ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
4.73K subscribers
454 photos
10 videos
20 files
413 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
🌘 #ንነጽር_፺፩

አንዳንድ ሰዎች
#ስኬት ማለት ብር ማግኘት ብቻ ሆኖ የሚታያቸው አሉ። ታድያ እነዚህ ሰዎች አላማዬ ሊያሳካልኝ ይችላል ብለው ከሚስቡት ሰው ውጪ ሌላ ሰው እንደ ተራ አድርገው ይቆጥሩታል። ከዚያም በትንሽ ሰዎች ዘንድ ተፈላላጊነትን፤ ከብዙ ሰዎች ግን መራራቅን ያተርፋሉ።
◦ ◦ ◦
ወዳጄ
#ስኬት_ማለት_በታናሽም_በታላቅም_ዘንድ_መከበር እንጂ በሀብት ብዛት ጭንቅላት ማሳበጥ አይደለም!
አንድም
#ስኬት_ማለት_ሠርተህና_ለፍተህ_ያመጣኸው_የሥራህ_ውጤት_እንጂ_በአቋራጭ_ባገኘኸው_ዕድል_ተጠቅመህ_በቀላሉ_ብር_መቁጠር_መቻልህ_አይደለም!

◦◎●Join us on telegram
@MekuriyaM
🌗 #ንነጽር_፺፪

ተንገዳግደህ ሳትወድቅ ከቆምክ አመስግን እንጂ ለምን ተንገዳገድኩ ብለህ አታማርር!
ወድቀው መነሣት ያልቻሉ ብዙዎች አሉ'ኮ!

ወዳጄ ቀጣይ እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ አኹን የተንገዳገድከው ምን አልባት ማስጠንቀቅያ ይሆንህ ዘንድ ይሆናል።

●◎◉Join us on telegram
@MekuriyaM
😓 #ንነጽር_፺፫

እኔ የከፋኹ ነኝ እኮ!

38 ዓመታት በበሽታ እየማቀቀ በበዛው ምሕረትህ፣ በሰፋው ፍቅርህ፣ በበረታው ክንድህ ያለ ድካምና ያለ ስስት አዳንኸው። ያዳንኸው እሱ አንተን ማመስገንና ዘለዓለም ለአንተና በአንተ መኖር ሲገባው ስለ አዳኝነትህ ጥፊን ሸለመህ።

ጌታ ሆይ አንድ ጊዜ ብቻ ነበር አይደል እጁን የዘረጋብህ? ምን አልባት ይሄ ሰው አንድ ቀን ተጸጸቶ ቢያለቅስ ይበቃው ይሆናል። ነገር ግን አምላኬ እኔ ስንት ቀናቶችን ባለቅስ ነው ለበደሌ ደመወዝ የሚሆነኝ? ስንት ቀናትን ላንባ? ስንት ሌሊታትን እንቅልፍ ልጣ? ስንት ስንት? እኮ ስንት ዓመታትን ልጸጸት?

በአካል አግኝቼ በጥፊ ባልመታህም፤ የጸሎቴን ምላሽ ስታዘገይብኝ እኮ በምናብ ስዬ ደጋግሜ መትቼሃለው።
በአካል አግኝቼ ባልዘባበትብህም፤ ያው ትሰማለህ ብዬ እኮ ስድብን ሸልሜሃለው።
ክርስቶስ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ እኮ እጅ በሌለው ምላሴ መትቼሃለው።

ታድያ ስንት ዘመናት ብጸጸት ይበቃኛል? መሐሪ ነህ አውቃለው ዕድሜ ልክህን እየተጸጸትኽ ኑር አትለኝም። ወደ አንተ የመምጫ ጊዜዬ ሊደርስ ሲል ድጋሚ እንዳልመታህ እባክህን የመመለሻ ጊዜ ስጠኝ?😓

ምንም እንኳ ስሜ
#መጻጕዕ ባይሆንም #ከመጻጕዕ የከፋሁ #የመጻጕዕ ቀዳሚ #መጻጕዕ መሆኔን አልዘነጋም!

◦◎●Join us on telegram
         
@MekuriyaM

         🌘Dn Mekuriya Murashe
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (፩ Mekuriya Murashe)

🫳 #ንነጽር_፺፬

ፍቅር ኃይል የሆነ ኃይል አለው አይደል? አዎ አለው ግን ያ ኃይል እኮ ከፍቅር ያንሳል! ስለዚህ የግዴታ ፍቅርን መናገር ሳይሆን መኖር ይኖርብሃል ማለት ነው ምክንያቱም ስትኖረው ልኬት ታጣለታለህ። ያኔ ፍቅር ኃይል አለው አትልም ዝም ትላለህ እንጂ!
ወዳጄ በምላስህ ጫፍ ስለምታንቀረቅራት ብቻ የፍቅርን ዋጋ አታሳንሳት። ፍቅር እኮ ሞትን የምታስንቅ ናት!

◦◦◉Join us on telegram
        
@MekuriyaM
Forwarded from ፩ Mekuriya Murashe
🌎 #ንነጽር_፺፭

❝አባዬ ዓለም
#ለማን_ታዳላለች?❞

ልጄ ዓለም ለኹሉም እኩል ናት። ነገር ግን ለአንዳንድ ሰዎች የምታዳላ ይመስለኛል።

እነዚህም ሰዎች፦ በዚህ ዓለም ውስጥ ሲኖሩ ብዙ መከራን፣ ስቃይን፣ ዕንግልትን፣ ፈተናን፣ ውጣ ውረድን የመሳሰሉ ክፉ ነገሮች ደጋግመው ይገጥማቸዋል። ልጄ ዓለም የምታዳላው ለእነዚህ ሰዎች ይመስለኛል።

ምክንያቱም በዚህ ዓለም ውስጥ ስትኖር ብዙ ሕመም ካየህ፣ ብዙ ከቆሰልክ፣ ብዙ መከራ ከደረሰብህ ለማያልፈውና ዘለዓለማዊ ወደሆነው ዓለም መግቢያ ላይ ነህ ማለት ነው። ስለዚህ ዓለም ለእነዚህ ሰዎች ታዳላለች።

ይህች ዓለም ብልጭልጭታ ነገርን አጥብቃ ትወድዳለች፤ አንተ ግን የአንቺን ውዴታ አላሟላም ብለህ ከእሷ ከሸሽህና ፈተና ከደረሰብህ ዓለም እያዳላችልህ ነው ማለት ነው።

ይህቺ የምናያት ትርኪምርኪ የሆነች ምድር ከጠላሃት ያቺ የማታያትን ነገር ግን ተስፋ ወደምታደርጋት ዓለም ታስጠጋሃለች። ስለዚህ ዓለም እያዳላችልህ ነው።

ልጄ አትሳሳት ሰዎች ገፉኝ ብለህ መቼም እንዳትቆጭ፣ ፈተናው ማለፍ ተሳነኝ ብለህ መቼም ተስፋ እንዳትቆርጥ። ይህቺ አኹን ያለህባት ዓለም ስታሳድድህ ብቻ ነው ገነትን ልታገኛት የምትችል። ይህች ገነት ደግሞ በብዙ መከራና ጭንቅ እንጂ በብዙ ደስታና ጭፈራ አትገኝም።

መከራው ሲበዛብህ ነገን አሻግረህ ተመልከት። ፈተናው ሲደጋገምብህ ዓለም እያዳላችልህ እንደሆነ አስብ።

ለእውነተኞች ሰዎች ዓለም ሁሌም ታዳላለች በመከራ እየገፋች ወደ ዘለዓለማዊ ክብር ታደርሳለች።

ለእኛም ዓለም ስቃዩን ታብዛብንና ወደ'ዛኛው ዓለም ትቀላቅለን🙏

   ይህ ጦማር በ ፲/፰/፪፻፲፮ ዓ.ም በዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ ተከተበ
#እውነተኛ_ሰዎች ናቸው ብለው የምታምኗቸው ሰዎች ዘንድ አድርሱት።

◦◉◉Join us on telegram
@MekuriyaM
🧬 #ንነጽር_፺፮

❝የሕይወት ትርጕሟ ምንድር ነው አባዬ?❞

ልጄ በእኛ በዓለማውያን ዘንድ ለሕይወት ትርጕም ሰጥተናታል ወይም ለሕይወታችን ትርጕም አላት ለማለት ያዳግታል።

ነገር ግን ልጄ የሕይወት ትርጕሟ የምትገለጥባቸው ሰዎች ከሞላ ጎደል አሉ። እነሱም እኔና አንተ በምንገኝባት ዳንኪራ በበዛባት ዓለም ውስጥ አይኖሩም። ጊዜአቸው ሙሉ ለእግዚአብሔር የሰጡና ኑሮአቸው ከእርሱ ጋር በበረሐ፣ በገዳም ያደረጉ ሰዎች ካየህ የሕይወት ትርጕም እነርሱ ናቸው።

በዚህ እኔና አንተ ባለንበት ሕይወት ውስጥ ጎልቶ እየታየ ያለው ጭካኔና ንቅት ነው። እነዚህ ደግሞ ከሕይወት ትርጕም ተቃርነው የሚቀመጡ እንጂ የሕይወት ትርጕሟ አይደሉም።

በሥጋ የሞተላቸው ኢየሱስ ክርስቶስን እነርሱም መልሰው ሥጋቸውን ሲገድሉለት፣ የተሰቀለላቸው ክርስቶስን እነርሱም መልሰው መጥፎ ሐሳባቸውን ሲሰቅሉለት ካየህ እነዚህ ሰዎች የሕይወት ትርጕም ናቸው።

ስለዚህ ልጄ የሕይወት ትርጕሟ በደንብ እንዲገባህና እንድታየው በመንፈሳዊ ሕይወት መመላለስን ቸል አትበል።

◦◦◉◉Join us on telegram
@MekuriyaM
😢 #ንነጽር_፺፯

አሰሩህ፣ በጥፊ መቱህ፣ ደበደቡህ፣ ተዘባበቱብህ፣ ምራቃቸውን ተፉብህ፣ አዳፉህ፣ ሰቀሉህ... ነገር ግን ይቅር አልካቸው።
የተነሣሁብህ ሆይ፥ የሰቀሉህ እነ'ሱ ትንሣኤህን ባዩ ጊዜ ምን ብለው ተረቱ?

እኔስ እንደ ምርጥ ዕቃህ እንደ ጳውሎስ እንዲህ አልኩ “ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥55

ከኃጢአት የመመለሻ በዓል ይሁንልን!
ዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ

They arrested you, slapped you, beat you, abused you, spat on you, hunted you down, crucified you... but you forgave them.
I have risen from you, what did those who crucified you say when they saw your resurrection?

And I, as your best vessel, said like Paul, “O death, where is your sting? Hell, where is your victory?”
— 1 Corinthians 15:55

Let us celebrate the return from sin!
D/n Mekuria Murashe
😓 #ንነጽር_፺፰

ከሰኞ እስከ ዕለተ አርብ ድረስ እየሰቀልኩት ነበር፤ አልሰቀል ብሎ አስጨንቆኝ፤ ግን የተሰቀለው ክርስቶስ ረዳኝ መሰለኝ ልክ ዕለተ አርብ ላይ ሰቅዬ ጨረስኩት። በዚያው ዕለት ደግሞ ከጌታዬ ጋር መቃብር ውስጥ ጨመርኩት። ዛሬ በዕለተ እሑድ ክርስቶስ ሲነሣ እኔ ቀብሬው የነበረው ግን አልተነሣም።

ሳስበው ግን እንዳይነሣ ያደረገው ሞቶ የተነሣው ክርስቶስ ነው። ምክንያቱም ስሰቅለውና ስቀብረው ያየው እርሱ ነበራ! ተነሥቶ እንዳይከተለኝ አጥብቄ የለመንኩት ለክርስቶስ ነበራ!

ስሰቅለው ግን በጣም ነበር ያስቸገረኝ። አንዱን ስሰቅለው ሌላ ይመጣል፤ ጨርሼ ሰቀልኩ ብዬ ላርፍ ስል ሌላላ ይታወሰኛል። እያልኩ እያልኩ ከሰኞ እስከ አርብ ደረስኳ። አርብ ከስንት ስቃይ በኋላ ሰቀልኩትና ዕረፍትን አገኘኹ። መሰቀሉን ያረጋገጥኩት ደግሞ በዕለተ አርብ መጨረሻ ላይ እካህኑ ጋር ሄጄ ጠብጠብ... ጠብጠብ...እያደረጉ ቃሌን የሰጠኋቸው ጊዜ ነው።

ጌታዬ ሆይ በዕለተ አርብ የሰቀልኳትን
#ኃጢአቴን ትንሣኤ ስለሌላት በብዙ እባርክሃለው። እኔ እንደሰቀልኳት አንተ ደግሞ ቀብረህ አስቀርተሃታልና አመሰግንሃለው🙏

#ኃጢአቴን_ነው_የቀበርኳት!

መ ል ካ ም የ ት ን ሣ ኤ በ ዓ ል !

@MekuriyaM
👌 #ንነጽር_፺፱

ትሕትና ማለት ለካ ከልብ ዝቅ ማለት እንጂ ከላይ ከላይ ዝቅ ማለት አይደለም።
ጣዕም አለው ለካ ትሕትና! ለዚያ ነዋ አባቶቻችን ራሳቸውን ዝቅ እያደረጉ ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጸጋ የሚጎናጸፉት!

ይህንን ጽሑፍ ደርሷችኹ ማንበብ ከቻላችኹ በሕይወታችኹ ዛሬ አንድ ቁም ነገር ለመሥራት ብቁ እስኪ!
የእውነት ከልቤ ልምከራችኹ ያለምንም ማጉረምረምና መሳቀቅ ከልብ ዝቅ ማለትን ተለማመዱ።

ከልብ ዝቅ ማለትንና ትሕትናን ልትላበሱ ወስናችኹ እንደሆን አንድ መንገድ ልጠቁማችኹ ነው።

ወዲህ ወድያ እየተረማመሰ የምታዩት ሰው ላይ ምንም ሐሳብ አይኑራችኹ። ከላይ ከፍ የሚያደርግ አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ብቻ ልብ በሉ። ክርስቶስን በልባችኹ አንግሡት!

እደግመዋለው!
   የምታውቃቸውም ሆነ የሚያውቁህ ሰዎች ሁሉንም ጠቅለል አድርግና የሆነ ቦታ ስጣቸው። አዕምሮህ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥጦታዎችና ሀብቶች ብዛት እንዲመላለሱ ፍቀድ። እነዚያ ጸጋዎች በሙሉ ከትሕትና ሥር መቀመጣቸውን አገናዝብ። እናማ ሰዎች የፈለገ ነገር ያድርጉልህ/ያድርጉልህ፤ አንተ ግን ኢየሱስን በልብህ ዙፋን አስቀምጠውና መሬት መሬቱን ውደድና ከመሬት ተቀመጥ ትልቅ ክብር አትፈላልግ።

ይኸውልህ
ሰዎች ያልክ እንደሆነ ስለ አንተ አይገዳቸውም። እመነኝ ብትራብም ሆነ ብትጠማ ከልቡ እኔን የሚልህ ልታገኝ አትችልም! ስለዚህ ከልብህ ዝቅ በልና በእግዚአብሔር ታመን እንጂ!

ያኔ ከልብ ዝቅ ማለትን ክብርን እንደሚሰጥ፤ ትሕትና ደግሞ የተለየ ደስታና ሰላም እንዳለው አይቶ መጓዝ ብቻ ነው!
'በጊዜው ከፍ ለማለት ለጊዜው ዝቅ ማለት'ን ይበጃልና ዝቅ በል ዝቅቅቅ!

◎●●Join us on telegram
      
🛑 #ንነጽር_፻ |100|

#ሕጻናት_በነበርን_ጊዜ
የእግዚአብሔርን መኖር አናውቅም። ከእናትና ከአባታችን በቀር ማንም ጠባቂ እንደሌለን ነበር የምናውቀው። ከወላጆቻችን በላይ የምንቀርበውም ሆነ የምንወደው ማንም አልነበረም።

#ትንሽ_ከፍ_ስንል
ሰዎች "እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር' ሲሉ ስንሰማቸው 'እግዚአብሔር ማን ነው?' ብለን መጠየቅ ጀመርን። ከዚያም 'እግዚአብሔር አይታይም፥ ድምጹም አይሰማም እሱ ግን ለሁላችንም ያየናል። ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ስናደርግ ይመለከተናል።' ተብሎ ስለሚመለስልን እግዚአብሔርን እንፈራው ነበር።

#ወደ_ወጣትነት_ስንሸጋገር
እግዚአብሔርን አወቅነው ግን መግለጥ ተሳነን። መኖሩንም አረጋገጥን ግን መፍራት ከበደን። ተቅበዘበዝን የምንይዘው፣ የምናየው ነገር በሙሉ እኛን አናስቆም አለ። ያኔ ልጅ እያለን እናትና አባታችንን እጅግ እንወድ የነበርነው መልካም ሕጻናቶች እዚህ ጋር ስንደርስ እነርሱን መሳደብና መምታት ጀመርን። ትንሽ ካደግን በኋላ እንፈራው የነበረውን እግዚአብሔር ወደ ጎን ገፍተር አደረግነው።

#ከዚያም_አለፍንና
አባት ወይም እናት ወደ መሆን በቃን። ልጅም ኖረን። "ለልጆቻችን ስለ እግዚአብሔር መናገር እያለብን፤ ለእግዚአብሔር ስለ ልጆቻችን መናገር ጀመርን።" እኛ ላይ ደርሶ ያየነው አላዋቂነት ለልጆቻችንም ለማትረፍ በቃን። ከመንግሥቱና ከጽድቁ ይልቅ ስለ ልጆቻችን ማሰብ ጀመርን። ከእግዚአብሔር ራቅን። ከልጅነት እስከ ሽምግልና ድረስ ያለውን ዘመናችን እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከመታዘዝ ይልቅ፥ በዓለም ዲስኩር ታጅበን፣ በብልጭልጭታው ታጭቀን፣ በዘፈን በዳንኪራው ተመስጠን፣ በዲያቢሎስ ሐሳብ ተውጠን ይኸው ዛሬም እዚያው አለን።

❝አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይኹን!❞

◍◍◍Join us on telegram
@MekuriyaM
🌿 #ንነጽር_፲፩

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  — ፊልጵስዩስ 4፥6

ሐዋርያው "አትጨነቁ" ሲል ምን ማለቱ ነው? እንዴት ነው አለመጨነቅ የምንችለው ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም።
:
በእርግጥ ምንም እሚያስጨንቅ ነገር የለም ማለት አንችልም። ምክንያቱም
#ጭንቀት ባይኖር ኖሮ #አትጨነቁ ባልተባልን ነበር።

እንዲሁ
#አትጨነቁ ብቻ ብሎ ዝም ቢለን፤ ታድያ ምን እናድርግ ማለታችን አይቀርም ነበር። ነገር ግን ከእነ መፍትሔው ስለተቀመጠልን #ጭንቀትን የማስወገድ አቅማችን እጅግ እንዲጨምር ያደርገዋል።

እኛ ለጌታ ሩቅ ብንሆንም እርሱ ለእኛ ቅርብ እንደሆነ ገና ከጅምሩ ተስፋችንን እንዲለመልም አበሠረን። ቀጠለና በክፉም በደጉም ወደ ፈጣሪያችን መጮህ እንዳለብን ነገረን። ምክንያቱም እርሱ ለእኛ ቅርብ ነውና።

#የሚያስጨንቃችኹን ነገር እስኪ ለአንዳፍታ ቆም ብላችኹ አስቡት..... ይሄኔ'ኮ በአላፊ ጠፊ ነገር ትጨነቁ ይሆናል። ግዴ'ለም በጸሎትና በምልጃ ከምስጋናም ጋር ወደ እግዚአብሔር ጩኹ እንጅ በአ ን ዳ ች #አትጨነቁ
አንድ ሰው ሲጨነቅ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን እየተጠራጠረ ነው ወይም አያምንም ማለት ነው።

አንድ ሰው ሲጨነቅ በእግዚአብሔር ቃል ይጠራጠራል ወይም ማመን ከብዶታል ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ተጨንቀን እናውቃለን። ይህን ቃል ሥናስታውስ ግን ጭንቀታችን እንደሚቀል 100% እርግጠኛ ነኝ።

ይህን በመሰለው ግን
#መጨነቅ ይገባናል እላለኹ👇

“በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።”
  — 2ኛ ቆሮ 2፥4

JOIN
@MekuriyaM
👁‍🗨 #ንነጽር_፻፩

   ፍቅር   ይዞኛል

አዎ አልዋሽም ይዞኛል፡
የማፍቀር ወግ ደርሶኛል።
መቼም አትሰለቸኝ፡
ፍቅሯም ተመቸኝ።
ደግሞ ሁሉም ይወዳታል፡
በእንተዝ ናፈቅረኪ ይሏታል።

ከምድር ያይደለ ነው እንጂ ከአርያም፡
ፍቅር ይዞኛል ከድንግል ማርያም

◦◦◦JOIN US ON TELEGRAM
          @MekuriyaM
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (Mekuriya ፩)
🌿 #ንነጽር_፳፰
ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች "ሕይወት ውስብስብ ናት፤ ፈተናዋም እጅግ የበዛ ነው።" ሲሉ ይደመጣሉ።
◦◦◦
አዎ ትክክል ነው... በዚህ ምድር ላይ ከኖርክ አይቀር ትወሳሰባለህ፤ ትፈተናለህም!
◦◦◦
ነገር ግን ወዳጄ የአንተ የሕይወት መስመር ልትረዳው የምትችለው በገጠሙህ ፈተናዎች አይደለም፤ በገጠሙህ ፈተናዎች ላይ በሰጠኸው ምላሽ እንጂ።

ሰላም ለምድራችን🙏
@MekuriyaM
ፍቅር ለሕዝባችን🙏
#ንነጽር_107

የቀረ ነገር አለ!

ወተት ውስጥ ጥቁር ነገር ወይም ደስ የማይል ሽታ ያለው ነገር ገብቶበት ካየኸው ወተቱን ትደፋዋለህ። ማር ቢገባበትሳ? ከወተቱ የበለጠ ጣፋጭ ነገር ስለተጨመረበት ብለህ ትጠጣዋለህ እንጂ አትደፋውም አይደል? ነገር ግን ጣዕሙን ይቀይረዋል፤ ከወተትነት ጣዕም ሊወጣ ይችላል።

አየህ! ከዚያ በኋላ ግን ወተት ጠጥቻለሁ ብለህ ከተናገርክ ውሸት ተናግረሃል ማለት ነው። ምክንያቱም የወተቱ የራሱ ጣዕም ብቻ አይደለም ያጣጣምከው፤ የጠጣኸው ወተት ብቻ አይደለም ከማር ጋር ነው የጠጣኸው።

ጣዕሙን ይበልጥ ማራኪ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን የወተቱ ጣዕም ብቻ እንዳልሆነ ልብ በል!
በዚያው ተቃራኒ ሊያበላሸውም ይችላል። ሊያበላሸው የቻለው ማሩ እንደሆነም ጠንቅቅ!

ላወራ የፈለግኩት ስለ ወተት ጣዕም አይደለም!

ወዳጄ! ሕይወትህ ውስጥ ሊገቡ የምትፈቅድላቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? መልካም እየመሰሉ የኋላ ኋላ ግን ሕይወትህን የሚመርዙ ከሆኑስ አስበህበት ታውቃለህ? አንተ የአንተን ሕይወት መምራት አቅቶህ ስንት ሰው ጠየቅክ? ከዚያስ እነሱ በሰጡህ ውሳኔ ሄድክበት?

ምላሽህ "አዎ!" ከሆነ የእነሱ ውሳኔ በአንተ ሕይወት ላይ እያዩት ነው እንጂ እኮ አንተ የራስህን የሕይወት መንገድ እየገሰገስክ አይደለም። አንተ ጭንቅላት የለህም አታስብም? አስብ አሰላስል ት ች ላ ለ ህ!

ሁለት ተመሳሳይ ስልኮች በአንዳንድ እጅህ ያዛቸው። ከዚያም አንደኛው ላይ Data on አድርግና Internet ተጠቀም። አንደኛው ላይ ግን Data'ውን off አድርውና Internet ለመጠቀም ሞክር። ልዩነት ፈጥረሃል አይደል? ለዚያውም ትልቅ ልዩነት ነገር ግን ሁለቱም ተመሳሳይ ስልኮች ናቸው። የሁለተኛውን ስልክ Data on ብታደርገውስ እሱም እንደ መጀመርያው ይሠራል።

ስለ ስልክ አጠቃቀም ልነገርህ አይደለም!

አንተ ጋር የሆነ የቀረ ነገር አለ። እሱን አግኘውና አብራው! ከዚያስ?የራስህን ሕይወት በራስህ ሐሳብና አቅም ምራው!!

ሐምሌ 13/2016
ወልቂጤ ኢትዮጵያ
🫳 Dn Mekuriya Murashe

🌝 ስለማከብርህ(ሽ) ላክኩልህ(ሽ)፤ ካከበርከኝ(ሽኝ) Join እና Follow አድርገኝ(ጊኝ)እጅግ ካከበርከኝ(ሽኝ) Share አድርግልኝ(ጊልኝ)

🫵Join us on Telegram
t.me/Dilla_Live
t.me/Dilla_Live

t.me/MekuriyaM
t.me/MekuriyaM

🫵 Follow us on Tiktok
http://tiktok.com/@mekuriya19

“እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥6

አሳዳጊው ሆይ በሁሉ አሳድገን🙏
ማንን ነው የሰጠኸኝ?

🫵
#ንነጽር_109

በጨነቀኝ ጊዜ አጽናኝ ይሆነኝ ዘንድ
#ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ልፋቴን ሳዋየው መፍትሔ እንዲሆነኝ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ብኩንነቴን ሲገባኝ ያበረታኝ ዘንድ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ምድር ስትመሽብኝ ማረፍያ ይሆነኝ ዘንድ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ብዬ ስጠይቅህ ምላሽ ይሰጠኝ ዘንድ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ??

"ልጄ ሆይ ምላሽ ይሆንህ ዘንድ
#መጽሐፍ_ቅዱስን፤ አጽናኝ፣ አበርታች... ይሆንህ ዘንድ #ቃሌን አልሰጠሁህምን?" የምትለኝ የምትለኝ መስሎ ታየኝና አጽናናኸኝ።

ከአንተ እና ከባለሟሎችህ ውጪ ለካ ማንም የለኝም!

ክርስቶስ ሆይ! አንተንና ባለሟሎችህን ብቻ እንድቀርብ ቀርቤም ሰው እንድሆን እርዳኝ🙏

“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ" አቤቱ ሆይ ስማኝ🙏

https://t.me/MekuriyaM
https://t.me/MekuriyaM