Kokebe Tsibah General Secondary School
2.43K subscribers
1.67K photos
14 videos
116 files
77 links
Since 1924
Download Telegram
Forwarded from KOKEBE TSIBAH GENERAL SECONDARY SCHOOL GRADE 12 D/T EXAM QUESTIONS (︎ⓤ︎ⓛ︎ⓔ︎)
💢 HYBRIDIZATION 💢

Chemistry Grade 11 unit 3

🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🅰️🔤
follow and share for more
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kokebetsibahexam
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Maths workbook.pdf
3.6 MB
📋📐🖍️💢Maths💥🖍️📐📋

EUEE 2009-2013 questions with detail explanation



follow and share for more
  👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇   
https://t.me/kokebetsibahexam
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ብሪቲሽ ካውንስል ከብሪቲሽ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ባካሔዱት ውድድር የእኛዋ ጀግና ተማሪ መቅደላዊት ደስታው (10ኛ E) ክፍል በውድድሩ ከተሳተፉት 303 ተማሪዎች መካከል በማሸነፍ የምስክር ወረቀቷን ከአምባሳደሩ እጅ ተቀብላለች፡፡
👉 ይህ ዉጤት እንዲገኝ ከፍተኛ ክትትል እና ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩት የት/ቤቱ እንግሊዝኛ ትምህርት ክፍል መምህር ለሆኑት ለመ/ር አንዋር ከማል ላቅ ያለ ምሰጋና እናቀርባለን::
👉 ተማሪ መቅደላዊት ደስታዉ እንኳን ደስ አለሽ!!
/ቤቱ
ኩረጃ ምንድን ነው?
(በድጋሜ የተለጠፈ)

ከዚህ ቀደም ቢቢሲ በሰራው አንድ ዘገባም  ተማሪዎች ለኩረጃ ይመቻቸው ዘንድ ከጎበዝ ተማሪዎች ጋር በማመሳሰል ስማቸውን በፍርድ ቤት አስለውጠዋል።

ኩረጃ በአንድ የፈተና ክፍል ውስጥ ብቻ የሚካሄድ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚዳብር መሆኑን ጨምረው ያስረዳሉ።

የራስ ያልሆነን ስራ እንደራስ አድርጎ ማቅረብ፣ ትክክለኛ ምክንያት ባለመስጠት መምህሩን ማሳሳት እና የማይገባውን ውጤት ለማግኘት የሚደረግ ጥረት፣ ያልተገባ ውጤት ለማግኘት መምህርን ማታለል በአጠቃላይ ኩረጃ ነው ይላሉ ወንድይፍራው (ዶ/ር)።

ጓደኛ እንዲኮርጅ መርዳት፣ በግል የተሰጠ ምዘናን ወይንም የቤት ሥራ በቡድን መስራት ሁሉ በኩረጃ ስር እንደሚጠቃለሉ ጨምረው ይገልጻሉ።

በትምህርት ቤት ሕይወታቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ በኩረጃ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በርካታ መሆናቸውን በተለያዩ አገራት የተሰሩ ጥናቶች ያሳያሉ።

ተማሪዎች የሚኮርጁት ለፈተናው ወይንም ደግሞ ምዘናው በቂ የስነልቦና ዝግጅት ሳይኖራቸው ሲቀር መሆኑን ይናገራሉ።

ተማሪዎች በተገቢው መጠን ራሳቸውን ካለመዘጋጀት ውጪ፣ ትምህርትን በአግባቡ አለመከታተል፣ ኩረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሌለው ግንዛቤ መያዝ ወደ ኩረጃ የሚገፉ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ይላሉ።

ከዚህም በተጨማሪ ወንድይፍራው (ዶ/ር) እንደሚሉት የወላጆች 'ልጆቼ ተምረው፣ ሕይወቴን ይለውጡኛል' የሚለው ገለጻ ልጆች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል።ይህ ቤተሰብ የሚያደርገው ጫና ተማሪዎችን ለማበረታታት የተደረገ ነገር ቢሆንም ለኩረጃ እንደሚገፋም ያስረዳሉ።

በራሱ ጥረት ወላጆቹ ወዳሰቡለት ስኬት መድረስ ያልቻለ ተማሪም የወላጆቹን ጫና ለመሸሽ ጎበዝ የሚባሉ ተማሪዎችን በመደገፍ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ይሞክራል በማለት ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ኩረጃ ከክፍል ክፍል ሲኬድ እያደገ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን፣ በሕይወት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ተጽዕኖ እንዳለውም ጨምረው ገልፀዋል።

"ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በትምህርት ዓለም የነበረን የኩረጃ ሕይወት ወደ ሥራ ዓለም ስንገባም ያንኑ የመተግበር እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ እና ተያያዥነት እንዳለው ነው፤ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በኩረጃ ታግዞ ወደ ከፍተኛ ተቋም ሲገባ፣ እዚያም በኩረጃ ታግዞ ቢመረቅ በስራው ዓለም መደለያ ለመቀበል አያቅማማም።"

ተማሪዎች በጓደኞቻቸው ዘንድ ሰነፍ ሆኖ ላለመታየት፣ በውጤት አንሶ ላለመገኘት፣ ወደ ኩረጃ እንደሚገቡም አክለው ተናግረዋል።ተማሪዎቹ ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፣ ለኩረጃ ሲዘጋጁ ኔትወርክ ፈጥረው፣ የመጀመሪያው እቅድ ባይሳካ በሚል ሁለት እና ሶስት እቅዶችን ነድፈው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የነደፉት ስልት በፈተና የመጀመሪያ ቀን ካልሰራ፣ ለቀጣዩ ፈተና ቀን ሌላ ስልት ነድፈው እንደሚመጡም ይናገራሉ።ከዚህ የሞባይል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በሚያደርጉት ኩረጃም ከትምህርት ቤት ውጪ ያሉ ግለሰቦችን እንደሚያካትቱ ጨምረው ያስረዳሉ።

✔️ለፈተና ራሳችንን እናዘጋጅ
✔️ኩረጃን/ስርቆት እንጠየፍ

ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76

ክፍል ሁለት ይቀጥላል
👇👇👇👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Kokebe Tsibah General Secondary School
ዉድ የት/ቤታችን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የምትሰሩበት ቻናል መክፈታችን ይታወቃል ታዲያ ምን ያህላችን ይሄን ቻናል ተቀላቅለዋል::

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kokebetsibahexam 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከላይ ባቀረብነው መጠይቅ መሰረት የትምህርት ቤታችን የ12 ክፍል ተማሪዎች ለ12 ክፍል የተለያዩ የማትሪክ ጥያቄዎች÷ አጫጭር ማስታዎሻዎችን የምንለቅበት የቴለግራም ቻናል መክፈታች የማታዉቁ ተማሪዎች መኖራችሁን መረዳት ችልናል:: ስለሆነም ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሊንክ/link በመግባት እንድትጠቀሙ እናሳስባለን::


ይከታተሉ እና ለበለጠ ያካፍሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kokebetsibahexam
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በ2017 ዓ.ም 11ኛ ክፍል በሚጀመረዉ የስራ እና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነት ምርጫ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ከግንቦት 6-7/2016 ዓ.ም ለተማሪዎች እና ወላጆች/አሳዳጊዎች የተፈጠረላችሁን ግንዛቤ መሠረት አድርጋችሁ ትመርጣላችሁ::በመሆኑም ይህ የተለጠፈላችሁ የመምረጫ ቅፅ በሃርድ ኮፒ ማክሰኞ ተሰጥቶአችሁ ከወላጅ/አሳዳጊ ጋር በመመካከር ሞልታችሁ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ሐሙስ እንድትመልሱ ይደረጋል::
👉 በመሆኑም ሁሉም የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም የምርጫ ፎርሙን መዉሰድ ይጠበቅባችሗል::
ት/ቤቱ
👌ዛሬ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም
1ኛ.ጠዋት የህፃናት ማቆያ ስፍራ ለህፃናቱ ምቹ በሆነ ሁኔታ በግብዓት አሞልተን ስራ ለመጀመር ምቹ አድርገናል::
👉መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች 20 ህፃናት እንዲቆዩላቸዉ አስመዝግበዋል::
👉 ሰኞ ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ህፃናትን ተቀብለን ማቆየት እንጀምራለን::
2ኛ. ለ800 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የክ/ከተማዉ ትምህርት ፅ/ቤት ሱፐርባይዘሮች በተገኙበት የስራ እና የተግባር ትምህርት የመምረጫ ፎርም ለተማሪዎች ስለቅፁ አሞላል ገለፃ በማድረግ ሰጥተናል::
/ቤቱ