ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
"በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን"።

            #የካቲት ፳ (20) ቀን።

እንኳን #መኰንን_አርያኖስን_ለሚያጫውተው ለበገና ደርዳሪው #ለቅዱስ_ፊልሞንና ለጓደኛው #ለአናጉንስጢስ_ለቅዱስ_አስቃሎን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለእስክድርያ አገር ሃያ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ #ከሐዋርያው_ቅዱስ_አትናቴዎስ በኋላ ለተሹመት #ለአባ_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከማታሰቡ፦ ከከበሩ #ከቅዱሳን_ባስልዮስ_ከቴዎድሮስና #ከጢሞቴዎስ_በእስክድርያ አገር በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
                          

                           
በገና ደርዳሪው #ቅዱስ_ፊልሞን ጓደኛው #ለአናጉንስጢስ_ለቅዱስ_አስቃሎን ፦ በአንዲትም ዕለት አርያኖስ አናጉንስጢስ አስቃሎንን ጠርቶ "ለአጵሎን ሠዋ" አለው አስቃሎንም ወደ ፊልሞን ሒዶ "በእኔ ፈንታ ብትሠዋ አራት የወርቅ ዲናር እስጥሃለሁ" አለው  ፊልሞንም "ልብስህን ስጠኝና ተሸፋፍኜ በአንተ ፈንታ እሠዋለሁ" አለው። በገባም ጊዜ አውቀውት "ምን ሆንክ" አሉት ፊልሞንም "በክርስቶስ የማን ክርስቲያን ነኝ"አላቸው። አርያኖስም "በሕይወት እንድትኖር ለአማልክት ሰዋ" አለው። "ፊልሞንም በክርስቶስ ስም ከመሞት በቀር ሕይወት የለም" አለው። አርያኖስም "ጥምቀትን ሳታገኝ ፈጥኜ እገድልሃለሁ ተስፋህን ታጣለህ" አለው። ፊልሞንም ሰምቶ የክርስትና ጥምቀትን ያድለው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከሰማይ ብሩህ ደመና መጥቶ አጠመቀው። አርያኖስም አፍሮ ቢመለስ ብሎ ሦስት ወታደሮች እንዲጸፋት አዘዘ ፊልሞንም "የእግዚአብሔር መላእክት ስለ እኔ ደስ ሲላቸው አያለሁና ከዚህ የከፋ ቢጻፋኝም አልፍርም" አለ። አርያኖስም ባላ ባለው ግንድ ላይ ሰቅለው በፍላፃዎች ይነድፉት ዘንድ አዘዘ ግን ምንም የነካው የለም ፍላፃውም እንዳልካው ለአርያኖስ ነገሩት ዳግመኛም እርሱ እንደ ቆመ ይነድፉት ዘንድ አዘዘ አንዲትም ፍላፃ ተመልሳ፡ የአርያኖስን ዐይን ነድፋ ዐሳወረችው በዚያን ጊዜ ከተሰቀለበት አውርደው ከአናጉንስጢስ አስቃሎን ጋር ራሱን እንዲቆርጡ አዘዘ ገድላቸውን፡ ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊል የካቲት20 ተቀበሉ።

መኰንኑም በፍላፃው ሕመም በተሠቃየ ጊዜ ከቅዱሳን ደም ወስዶ ከዐይኑ ውስጥ እንዲጨምር ሰዎች መከሩት ይህንንም ሲያደርግ ዳነ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመነ እሥረኞችንም ሁሉ ፈታቸው እርሱም መጋቢት ስምንት ቀን በዲዮቅልጥያኖስ እጅ በሰማዕትነት ዐረፈ። የሰማዕታትም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን።
                         
                           
#አባ_ጴጥሮስ፦ የእስክድርያ ሃያ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ ነው። ይህንንም ቅዱስ ከሐዋርያዊ አትናቴዎስ በኋላ በሹመቱ ወንበር በተቀበጠ ጊዜ ከንጉሥ ዳርዮስ ከከሀዲ አርዮስ ወገኖች ብዙ መከራ ደርሶበታል። ሊገሉትም በፈለጉ ጊዜ ሸሽቶ ሁለት ዓመት ያህል ተሠወረ አርዮሳውያንም ሉቅዮስ የተባለ ከሀዲውን ሰው በእርሱ ፈንታ በወንበሩ ላይ አስቀምጠው ሁለት ዓመት ኖረ። ከዚያም በኋላ ሃይማኖታቸው የቀና ምዕመናን ሁሉም ተነሥተው አርዮሳዊ ሉቅዮስን አሳደዱትና ይህን አባት ጴጥሮስን ወደ መንበረ ሢመቱ መለሱት አርዮሳውያንንም በመጣላት እያወገዛቸው እያሳደዳቸው ሰባት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የካቲት20 ዐርፎ ወደ ዘላለም ዕረፍት ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 20 ስንክሳር።
                           
                            
"#ሰላም_እብል_ለባስልዮስ_ብፁዕ። #ወቴዎድሮስ_ካዕለ#ወጢሞቴዎስ_ሣልስ ቅኑታነ ኃይል ወጽንዕ። ውስተ ቤተ መረዓ አምሳለ እሡራን ሰብእ። ዘተጸዋዕክሙ ኅቡረ ለስምዕ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_20


                           
#የዕለቱ_ምስባክ፦ "ኵሉ ማዕበልከ ወሞገድከ እንተ ላዕሌየ ኃለፈ። ዓልተ ይኤዝዝ እግዚአብሔር ሣህሎ ወሌሊተ ይነግር። እምኀቤየ ብፅዐተ ሕይወትየ ለእግዚአብሔር"። መዝ 41፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥1-6፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 14፥21-24። የሚበበው ወንጌል ማቴ 16፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም፣ የጸሎትና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። 
                               
@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL    
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

            #የካቲት ፳፪ (22) ቀን።

እንኳን የፋርስ ንጉሥ ልጅ በጸሎቱ ከነበረባት ጋኔን ለፈወሳት #ለኤጲስቆጶስ_ለአባ_ማሩና ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያና በከሀዲ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን #በፋርስ_አገር_ለተገደሉ_ሰማዕታት ለሥጋቸው ለፈለሰበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰቡ፦ ከከበረ #ከአባ_ቡላና_ከሦስት_መቶ_ሰማንያ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                            
#አባ_ማሩና፦ ኤጲስቆጶስ ማሩናንም ስለ ድንቆች ተአምራቶቹ ስለ ትሩፋቱና ስለ ጽድቁ የአኖርዮስና የአርቃድዎስ አባት ታላቁ ቴዎዶስዮስ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋር እጅ መንሻ በመካከላቸው ስለ አለው ፍቅር ተላከ። ወደ ሳቦር ወደ ፋርስ ንጉሥም በደረሰ ጊዜ ታላቅ ክብርንም አከበረው በቤተ መንግሥቱም እልፍኝ ውስጥ አኖረው።

ይህ ቅዱስም የንጉሡ ልጅ ጋኔን አድሮበት እንደታመመች በሰማ ጊዜ የከበረ አባ ማሩና ብላቴናዪቱን ጠርቶ በፊቱ አቁሞ በላይዋ ጸለየ ጋኔኑም ከእርሷ ወጥቶ ዳነች ንጉሡም ልጁ እንደ ዳነች አይቶ እጅግ ደስ አለው የአባ ማሩናንም ፍቅርና አክብሮት ጨመረ። ከዚህም በኋላ አባ ማሩና በፋርስ አገር በሰማዕትነት ስለሞቱ የከበሩ ሰማዕታት ሥጋቸውን ስለ መሰብሰብ ከንጉሥ ዘንድ ፈለገ ንጉሡም የሰማዕታትን ሥጋቸውን ይሰብስቡ ዘንድ አዘዘ ያች ቤተ ክርስቲያንም በዚች ዕለት ከበረች። ዳግመኛም በታላቋ ከተማ ውስጥ በከበረ አባ ማሩና ስም ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠሩ እርሷም ማረፊያ የተባለች ናት።

ከዚህም በኋላ ይህ አባት ወደ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ተመልሶ በሮሜ አገር ሁለት ዓመት ተቀመጠ የእነዚያ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በዚች በየካቲት22 ዕለት ዐረፈ ከቤተ ክርስቲያኒቱም ክብር ጋር በዓሉንና መታሰቢያውን የሚከብሩበት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባ ማሩና በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 22 ስንክሳር።

                            
"#ሰላም_ለማሩና_ሠናየ_ተልእኮ_ቀሲስ። ወዓዲ ካዕበ ኤጲቆጶስ። ቤተ ሰማዕታት ሐኒፆ በአገረ ፋርስ። በዕለተ ቀደሳ #በስመ_ኢየሱስ_ክርስቶስ። ተጸውዐ ዮም ለመርዓ ሐዳስ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_22

                            
#የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዘይሰማዕ ግብር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ። እስመ ኪያከ ተወከልኩ እግዚኦ። ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተ እንተ ባቲ አሐውር"። መዝ 142፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 12፥1-14፣ 1ኛ ጴጥ 1፥6-10 እና የሐዋ ሥራ 16፥16-19።  የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 13፥10-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL
                             
#አባ_ቄርሎስ፦ ይህም አባት የእስክንድርያ ሰባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ነው። እርሱም በምግባሩ ፍጹም ዐዋቂ ሆነ በአገሩ ፍዩም ይባላል በእርሷም ቅስና ተሹሞባት ነበር። ከዚያም ለቆ ወደ አባ ፊቅጦር ገዳም ደረሰ እርሱም ከምስር ከተማ ውጭ የኢትዮጵያውያን ዐዘቅት የዐባይ ግድብ በአለበት ነው። በዚም ታላቅ ገድልን እየተጋደለ ብዙ ዘመናትን ኖረ። ብዙ መጻሕፍትንም ተምሮ ትርጓሜያቸውንና ምሥጢራቸውን ጠንቅቆ ዐወቀ። አሸናፊ ወደሚባለውም ንጉሥ አደባባይ ቀርቦ የእስላሞች ታላላቅ ሊቃውንቶቻቸውና ከምሁራኖቻቸው ውስጥ መምህሮታቸውን ተከራከሩት። ጠቃሚ የሆነ ዕውቀት የተመላበትን መልስ አገኙ የሚጠይቁትንም ሁሉ በመልካም አመላለስ ነገራቸው ከዚህ በኋላ የዕውቀቱና የቅድስናው ዜና በተሰማ ጊዜ ያለ ፈቃዱ ይዘው በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት መንጋውንም ጠበቀ በጸሎትና በቅዳሴ ያገለግሉ ዘንድ ለካህናት ሥርዓትንና መመሪያን ሠራ።

ይህም አባት በሊቀ ጵጵስናው ሰባት ዓመታት ከዘጠኝ ወር ከዐሥር ቀኖች ኖረ። ከቀኑም በሦስት ሰዓት መጋቢት14 ቀን ዐረፈ። በምስክርነት አደባባይም ተቀበረ። ከአባ ቄርሎስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

                             
የከበሩ #ቅዱሳን_አጋንዮስ_አውንድርያኖስና_ብንድዮስ፦ እሊህም ቅዱሳን ከአባቶቻቸው ጀምሮ ክርስቲያኖች ናቸው። አምላካዊ ትምህርትንም ሁሉ የተማሩ ናቸው።

በእግዚአብሔርም ሕግ ጸንተው ሲኖሩ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አርሞስ መርጦ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ ሾማቸው ግን በታወቁ ቦታዎች ላይ አይደለም በብዙዎች አገሮች ውስጥ እንዲሰብኩ ላካቸው እንጂ። በአገሮችም ያሉ ከሀድያን ያዟቸው ያለርህራሄም አብዝተው ገረፏቸው በደንጊያም ወገራቸው መጋቢት 14 ቀን ነፍሳቸውንም በጌታች እጅ ሰጡ። የከበሩ ቅዱሳን አጋንዮስ፣ አውንድርያኖስና ብንድዮስ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት14 ስንክሳር።

                             
"#ሰላም_ለቶማስ_እንዘ_ይገብር_መድምመ። እምነ ብእሲት አግኂሦ ትድምርተ ጋኔን ኅሡመ። መንጽሔ ኃጢአት መጠዋ ሥጋ ወደመ። በጊዜ ትቤሎ ሀበኒ ማሕተመ። ከመ ላዕሌየ ኢይግባእ ዳግመ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢ_14

                            
#የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥9-ፍ.ም፣ ያዕ 4፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 6፥1-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 7፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw
🌹 "#ሰላም_ለአበይዶ_መጠነ_ዮሐኒ_መጠኑ። እስመ ውእቱ ረድኡ ወውስተ ኵሉ ምእመኑ። ለዝ ፃማዊ #ወፈጻሜ_መልእክት_ዘበበበይኑ። ጼና አልባሲሁ ከመ ጼና ስሂን ይጼኑ። ወይበርህ እምፀሐይ ምስብዒተ ስኑ"። ትርጉም፦#የማዕርጉ_መጠን_እንደ_ዮሐኒ ማዕርግ መጠን ለኾነ #ለአባ_አበይዶ_ሰላምታ_ይገባል እርሱ አገልጋዩና በኹሉም ውስጥ ታማኙ ነውና፤ በየወገኑ አገልግሎትን ለሚፈጽምና ለዚኽ ትጉህ ለኾነ ሰው የልብሶቹ ሽታ እንደ ዕጣን መዐዛ ይሸታል፤ የልብሱ ሽታ እንደ ዕጣን ጢስ ይሸታሉ፤ ደም ግባቱም ከፀሓይ ሰባት እጅ ይበራል። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር_4

🌹 "#ብፁዕ_ውእቱ_አባ_አበይዶ ረድአ ዘኮኖ #ለአባ_ዮሐኒ ብፁዕ ብእሲ በትዕግሥቱ ዘፈጸመ ገድሎ"። ትርጉም፦ #ለአባ_ዮሐኒ_አገልጋይ የኾነው #አባ_አበይዶ ንኡድ ክቡር ነው፤ ተጋድሎውን በትዕግሥቱ የፈጸመ የኾነ ርሱም ንኡድ ክቡር ነው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ

🌹 "#ሰላም_ለአባ_አብይዶ ለጸላኢ ዘኬዶ"። ትርጉም፦ ጠላትን የረገጠው ለኾነ #ለአባ_አበይዶ_ሰላምታ_ይገባል#ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ

🌹 #የአባ_አበይዶ ታሪክ ከአባታቸው #ከአባ_ዮሐኒ ጋር ነገ #በኅዳር_5 አብሮ ይቀርባል።