❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን #መኰንን_አርያኖስን_ለሚያጫውተው ለበገና ደርዳሪው #ለቅዱስ_ፊልሞንና ለጓደኛው #ለአናጉንስጢስ_ለቅዱስ_አስቃሎን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለእስክድርያ አገር ሃያ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ #ከሐዋርያው_ቅዱስ_አትናቴዎስ በኋላ ለተሹመት #ለአባ_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከማታሰቡ፦ ከከበሩ #ከቅዱሳን_ባስልዮስ_ከቴዎድሮስና #ከጢሞቴዎስ_በእስክድርያ አገር በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በገና ደርዳሪው #ቅዱስ_ፊልሞን ጓደኛው #ለአናጉንስጢስ_ለቅዱስ_አስቃሎን ፦ በአንዲትም ዕለት አርያኖስ አናጉንስጢስ አስቃሎንን ጠርቶ "ለአጵሎን ሠዋ" አለው አስቃሎንም ወደ ፊልሞን ሒዶ "በእኔ ፈንታ ብትሠዋ አራት የወርቅ ዲናር እስጥሃለሁ" አለው ፊልሞንም "ልብስህን ስጠኝና ተሸፋፍኜ በአንተ ፈንታ እሠዋለሁ" አለው። በገባም ጊዜ አውቀውት "ምን ሆንክ" አሉት ፊልሞንም "በክርስቶስ የማን ክርስቲያን ነኝ"አላቸው። አርያኖስም "በሕይወት እንድትኖር ለአማልክት ሰዋ" አለው። "ፊልሞንም በክርስቶስ ስም ከመሞት በቀር ሕይወት የለም" አለው። አርያኖስም "ጥምቀትን ሳታገኝ ፈጥኜ እገድልሃለሁ ተስፋህን ታጣለህ" አለው። ፊልሞንም ሰምቶ የክርስትና ጥምቀትን ያድለው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከሰማይ ብሩህ ደመና መጥቶ አጠመቀው። አርያኖስም አፍሮ ቢመለስ ብሎ ሦስት ወታደሮች እንዲጸፋት አዘዘ ፊልሞንም "የእግዚአብሔር መላእክት ስለ እኔ ደስ ሲላቸው አያለሁና ከዚህ የከፋ ቢጻፋኝም አልፍርም" አለ። አርያኖስም ባላ ባለው ግንድ ላይ ሰቅለው በፍላፃዎች ይነድፉት ዘንድ አዘዘ ግን ምንም የነካው የለም ፍላፃውም እንዳልካው ለአርያኖስ ነገሩት ዳግመኛም እርሱ እንደ ቆመ ይነድፉት ዘንድ አዘዘ አንዲትም ፍላፃ ተመልሳ፡ የአርያኖስን ዐይን ነድፋ ዐሳወረችው በዚያን ጊዜ ከተሰቀለበት አውርደው ከአናጉንስጢስ አስቃሎን ጋር ራሱን እንዲቆርጡ አዘዘ ገድላቸውን፡ ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊል የካቲት20 ተቀበሉ።
❤ መኰንኑም በፍላፃው ሕመም በተሠቃየ ጊዜ ከቅዱሳን ደም ወስዶ ከዐይኑ ውስጥ እንዲጨምር ሰዎች መከሩት ይህንንም ሲያደርግ ዳነ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመነ እሥረኞችንም ሁሉ ፈታቸው እርሱም መጋቢት ስምንት ቀን በዲዮቅልጥያኖስ እጅ በሰማዕትነት ዐረፈ። የሰማዕታትም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ጴጥሮስ፦ የእስክድርያ ሃያ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ ነው። ይህንንም ቅዱስ ከሐዋርያዊ አትናቴዎስ በኋላ በሹመቱ ወንበር በተቀበጠ ጊዜ ከንጉሥ ዳርዮስ ከከሀዲ አርዮስ ወገኖች ብዙ መከራ ደርሶበታል። ሊገሉትም በፈለጉ ጊዜ ሸሽቶ ሁለት ዓመት ያህል ተሠወረ አርዮሳውያንም ሉቅዮስ የተባለ ከሀዲውን ሰው በእርሱ ፈንታ በወንበሩ ላይ አስቀምጠው ሁለት ዓመት ኖረ። ከዚያም በኋላ ሃይማኖታቸው የቀና ምዕመናን ሁሉም ተነሥተው አርዮሳዊ ሉቅዮስን አሳደዱትና ይህን አባት ጴጥሮስን ወደ መንበረ ሢመቱ መለሱት አርዮሳውያንንም በመጣላት እያወገዛቸው እያሳደዳቸው ሰባት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የካቲት20 ዐርፎ ወደ ዘላለም ዕረፍት ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 20 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ለባስልዮስ_ብፁዕ። #ወቴዎድሮስ_ካዕለ#ወጢሞቴዎስ_ሣልስ ቅኑታነ ኃይል ወጽንዕ። ውስተ ቤተ መረዓ አምሳለ እሡራን ሰብእ። ዘተጸዋዕክሙ ኅቡረ ለስምዕ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_20።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ኵሉ ማዕበልከ ወሞገድከ እንተ ላዕሌየ ኃለፈ። ዓልተ ይኤዝዝ እግዚአብሔር ሣህሎ ወሌሊተ ይነግር። እምኀቤየ ብፅዐተ ሕይወትየ ለእግዚአብሔር"። መዝ 41፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥1-6፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 14፥21-24። የሚበበው ወንጌል ማቴ 16፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም፣ የጸሎትና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

Telegram
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)
❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886