ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
4.76K subscribers
455 photos
10 videos
20 files
414 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
ጥር 16

 ማር ዳንኤል
"ዘዓምድ" በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል አራቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ።

እነዚህም፦

፩.ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ

፪.ቅዱስ አጋቶን ዘዓምድ

፫.ቅዱስ ዳንኤል ዘዓምድ እና

፬.ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ናቸው።
"ዘዓምድ" የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው 'THE STYLITE' ይሉታል። የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል። ይህም በሁለት ምክንያቶች ነው።
አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው። ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ፣ አስተማሪ፣ መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው።
ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው። በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ማር ዳንኤልን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል።
ይህ ቅዱስ ሰው ሶርያዊ ሲሆን ተወልዶ ያደገባት አካባቢ በቀድሞው አጠራር "ሃገረ ዓምድ" ይሏታል።

"ማር" የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቅድስናንና አለቅነትን የሚገልጽ ስም ነው። በዚህ ስም ጥቂቶች ብቻ ሲጠሩበት ለሊቃውንትም፣ ለሰማዕታትም፣ ለጻድቃንም አገልግሏል።
ቅዱሱ "ማር" ብቻ ሳይሆን "ዘዓምድ" ተብሎም ተጠርቷል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እርሱም በፊት እንደ ጠቀስናቸው አበው ምሰሶ ላይ ተጠግቶ (ቆሞ) ትኩል ከመ ዓምድ ሆኖ በመጸለዩ ነው።
ማር ዳንኤል በምድረ ሶርያ ስመ ጥር ጻድቅ ነው። በዘመነ ጻድቃን መጨረሻ አካባቢ ከክርስቲያን ወገኖቹ ተወልዶ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ ገና በልጅነቱ ለቤተ እግዚአብሔር ተሰጥቷል።...

#መልካም_ቀን🙏🙏🙏

@MekuriyaM
ሲም እግዚኦ ዓቃቤ ለአፉየ፣
በለኒ ኵለሄ አንተኑ ወልድየ።
.
.
.
እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ፣
ፈተናን ላለፈ ይሰጠዋል ዋጋ።


@MekuriyaM
@MekuriyaM

#ሠናይ_መዓልት!
#መልካም_ቀን!
ከሰው ውለታ አልጠብቅም፣
የያዝኳት እናቴ ማርያምን አለቅም።


#መልካም_ቀን!

@MekuriyaM
#ለመናፍቃን
"እንኳን 'መንፈስ ቅዱስ ተገለጠልኝ' ብሎ ለመናገር ቀርቶ፤ጠላት ዲያብሎስ ራሱ ወዳጅነት ይጠይቃል።"
🌿ቆሞስ አባ ኤልያስ🌿
🌿 🌿 🌿

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@MekuriyaM (channel)
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@Yodahe2 (group)
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#መልካም_ቀን!
🌿 #ንነጽር_፸፯

እኛ ሰዎች ከክፉነት መልካምነት እንደሚልቅ ጠንቅን እናውቃለን።
አፈጻጸማችን ግን ለ'የቅል ነው። ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምሕረት አምላክ ነው ይምረናል ብለን ስለምናስብ።
...
እዚህ ጋር ያለን እምነት እንደው ምን አለ ልባችን ውስጥ አስርጸን በ'የ ማይክሮ ሰከንዱ ፈጣሪን ማስታወስ ብንችል?
እንግዲህ ያኔ የመልካምነትና የክፉነት ጠባይ በደንብ ገብቶናል ማለት ነው።

ይኸውልህ ወዳጄ አንድ ክፉን ሰው ወደ
መልካም ሰው እቀይረዋለኹ ብለህ አስበህ... ከሆነ ስሕተት ላይ ነህ። ምክንያቱም አንተስ መች መልካም ሰው ነህና¹? አንድም ጳውሎስ ለቆሮንቶስ መልእክቱን ሲልክ ❝ክፉ ባልጀራነት መልካሙን አመል ታበላሸዋለች❞ እንዲል
...
እናም
መልካም ሰው መሆን ካልቻልክ ስለ መልካምነት ዕወቅ። ያኔ ክፉ ሰውን መመለስ ባትችል እንኳ አንተ ጭራሽኑ ወደ እርሱ እንዳትሄድ ያደርግሃል።
ምድራችን ያጣችው ስለ መልካምነት የሚመክር ሳይሆን መልካምነትን የተዋሐደን ሰው ነው።

ወገን የሕይወት የመጨረሻ ግቡ ዕውቀት አይደለም ተግባር እንጂ👌
#መልካም_ቀን

◦◦◉●Join us
@MekuriyaM

¹አንዳንድ ሰዎች እንደምትኖሩ አምናለኹ
#ሰማዕቷ ፌብሮኒያ

መግቢያ፦ ሰይጣን አራት ነገሮችን ይጠላል እነሱም፦ ትህትና፣ ድንግልና እወቀትና ንጽሕና እነዚህ የምግባራት አምዶች ናቸው፤ በዚህ ዘመን ንጽሕናን ጠብቆ ማቆየት በሰነፎች ቋንቋ "ፋርነት" ሆኗል፡፡ ጠላት በቀላሉ የሚማርካቸው (የሚነጥቃቸው) ተራ ነገሮች ሆነዋል፡፡ በሚያሳዝን መልኩ በዚህ ዘመን ንጽሕናን መጠበቅ የሚታፈርበት የሚያሸማቅቅ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በተለይ በሴት እህቶቻችን የሚስተዋል ነው፡፡ 

ድንግል በዚህ ዘመን ልብስ ክብረ ሳይሆን ግልበ-ክብረ፣ በዕለ-ክብረ ከመሆን ኀሳረ-ክብር ወደ መሆን ተለውጧል፡፡

ራስን መግዛት፦ በክርስትና ሕይወት ራስን መግዛት (መቆጣጠር) ለመንፈሳዊ ሕይወት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ ብዙዎች በኃጢአት ለመውደቃቸው ቃላትን በማሰማመር ካቅሜ በላይ ስለሆነ፣ ስሜቴን መቆጣጠር ስላቃተኝ፣...ወዘተ በሚሉ ቃላት ስንፍናቸውን ለመሸፋፈን፣ ሲሞክሩ እንመለከታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነገረን እግዚአብሔር ራስን የመግዛት መንፈስ ነው የሰጠን፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክታቱ ራስን ስለመግዛት በሰፊው ጽፏል፡፡ "ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ.." (1ቆሮ.7፥5) ብሎም ይመክረናል፡፡ በሌላም ሥፍራ "ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርን በመምሰል በአሁኑ ዘመን አንድንኖር ያስተምረናል..." (ቲቶ.2፥12-13) እውቀት ራስን ከመግዛት ጋር ካልሆነ ከንቱ ነው፡፡ ለዚህም ነው፣ ብዙ ያውቃሉ የምንላቸው ሰዎች ራሳቸውን መግዛት ባለመቻላቸው ክብራቸውን፣ ጸጋቸውን፣ ቅድስናቸው አጥተዋል፡፡ ስለዚህም ነው ሐዋርያው ጴጥሮስ በመልእክቱ "በበጎነትም፣ እውቀትን፣ በእውቀትም፣ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛትም መጽናትን..." (2ጴጥ.1፥6) ጨምራችሁ ያዙ የሚለን፡፡ በአሪት ዘፍጥረት ላይ ተከትቦ የምናነበው የወጣቱ ቅዱስ ዮሴፍ ራስን ስለመግዛት ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ በማር ይስሐቅ አባ መትርያኖስ የተባለ መነኮስ የገጠመውን ፈተናና እንዴት ራሱን በመግዛት ራሱንም ሌላውንም ሰው እንዳተረፈ ታሪኩ ከምንጩ እጠቅሳለሁ፡፡ "ከተግባሩ ወደ ቤቱ ሲመለስ ዘማት ተሰብስበው ይህ መነኩሴ ኃያል ነው የሚያስተው የለም አሉ፡፡ አንዲቱ እኔ ባስተውስ ባታስችውስ ተወራርደው መጣች ቀን የሆነ እንደሆነ አይቀበለኝም ብላ ሲመሽ ከደጅ ቆማ እጅ ጸፋች (አንኳኳች)፡፡ ወጽቶ ምንድርነሽ አላት ከሩቅ ሀገር የመጣሁ የእግዚአብሔር እንግዳ የምጸጋበት አጥቼ አለችው ያወጣ ያወርድ ጀመረ ብትገባ ፆር ይነሣብኛል አይሆንም ብላት ነግደ ኮንኩ (እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበልኸኝም) ብሎ ይፈርድብኛል ብሎ ኪፈርድብኝ እታገሠዋለሁ እንጂ ምን አደርጋለሁ ብሎ ይዟት ገባ እሳቱን አነደደላት ተቀመጠች እሱ ጸሎቱን ያዘ ሠውራ ይዛለችና የምትቀባውን ትቀባ የምታጤሰውን ታጤስ ጀመረ እግሩን ከእሳት ጨመረው የሷን መዓዛ እስኪያጠፋው እስኪለውጠው እሷም ይህን ተመልክታ ከዚህ ሁሉ ያደረስኩ እኔ እንጂ ነኝ አባቴ አላበጀሁም ማረኝ ብላ ንስሐ ገብታለች፤ አንድም ገልጻ እንተኛ አለችው ከእሳቱ አንጥፊ አላት ይህማ እሳቱ ይፈጀን የለም አለችው፡፡ የዚህን ዓለም እሳት ካልቻልነው የወዲያኛውን እንደምን እንችለዋለን ይሆንልሽ እንደሆነ አንጥፊው አላት፡፡ ነገሩን አይታ አባቴ አላበጀሁም ማረኝ ብላ ንስሓ ገብታለች ራሷን ላጭቶ አመንኵሶ በዓቱን ለቆ ወፅቶ ሂዷል፡፡" ( ማር ይስሐቅ፣ ገጽ14 1982 ከፊል አጽንኦት የእኔ ነው) ራስን መግዛት ከላይ እንደተመለከትነው ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ከኃጢአት መጠበቅ፣ መጽናት ወሳኝ ምግባር ነው፤ ፈጣሪ ይህንን እንዲሰጠን መለመን መማጸን በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡

     ፌብሮኒያ ስለ ንጽሕናና ስለ ድንግልና ስትል ሞትን የመረጠች የሴት ጀግና ናት፡፡

በ749 ዓ/ም በግብጽ ላይ ስቃይ በወረደ ጊዜ በላዕላይ ግብጽ ከነገሱት የአማዊን ገዥዎች መካከል የመጨረሻው ገዥ የነበረው ማራዋን ኢቢን መሐመድ ኤክሚም የምትባለው ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች ገዳም ገቡ፡፡ በገዳሙ ውስጥ ያለውን ማንኛውም ዓይነት ንብረት ከዘረፋ በኋላ ፌብሮኒያ የተባለችውን ቆንጆና ድንግላዊት መነኩሲት ሊደፍሯት ፈለጉ፡፡

.
ፌብሮኒያ ራሷን ጨካኝና ግፈኛ የሆኑት ወታደሮች ፊት ለፊት አቀረበችና ወደ በአቷ ደርሳ የምትመለስበትን ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዲሰጧት ጠየቀቻቸው፡፡ ወደ በአቷ ከገባች በኋላ ራሷን በእግዚአብሔር እጆች ላይ በመጣል አለቀሰችና እርሱ እንዲመራትና አብሯት እንዲሆን ጠየቀችው፡፡

.
ከዚህ በኋላ ከበአቷ ወጣችና አስቀድማ በምሥጢር ጠብቃ ያቆየችውን በብልቃጥ ውስጥ የታሸገ ዘይት አሳየቻቸው፡፡ ከዚያም ማንኛውም ሰው በዚህ ብልቃጥ ውስጥ ያለውን ዘይት በሰውነቱ ላይ ቢቀባው የተቀባውን የሰውነቱን ክፍል ሰይፍ ሊቆጥረው አይችልም አለቻቸው፡፡ ይህን ለእነርሱ ለማረጋገጥም አንገቷን በዘይቱ ቀብታ ስታበቃ ከወታደሮቹ አንዱ ሰይፉን በአንገቷ ላይ እንዲቃጣ ጠየቀችው፡፡

ወታደሩ የተነገረውን ሲያደርግ ወዲያውኑ ጭንቅላቷ ከሌላው የሰውነቷ ክፍል ተከልሎ ወደቀ፡፡ በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ የሆነውን ነገር ሲመለከቱ እጅግ ስለ ተሰቀቁ የዘረፉትን ንብረት በሙሉ እዚያው ተዉና ከገዳሙ ወጥተው ሄዱ፡፡


#መልካም_ቀን!