዲስ ተማሪዎች እየመዘገብን እና እያስተማርን የቆየን መሆናችን ይታወቃል።
በ2015 ዓ/ም በ5 ክፍል ተማሪዎች እያስተማርን ነበር አሁንም እስከመጨረሻው በዚሁ የምንቀጥል መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
ለትምህርት ጥራት እና ለተማሪዎች ውጤታማነት ስባል የ2015 ትምህርት ዘመን የ2015 ተፈታኞች ምዝገባ የሚቆምበትን ቀን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

🕹ከዛሬ (ሚያዝያ 24) ጀምሮ አዲስ  የEntrance Hub ቤተሰብ መሆን የሚቻለው እስካ ግንቦት 6 2015 ዓ/ም[ may 14  / 2023] ብቻ! መሆኑን እንገልፃለን
የ2015 የምዝገባ ፕሮግራም ግንቦት 6 ከሌሊቱ 6:00 ስሆን የሚቆም ይሆናል።
ከግንቦት 6 2015 በኃላ ማንኛውም አዲስ ተመዝጋቢዎችን አንቀበልም!!
  ከዚህ በፊት በEntrance Hub ተመዝባችሁ ቤተሰብ የሆናችሁ ይህ መልዕክት እናንተን አይመለከትም😊
እናንተ እስከ ፈተና ቀን ድረስ አብረን እንጓዛለን።
አዲስ መመዝገብ ለሚትፈልጉ ዛሬ በራችን እስከ ግንቦት 6 ክፍት ነው😊
💫ለመመዝገብ ይህን ቦት ይጠቀሙ👇
     ➠   
@EntranceHubBot
💫ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎብኙ 👇
       
@ENTRANCEHUBETHIOPIA
    ✉️እኛን ለማግኘት ከፈለጉ ያናግሩን
          
@EntranceHub_Admin