ቅንጭብጭብ
7.18K subscribers
413 photos
9 videos
5 files
502 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ቅንጭብጭብ
#B ዛሬም ልደቴ ነው፤ አዎ ድፍን ፳፫ አመቴ #Bcrazykid የቤቱ አባወራ ® (ማነው መልካም ልደት የሚለኝ፤ መልካም የሚመኝልኝ 😊)
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ከዓመታት በፊት በግንቦት 1988ዓ.ም በጳውሎስ ሆስፒታል በተነሳ መውለጃቸው በደረሰ የእርጉዝ ሴቶች ሰላማዊ የጭንቅ (የሕመም) ጩኸት (ምጥ) ንፁሀን ጨቅላዎች ከሞቀ የዘጠኝ ወር የእናት ቤታቸው በዶክተሮች አፈናቃይነት ብዙ ጨቅላዎች ወደዚች ምድር ወጡ ከነሱም መሀል አንደኛው 52cm የሚረዝም 3.2 ኪ.ግ የሚመዝን ጨቅላ ነበር።

ጨቅለው ዛሬ ትልቅ ሰው ሆናል ብዙ መጠየቅ ብዙ ማወቅ ደስ ይለዋል፤ መሳቅ ሱሱ ነው በቁም ነገሮች ላይ ኮስተር ማለቱን ቢያውቅበትም ፈገግታው ታግላ ትወጣለች፣ ሰው ማናደድ ይወዳል ሲከፋቸው ግን ፍፁም ይከፋዋል ይቅር በሉኝ ብሎ አይጠግብም፣ ፍፁም ሰላም ይሠማዋል በሕይወቱ ሲበዛ ደስተኛ ነው። አጣሁ ብሎ የማይወፋው ይሉቁንም ደግ አረገ ብሎ የሚስቅ አገኘሁ ብሎ የማይመጻደቅ ሕይወትን እንደ ጨዋታ ቀለል አድርጎ የሚጫወት ሰው ነው።

በተገኘው አጋጣሚ ስለሐገሩ መደስኮር ይወዳል የልጅነት ሕልሙ ቢሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወጣትነት ዘመኑ በተለያዩ መድረኮች፣ ራዲዮና ቴሌቭዥን ጣብያዎች፣ በአደባባይ እንዲሁም በማሕበራዊ ትስስር ገጾች ኢትዮጵያዊነትን ለመንገር እድሉን አግኝቶ ተጠቅሞበታል።

ኢትዮጵያ ሲባል ደስ ይዋል፤ ሰንደቋን ሲያይና ሲዘምርላት አይኑ እምባ ያቀራል ከሰዎች ተሠባስቦ መለየት አይሆንለትም፤ ሲለያዩ ይከፋዋል። መዞር ይወዳል ሐገር ዞሮ ለማየትማ ማ ብሎት... በትንሽ ብር ሐገሬ ላይ ነኝ ምን እሆናለሁ ብሎ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ይሄዳል። ባገኘው አቀባበል ረክቶ ይመለሳል።

ከኦሮሞው በአምቦ ረብሻ ቤ/ክ ተጠልሎ ገበታ መጥቶለት ከእጃቸው በልቷል፤ ከአማራው ባሕርዳር ላይ እንጀራ ማር ያለ ወቅቱ ተቆርጦለት አጣጥሟል ፤ በጢስ አባይ ፏፏቴ ተደምሞ ሳይጨርስ በላሊበላ ፍልፍል ቤ/ክ ተደንቋል፤ በጎንደር ፋሲለደስ ግንብ ፎቶ ተነስቷል ወዳጆቹ ከፈተና ሰዓት ጊዜ ተሻምተው አዝናንተውታል፤ ከትግሬው በመቀሌ እንግዳ ነህ ተብሎ አልጋ ተለቆለት ባለቤቱ መሬት ተኝቶ እንግዳው ተከብሯል ፤ በሐረር ፍቅር በዝቶለት በተጣበበ ሰዓት ከስራ ሰዓት ተሻምታው የምሳ ግብዣ ተደርጎለታል፤ በሐዋሳና አርባምንጭ ለም መሬት ሽር ብትን ብሎ ሰለቸን ሳይሉ ለወራት ተንከባክበውት ተመልሷል፤ በድሬ-ደዋ ጣፋጭ ባቅላትና ሙሸበክ በቁሙ ጎርሶ ሲበቃው ገዝቶ ተመልሷል፤ አክሱም ጽዮንን ተሳልሞ በአክሱም ሐውልት ቅርስ ፈዟል፣ ከሰሜን ከደቡብ ከምስራቅ ከምዕራቡ ተደመሩ ሳይባል ከእጃቸው በልቶ ጠጥቶ ተዋህዷል።
(jo, ግርማይ, ፋሲካው, ግርማ, ሳምሪ, ሕይወት... ምሥጋና ለእናንተ)

ይህ ሰው ዛሬም ይዞራል ለደቂቃ ያወቀውን ሰው ለሰዓታት ይናፍቃል፤ በነገሮች ሁሉ ስቆ ያልፋል ሰዎች ሊያናድዱት ሲፈልጉ ይብስበታል ከልክ በላይ ይስቃል። ስቀን ዓለምን እናስቃለን ይላል፤ ቆሞ ለመሄድ ከእግሩ ይልቅ የቆመበትን መሬት ያመሠግናል።

ፍላጎቱ የተገደበ አይደለም፤ ማስቀደም ያለበትን ግን ያስቀድማል ተፈጥሯዊ ነገሮች ይሥቡታል የእግር መንገድና ሙዚቃ ሃኪሞቹ ናቸው ሳቁ ለሁሉ መድኃኒቱ ናት በቃ ዝምብሎ መሳቅ ይወዳል። ሲከፋው መሳቅ፣ ሲደሰት መሳቅ፣ ሲያጣ መሳቅ፣ ሲያገኝም መሰቅ . . . ከሳቅ ውጪ አያውቅም
"በምኒ ምን ያውቃል፤ ሲሰድቡት ይሥቃል።" ወዳጁ የተረተበት ተረት ነው። (ሮቤል)

ይህ ሰው አሁን አድጓል ባለ ጢም ባለ ጎፈሬ ነው ዞሮ ማየት ከሚፈልጋቸው የሐገሩ ከተሞች ሐመር፣ አፋር፣ ባሌ ቢቀሩትም በቅርቡ መጣለሁ ይላቸዋል ከ 1 ዓመት በፊት እመጣለሁ ያላቸውን ሄዶ አይቷቸዋል ደስ ብሎታል ኧረ ጭራሽ ሊደግማቸው ነው። ጉራ የለበትም የሆነውን ነኝ ማለትም አያፍርም፣ ከባድ የሚባሉ ኃላፊነቶችን መውሰድ ያስደስደስተዋል፤ በድል እንደሚወጣው ያምናል! ካልሆነም በብልሃት አልፎት መማሪያው ያደርገዋል። [ይልቅ እቆምለታለሁ ብሎ ያሰበው የጾታ ትንኮሳ ጉዳይ ባይሳካለትም አንዳንድ ሃሳቦቹ በሌሎች ሰዎች ስለተሰሩ ደስተኛ ነው። (መሠራቱ እንጂ የግድ እኔ ካልሰራሁት አይልም) መሥራት የሚፈልገው ጥግ ድረስ ግን ይሰራዋል።]

ገና ለገና በዶክተር አፈናቃይነት ከእናቴ ማኅፀን ከወጣሁ 23 ዓመት ሆነኝ ብሎ እንዲህ ከደሰኮረ ይሄን ሰው በድጋሚ ከ 23 ዓመት በኋላ አስቡት ምን ያህል ተረት/ታሪክ ሊደሰኩር እንደሚችል 😊😁

ለማንኛውም ይህ ሰው ዛሬ ልደቱ ነው፤ ይህ ሰው እኔ ነኝ ይኸው 23 ዓመቴን ቀብ አደረኳት። ስወለድ የነበረኝ አልቃሻነት ዛሬ በሳቅ እና ሳቅ ብቻ ተቀይሯል።

ስትስቁ ዋሉ፤ መወለድ ብርቅ አይደለም ለምን ተወለድኩ ማለትና አውቆ መኖር ግን መልካም ነው።

እዚህ ለመድረሴ መጀመሪያ ለፈጠረኝ እርሱ እንዲህ ለመሆኔ በመልካምም በመጥፎም ለሠራችሁኝ ሁሉ ክብርና ምሥጋና ለእናንተ. . .

® አባወራው
እንኳንም ተወለድኩ
#መልካም_ልደት ለኔ!
#ኢትዮጵያ | @Bcrazykid
@kinchebchabi @roviben