Kokebe Tsibah General Secondary School
3.35K subscribers
2K photos
15 videos
123 files
89 links
Since 1924
Download Telegram
ማሳሰቢያ!!
ለሁሉም ተማሪዎች/9-12/
👌 እንደሚታወቀዉ በ2016 ዓ.ም ያሉት የትምህርት ቀናት በበጀት ዓመቱ የትምህርት ካሌንደር በግልፅ ተቆጥረዉ ተቀምጠዋል::

👉 ይሁን እንጅ ተማሪዎች በህግ እና በአሰራር ባልተፈቀደ ሁኔታ ከበዓል ማግስት በራሳችሁ የተሳሳተ ዉሳኔ[አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት] ት/ቤት እየመጣችሁ አለመሆኑን ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም አረጋግጠናል::
👉 ስለሆነም ይህ አይነት አካሄድ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚበልጥ እንዲሁም በቀጥታ ተጎጅዎች ራሳችሁ ተማሪዎች በመሆናችሁ ከነገ ሚያዚያ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሁላችሁም ተማሪዎች በትምህርት ገበታችሁ እንድትገኙ ስንል በጥብቅ እናሳዉቃለን::
👉 ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጆቻችሁ ከበዓል ማግስት ከት/ቤት ሲቀሩ ለምን ብላችሁ በመጠየቅ ወደ ት/ቤት በሰዓቱ እንድትልኩ ስንል እናሳስባለን::
👉 ትምህርት ቤታችን ለመማር የሚመጡ ተማሪዎችን ለማስተማር ከበዓል ማግስት ጀምሮ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳን::
👉 ከነገ ጀምሮ በትምህርት ገበታ ላይ የማይገኝ ተማሪን በተማሪዎች የዲስፕሊን አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ተጠያቂ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን::
👌 ያላግባብ የትምህርት ብክነትን በጋራ እንከላከል!!
ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም
/ቤቱ
ከበዓል ማግስት ሚያዚያ 29/2016 ዓ.ም ለመማር የመጡ ተማሪዎችን ልዩ ክፍሎች በየክፍል ደረጃዉ በማደራጀት የመማር ማስተማር ሂደቱን አስቀጥለናል::
👉 ዛሬ ለመማር የመጣችሁ ተማሪዎችን እና ወላጆችን/አሳዳጊዎችን እያመሠገን በተለያየ ምክንያት ያልተገኛችሁ ተማሪዎች ነገ መገኘት ይኖርባችሗል::
ት/ቤቱ
የኛ ጀግኖች በ KUE (በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ) በተደረገዉ የሳይንስና ፈጠራ ዉድድር ከ ዩኒቨርሲቲዉ የሳይንስና ሼርድ ተማሪዎች በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ይዛችሁ በማጠናቀቃችሁ የተሰማን ደስታ ወደር የለዉም:: በሳይንስና ፈጠራዉ የተሻለ ከሰራን ከዚህ የሚበልጥ ዉጤት ማምጣት እንደምንችል ይህ ትልቅ ማሳያ ነው::

ኮከበ ፅባህ አጠ 2ኛ ደ/ት/ቤት