መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
#በሃገራችን_በኢትዮጵያ_ጥር_4_የቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸውን_ #13ቱ_ቦታዎች_እንጠቁማችሁ_
**** #ደብረ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስና_መካነ_ጎልጎታ_ማርያም_ቤ_ክ_ማዕከላ_ለአዲስ_አበባ /መሐል አዲስ አበባ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አጠገብ የሚገኝ፤ ታቦተ ሕጉ ከኢየሩሳሌም የመጣና በአዲስ አበባ ብቸኛው የወልደ ነጐጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ./፤ (አዲስ አበባና በአካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንድንገናኝ ይሁን)

1ኛ) #ደቡብ_ወሎ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ጥንታዊው ደብር፤ ከመካነ ሥላሴ አጠገብ የሚገኝ/፤ (መላው ወሎ በዚሁ ደብር እንገናኝ/
2ኛ) #ሐይቅ_ደብረ_ነጎድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ (የሐይቅና የደሴ ነዋሪ በዚህ ታላቅ ደብር እንገናኝ)
3ኛ) #ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /#ከታላቁ_ደብር_ከደብረ_በንኰል_ገዳም_አጠገብ/ (ሰለኽላኻ ሽሬና አካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ)
4ኛ) #አደቁዋረክ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ማኅበረ ዴጎ አጠገብ/፤ (አኵስምና በአካባቢው ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ)
5ኛ) #ገደፈና_ዮሐንስ /ማይጨው አጠገብ/፤ (ማይጨው ራያና መቀለ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ)
6ኛ) #ዣት_ደብረ_ፀሐይ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ሰሜን ሸዋ፥ ጅሩ/ (ሙሉ ሸዋ በዚሁ ደብር እንገናኝ)
7ኛ) #ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ /ደምበጫ አጠገብ/፤ (ጎጃም በሙሉ በዚሁ ደብር እንገናኝ)
8ኛ) #ዘንስር_ደብረ_ተድላ_ዮሐንስ_ማዕከላ_ለጐንደር፤ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፤ በጎንደር ከተማ የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ወደ ግምጃ ቤት ማርያም ከመዛወሩ በፊት በብቸኝነት የጎንደርና የመላው ኢትዮጵያ ሊቃውንት የማኅሌተ ጽጌን ቁመት ለመቆም የሚተሙት ታላቅ ደብር/፤ (ጎንደርና አካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንገናኝ)
9.1ኛ) #ደብረ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስና_መካነ_ጎልጎታ_ማርያም_ቤ_ክ_ማዕከላ_ለአዲስ_አበባ /መሐል አዲስ አበባ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አጠገብ የሚገኝ፤ ታቦተ ሕጉ ከኢየሩሳሌም የመጣና በአዲስ አበባ ብቸኛው የወልደ ነጐጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ./፤ (አዲስ አበባና በአካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንድንገናኝ ይሁን)
9.2ኛ) #ምስካየ_ኅዙናን_መድኀኔ_ዓለም_ገዳም (ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ባይከብርም ከጥንት ጀምሮ በውዳሴ በቅዳሴ ይከበራል፡፡)
10ኛ) #ቦኮሙራ_ወልደ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ ቤ.ክን /ሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሚሻ ወረዳ ቦኮሙራ ቀበሌ/፤ (በሀድያ፣ በስልጤ፣ በጉራጌና በደቡብ የምትገኙ ሁሉ በዚሁ ደብር እንድንገናኝ ይሁን፡፡)
11) #ናዝሬት_ደብረ_ፍስሐ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ቤ/ክ
12) #ደሴ_ዩኒቨርሲቲ_ደብረ_ነጎድጓድ_ቤ/ክ
13) #መቱ_ደብረ_ሳሌም_ሐይቅ_ደብረ_ነጎድጓድ_
#በሠረገላ_ተመሠለት_ቤተ_ክርስቲያን_ደብረ_ተድላ(#ደብረ_ነጐድጓድ_/#_ዮሐንስ_/)፤/፪/
#እንተ_፬ቱ #_ገበዋቲሃ_፬ቱ_ወንጌላውያን፡፡/፪/
#ሰላም ለከ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ፤
ሰላም ለከ ዮሐንስ ታዎጎሎስ፡፡
ሰላም ለከ ዮሐንስ ፍቊረ እግዚእ፤
ሰላም ለከ ዮሐንስ ድንግል፤
ሰላም ለከ ዮሐንስ ዘረፈቀ ውስተ ሕፅኑ ለኢየሱስ፡፡
@petroswepawulos
#ጥር 4 ተዝካረ ፍልሰቱ #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሐዋርያ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ

#በተለያዩ_ቅጽል_ስሞች_የሚጠራ፤ (100 አካባቢ ከሚጠጉ ስሞቹ ጥቂቶቹን /21ዱን ስሞች ከጽሑፍ በስተመጨረሻ ይመልከቱ)
#ሰዓሊ_የኾነ፤ የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለ፡፡
#ከ81ዱ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሎች_5ቱንና_ሌሎች_መጻሕፍትንም_(ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤
#ብዙ_ደቀ_መዛሙርትን_ያስተማረ

#share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ
ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡
✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤)
✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤)
✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /እመጽሐፈ ሰዐታት/

፨ ‹‹ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፤
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ›› /መልክአ ኢየሱስ/
፨ ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዓሞ፤
ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፤
ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፤
ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፤
ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ፡፡ /መልክአ ሥዕል/

#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ
ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡
ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
ወልደ #ዘብድዮስ
ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥
ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ
ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡)
ዮሐንስ #ወንጌላዊ
ዮሐንስ #ድንግል
ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡

1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ)
2. ዮሐንስ ድንግል
3. #ዮሐንስ_ፍንው
4. #ዮሐንስ_ካህን
5. #ዮሐንስ_ኅሩይ
6. ዮሐንስ ሥርግው
7. #ዮሐንስ_ምዑዝ
8. ዮሐንስ ቅኑይ
9. #ዮሐንስ_ማኅቶት
10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ
11. #ዮሐንስ_ክቡር
12. ዮሐንስ ጻድቅ
13. #ዮሐንስ_ረድእ
14. ዮሐንስ ማኅቶት
15. #ዮሐንስ_ድንግል
16. ዮሐንስ ንጹሕ
17. #ዮሐንስ_ለባዊ
18. ዮሐንስ መረግድ
19. #ዮሐንስ_ዕንቈ
20. ዮሐንስ መልአክ
21. #ዮሐንስ_ኪሩብ
22. #ቁጽረ ገጽ
ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡

ዓለምን ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገድ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው ካዛም እንዲህ አለ እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራቹ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም ፡፡ እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ፡፡ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡
በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን

#share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ

✤✤✤✤በኢዲስ አበባ ማክበር ለምትፈልጉ✤✤✤✤
✤✤✤✤✤#ደብረ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስና_መካነ_ጎልጎታ_ማርያም_ቤ_ክ_ማዕከላ_ለአዲስ_አበባ /መሐል አዲስ አበባ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አጠገብ የሚገኝ፤ ታቦተ ሕጉ ከኢየሩሳሌም የመጣና በአዲስ አበባ ብቸኛው የወልደ ነጐጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ./፤ (አዲስ አበባና በአካባቢዋ ያላችሁ በዚሁ ደብር እንድንገናኝ ይሁን)

✤✤ሥርዓተ ማኀሌቱን ከታች ይመልከቱ::
#ጥር 4 (#የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል ፤ የአባ ናርዶስ ዘደብረ ቢዘን እረፍቱ ፡፡ የጊዮርጊስ፤ የሊቀ ጳጳሳት ማርቴና፤ የሰማዕት ታኦድራ፤ የአባ ሊቃኖስ፤ የቀውስጦስ መታሰቢያቸውም ነው፡
@petroswepawulos