ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
4.73K subscribers
454 photos
10 videos
20 files
413 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
😓 #ንነጽር_፺፰

ከሰኞ እስከ ዕለተ አርብ ድረስ እየሰቀልኩት ነበር፤ አልሰቀል ብሎ አስጨንቆኝ፤ ግን የተሰቀለው ክርስቶስ ረዳኝ መሰለኝ ልክ ዕለተ አርብ ላይ ሰቅዬ ጨረስኩት። በዚያው ዕለት ደግሞ ከጌታዬ ጋር መቃብር ውስጥ ጨመርኩት። ዛሬ በዕለተ እሑድ ክርስቶስ ሲነሣ እኔ ቀብሬው የነበረው ግን አልተነሣም።

ሳስበው ግን እንዳይነሣ ያደረገው ሞቶ የተነሣው ክርስቶስ ነው። ምክንያቱም ስሰቅለውና ስቀብረው ያየው እርሱ ነበራ! ተነሥቶ እንዳይከተለኝ አጥብቄ የለመንኩት ለክርስቶስ ነበራ!

ስሰቅለው ግን በጣም ነበር ያስቸገረኝ። አንዱን ስሰቅለው ሌላ ይመጣል፤ ጨርሼ ሰቀልኩ ብዬ ላርፍ ስል ሌላላ ይታወሰኛል። እያልኩ እያልኩ ከሰኞ እስከ አርብ ደረስኳ። አርብ ከስንት ስቃይ በኋላ ሰቀልኩትና ዕረፍትን አገኘኹ። መሰቀሉን ያረጋገጥኩት ደግሞ በዕለተ አርብ መጨረሻ ላይ እካህኑ ጋር ሄጄ ጠብጠብ... ጠብጠብ...እያደረጉ ቃሌን የሰጠኋቸው ጊዜ ነው።

ጌታዬ ሆይ በዕለተ አርብ የሰቀልኳትን
#ኃጢአቴን ትንሣኤ ስለሌላት በብዙ እባርክሃለው። እኔ እንደሰቀልኳት አንተ ደግሞ ቀብረህ አስቀርተሃታልና አመሰግንሃለው🙏

#ኃጢአቴን_ነው_የቀበርኳት!

መ ል ካ ም የ ት ን ሣ ኤ በ ዓ ል !

@MekuriyaM