ቅንጭብጭብ
7.66K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ከማስታዎሻየ_ማህደር!!
.
.
#ሌላ_ዓለም!!
(ክፍል አንድ)
.
.
.. ትናንት ህዳር 8/2015 ዓ.ም "አርባተንሳ" ክብረ በዓልን ልታደም ወደ ገጠራማው መንደር ካ'ንድ ወዳጄ በቀረበልኝ ጥሪ መሰረት ወርጀ ነበር። ወዳጀ ካለኝ ቦታ ደርሸ ካገኘሁት በኋላ ያው እንደተለመደው 'ቅርብ ነው ደርሰናል!' እያለ ሰፈር ለሰፈር ትንሽ ተጉዘን ከቤታቸው ደረስን የቤቱ ግቢ በላም በጥጃዎችና በእርሻ የተከበበ ነው። ግቢው በር ላይ የተቀመጡ ሰዎችን ሰላምታ ሰተን ወደ ቤቱ ዘለቅን.. የቤቱ አባወራ ከሳሎኑ ጥግ ይዘው ተቀምጠዋል..ቅድሚያ እርሳቸዉን ሰላምታ ሰተን በቤቱ ያሉ እንግዶችንም ጨበጥናቸው እና የበግ ቆዳ ከተጎዘጎዘበት መደብ ቁጭ አልን። ወዳጄ ቀልጠፍ አለና ወደ ኩሽናው ዘልቆ እህቱን ምግብ እንድታመጣ አዘዛትና "ክቡር ዘበኛ" እሚባለዉን ብርጭቆና በጆክ ጠላ ይዞ መቶ ከፊቴ ቆመ.. እኔም ከቤቴ እንደበላሁና ያው ጠላም እንደማልጠጣ በመናገር አስቤ የመጣሁት "ወተት ለመጠጣት!" እንደሆነ አስታወስኩት!😋 ቢሆንም 'ካልበላህ ወተት የለም!'😑 እሚል እይታ አሳይቶኝ ለራሱ ጠላዉን ቀድቶ ቁጭ አለ። በልቤም አንድ ቁርጥ አንስቼ እበላና ወተቴን እጠጣለሁ ብየ መጠበቅ ያዝኩ ታዲያ የወዳጄ እህት በሰሃን(ባቲ) የሰማይ ስባሪ እሚያክል እንጀራ በድንች በስጋ ወጥ ይዛ መታ አስረከበችኝ!! 'ኧረ በዝቷል ይተርፋል!' ብልም ሰሚ ስላላገኘሁ ወደ ወዳጄ አባት ፊቴን መልሸ 'አባት ይባርኩልኝ?' አላኳቸው(አክባሪ ለመባል) ምን ዋጋ አለው! 'ለወንድ አይባረክም! ዝም ብለህ ብላ!' ብለው ጨነገፉኝ።😬 ኩርኩሜን ተቀብየ ከወዳጀ ጋር የቀረበልኝን ምግብ መብላት ጀመርኩ.. ወዳጄ ምግቡን አቋርጦ ወደ ኩሽናው ተወነጨፈና በግራም ሰሃን እርጎ ይዞ መጣና እንጀራዉን መሸከም ያቃታት ሰሃን(ባቲ) ላይ እርጎዉን አጥለቀለቀው..😇 በላየላይ የወረደዉን መና እያጣጣምኩ በላሁ..😋 ታዲያ በየ መሃሉ አባወራው በመገረም ለምን ጠላ እንደማልጠጣ እየደጋገሙ ይጠይቁኛል! እኔም የተለያዩ መልሶችን እነግራቸዋለሁ.. ወዳጄና እህቱም እንጀራና ወጥ እያመጡ ጨምር እያሉ ከድንች በስጋው ወጥም ከእርጎና ከንጀራዉም ይከምሩብኛል..🙄'ኧረ በቃኝ!' ብልም የቤቱ አባዎራ ጨምሮ እንግዳቹ ሁሉ 'ትንሽ ብላ እንጅ!' እያሉ አጨናነቁኝ እኔ ግን ተሎ መሃላ ዉስጥ ገብቼ ድርቅ በማለት እጄን ታጠብኩና ቁጭ አልኩ..መቼም የገጠር ሰዎች እማይበላ እማይጠጣ አይወዱም።
.
.
ይቀጥላል..


✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ከማስታዎሻየ_ማህደር!!
.
.
.
#ህይወት_የመኖር_እዳ!!
.
.
.. ከተወለድኩ ጀምሮ እድሜዬ በጨመረ ቁጥር ወደ ህይወት እየመጣሁ ይሆን ወይስ ወደ ሞት እየሄድኩ እንደሆን አላዉቅም! ስለ ህይወት እያወኩ ለመኖር እየጀመርኩ ግን ወደ ሞት እየሄድኩ ይመስለኛል! መኖር ታዲያ እንዴት ስጦታ ሊሆን ይችላል?? ሐይማኖተኛ ሰዎች አንደበት ላይ እማይጠፋ ቃል "በህይወት ስላለህ ብቻ አመስግን!!" እሚለው ነው!! ግን ለኔ አይታየኝም! መፈጠሬን እንደስጦታ አይቼ ለማመስገን ህይወት በቃኝ እስክል መኖር አለብኝ! ካልሆናማ እንዲሁ ወደ ህይወት እየመጣሁ ወደ ሞት ከሄድኩ ስጦታነቱ ቀርቶ ኑሮ እዳ ይሆንብኛል!! ሳልሞት በፊት ተሽቀዳድሜ መኖር ያለብኝ እዳ ሁኖ ይሰማኛል። ሰው ሳይኖርም ይሞታል!
   ህይወት ከፈጣሪ እምትሰጠን ብድር ትመስለኛለች ብድራችን ለመክፈል ስንፈጋ ስንታገል የተሰጠን የክፍያ የቀን ገደብ አልቆ እኛም በነፃነት ሳንኖር እምንነጠቃት ናት። የሰው ልጅ ሁሉ "የህይወት ግብ ደስተኛ መሆን ነው!" በምትለው ህግ ይተዳደራል! ይሄን ህግ ሐይማኖተኞች ቢያጥላሉትም በነሱ ልብ እንደማያምኑበት ቢናገሩም እነሱም በሆነ የህይወት ዘመናቸው ይከተሉታል። ሁሉም ሰው በራሱ ዛቢያ ኑሮን ለማሸነፍ ይሽከረከራል፤ ኑሮን ማሸነፍ ያው ሀፍታም መሆን ነው! ብሎ አዕምሮው ላይ በሰቀለው ሃሳብ ይነዳል። መፈጠሩን እንደ እዳ ለማየት ወይንም እንደ ስጦታ ለመቀበል በቀላሉ በአኗኗር ዘይቤው ይወስናል፤ ብዙዉን ጊዜ ሀፍትን ካካበተ ስጦተነቱን በተቃራኒው በድህነት ከተሰቃየ ደግሞ እዳነቱን ይቀበላል፤ እዚህ ላይ አንዳንድ ነገረኛ አንባቢ "ታዲያ አንተ በድህነት ተሰቃይተህ ነው! ህይወት የመኖር እዳ ናት የምትል" ይል ይሆናል! ግን ህይወት እንዳለህ ሀብት ወይም እዉቀት የምትወሰን ናት በሚለው አልስማማም!! ምክኒያቱም ህይወት አወቅንም አላወቅን ሀፍታም ሆን ወይ ፀደቅን እስክንሞት ድረስ እዳ ናት!! አዋቂው ህይወትን ተረዳኋት ባላት መጠን ሲያብራራና ሲያወጣ ሲያወርዳት ትንሽ በተጠጋት ቁጥር እማያዉቀው እልፍ መሆኑን እየተረዳ አለማወቁን አዉቆ እንኳ እረፍት ሳያገኝ የእዉቀት ጥሙን ሳያረካ ያርፋል!! አላዋቂዉም መኖር ባለማወቅ የሰጠችዉን ሰላም ተቀብሎ መኖሩ ሳይታወቅ በሚራመድበት መሬት የሆነ መስመር የእግሩ አሻራ ሳይታይ ይሞታል!! ሀፍታሙ ሃፍቱን የደከመበትን ያህል ሳያጣጥመው ወይ ደግሞ በሀፍቱ ልክ ደስተኛነቱ የወረደ ሲሆንበት! ወይ ሀፍቱ እረፍት እንደነሳው ሌላ አስደሳች ግብ ወይ ምላሽ ሲፈልግ ያልፋል!! ፃዲቁ ደግሞ የፈጣሪው ፍርድ እያስፈራው በአካባቢው ያሉ ሰዎች ኑሯቸዉን በሐጢያታቸው እየለካ የመኖር ጣእሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ ሞቱ እንዲቀርብለት እየፀለየ ይኖራል!? መፈጠሩ ስጦታ ነው ብሎ ግን መኖሩን ከመሞት በላይ አይወደዉም! ስጦታ ብሎ የተቀበለዉን ህይወት በሞት መነጠቅን ይናፍቃል እንደናፈቀዉም አይቀርምና ያገኘዉና ይቀበላል!!
   በነዚህ ሁሉ መሃል እኛ "ሁሉን ቀመስ!" እምንባል አይነት ሰዎች አለን!! የማህል ዳኛ ማለት ነን፤ ሌሎች በተለያየ አቅጣጫ የመኖራችን ግብ ብለው ያመኑበትን ሲያስቆጥሩ እምናጨበጭብ አንዳንዶች ደግሞ ሲደናቀፉም (ፋዎል) ሲሰሩ እምንታዘብ!! አለን። ለኛ ህይወት ጥያቄ እንጅ መልስ ሁና እማታዉቅ!! ህይወት የመኖር እዳ እንጂ ስጦታ ሁና እማትታየን!! ብዙ የገባን ይመስለናል ግን አንዳች ነገር አንፈታም! እምናምን ግን ደግሞ እማናምን! ወደ ህይወት እንመጣል ግን ደግሞ እማንደርስ! ወደ ሞት እምንሄድ!! እዉቁ ፈላስፋ.. "ያልተመረመረ ህይወት ለመኖር ያልተገባ ነው!" እንዳለው የኛ እዳ ጥያቄ የሆነ ነን። የናንተስ የመኖር እዳ ምንድን ነው?? እዳ ካልሆነ ስጦታነቱን በምን አመናቹህ? ስጦታነቱ ምኑ ላይ ነው? ተሰቶ እሚነጠቅ ስጦታ መሆኑንስ እንዴት ታዩታላቹህ? ወደ ህይወት እየመጣቹህ ነው ወይስ ወደ ሞት እየሄዳቹህ??
.
.
.
ህዳር 28/2015 ዓ.ም

✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

join 👇👇👇
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23


@kinchebchabi @kinchebchabi