Intrance result.neaea.gov.et
1.35K subscribers
545 photos
29 videos
301 files
551 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ ከነገ ጀምሮ ከ60 ሺህ የማይበልጡ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና ይወስዳሉ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ #ከነገ_ጀምሮ በትግራይ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በ2012 ዓ/ም መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ ሲሆን በወቅቱ 120,000 ገደማ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ነበር።

አሁን ከነገ ጀምሮ በሚጀምረው የ8ኛ ፈተና ከ60 ሺህ የማይበልጡ ተማሪዎች ብቻ ለፈተናው ይቀመጣሉ።

ተፈታኝ ተማሪዎች የተሰጣቸው የትምህርት ጊዜ አጭር ቢሆንም በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቀ ትምህርት የተማሩ በመሆናቸውና በወላጅ መምህራን የተቀናጀ ጥረት ፈተናውን ለመውሰድ እንደማይቸገሩም አመልክተዋል ተብሏል።

ነገ የሚጀምረው ፈተና ለሶስት ለተከታተይ ቀናት ይቆያል።

#shere & #join
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Tigray

የ12ኛ ክፍል ፈተና ተራዘመ።

" በሚቀጥለው ጥር ወር 2016 ዓ.ም ለመስጠት የታቀደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል " ሲል የትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ለሚድያ ባሰራጨው ፅሑፍ እንዳለው ፤ የትግራይ ትምህርት ከትምህርት ሚኒስቴር በመግባባት በክልሉ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ሳይሰጥ የቆየው የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና መስከረም 29/2016 ዓ.ም ፣ ጥር 6 /2016 ዓ.ም እና ግንቦት 2016 ዓ.ም ለመስጠት አቅዶ በሚድያ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ አስታውሷል።

ይሁን እንጂ በሚቀጥለው ጥር 6/2016 ዓ.ም ለመስጠት ያቀደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታህሳሰ 9/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ደብዳቤ አስታውቋል።

ቢሮው ፈተናውን ለማራዘም ያስገደዱት ሶስት ምክንያቶች ዘርዝሯል። እነሱም ፦

1. ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች ዘግይተው ተማሪዎች በመቀበላቸው ምክንያት ሊሰጥ የታቀደው ፈተና ዩኒቨርስቲዎቹ ካወጡት የትምህርት ፕሮግራም የማይጣጣም በመሆኑ፤

2. የአገር አቀፍ የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት የዝግጅት ጊዜ እጥረት እንደገጠመው በመግለፁ፤

3. ተማሪዎች ለፈተና መዘጋጃ የሚሆን የጊዜ እጥረት መኖሩ በመረዳት፤

ጥር 6/2016 ዓ.ም ለመስጠት የታቀደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል ብሏል። 

በተያያዘ ከታህሳስ 18 አስከ 20/2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ፈተናውን ለመፈተን 60 ሺህ ተማሪዎች መመዝገባቸው ቢሮው ማስታወቁ ጠቅሶ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
📥 ትክክለኛው
👇👇👇👇👇👇👇👇
ተጨማሪ ትምህርታዊ join
Shere 👇🙏🙏🙏
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor