Intrance result.neaea.gov.et
2.79K subscribers
588 photos
31 videos
302 files
639 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መርሃግብር

መልካም እድል


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል።

ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በትግራይ ክልል በወረቀትና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ተጀምሯል።

ፈተናው በክልሉ በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡

ተፈታኞች በአጠቃላይ የፈተና ዲሲፕሊን ዙሪያ ገለፃ በተቋማቱ ተደርጎላቸዋል፡፡


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ 2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል::

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

https://aa.ministry.et/account#/student-result

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219  በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#ማለፊያ_ነጥብ

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።

ውጤት ለመመልከት👇
https://aa.ministry.et/account#/student-result


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በወረቀትና በኦንላይ የሚሰጠውን የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል።

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ ከ 9-11/ 2016 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በበይነ መረብ (Online) እና በወረቀት ፈተናው ይሰጣቸዋል።

ፈተናውን የምትወስዱ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በሙሉ መልካም እድልን እንመኝላችኋለን።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ተማሪዎች የፕሮግራም ድልድል የሚሰሩበትን መስፈርት አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በቀን ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።


በደብዳቤው የሪሚዲያል ተማሪዎቹን ወደ ፕሮግራም ለመመደብ በሚደረግ ድልድላ ተመሳሳይ መሰፈርት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ሁሉም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 20%፣ በአንደኛ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 50% እና ወደ መስክ መግቢያ ፈተና 30% ብቻ የሚደለደሉ መሆኑን ደብዳቤው ያስረዳል።



#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#EAES

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

"በወረቀት እና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና፥ በሰላምና እጅግ በጣም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል" ብሏል አገልግሎቱ።

በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል እየተሰጠ ያለው የመልቀቂያ ፈተና ነገ ከሰዓት በፊት እንደሚጠናቀቅ አገልግሎቱ ገልጿል።

አገልግሎቱ በፈተና የመስጠት ሒደቱ ለተሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ትምህርት ቢሮዎች፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣ የፈተና አስፈጻሚዎች፣ አመራሮች እና ተማሪዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
አጭር ምክር - ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች

ከትንሽ ጊዜ በኃላ ዩኒቨርስቲ ምርጫ እንድትሞሉ ትጠየቃላቹ፡፡  ዓምና ውጤት ከመጣ በኃላ በድጋሚ ዩኒቨርስቲ ምርጫቸውን እንዲያስተካከሉ እድል ተሰቶዋቸው ነበር ፤ በዚህ ዓመት ከተቀየረ አናቅም፡፡

ዩኒቨርስቲ ለዓመታት የምትቆዩበት ስለሆነ ፤ ዩኒቨርስቲ ስትመርጡ እነዚህን ማወቅ አለባቹ:

1. የምትመርጧቸው ዩኒቨርስቲዎች የምትፈልጉት field/department እንደሚሰጡ ማወቅ አለባቹ ይሄ ዋነኛው ነው። መማር የምትፈልጉትን field/department  ካልወሰናቹ ካሁኑ shortlist አድርጓቸው፡፡

2. ስለዩኒቨርስቲው ትምህርት ጥራት በተለይ እናንተ መማር የምትፈልጉት field/department  በደንብ አጣሩ፡፡

3. የምትመርጧቸውን ዩኒቨርስቲዎች እና ከተማውን youtube ላይ እዩ ፤ እዛ ዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚማር ተማሪ ሰው በሰው ጠይቁ፡፡ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ወንድም / እህት ካላቹ ከእነሱ ጋር High school አብረው የተማሩ ሌላ ጊቢ የደረሳቸው ተማሪዎች ስለሚኖሩ እነሱ ሊያጠያይቁላቹ ይችላል፡፡

4. እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (AAU) በጣም ሀሪፍ የሚባሉ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በጣም ተፈላጊ የሆኑ department እንደ Medicine, Software Engineering መግባት በጣም ከባድ ነው፡፡ ውጤት በደንብ ካልሰራቹ በስተቀር በጣም ተፈላጊ የሆነ department የማግኘታቹ እድል ጠባብ ነው፡፡ የመጀመሪያ ምርጫቹ ያልሆነ department ውስጥ ልትመደቡ ትችላላቹ፡፡

5. ዩኒቨርስቲ ምርጫ ስትሞሉ ከክፍል ጓደኞቻቹ ወይም ዩኒቨርስቲ ከሚማር ወንድም/እህታቹ ጋር አብሯቹ ሙሉ። የምትሞሉት ዩኒቨርስቲ እንደየፍላጎታቹ እና እንደምታገኙት ውጤት ሊለያይ ይችላል። ግን አብሯቹ ያሉት ጓደኞቻቹ ወይም ወንድም/እህታቹ ስለ አንዳንድ ዩኒቨርስቲ መረጃ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

6. የምትመርጧቸው ዩኒቨርስቲ ከከተማቹ ውጪ ከሆነ ፤ ስለከተማው ደህንነት እና ጸጥታ መረጃ አሰባስቡ፡፡

7. ዩኒቨርስቲው ያለበት ከተማ አየር ጸባይ ከግምት ውስጥ አስገቡ። አንዳንድ ተማሪዎች በጣም ሞቃታማ ቦታ ለዓመታት መኖር ሊያስቸግራቸው ይችላል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
"ከዚህ በኃላ በወረቀት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና እየቀነሰ በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና ቁጥር እየጨመረ የሚሔድ ይሆናል፡፡" - ትምህርት ሚኒስቴር

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን በተሰጠው ፈተና 29,718 ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸውም ተገልጿል፡፡

"የመሠረተ ልማት ሥራና የኮምፕዩተሮች አቅርቦትን አጠናክሮ በመቀጠል ወደፊት ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት እየተሠራ እንደሚገኝ" ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከሦስት ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት መንግሥት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል፡፡


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor