ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#እግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን #መስቀልና#መድኃኔዓለምን ታቦት ሰጠው፡፡ ዳግመኛም የ #እግዚአብሔር መልአክ የተዘጋጀ ኅብስትና የተቀዳ ጽዋን፤ ለመሥዋዕት የሚሆነውንም ሁሉ ሰጠው፤ አባታችንም ከካህናት ጋር በዚያች ቤተ ክርስቲያን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሰጣቸው፡፡

በቤተ ክርስቲያን አጠገብ አንዲት የዋንዛ ዛፍ ነበረች፤ ሕዝቡም ይሰበሰቡባትና በሥሯ ተቀምጠው ክፉ ሥራ ይሠሩ ነበር፤ አባታችንም ‹‹ለምን እንዲህ የማይገባ ሥራ ትሠራላችሁ? ሲላቸው እነርሱ ግን አልሰሙም፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችንም ያቺን ዛፍ ‹‹ከበታችሽ ካሉት ሕዝብ ጋር ተነሥተሽ ሒጂ›› ብሎ በቃሉ አዘዛት፡፡ ያን ጊዜም ያች ዛፍ ከሕዝቡ ጋር ተነሥታ የሁለት ጦር ውርወራ ያህል ሔደች፡፡ #ጌታችን በቅዱስ ወንጌሉ ‹‹የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁና ይችን ሾላ ተነስተሽ ወደዚህ ነይ ብትሏት ትመጣለች፤ ይህን ተራራ ከዚህ ሂድ ብትሉት ይሄዳል›› እንዳለ አባታችን አባ ዘግሩምም ይህንን አደረጉ፡፡

ከአባታችን ይባረኩ፤ እጅ ይነሡም ዘንድ አርባ አራት ቅዱሳን በደመና ተጭነው አባታችን ካለበት ቦታ ወደ ዐደል መጡ፡፡ ሶምሶን ከአህያ መንጋጋ፤ ሙሴ ከዐለት ውሃ እንዳፈለቁ ሁሉ ለሚያስፈልጋቸው ነገር ይጠቀሙበት ዘንድ አባታችንም በጸሎቱ በአንድ ጊዜ አርባ አራት የውሃ ምንጮችን አፍልቆ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ይህን አይተው አደነቁ፤ ስምህ ዘግሩም ይሁን አሉት፤ ስለዚህም አባታችን አባ ዘግሩም ተባለ፤ ምንጮቹም ድውያንንና ሕሙማንን የሚፈውሱ ሆኑ፡፡

ዳግመኛም ለአባታችን የሚገለገልበት አንድ አህያ ነበረው፤ የሚጭነው ሰው ሳይከተለው ለሁለት ቀናት ሔዶ ወደ ጫነው ሰው ቤት ይመለስ ነበር፤ የአገሩ ሰዎችም ይህን አይተው ያላቸውን ሁሉ ይጭኑትና ብቻውን ሔዶ ወደ አባታችን ይመለስ ነበር፡፡

የአቡነ ብርሃነ መስቀልን ተአምራቱን ዜናውን በሰማ ጊዜ ከንጉሡ ባለሟሎች አንዱ መጣ፡፡ ሌላም በቤቱ አጠገብ የሚኖር አንድ ሰው መጣና ‹‹ጨው ጭኜ ወደ ገበያ እወስድበት ዘንድ አህያህን ስጠኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ የተቸገሩትን ለመርዳት የሚልከው አንድ አህያ ነበረውና አባ አብርሃምም ‹‹የጨው መጠን ምን ያህል ነው?›› አለው፡፡ ያ ሰውም ‹‹በሰቅል ስሳ ይሆናል›› አለው፡፡ አባታችን አብርሃምም ‹‹ውሰደው ከተናገርኸው በላይ ግን አትጫነው›› አለው፡፡ ሰውየውም አህያውን ወስዶ አባታችን እንዳለው ጫነው፤ ለአባታችን ያልነገረውን በቤቱ የተረፈውን ግን ያ ሰውና ወንድሙ ተሸከሙት፡፡ እነርሱም ተካፍለው ተሸክመው መንገዳቸውን እየሄዱ ሳለ ከአገር ብዙ በራቁ ጊዜ ወንድሙን ‹‹ና አህያውን እንጫነውና እንደፈቀድነው እንሒድ የሚያየን የለምና›› አለው፡፡ በዚሀመ ምክራቸው መሠረት ተሸክመውት የነበረውነ በአህያው ላይ ጫኑት፡፡ ነገረ ግን አህያው መንቀሳቀስን ፈጽሞ እምቢ አለ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ ሲገፉትና ሲደበድቡት ብዙ ደከሙ፤ እንዲህ እያደረጉ ሳሉ አንድ አገልጋይ የንጉሥ መልእክት ይዞ መጣ፡፡ እኒህን ስሕተተኞችም አገኛቸውና ‹‹ጌቶቼ ለምን ትደክማላችሁ?›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ይህ አህያ አልሄድም አለን›› አሉት፤ የንጉሡ መልእክተኛም #መንፈስ_ቅዱስ አነሳሳውና ከፊታቸው ቆመና ‹‹የዚህ ነገር ምክንያቱ ምንድን ነው?›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ይህን አህያ ከአንድ #መንፈስ_ቅዱስ ካደረበት ቀሲስ አመጣነው፤ በዚህ ቀሲስ ቃል ላይ በጨመርን ጊዜ መሔድን እምቢ አለን›› በማለት የሠሩትን ነገሩት፡፡ ‹‹እስኪ የጨመራችሁትን ቀንሱለት›› አላቸው፤ ቀነሱለትና ያን ጊዜ አህያው ተነሥቶ እነርሱም ወደሚፈልጉበት ቦታ ሔዱ፡፡ ይህንንም ሁለት ጊዜ ሦስት ጊዜ ደጋግመው አደረጉ እምቢም አላቸው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የቅዱሱን ቃል በመተላለፋቸው እንደሆነ አወቁ፤ ያም የንጉሡ አገልጋይ ተደንቆ ‹‹ኑ ይህ ቅዱስ ካለበት አድርሱኝ›› አላቸው፡፡ አባታችን ካለበት ቦታም ደርሶ ከእርሱ ዘንድ ተባረከ፡፡

ያም አህያውን የወሰደው ሰው ከአቡነ ብርሃነ መስቀል እግር ሥር ተንበርክኮ ‹‹በፊትህ በድያለሁና ቃልህንም አሳብያለሁና አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ፤ አህያውም መሄድን እምቢ አለ፤ የጨመርንበትን ሸክም በቀነስንለት ጊዜ ግን ይሄዳል›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹…እኔ ግን እንደ እኔ አይነት ሰው ነህ መስሎኝ ቃልህን አፈረስሁ፤ አንተ ግን በፍቅርህ ገመድ ሳብኸኝ›› አለው፡፡ አባታችን ብርሃነ መስቀልም ‹‹ለምን ሐሰት ተናገርህ? መጽሐፍ ‹ሐሰት የኀጢአት መጀመሪያ ናት፤ ሐሰተኞችም የ #እግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም› ይል የለምን?›› በማለት ከመከረው በኋላ በሰላም ወደቤቱ እንዲሔድ ነገረው፡፡

ያም ሰው ከአቡነ ብርሃነ መስቀል ዘንድ ወጥቶ መንገዱን ሔደ፤ ያ የንጉሡ መልእክተኛም አብርሃም ከተባለ ከአቡነ ዘግሩም ዘንድ ተባርኮ ወጣ፤ የቤተ ክርስቲያኗንም አሠራር አይቶ የአባታችን የአብርሃምን ተአምር አደነቀ፤ የንጉሡን ትእዛዝ ይፈጽም ዘንድም መንገዱን ሄደ፡፡ ከብዙ ቀናት በኋላ ያ መልእክተኛ ከንጉሡ ዘንድ ደረሰ፤ ስመ መንግሥቱ ቆስጠንጢኖስ ለተባለ የ #እግዚአብሔር ወዳጅ ለሆነ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩን ነገረው፡፡ ‹‹ጻድቅ ንጹሕ የሆነ ቀሲስ አለ፤ በዚህ ዘመን በመንግሥትህ ሀገር ሁሉ እንደርሱ ያለ ሰው የለም፤ ሥራው ሁሉ እንደቀደሙት አባቶች ነውና›› አለው፡፡

በዐይኑ ያየውን፤ በጆሮው የሰማውን ሁሉ ስለሠራት ቤተ ክርስቲያንም ነገረው፤ ንጉሡም ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ በልቡ ተደሰተ፤ በመንፈሱም ሐሴትን አደረገ፤ #እግዚአብሔርንም አመሰገነው፤ እንዲህም አለ፡- ‹‹በዘመነ መንግሥቴ የተሰወረውን የሚያውቅ፤ ተአምራትን የሚያደርግ እንዲህ ያለ ጻድቅ ሰውን የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ #እግዚአብሔር ስሙ ይክበር፡፡ አባቴ ቤተ ክርስቲያን ማነጽ በፈለግህ ጊዜ ወደ እኔ ለምን አልላክህም ብሎ ላከበት፤ እኔ ከደቀ መዛሙርትህ እንደ አንዱ አይደለሁምን በረከትህን በተቀበልሁ ነበር አለ፡፡ በዚህ የመንግሥት ዙፋን ላይ ያለሁ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንጂ በራሴ ፈቃድ ይመስልሃልን በእስረኞች መካከል ሳለሁ ከእስረኞች መካከልም ተኝቼ ሳለ ከዚያ አውጥቶ በአባቶቼ በሰይፈ አርዕድና በዐምደ ጽዮን ዙፋን ላይ አስቀመጠኝ፡፡ አንተ ግን በኀጢአቴ አትናቀኝ፤ ለቤተ ክርስቲያን የምትፈልገውን ይህን ገንዘብ ውሰድ፡፡›› ዳግመኛም ለአባታችን ልብስ ላከለት፤ ሚስቱም እንዲሁ ላከች ‹‹በጸሎትህ አትርሳን›› አሉት፡፡

ከዚህም በኋላ ይመነኩስ ዘንድ ወደደ፤ የመላእክትና የቅዱሳን ልብስ የምትሆን የምንኩስና ልብስን ያለብሰው ዘንድ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድእ ወደ ሆነው ወደ አባ ብሶይ መጣ፡፡ ወደ እርሱ ደርሶ ሥርዐተ ምንኩስና ከፈጸመለት በኋላ አባታችን አብርሃም ‹‹የቀድሞ ስሜን ተውልኝ›› አለው፤ አባ ብሶይም ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ስም እንደ ለወጠላቸው ስምህን እለውጣለሁ እንጂ አይሆንም›› አለው፡፡ ‹‹ስምህንም አብርሃም፣ ጳውሎስ፣ ዮሐንስ ከሚሉት መካከል ዕጣ በማጣጣል እሰይምሃለሁ›› አለው፡፡

ሦስት ጊዜም ዕጣ ጣሉ፤ አብርሃም የሚለውም ስም ወጣ፤ ይህ ነገር ከ #እግዚአብሔር እንደሆነ አወቀ፡፡ ከታናሽነቱ ጀምሮ የአብርሃም ምግባር የሆነውን እንግዳ መቀበልን፣ እግር ማጠብንና የተራበውን ማብላት ጀመረ፤ ስለዚህ አብርሃም መባል ተገባው፡፡ ‹‹ከታናሽነቴ ጀምሮ የአብርሃምን ሃይማኖት እንደወደድሁ፣ እንግዳ በመቀበል እንደ ኖርሁ ይህን ስም የሰጠኝ #እግዚአብሔር ይመስገን›› አለ፡፡ መንኩሶ በፈቃዱ አብርሃም ተብሎ ተጠርቷልና በብዙ ገድልና በትሕርምት በዚያች ቦታ ኖረ፡፡
የነዳያን ፍቅር በልቡ ውስጥ አለ፤ ሁል ጊዜ ስለ ምግባቸውና ስለ ልብሳቸው ያስብ ነበር፤ ለሚያስፈልጋቸው ነገርም ገንዘብ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ለድኆች ልብሱን ያካፍላል፤ ለእነርሱም ሰጥቶ እርሱ ራቁቱን ይቆማል፤ ልጆቹም ይመጣሉ፤ ‹‹ልብስህ ወዴት ነው?›› ይሉት ነበር፤ እርሱም ‹‹ሌቦች በማያገኙበት ቦታ አለ›› ይላቸው ነበር፡፡ ልጆቹ ግን ሥራውን አያውቁም ነበር፤ ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንበት ሁሉን ይሠውር ነበር፤ አይገልጥላቸውም ነበር፤ ድኃ ባየ ጊዜ አጽፉን ይሰጥ ነበር፤ አጽፉን ይቅርና ምንም ልብስ አያስቀርም ነበር፡፡

አንድ ቀን አንድ ድኃ መጥቶ ስለ #እግዚአብሔር ስም ምግብና ልብስ ለመነው፡፡ አባታችን ያን ድኃ ባየው ጊዜ አጽፉን ሰጠው፤ ዳግመኛ አንድ ድኃ መጣ፤ በቤቱም የሚሰጠውን አጣ፤ መጠምጠሚያውን አውርዶ እርሷንም ለድኃው ሰጠውና በቤቱ ተቀመጠ፡፡ አንድ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ መጥቶ ራቁቱን አገኘውና ተቆጣበት፤ ‹‹ክቡር አባቴ ሆይ! ለምን እንዲህ ትሆናለህ? አለው፡፡ ‹‹ለምትበላውና ለምትለብሰው ሳታስቀር ያለ አቅምህ ለምን ምጽዋት ትሰጣለህ? ልብስህንና መጎናጸፊያህን ሰጥተህ አንተ ራቁትህን ትሆናለህ፡፡›› አባታችንም ‹‹ልጄ ሆይ! ፈጽሞ ስለሚያረጅና ስለሚጠፋ የዚህ ዓለም ልብስ ፈንታ የብርሃን መጎናጸፊያ የሚያለብሰኝ አምላኬ አለልኝ›› አለ፤ ልጆቹም ሌላም ልብስ አምጥተው አለበሱ፡፡ ‹‹ይህንም እንደ ቀደመው አታድርግ›› አሉት፤ እርሱ ግን ስለ ድኆችና ስለ ችግረኞች ፍቅር ብዙ ጊዜ ምጽዋት ያደርግ ነበር፤ ቅብዓት በሰውነት፣ ውሃ በአንጀት እንዲገባ የነዳያን ፍቅር ወደ ልቡ ገባ፡፡

የነዳያንን የጩኸት ድምፅ በሰማ ጊዜ ከልቡ ደስታ የተነሣ ለመነሣት ይፈልጋል፤ ከማእድ ላይ ቢሆንም እንኳን ድምፃቸውን ከሰማ እጁን ወደ ማእድ አያወርድም ነበር፤ ይሰጣል እንጂ ምንም ነገር አያተርፍም ነበር፡፡ ነዳያን ግን ዘወትር ጩኸትና ልመናን አያቋርጡም ነበር፤ አባታችን ስለ ምግባቸውና ስለ ልብሳቸው እንደሚያስብ አውቀው ከቤቱ አይርቁም ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ አንዲት ታላቅ ሀገር ሔዶ ከዚያ ደረሰ፤ በሰንበት ምሽት ለእሑድ አጥቢያ ከዚያ አደረ፤ ሥርዓተ ቁርባን ከተፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሩን ‹‹ልጄ የምንበላው ነገር አለህ ወይስ የለህም?›› አለው፤ ያ ደቀ መዝሙርም ‹‹አባቴ አዎን አለኝ›› አለው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ያያቸውን ታላላቅ መነኮሳት ሰበሰበ፤ ቁጥራቸውም ዐራት መምህራን ነበሩ፡፡ የተዘጋጀ ምግብና ጠላ ያን ጊዜ እነርሱም ከቤታቸው እንጀራ አመጡ፤ ሁለት ያመጣ አለ፤ ሦስትም ያመጣ አለ፤ ሁላቸውም እንደ አቅማቸው አመጡ፤ አባታችንም ጸሎት ያደርግ ዘንድ ተነሣ፤ ባረከላቸውም፡፡

ደቀ መዝሙሩንም ‹‹ጠላውን አምጣው›› አለው፤ ሁለት መነኮሳትም እንሥራውን አመጡት፤ ከመካከላቸው አንዱን ጠጣ አለው፤ ቀምሶም ለአባታችን ሰጠው፤ ጣዕሙ ደስ ባሰኘው ጊዜ አባታችን ከሩቅ ሀገር የመጡ የተራቡ ሰዎች ከቤቱ ደጃፍ እንዳሉ አወቀ፡፡ መነኮሳቱንም ‹‹አባቶቼ፣ ወንድሞቼና ልጆቼ ፈቃዳችሁ ከሆነስ ለ #ክርስቶስ እንሰጠው ዘንድ ለነዳያንና ለችግረኞች እንስጣቸው›› አላቸው፡፡

በቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ወንድሞች መነኮሳት፣ ክቡራን ካህናት፣ ዲያቆናትና ሕዝቡ የ #መንፈስ_ቅዱስ ማደሪያ የሆነ፣ በወንጌል ወተት ያደገ፣ የ #እግዚአብሔር ሰው የሆነ የአባታችንን ትሕትና፣ ትሩፋትና ቅድስና ባዩ ጊዜ አዘኑበት፡፡ ምንም ቃል አልመለሱለትም፤ በቦታቸው ወይም በቤታቸው አልነበሩምና፤ በልባቸው ‹‹እኛስ ከሩቅ ሀገር የመጣን አይደለምን?›› አሉ፡፡ እነርሱ ግን ከዚያው ይኖሩ ነበር፤ አባታችን ግን ነዳያንን ሰብስቦ ያንን ምግብ ሰጣቸው፡፡

ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡ እነዚያ መነኮሳትም አንዲት ቃል አልተናገሩም፤ ነገር ግን በልባቸው ተቆጡ፤ በጣምም አዘኑ፤ አባታችን ግን ደቀ መዛሙርቱን ሌላ ማእድ ያቀርቡ ዘንድ አዘዘ፤ ከመንገድ ስንቅ ይመገቡ ነበርና ጥቂት አመጡ፡፡ ገና ሳይቀምሱም ከሕዝብ አንዱ ‹‹አባቴ ሆይ! ጸልይልኝ፤ ይህን ጥቂት በረከትም ተቀበል›› ብሎ ብዙ ጠላ ላከ፤ እነዚህ መነኮሳት ግን ይህን ባዩ ጊዜ ፈጽመው ተደነቁ፤ ፈጽመው ፈሩ፤ ተንቀጠቀጡም፡፡ አባታችንም ተነሥቶ ለ #ክርስቶስ ሰጠሁት፤ ለተራቡትም አስቀደምሁ፤ ለድኆች የሚሰጥ ለ #እግዚአብሔር ያበድራል የሚል ተጽፏልና አላቸው፡፡

እነዚህ መነኮሳትም ‹‹አባታችን መምህራችን ሆይ! ይቅር በለን አንተ ብዙ ሐዘንን ታውቃለህና፤ እኛ ስለሆዳችንና ስለልብሳችን አዘንን፤ አንተ ግን እንደ ጌታህ #ክርስቶስ የድኆችና የችግረኞች ወዳጅ ነህና›› አሉት፡፡ ‹‹አላወቅንምና አባታችን ይቅር በለን፤ አንተ ፈቃደ #እግዚአብሔርን ትፈጽማለህ፤ እርሱም ልመናህን ይሰማልና›› አሉት፡፡ ‹‹እንዲሰጥህ አላወቅንም፤ ነገር ግን ጎተራህን ሁሉ እንደሚሞላልህ ሰምተን ነበር፤ የተዘጋጀ ምግብንም እንዳወረደልህ ሰምተን ረሳን፤ አሁንም አባታችን ይቅር በለን፤ ባንተ ላይ ተቆጥተን ነበር፤ #እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሆነ አላወቅንም፤ አንተ ግን አስቀድመህ ለተራቡት ሰጠህ፤ ቀጥሎም ከአምላክህ በረከት ለእኛ ለመብላት ለተዘጋጀን ሰጠኸን›› አሉት፡፡ አባታችን ዘግሩምም ‹‹ወንድሞቼና ልጆቼ ይህን የማደርገው ለሰው ልታይ ብዬ አይደለም፤ ለትምክህትም አይደለም፤ #እግዚአብሔር የሰጠኝ ሀብት ነው እንጂ›› አላቸው፡፡ ‹‹እኔ እሰጣለሁ፤ እርሱም የሚያስፈልገኝን ነገር አላሳጣኝም›› አላቸው፤ እነርሱም ከእርሱ ተባረኩ፤ ከዚህም በኋላ ታላላቅ ተአምራትና ድንቅ ነገርን የሚያደርግ የ #እግዚአብሔርን ገናናነት ተነጋገሩ፡፡

ከዕለታት አንድ ቀንም አባ ዘግሩም ቆሞ ሳለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ እርሱ መጣ፤ ቅድስት የሆነች የጎኑን መወጋትና ቁስሎቹን ሁሉ አሳየው፡፡ በደሙ መፍሰስም ተደሰተ፤ ሰግዶም እንዲህ አለ፤ ‹‹#ጌታየ የሚፈሰውን ደምህን እዳስስ ዘንድ ፍቀድልኝ›› አለው፤ #ጌታችንም ቅዱስ የሆነ ደሙን ይዳስስ ዘንድ ፈቀደለት፤ እንደ ቅዱስ ቶማስም ጎኑን ዳሰሰ፤ ቅዱስ ቶማስስ ደቀ መዛሙርቱን ስላላመነ ነበር፤ ይህ አባታችን ግን #ጌታችን ‹‹ሳያዩኝ የሚያምኑኝ ብፁዓን ናቸው›› ብሎ እንደተናገረው ሳያይ ያመነ ነው፡፡ ይህ አባታችን ግን ሳያይ አመነ፤ በቅዱስ ደሙ መፍሰስም ደስ አለው፤ ወንድሞቼ ሆይ ለአባታችን የተሰጠውን ጸጋ ተመልከቱ፤ የ #መድኃኒታችንን ቁስሎች ዳስሷልና፤ ለድኆች የማዘን ፍሬው ይህ ነው፤ ‹‹ለድኆች የሚራራ ለ #እግዚአብሔር ያበድራል›› ተብሏልና፡፡

ለሰው ልጅ የሚሰጥ ታላቅ ጸጋን አገኘ፤ ከሀገሮች ሲመለስም ወደ ደብረ ጽዮን ለመሄድ ግባ ከተባለ ታላቅ ወንዝ ደረሰ፤ ከፈሳሹ ብዛት የተነሣ ስትበረታታ አገኛት፡፡ ብዙ ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ የሚያደርጉትንም አጡ፤ ብፁዕ አባታችን ግን ከወንዙ ዳር ቆመ፤ በምርጉዙም በባሕሩ ላይ አማተበ፤ ያን ጊዜ ወንዙ ወዲያና ወዲህ ተከፈለ፤ በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተሻገሩ፡፡ ነቢዩ ሙሴ የኤርትራን ባሕር በከፈላት ሕዝቡንም በመራ ጊዜ እንደ ተሻገሩ ሁሉ ተሻግረዋልና #እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ይህም አባታችን ባሕርን በየብስ አሻገራቸው፤ ከዚህ በኋላ በሰላም ወደ ቤቱ ደረሰ፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ገድለ_ቅድስት_ጸበለ_ማርያም#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_24 እና #ከገድላት_አንደበት)
#ጥቅምት_25

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) አረፈ፣ የመላእክት አምሳል የሆነ #አባ_እብሎይ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው፣ የደብረ ሊባኖሱ #አባ_ሕፃን_ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ)

ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን ታላቅና ክብር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው እነርሱም ከሮሜ አገር ሉፊ ከሚባል አውራጃ ናቸው በዘመናቸውም ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራ ስለ አመጣ ስደት ሁኖ ነበርና እነርሱም በስደት ብዙ ዘመን ኖሩ።

ልጅንም በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ #እግዚአብሔር ለመኑ የ #እግዚአብሔርም መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው።

ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ ቡላ የ #እግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው የሚል ጽሑፍ ነበረበት።

በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን #ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው እርሱም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው እናትና አባቱም ሳይነግሩት ቡላ ስለ ሰየመው አደነቁ ዕፁብ ዕፁብ አሉ።

ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ በጸለየ ጊዜ የቊርባን ኅብስትና ወይን የተመላ ጽዋ ከሰማይ ወረደ እርሱም ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከሕፃኑ ጋር አቀበላቸው በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ የአንድ ዓመት ልጅ ሲሆን በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከ #ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ #አብ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከ #አብ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ #ወልድ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በ #አብ#ወልድ ጋር አንድ የሆነ #መንፈስ_ቅዱስ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ ተናገረ።

ከጥቂት ዘመንም በኋላ አባትና እናቱ ኅዳር ሰባት ቀን ሙተው ሕፃኑ ብቻውን ቀረ።

ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በአካል ታናሽነቱን አይቶ እጅግ አደነቀ በዚያንም ጊዜ በችንካር እንዲቸነክሩት ሥጋውንም እንዲሠነጣጥቁት ቆዳውንም ከዐጥንቱ እንዲገፉ እጆቹንና እግሮቹንም በመጋዝ እንዲቆርጡ ጀርባውንም እንዲገርፉ በሾተሎችና በጦሮች መካከል አድርገው ከመንኰርኵር ውስጥ እንዲጨምሩት ዳግመኛም በመንገድ ላይ እንዲጐትቱት አዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው።

ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ መኰንን ሒዶ እርሱንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ መኰንኑም ተቆጥቶ በሚያዝያ ወር ዐሥራ ስምንት ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ የምንኲስና ልብስንና አስኬማን በ #መስቀልም ምልክት አለበሰው። እንዲህም አለው ከቅዱሳን ጻድቃን አንድነት ትሆን ዘንድ #እግዚአብሔር አዝዞሃል።

ያን ጊዜም ቅዱስ አባ ቡላ ከደረቅ ተራራ ላይ ወጣ ያለ ማቋረጥም በውስጧ እየተጋደለ ኖረ። የ #ጌታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን መከራውንና ስቅለቱን በአሰበ ጊዜ ከረጅም ዕንጨት ላይ በመውጣት ራሱን ወደታች ሁል ጊዜ ይወረውር ነበር።

በአንዲትም ቀን ከዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን ሊገድለው ስለ በረታበት ሞተ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና #መድኃኒታችን ከሞት አነሣውና እንዲህ አለው ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ይባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህና።

እርሱም የ #ክርስቶስን ፍቅር እጅግ ጨመረ ፊቱንም እየጸፋ ሥጋውን በየጥቂቱ እየቆረጠ ጀርባውንም ሰባት መቶ ጊዜ እየገረፈ ኖረ #ጌታችንም ይፈውሰው ነበር በየእሑድም ቀን ከቅድስት ድንግል እመቤታችን #ማርያም እንደተወለደ በሌሎች ቀኖችም እንደተያዘና ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበለ ሁኖ ይገለጽለት ነበር።

ስለዚህም ሳይበላ ሳይጠጣ አርባ ሁለት ዓመት ኖረ ዳግመኛም ናላው ፈስሶ እስቲአልቅ ዐሥራ ሁለት ወር በራሱ ተተክሎ ኖረ። በአንዲትም ቀን የ #ጌታችንን መከራ በአሰበ ጊዜ ሰይፉን በአንጻሩ ተከለ ከዕንጨት ላይም ወጥቶ በላዩ ወድቆ ሞተ ቅድስት ድንግል እመቤታችን #ማርያምም ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥታ የእኔና የልጄ ወዳጅ ሰላምታ ይድረስህ አለችው ። ከበድኑም ቃል ወጥቶ የሰማይና የምድር ንግሥት #እመቤቴ ሰላምታ ይገባሻል አላት እርሷም በከበሩ እጆቿ ዳሥሣ ከሞት አስነሣቸው።

ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለት ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔ ና ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንደ በራሴ ማልኩልህ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ ይህንም ብሎ አፉን ሳመው በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አቡነ አቢብ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_እብሎይ

ዳግመኛም በዚህችም ቀን ደግሞ አክሚም ከሚባል አገር የመላእክት አምሳል የሆነ አባ እብሎይ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አሞኒ የእናቱ ስም ሙስያ ነው ሁለቱም በ #እግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሆኑ በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ድኆችንና መጻተኞችን የሚወዱ የሚረዱ ናቸው።

ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም ሙስያም ዕንጨት የያዘ ብርሃናዊ ሰው በቤቷ ውስጥ ሲተክለውና ወዲያውኑ ለምልሞ አብቦ ሲያፈራ ያ ብርሃናዊው ሰውም ከዚህ ፍሬ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል ሲላት እርሷም ከፍሬው ወስዳ ስትበላና በአፏ ውስጥ ጣፋጭ ሲሆንላት በልቧም ፍሬ ይሆንልኝ ይሆን ስትል ራእይን አየች።

ከእንቅልፏም በነቃች ጊዜ ራእይን እንዳየች ለባሏ ነገረችው እርሱም እርሷ እንዳየችው ያለ ማየቱን ነገራት #እግዚአብሔርንም አብዝተው አመሰገኑት ትሩፋትንና ተጋድሎን በመጨመር በየሁለት ቀን የሚጾሙ ሆኑ ምግባቸውም እንጀራና ጨው ነው።

ይህን ቅዱስ እብሎይን በፀነሰችው ጊዜ እናቱ በገድል ወንዶችን እስከምታሸንፍ ድረስ በየሌሊቱ ሁሉ አንድ ሽህ ስግደትን ትሰግዳለች ሕፃኑን እስከ ወለደችው ድረስ ዘጠኝ ወር ያህል እንዲህ ስትጋደል ኖረች።

በወለዱትም ጊዜ እብሎይ ብለው ሰየሙት በጐለመሰም ጊዜ የምንኩስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ምክንያትም እስቲያገኝ እንዲህ ኖረ አቢብ የሚባል ወዳጅ ነበረውና እርሱ በሌሊት ወሰደው ከላዕላይ ግብጽ በሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ መነኰሰ በገድልም በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ።
ከጥቂት ወራትም በኋላ በጥቅምት ወር ሃያ አምስት ቀን አባ አቢብ አረፈ ያን ጊዜ አባ እብሎይ አብሎግ ወደሚባል ገዳም ሔደ ወደርሱም ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እርሱም በበጎ አምልኮ #እግዚአብሔርን መፍራትን የሚያስተምራቸው ሆነ።

ቅዱስ አቢብም በአረፈበት ቀን መታሰቢያውን ሲያደርጉ ይህ ቅዱስ አባ አብሎይ ወንድሞች ሆይ በአባ አቢብ ስም ዛሬ ጸሎትን የሚጸልየውን ኃጢአቱን #እግዚአብሔር ያስተሰርይለታል በዕረፍትህ መታሰቢያ ቀን የአባ አቢብ ፈጣሪ ሆይ ኃጢአቴን ሁሉ ተውልኝ ብሎ አንዲት ጸሎትን የሚጸልየውን ሁሉ እኔ ኃጢአቱን እተውለታለሁ ሲል ቃል ኪዳን ሰጥቶታልና አላቸው።

በዚያችም ሰዓት ከመነኰሳት አንዱ አረፈ እነርሱም ሊገንዙት በዚያ ቁመው ሳሉ አባ እብሎይ ስለ ተናገረው ቃል ከመነኰሳት አንዱ ተጠራጠረ በዚያንም ጊዜ ያ የሞተው ተነሥቶ ይናገር ዘንድ ጀመረ አባ እብሎይ ስለተናገረው ቃል ለምን ትጠራጠራላችሁ ለአባታችን አቢብ በመታሰቢያው ቀን በዚህ ቃል ኪዳን #እግዚአብሔር ሰጥቶናልና አላቸው ። ይህንንም ብሎ ተመልሶ አረፈ መነኰሳቱም አደነቁ ምስጉን #እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ይህ አባ እብሎይም ብዙ ዘመናት ኖረ ልጆቹ መነኰሳትም በዙ ብዙ ገዳማትም ተሠሩለት። የኖረበትም ዘመኑ በታላቁ አባ መቃርስ ዘመን ነው የአባ እብሎይንም የትሩፋቱን ዜና አባ መቃርስ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኘበት እርሱን እያጽናና እያረጋጋ መነኰሳት ልጆቹንም #እግዚአብሔር የሚወደውን በመሥራት ያጸናቸው ዘንድ መልእክትን ጻፈለት።

ይህንንም በአስቄጥስ ገዳም ሁኖ አባ መቃርስ ሲጽፍ አባ እብሎይ በላዕላይ ግብጽ ሳለ በ #መንፈስ_ቅዱስ አውቆ በዙሪያው ያሉትን መነኰሳት እንዲህ አላቸው። እነሆ ማጽናናትን የተመላች መልእክትን አባ መቃርስ ጻፈልን። ከዚህም በኋላ ከአባ መቃርስ ዘንድ የተላኩትን መነኰሳት ሁሉ ወጥተው በደስታ ተቀብለው አስገቧቸው መልእክቱንም በመነኮሳቱ ሁሉ ፊት አነበቡ በታላቅ ደስታም ደስ አላቸው።

ይህም አባ እብሎይ ወደ አባ አሞንዮስ የሔደ ከእርሱ ዘንድም የምትኖረውን ስሟ የዋሂት የተባለችውን የተቀደሰች ሴት ያየ ነው። ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው ወዶ በየካቲት ወር በአምስተኛው ቀን አረፈ እኛ ግን የአባ እብሎይን ዜና ከወዳጁ ከአባ አቢብ ጋር ጻፍን።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ እብሎይ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን ዳግመኛ አቅፋሐስ ከሚባል አገር ሰማዕት ለሆነ ለቅዱስ ዮልዮስ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው።

ይህም ቅዱስ ዮልዮስ በሀገረ ጥዋ በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ በገድሉ እንደተጻፈ ዲዮቅልጥያኖስ ከጠፋ በኋላ ጻድቅ ሰው ቈስጠንጢኖስ ሳይጠመቅ ነገሠላቸው በጥቂት ወራትም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ የቤተ ክርስቲያንም ሥልጣን ከፍ ከፍ አለ ከሀድያን ነገሥታት ለገደሏቸው ንጹሐን ሰማዕታት በስማቸው አብያተ ክርስቲያናት ታነፁ።

ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትም ስለ ሥጋቸው እንዲአስብ ገንዞ በመሸከም ወደ አገራቸው እንዲአደርሳቸው ከአገልጋዮቹም ጋር ገድላቸውን እንዲጽፍ #እግዚአብሔር እንደአቆመውና እንደጠበቀው ከዚህም እርሱ ራሱ በሰማዕትነት እንዴት እንደ ሞተ የቅዱስ ዮልዮስን ዜና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በሰማ ጊዜ ስለበጎ ተጋድሎው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቅዱስ ዮልዮስን አመሰገነው ።

ስለዚህም ለቅዱስ ዮልዮስ ያማረች ቤተ ክርስቲያን በግብጽ አገር ሠርተው ሥጋውን በውስጧ ያኖሩ ዘንድ ንጉሡ ወደ ግብጽ አገር ብዙ ገንዘብ ላከ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ እንዳዘዘ አነፁለት ። የቅዱስ ዮልዮስንም ሥጋ አፍልሰው በውስጧ አኖሩት ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር አከበራት እንደዛሬዪቱም ቀን በዓል አከበረባት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮልዮስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሕጻን_ሞዐ_ዘደብረ_ሊባኖስ

በዚህችም ቀን የደብረ ሊባኖሱ አባ ሕፃን ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው። በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡

እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡

ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወሰ ነው፡፡

ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_25 እና #ከገደላት_አንደበት)
#ጥቅምት_26

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ #ሐዋርያ_ቅዱስ_ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ፣ የጌታ ወንድም የተባለው #ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ መታሰቢያው ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሐዋርያ_ጢሞና

ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ቀን #ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ ጢሞና ሰማያዊ ሀብትን መለኮታዊ ኃይልን ገንዘብ አድርጎ በሽተኞችን ፈወሳቸው አጋንንትም ተገዙለት ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ _ክርስቶስ በሥጋ በምድር ሳለ አገለገለው። ወደ ሰማይም ከዐረገ በኋላ ሐዋርያትን አገለገላቸው በሃምሳኛው ቀንም ጰራቅሊጦስ በወረደ ጊዜ የአጽናኝ #መንፈስ_ቅዱስን ጸጋ ከእርሳቸው ጋር ተቀበለ።

ከዚህም በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ሐዋርያት ሾሙት እነርሱ #መንፈስ_ቅዱስን ዕውቀትንም የተመሉ እንደሆኑ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምስክር ሁኖአል።

በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ሃይማኖት አስተማረ ከዮናናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።

የዚያች አገር ገዥም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ

ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ መታሰቢያ ነው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ የ #ጌታችን ወንድም የተባለውና የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የነበረው ነው፡፡

እርሱም የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ሲሆን ከልጆቹ ሁሉ ትንሹ ነው፡፡ ድንግልና ንጹሕ ሆኖ ከ #ጌታችን ጋር እየተጫወተ አብሮ አድጓል፡፡ የያዕቆብ ወላጅ እናቱ በልጅነቱ ስለሞተችበትና የብርሃን እናቱ የሆነች ወላዲተ አምላክ #ድንግል_ማርያምን ዮሴፍ አረጋዊ በ83 ዓመቱ ጠባቂ ይሆናት ዘንድ ወደቤቱ ሲወስዳት #ድንግል_ማርያም ያዕቆብን የሙት ልጅ ሆኖ አግኝታው ከወለደችው ከ #መድኃኔዓለም_ክርስቶስ ጋር አብራ ተንከባክባ አሳድጋዋለች፡፡

ቅዱስ ያዕቆብ ከ #ጌታችን ጋር አብሮ እየተጫወተ እያለ አንድ ቀን ትግል ይገጥማሉ፡፡ ያዕቆብም #ጌታችንን አንስቶ ጣለው፡፡ ድጋሚ ተያያዙና አሁንም ያዕቆብ #ጌታችንን ጣለው፡፡ ሦስተኛ ጊዜም እንዲሁ ሆነና ያዕቆብ የልብ ልብ ተሰማው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ድጋሚ ትግል ሲያያዙ ግን #ጌታችን ያዕቆብን ወደ ሰማይ ወርውሮ መሬት ላይ በኃይል ጣለው፡፡ ያዕቆብም እጅግ ደንግጦ "ኃይልህን ደብቀህ ቆይተህ አሁን ምነው እንዲህ ታደርገኛለህ?" ሲለው #ጌታችንም "እኔኮ ካልጣሉኝ አልጥልም" አለው፡፡

#ጌታችን ዕርገት በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አድርገው ሾመውታል፡፡ ብዙዎችንም አስተምሮ ወደ ቀናች ሃይማኖት መልሷቸዋል፡፡ ሕዝቡም የታመሙትን ድውያንን ሁሉ እያመጡለት ይፈውሳቸው ነበር፡፡ ከኢየሩሳሌምም ውጭ እየሄደ ያላመኑትንም አስተምሮ እያጠመቀ ቤተ ክርስቲያን ይሠራላቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በጾም በጸሎት ሆኖ በመቆም ብዛት እግሮቹ አብጠው ነበር፡፡

አንድ ቀን አይሁድ ተሰብስበው መጥተው #ጌታችን የማን ልጅ እንደሆነ ይነግራቸው ዘንድ ወደ ያዕቆብ መጡ፡፡ እነርሱም ወደ ያዕቆብ የመጡት #ጌታችን የዮሴፍ ልጅ እንደሆነና የእርሱም የሥጋ ወንድም እንደሆነ እንደሚነግራቸው አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ያዕቆብ ከፍ ካለው ከሦስተኛው መደብ ላይ ወጥቶ #ጌታችን የራሱ የያዕቆብና የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን መሰከረባቸው፡፡ ዳግመኛም #ጌታችን ፍጹም አምላክ መሆኑን፣ የ #እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ከ #አብም ጋር ትክክል እንደሆነ መሰከረባቸው፡፡ ይህንንም በሰሙ ጊዜ አይሁድ እጅግ ተናደው በጽኑ ግርፋት ካሠቃዩት በኋላ ራሱን ቀጥቅጠው ገደሉት ሰማዕትነቱን ሐምሌ 18 ቀን በድል ፈጽሟል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_26)
#ጥቅምት_28

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ስምንት በዚህች ቀን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት #ጻድቁ_አቡነ_ይምዓታ አረፉ፣ዳግመኛም በዚህች ቀን #ቅዱስ_መርትያኖስና_ቅዱስ_መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ይምዓታ_ጻድቅ

ጥቅምት ሃያ ስምንት በዚህች ቀን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አቡነ ይምዓታ አረፉ።

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት። አባ ይምዓታ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው። ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው።

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው #መንፈስ_ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው። በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር፦
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
2.ዓላማ (የ #እግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው።

አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው። እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል። አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል።

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ። ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ።

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም። ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ።

ንጉሡም ሲጀመር የ #እግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው። ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው። ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች።

አባ ይምዓታና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር። ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ። በወቅቱ በአቡነ ሰላማ፣ በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት።

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት። የካደውን እየመለሱ የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ። ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ።

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው። በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር። በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር። ጸጋ #እግዚአብሔር አልተለያቸውም።

የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ። ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው። እያንዳንዱም #መንፈስ_ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ:: ዸንጠሌዎን በጾማዕት፣ ገሪማ በመደራ፣ ሊቃኖስ በቆናጽል፣ አረጋዊ በዳሞ፣ ጽሕማ በጸድያ፣ ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ።

አባ ይምዓታ ደግሞ በ #መንፈስ_ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ (እዛው ትግራይ) ሆነ። ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ (ባሕር) ተከፍሎላቸዋል። ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል። በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ለዘመናት ተጋድለው በገርዓልታ በዚህች ቀን አርፈዋል።

የአቡነ ይምዓታ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ትግራይ ገርዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ እርሱም ቢሆን በገዳሙ አባቶች እገዛና ድጋፍ ካልሆነ መውጣት የማይቻል ነው፡፡

ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡ ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ "በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል በማለት ይገልጻል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ይምዓታ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መርትያኖስና_ቅዱስ_መርቆሬዎስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ መርትያኖስና መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፉ። እሊህም ለቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱ ናቸው።

ይህም እንዲህ ነው አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በተጣላው ጊዜ ወደ አርማንያ አጋዘውና በዚያም በሥውር በእሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት አደረገ እሊህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ ግን የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ አርዮሳዊውንም ንጉሥ ረገሙት።

አንድ ክፉ ሰውም ወደ ንጉሡ ሒዶ እነርሱ እንደረገሙት ወነጀላቸው። ንጉሡም ያን ጊዜ ከአታክልት ቦታዎች በአንዲቱ ቦታ ተቀምጦ ሳለ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም እንዲገድሏቸው አዝዞ ገደሏቸው። በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቊስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያመረች ቤተ ክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን በዓልን አደረገላቸው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ጥቅምት_28 እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
#ጥቅምት_29

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ አረፉ፣ በከሀዲው ንጉሥ በመክስምያኖስ ዘመን #ቅዱስ_ድሜጥሮስ ዘተሰሎንቄ በሰማዕትነት አረፈ፣ የደብረ ዘኸኝ #መምህር_ጸቃውዐ_ድንግል አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ሳሙኤል_ጻድቅ (ዘደብረ ወገግ)

ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ አረፉ፡፡

ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡ የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ #እግዚአብሔር ተገልጾላቸው " #እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡

አቡነ ተክለሃይማኖትም በአባቱ እንድሪያስ በኩል የሥጋ ዘመዱ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናውን "ሳሙኤል" አሉት፡፡ ትርጓሜውም " #እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ" ማለት ነው፡፡ ከሕፃንነትም ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኩሰውታል፡፡ "ደብረ ወገግ" የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል የ #ጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ አስቦ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ አስቦን የብርሃን ውጋጋን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም "ቦታውን ደብረ ወገግ" (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም "ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት" ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት እንዳረገ ድርሳነ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡

በቦታው ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡

ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን ሚስት እንጀራ እናቱን በማግባቱ ምክንያት አቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው ያወገዙትን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ወገኖች በየአውራጃው በተናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስንም ደሙ በምድር ላይ እስከሚንጣለል ድረስ ገርፈው ወደነበረበት ቤቱ ወሰዱት፤ ፊሊጶስም በሚሄድበት ቦታ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ሞተ፡፡ እንድርያስ፣ አኖሬዎስና ተክለ ጽዮን ሁላቸው ከተከታዮቻቸው ጋር በሰማዕትነት አርፈው እነስድስተይ በምትባል ምድር ተቀበሩ፡፡ ጳጳሱን አቡነ ያዕቆብንም ደሙ በምድር ላይ እንደውኃ እስኪወርድ ድረስ ገርፈው ወደ ሀገሩ እንዲሰደደ አደረጉት፡፡ ከዚያም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የ ቅዱስ ሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ በእነስድስታይ አገር ላሉ ሰዎችም ሁሉ አባት ሆናቸውና የ #መንፈስ_ቅዱስ ልጁንም ታዲዮስን መምህርና አባት አድርጎ ሾመላቸውና ጽላልሽ ሄዶ እናቱን ይዞ ጽጋጋ ምድረ ወገግ ወስዶ አመነኮሳት፡፡

አቡነ ሳሙኤል ወደ ምድረ ርስቱ ደብረ ወገግ እየሄደ በዚያ ያሉ ልጆቹን እያጽናና ወደ እንደግብጦን አውራጃም እየተመለሰ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስትና እየቀየረ፣ አጋንንትንና መመለኪያ ቦታዎቻቸውን እያጠፋ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ በቅዱስ ገድሉ ውስጥ በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ እጅግ ብዙ ታሪኮች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮች ውስጥ አቡነ ሳሙኤል በሀገራችን በጣም ብዙ ጣዖታትንና መመለኪያ ቤቶቻቸውን እያጠፉ፣ በሰዎች (በጠንቋዮች) ላይ፣ በዛፍና በባሕር ውስጥ አድሮ ይመለኩ የነበሩ ሰይጣናት አጋንንትን በሚያመልኳቸው ሰዎች ፊት እያጋለጡና እያዋረዱ ሰዎቹን አስተምረው አጥምቀው ወደ አምልኮተ #እግዚአብሔር እየመለሷቸው ቤተክርስቲያንም በመሥራት ሐዋርያትን መሰሉ፡፡

ሰይጣን አድሮባቸው የነበሩ ጠንቋዮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዕቃዎችን ጻድቁ እየባረኩና እየቀደሱ ለቤተክርስቲያን መሥሪያና መጠቀሚያነት ያውሉት ነበር፡፡ ይህም ገና ሳይወለዱ በአቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ይሆናል›› ብሎው ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የ #እግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡

ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፣ ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፣ በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፣ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፣ በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፣ በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ እንደዚሁም ሌሎች ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በትእምርተ #መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከ #ጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ድሜጥሮስ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን በከሀዲው ንጉሥ በመክስምያኖስ ዘመን ቅዱስ ድሜጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ከተሰሎንቄ ሀገር ነው የከበረች የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ በቀናች ሃይማኖት ጸና ሕዝቡንም የሚያስተምር ሆነ ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ ሃይማኖት በመስበክ ብዙዎችን ከስሕተት መለሳቸው።

ስለዚህም በከሀዲው ንጉሥ ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደርሱ እንዲአመጡት አዘዘ በንጉሡም ዘንድ አንድ ሥጋው የደነደነ የጸና ዐጥንቱ የሰፋ ሰው ነበረ ለሰዎችም ሁሉ እሱ ሁሉን የሚያሸንፍ እሱን የሚያሸንፈው የሌለ ይመስላቸው ነበር ንጉሡም ይወደዋል ይመካበታል እንዲህም ይል ነበር ይህን አካሉ ግዙፍ የሆነ ሰው ለሚያሸንፍ እኔ ብዙ ገንዘብ እሰጠዋለሁ።
በዚያንም ጊዜ ስሙ በስጥዮስ የሚባል አንድ ክርስቲያናዊ ሰው ተነሥቶ ወደ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሔደ እንዲጸልይለትና በሥጋውም ሁሉ አሸናፊ በሆነ በ #መስቀል ምልክት እንዲአማትብበት ለመነው። እርሱም በላዩ ጸለየለት በሥጋውም ሁሉ ላይ በ #መስቀል አማተበበት ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ገብቶ ከዚያ ሥጋው ግዙፍ ከሆነው ጋር ያታግለው ዘንድ ለመነው ንጉሡም ፈቀደለት በታገሉም ጊዜ ሥጋው የደነደነውን ያ ክርስቲያናዊ ሰው አሸንፎ ጣለው ንጉሡም አዘነ አደነቀም ሥጋው የደነደነውም በመሸነፉ አፈረ ተመክቶበት ነበርና።

ንጉሡም ስለዚህ ነገር ወታደሮቹን ጠየቀ እነርሱም ቅዱስ ድሜጥሮስ በላዩ እንደጸለየለትና በሥጋውም ላይ በ #መስቀል ምልክት እንዳማተበበት ነገሩት።

ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ በቅዱስ ድሜጥሮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ለአማልክትም ዕጣን እስከሚአሳርግ ድረስ እንዲገርፉት አዘዘ ንጉሡም እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉበት የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰማ ጊዜ እስከሚሞት በጦሮች እንዲወጉት ሁለተኛ አዘዘ።

ለቅዱስ ድሜጥሮስም ይህን ፍርድ ነገሩት ሃይማኖቱን ትቶ ለአማልክት የሚሰግድ መስሏቸው ነበርና ቅዱስ ድሜጥሮስም እኔ ከዕውነተኛ አምላክ ከሕያው #እግዚአብሔር ልጅ ከ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ለረከሱ አማልክት እሰግድ ዘንድ ዕጣን ማሳረግም አልፈቅድም የወደዳችሁትን አድርጉ አላቸው።

በዚያንም ጊዜ ንጽሕት ነፍሱን በ #እግዚአብሔር እጅ እስከ ሚሰጥ በጦር ወጉት ሥጋውንም በጣሉት ጊዜ ምእመናን ወደ ርሳቸው ወሰዱት የስደቱም ወራት እስከሚያልፍ በሣጥን አድርገው በቤታቸው ውስጥ ሠውረው አኖሩት።

የስደቱም ወራት ከአለፈ በኋላ #እግዚአብሔር ገለጠውና ከዚያ አወጡት ያማረች ቤተ ክርስቲያንንም በተሰሎንቄ አገር ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ድንቅ የሆነ ታላቅ ተአምርን እያደረገ እስከ ዛሬ አለ።

ሽታውም እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከእርሱ ይፈሳልና በእምነት የሚቀቡትን በሽተኞች ሁሉንም ያድናቸዋል። ይልቁንም በዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን ከሌሎቹ ዕለታት ተለይቶ በብዛት ይፈሳል ከአውራጃው ሁሉ ብዙዎች ሰዎችም ይመጣሉ ከዚህም ቅባት ወስደው በማሰሮቻቸው ያደርጋሉ ይቺ ምልክትም እስከ ዓለም ፍጻሜ በመኖር እንደምትገኝ ደጋጎች ካህናት ምስክሮች ሆኑ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ኮእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ጸቃውዐ_ድንግል (ዘደብረ ዘኸኝ)

በዚህችም ቀን የተመሰገነና የከበረ የደብረ ዘኸኝ መምህር ጸቃውዐ ድንግል አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ ካህን ነው በጥበብና በበጎ ተግሣጽም አሳደገው መለኮታዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማረው አድጎ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ከአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ለመምህርነትም ተመርጦ በአባ ገብረ ማርያም ወንበር ላይ ተሾመ።

በዚያንም ጊዜ አባቱ ለልጁ የምንኵስና ልብስ አለበሰው ስሙንም ጸቃውዐ ድንግል ብሎ ሰየመው ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ ያለ ማቋረጥ በጾም በጸሎት ብዙ በመስገድም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ። ከዚህም በኋላ አባቱ በአረፈ ጊዜ በአባቱ ፈንታ ተሾመ መንጋዎቹንም እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው።

በሌሊቱም ሁሉ ከባሕር ውስጥ ቁሞ ያድራል ከባሕሩም ሲወጣ ወዙ በምድር ላይ እስከሚንጠፈጠፍ ስግደትን ያዘወትራል ምግቡም ደረቅ እንጀራ ነው ጠጅ ወይም ጠላ አይጠጣም #እግዚአብሔርም በእጆቹ ላይ ተአምራትን አደረገ በጐዳናም ሲጓዝ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሒዶ የማያውቅ መፃጉዕን አገኘ በስመ #አብ #ወወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ብሎ የተጸለየበትን ውኃ በላዩ ረጨ በ #መስቀልም ምልክት አማተበው በዚያንም ጊዜ ዳነ ። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ጥቂት ታሞ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_29 እና #ከገድላት_አንደበት)
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

         ጥቅምት ፳፱ (29) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽ_ግመልን_በመርፌ_ቀዳዳ አሳልፈው ሙት አስነስተው ብዙ ሕዝብ ላሳመኑበት ለተአምራት በዓላቸው፣  እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።

                          
#አቡነ_ታዴዎስ_ያደረጉት_ተአምር_ይህ_ነው፦ በአቡነ ታዴዎስ አላምንም የሚል ኢሳ የሚባል አንድ የእስላም ንጉሥ ተነሳ እና እንዲህ አላቸው "ስም ታዴዎስ ነው ሐዋርያው ታዴዎስ ግመል በመርፌ ቀዳዳ አስወጥቷል ይባላል አስወጣና ልመንብህ" አላቸው። ይህን ቃል ሲናገራቸው አቡነ ታዴዎስ ሳቁበት "በል ግመልና መርፌ አምጣ እኔ አሳይሃለው" ሲሉት ሠላሳ ግመል አመጣ አቡነ ታዴዎስም "በል መርፌውን በእጅህ ያዘው ቀዳዳውን ወደ ግመሊቱ አዙረህ" አሉት ወደ ግመሊቱ ቀርበው "በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም አዝዝሻለሁ" ሲሏት አንገቷን በመርፌው አስገብታ ከልጇ ጋር ወጣችና ሃያ ስምንቱን መጀመሪያ የወጣችቱ ግመል እንደ ሰው እየጠራቻቸው ወጡ ይህንን ድንቅ ስራ ያየ መርዩጥም ሆነ ሰራዊቱ የደብረ ማርያም ህዝብ ሲያደንቁ።

በዚያን ጊዜ የኢሳ ልጅ ሙሳ ሳቀ "በምትሃት እንጂ በብቃት አላወጣም" ብሎ ሲጠራጠር አንዲቱ ግመል ሆዱን በእርግጫ ስትመታው ሞተ አንጀቱ ተጎለጎለ በዚያን ጊዜ ሰው ሁሉ ደነገጠ ንጉሡም ደነገጠ ወዲያ ወዲህ እየሮጠ "አባቴ ሆይ እማፀንሃለው ማረኝ እንደ ሙሳ አልሳቅሁም" አቡነ ታዴዎስም "መዩጥ ሆይ ከልብህ እመን ከዚህ በላይ ታያለህ ከ #እግዚአብሔር የሚሆንን ነገር ምንም የሚያገኝህ ነገር የለም አትፍራ ከልብህ ካመንክ የሞተው ይነሳል ስላንተ አምላኬ ያነሳዋል" በዚህ ጊዜ መዩጥ አቡነ ታዴዎስን "እንዴት ሆኖ የሞተ ሰው ይነሳል በል አንተ አስነሳው የደራ ህዝብ ያምን ዘንድ በአምላክህ" አቡነ ታዴዎስ መዩጥን "ይቅበሩት እዘዝ ነገ ያነሳዋል ከተቀበረ በኋላ ነገ ሁሉ ሰው ከዳር እስከ ዳር ወንድ ሴት ትልቅ ትንሽ ሳይባል ይሰብሰብ ይህ ሬሳ የተነሳ እንደሆነ በአምላኬ እንድታምኑ ካልተነሳ እኔን ግደለኝ ከዚህ በኋላ ቅበሩት በዚች ቀን ጠዋት ከደብረ ማርያም ያልተገኘ ክፉ ሞት ይሞታል" አለ በዚች ሌሊት አቡነ ታዴዎስ ከደብረ ማርያም ቤተ ክክርስቲያን ውስጥ ከቅድስት ሆነው በየሰዓቱ መቶ መቶ ስግደት እየሰገዱ "ከመቃብር አላዓዛርን እንዳስነሳህ ይህንንም ሙት አንሳው" መዩጥ እንዲምን ብሎ እየጸለዩ ሳሉ ከሌሊቱ 11ሰዓት ጥቅምት 29 ቀን መልአከ #እግዚአብሔር ወርዶ "የሞተው ይነሳል ስለ አንተ ጸሎት ብሎ ይችን ደብረ ማርያምን አሥራት አድርጌ ሰጥቸሃለሁ በእኔም ስም ስላገኘህ ችግር በጾም በጸሎት ሃይማኖትን በማስተማር ከአጋንንት ጋር በመጋደልህ ከክፉ ሰዎች ጋር በመጋደልህ ደብረ ማርያምን የልጆችህ ርስት አድርጌ ሰጥችሀለሁ እስከ መጨረሻው ድረስ" ብሎት መልአከ #እግዚአብሔር ወደ ሰማይ አረገ።

አቡነ ታዴዎስም እስከ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ሲጸልዩ አደሩ ህዝቡ ተሰብስበው ሳለ መዩጥ መጣና ከሰራዊቱ መካከል ተቀመጠ አቡነ ታዴዎስም ጠራቸው "አባቴ ሆይ ትናት እዳልከኝ አድርግ በህዝቤ መካከል የሰበሰብኋቸው ስላንተ ነውና" ሲላቸው "በል የሙቱን አባት አምጣው ወደ እኔ" ሲሉ አቀረቡላቸው አቡነ ታዴዎስም ለአባቱ #መስቀላቸውን ሰጡትና እንደ "አላዓዛር ተነስ በለው ይነሳልሃል" አሉትና የአቡነ ታዴዎስን #መስቀል ይዞ ተነሳ ሲለው ሙቱ ተነስቷል ከዚህም በኋላ የደራ ህዝብ በመላው አምኖ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም አጥምቀው ሃይማኖትን አስተምረው 12 ቤተ ክርስቲያን አሳነጹ።

ከአባታችን አቡነ ታዴዎስ #እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን።

ምንጭ፦ የጣና ሐይቅ ደብረ ማርያም ገዳም አጭር ታሪክ ከምትላው መጸሐፍ።
#ጥቅምት_30

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው #ቅዱስ_ማርቆስ የተወለደበት ነው፣ #የመጥምቁ_ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በግልጽ የታየችበት ነው፣ በገድል የተጸመደ #ቅዱስ_አባት_ባሕታዊ_አብርሃም ያረፈበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ

ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ነው።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው። በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ። እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው።

በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ #እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ። ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ።

ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ቅዱስ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና። በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን ወንጌልን ጻፈ በሮሜ አገርም አስተማረበት። ከዚያም በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ።

በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ። ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም አንድ #እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ።

#እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ #ክርስቶስ ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ።

ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በ #ጌታችንም አመነ። ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው። ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።

ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር። በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በ #መድኃኒታችን የትንሣኤ በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ። ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት። እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር ። በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ።

ሌሊትም በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው። እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው። እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው። በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ ። በክብር ባለቤት #ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቀ_መለኮት

ዳግመኛም በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡

ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሄሮድያዳ ልጅ ርጉም የሆነ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገና እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ እርሱም አስቀድሞ "የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?" እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ እርሱም ስለማሐላው የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ በመጀመሪያም የሄሮድስ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሲሄዱ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በ #መንፈስ_ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ የንጉሡም ጭፍሮች የመጥምቁን ራስ በወጪት አድርገው ለንጉሣቸው ሄሮድስ ሰጡት፡፡ ሄሮድስም ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ግን በወጪት ላይ ሆና ሕዝቦቹና የመንግሥቱ ታላላቅ ሰዎች እየሰሟት በየመኳንንቱ ፊት ንጉሥ ሄሮድስን "የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም" እያለች መጀመሪያ ትዘልፈው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ዘለፈችው፡፡ መዓዛዋም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ ዐይኖቹም እንደፀሐይ ያበሩ ነበር፡፡
የሄሮድያዳም ልጅ የመጥምቁን ራስ ወስዳ ለእናቷ ልትሰጣት ስትል ዐይኖቹ እንደፀሐይ ሲያበሩ ብታየው "ንጉሡን አትፈራውምን?" በማለት ተቆጣች፡፡ በመቀጠልም "እነዚህን ዐይኖቹን በወስፌ እያወጣሁ እጥላቸዋለሁ፣ ምላሱንም ደግመኛ እንዳይገሥጽ ቆርጨ እጥላቸዋለሁ" በማለት ፊቱን በጥፊ ለመምታት እጇን ስታነሣ ያንጊዜ የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ በረረች፡፡ በአየር ላይ ሳለችም ዳግመኛ "የተረገምሽ ሄሮድያዳ የባልሽን ወንድም ሄሮድስን ማግባት አይገባሽም፣ ቀድሞ የምዘልፍሽ አሁንም የምዘልፍሽ እኔ ነኝ" እያለች የዮሐንስ ራስ የቤቱን ጣሪያ ሰንጥቃ እንደንሥር በአየር በራ ሄደች፡፡

ከዚህም በኋላ ለጥፊ የዘረጋቻቸው የሄሮድያዳ እጆቿ ከትከሻዋ እየተቆረጡ መሬት ላይ ወደቁ፤ እውነቷንም መሬት አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ዘፋኟ ልጇም አብዳ የቤተ መንግሥቱን ዕቃ ሁሉ መሰባበር ጀመረች፡፡ የንጉሡ አንዱ ጭፍራም የሄሮድያዳን በእሳት እንደተለበለበ የግንድ እሳት የመሰለና የተቆረጠ እጇን አምጥቶ ለሄድሮስ ሰጠውና የሆነውን ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገሩ እውነት መሆኑን ሄዶ ባየ ጊዜ በሀፍረት እጅግ ተሸማቀቀ፡፡ ዘፍና በማስደሰት የዮሐንስን ራስ እንዲያስቆርጠው ያደረገችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅም አብዳ በቤተ መንግሥቱ ስትለፈልፍ አገኛት፡፡ ሄሮድስም መኳንንቶቹን "በቤተ መንግሥቴ የተደረገውን ይህን ነገር ለማንም አትንገሩ" ብሎ አማላቸው ነገር ግን ያበደችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅ ራሷ ሄዳ ሄሮድስን "የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት ፈጽሞ አይገባህም" እያለች በመኳንንቶቹ ፊት ገሠጸችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ቃል ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደና "ቀደሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ በኋላ ደግሞ ምሥጢር ታወጣ ንሣ በሰይፍ ቁረጣት" ብሎ አንገቷን በሰይፍ አስቆረጣት፡፡ ሥጋዋንም ዓሣ አንበሪ ተቀብሎ ዋጣት፡፡ ሄሮድም የወንደሙን ሚስት ሲያገባ አስቀድሞ አግብቷት የነበረችውን ሚስቱን በግፍ አባሯት ነበር፡፡ እርሷም ይህንን ሄሮድስ ያደረሰባትን ግፍ ለአባቷ አርጣ ብትነግረው አባቷ ብዙ ጦር ሰብስቦ መጥቶ ምድረ ገሊላን በኃይል አፈራረሳት፡፡ የበላዩ ንጉሥ ቄሳርም የገሊላን መፍረስና መውድም ሲሰማ ምክንያቱን ቢጠይቅ ሄሮደስ ባደረገው ግፍ ምክንያት መሆኑን ነገሩት፡፡ ቄሳርም ሄሮድስን ከሥልጣኑ ሽሮ አጋዘውና በወህኒ ጣለው፡፡ ሄሮድስም በወህኒ ቤት ሳለ አብዶ ራሱን ስቶ የገዛ አካሉን እየነጨ እየበላ ቷ ብሎ ፈንድቶ ተልቶ ሸቶ እጅግ ክፉ አሟሟት ሞተ።

ከዚህም በኋላ #ጌታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ መለስ ብሎ እንዲህ በማለት ሥልጣን ሰጣት፡- "እነሆ መንፈስሽን በራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ በሰማይም የምትበሪበት እንደ ንሥር ክንፍ ሰጥቼሻለሁና እንደንስር በሰማይ እየበረርሽ በዓለም ሁሉ እየዞርሽ የሄሮድስንና የሄሮድያዳን ኃጢአት ግለጭባቸው፤ እስከ 15 ዓመት ድረስ ገቢረ ተአምራት የምታደርጊበት ኃይሌን መንፈሴን በእራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ" አላት፡፡ ዳግመኛም #ጌታችን ዮሐንስን "እኔም ከ3 ዓመት በኋላ ለአዳም የሰጠሁትን ተስፋ ፈጽሜ በሞቴ ወደ ሲኦል ወርጄ ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ ማርኬ በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ተነሥቼ ወደ ባሕርይ ክብሬ ተመልሼ ወደ ሰማይ አርጌ ባባቴ ቀኝ በተቀመጥኩኝ ጊዜ ከ15 ዓመት በኋላ ርጉም ሄሮድስ ካስፈጃቸው ከትንንሾቹ ሕፃናት ጋራ ትሆን ዘንድ በአባቴ ፈቃድ እራስህን ተሸክመው ወደ አባትህ ወደ ዘካርያስ ያመጧት ዘንድ እኔ መላእክትን አዛቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ግን ነፍስህን በእኔ ቀኝ ባባትህ በዘካርያስ አጠገብ አኑሬያታለሁ መንፈስህንም እስከ 15 ዓመት በእራስህ ውስጥ እንድትኖር አዝዣታለሁ፣ ሥጋህም ከነቢዩ ከኤልሳዕ ጋር እንዲቀመጥ አድርጌያለሁ" አለው፡፡

ከዚህም በኋላ #ጌታችን እንዳዘዛት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ እንደንስር በአየር ላይ እየበረረች የምታስተምር ሆነች፡፡ በምሥራቅ በኩል ሄዳ በዐረብ አገር ውስጥ በሰማይ ላይ ስታስተምር በዚህች ዕለት ጥቅምት 30 ቀን በግልጽ ታየች፡፡ ነጋዴዎች ድምጹዋን ሰምተውና አይተዋት እጅግ ተደስተው ገንዘባቸው ሁሉ ጥለው የቅዱስ ዮሐንስን እራስ ለመያዝ ሰውነታቸውን ብዙ አደከሙ፡፡ ነገር ግን ለመያዝ አልተቻላቸውም፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰማይ "የምትያዝበት ጊዜ ስላልደረሰ ሰውነታችሁን አታድክሙ" የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣላቸው፡፡ መፈለጋቸውንም ተው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስም እራስ 15 ዓመት ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዐረብ ሀገር ዐረፈች፡፡ የታዘዙ ቅዱሳን መላእክትም መጥተው ከቅዱስ ዮሐንስ እራስ ከተባረኩ በኋላ በታላቅ ዝማሬ እያመሰገኑ የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ወስደው በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ቀበሯት፡፡ ቅድስትን ነፍሱንም እያመሰገኑ ወደ ሰማይ አሳረጓት፡፡ በዚያም በ #ሥሉስ_ቅዱስ ዙፋን ፊት ወድቃ ከሰገደች በኋላ አባቷ ዘካርያስንና እናቷ ኤልሳቤጥን እጅ ነሳቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በ3ኛው ሰማይ ውስጥ ተቀመጠች፡፡ #ጌታችን ሦስቱን ሰማየ ሰማያት ርስት ጉልት አድርጎ ሰጥቶታልና፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_ባሕታዊ_አብርሃም

በዚህች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር በገድል የተጸመደ ቅዱስ አባት ባሕታዊ አብርሃም አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ #እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያመልኩ ናቸው በዚህም ዓለም ገንዘብ እጅግ ባለጸጎች ነበሩ።

ይህም ቅዱስ በአደገ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ሊለብስ ሽቶ በላዕላይ ግብጽ ወደሚገኝ ወደ ሀገረ አክሚም በመርከብ ተጭኖ ሔደ ወደ አባ ጳኵሚስም ደረሰ እርሱም የምንኲስና ልብስን አለበሰው በገድልም በመጸመድ ሥጋውን አደከመ በአባ ጳኵሚስም ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ሃያ ሦስት ዓመት ያህል በማገልገል ኖረ።

ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንዲአሰናብተው አባ ጳኵሚስን ለመነው እርሱም ፈቀደለት ዓሣ የሚያሠግሩበትን መረብ የሚሠራ ሆነ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም አንድ ሰውን አመጣለት ያም ሰው መረቡን ሽጦ ምግቡን አተር ይገዛለታል የተረፈውንም ለድኆች ይሰጣል የምግቡም መጠን ሁልጊዜ ማታ ማታ አንዲት እፍኝ ከጨው ጋር በውኃ የራሰ አተር ነው።

እንዲህም እየተጋደለ በዚያች ዋሻ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ ልብሱም ከገዳም ሲወጣ የለበሰው ከዘመን ርዝመት የተነሣ አርጅቶ ተበጣጠሰ ሥጋውንም በጨርቅ የሚሸፍን ሆነ። በየሁለት ዓመትም ወደ መነኰሳቱ ገዳም በመውጣት ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር። በዚያችም ዋሻ መኖር በጀመረባት ዓመት ሰይጣናት ወደ ርሱ በመምጣት ምትሐት እየሠሩ ተፈታተኑት እርሱ ግን ውሻን እንደሚአበር ሰው አበረራቸው።

ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ያን ሕዝባዊ ሰው ልኮ የአባ ጳኵሚስን ረድእ አባ ቴዎድሮስን አስጠራው በመጣም ጊዜ ሰግዶ ሰላምታ ሰጠው እንዲጸልይለትና በጸሎቱም እንዲአስበው ለመነው። ከዚህም በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም በርከክ ብሎ ነፍሱን በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠ አባ ቴዎድሮስም ወደ መነኰሳቱ ላከ እነርሱም መጥተው ከሥጋው በረከትን ተቀበሉ ሥጋውንም ወሰደው ከቅዱሳን ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት።

#እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምትና_30_ሚያዝያ
#ከገድላት_አንደበት)
#ኅዳር_1
#አንድ_አምላክ_በሚሆን_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም የተባረከ የኅዳር ወር ቀኑ ዐሥር ሰዓት ሲሆን ከዚህም ይጎድላል
ኅዳር አንድ በዚችም ቀን የጻድቁ የኢትዮጵያ #ንጉሥ_ነአኵቶ_ለአብ መታሰቢያው፣ #ቅዱሳን_መክሲሞስ#ማንፍዮስ#ፊቅጦርና #ፊልጶስ በሰማዕትነት አረፉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ነአኩቶ_ለአብ_ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)

ኅዳር አንድ በዚችም ቀን የጻድቁ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነአኵቶ ለአብ መታሰቢያው።

ሃገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት። በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው።

ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል። ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው።

➛እርሱ ንጉሥ ነው። ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው።
➛ሁሉ በእጁ ነው። እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው።
➛እርሱ የጦር መሪ ነው። ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም።
➛እርሱን "ወደድንህ ሞትንልህ" የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት። ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት #ክርስቶስ ነበር።
➛የሃገር መሪ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው። ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም።

እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ "ጊዜ የለኝም" ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል፣ ያንጽ፣ በክህነቱ ያገለግል፣ ማዕጠንት ያጥን፣ ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር።

እኛ "ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል" ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ ...ጦር በፊት በኋላ በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውኃ በምድር ላይ ፈሷል። ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው።

#ለመሆኑ_ቅዱስ_ነአኩቶ_ለአብ_ማን_ነው?

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም ሁለተኛ ነው። እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናቸው። ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው።

እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር። ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች። ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው።

እዚያው ላይም "ነአኩቶ ለአብ" (#አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት። ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ።

የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ #ክርስቶስን ተማረ። በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና። ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው 30 ደረሰ።

በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ። ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት። ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ።

በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው። ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር ቅዳሴ ሲቀድስ በጾም ይውላል። ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል።

ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል። ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል። እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል። በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ፣ እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር። እርሱ #መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና።

ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር። በተለይ በ1211 አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት። እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት ይቀድስባትም ነበር።

ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ። እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት። በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች።

ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው። ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ30 ዓመቱ ነው። ለ40 ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ 70 ዓመት ሞላው። በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና #መድኃኒታችን_ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ። ሰላምታንም ሰጠው።

"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ40 ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም። ክፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና። የሚያከብርህን አከብረዋለሁ። ደጅህን የሳመውን፣ ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን፣ መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው።

ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው። እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጠበል ይንጠበጠባል። ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን። ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና።

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል። የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር 1 ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ3 ነው ይላሉ። በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_መክሲሞስ#ማንፍዮስ#ፊቅጦር እና #ፊልጶስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ከአፍራቅያ የሆኑ ቅዱሳን መክሲሞስ፣ ማንፍዮስ፣ ፊቅጦርና፣ ፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን በሰማዕትነት አረፉ።

በዚህም ከሀዲ ንጉሥ ዘመን ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው የነቁ ከእርሱ በሸሹ ጊዜ ነው። እሊህም ቅዱሳን መስተጋድላን ክብር ይግባውና #ክርስቶስን ክዶ ክርስቲያኖችን ሲአሠቃይ በአዩት ጊዜ ሃይማኖታቸውን ግልጥ ያደርጉ ዘንድ በአንድ ምክር ተስማምተው በአንድነት ተሰብስበው ወደ ከሀዲው ንጉሥ ቀረቡ እኛ በ #እግዚአብሔር ልጅ በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በግልጥ የምናምን ክርስቲያኖች ነን ለእርሱም እንሰግዳለን እናመልከዋለንም ብለው ጮኹ።

ይህ ከሀዲ ዳኬዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገርፉአቸው አዘዘ አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም ታላቅ ግርፋትን ገረፏቸው በእሳት በአጋሉትም ከብረት በተሠሩ በትሮች ደበደቧቸው።
#ኅዳር_2

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሁለት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_ጴጥሮስ_ሣልሳዊ አረፈ፣ ስልሳ ሦስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ሱንትዩ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ጴጥሮስ_ሣልሳዊ

ኅዳር ሁለት በዚህች ቀን ከአባ ጢሞቴዎስ በኋላ የተሾመ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ጴጥሮስ ሣልሳዊ አረፈ።

እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ #እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈለት እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን።

ዳግመኛም በዚች መልእክት ውስጥ እንዲህ ብሎ ገለጠ የተዋሕዶ ጥቅም እንዳይሻር ከተዋሕዶ በኋላ የአካላዊ ቃልን መለኮቱን ከትስብእቱ ሊለዩት አይገባም።

ይህ አባ ጴጥሮስም እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት።

ከዚህም በኋላ ሌላ መልእክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳት መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ።

ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀድያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሹመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት።

ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሱንትዩ

በዚህችም ቀን ዳግመኛ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሱንትዩ አረፈ።

ይህም አባት መንጋዎቹን እያስተማረ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ አምስት ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ኅዳር_2)
ዕድሙያቸውም 180 ዓመት ነው፡፡

ዐፄ ፋሲል ጻድቁ የተከሏቸውን የጥድ ዛፎች በሙሉ ተቆርጠው የአክሱም ቤ/ክ እንዲሠራበት አዋጅ አወጁና መልእክተኞች መጥተው ዛፎቹን ሲቆርጡ መነኮሳቱ ግን ‹‹ጻድቁ አባታችን የተከሏቸው የጥድ ዛፎች መቆረጥ የለባቸውም›› ብለው ቢከራከሩም ሰሚ አላገኙም፡፡ መነኮሳቱም ወደ #እግዚአብሔር ቢያመለክቱ ጩኸታቸው ተሰምቶላቸው ወዲያው እየተቆረጡ ያሉት የጥድ ዛፎች በሙሉ በተአምራት ወደ ወይራ ዛፍነት ተለወጡ፡፡ የወይራ ዛፎቹም ለዐፀድ እንጂ ለሕንፃ የማይመቹ ጎባጣ ሆኑ፡፡ የዚህም ምልክቱ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ግንዱ ጥድ ዛፉ ግን ወይራ የሆነ ትልቅ ዛፍ ‹‹ወይራ ዘገብረ ተአምር›› በሚባል ቦታ አሁንም ድረስ ቆሞ ይታያል፡፡

ጻድቁ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ በ1312 ዓ.ም የመሠረቱት ገዳማቸው ደብረ በንኮል ከአክሱም በእግር ሦስት ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ይኸውም በንግሥተ ሳባ ቤተ መንግሥት አድርጎ የቀዳማዊ ሚኒሊክን መቃነ መቃብር አልፎ በመሄድ ነው፡፡ ወይም በመኪና ለመጓዝ አክሱም ጉበዱራን አቋርጦ ውቅሮ ማራይ ከተማን አልፎ በስተ ሰሜን አቅጣጫ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በስተ ምዕራብ የአቡነ አላኒቆስ ዘማይበራዝዮን ገዳም፣ በስተ ምሥራቅ የአቡነ ሰላማን ገዳም እየተለመከቱ እንደተጓዙ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነውን ደብረ በንኮልን ያገኙታል፡፡ ኅዳር 20 ጻድቁ ስለሚነግሱ ገዳሙም ለአክሱም ቅርብ ስለሆነ ይህ ለአክሱም ጽዮን ተጓዦች ተጨማሪ ትልቅ በረከት ነው፡፡

ደብረ በንኮል ማለት ‹‹ሙራደ ቃል›› ማለት ነው፡፡ ትርጉሙም የምሥጢር መውረጃ ማለት ነው፡፡ በቦታው ላይ ሱባኤ ለያዘ ሰው እንደ ቅዱስ ያሬድና እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምሥጢር እንደሚገለጥለት የሚጠቁም ነው፡፡ በ14ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩት ደጋግ መነኮሳት ሕይወታቸውን በሙሉ በምንኩስና፣ በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ሲፈልጉ ከደብረ ዳሞ፣ ከሐይቅ እስጢፋኖስ፣ ከደብረ ሊባኖስና ከሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች እየተነሡ ወደ ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነበር የሚሄዱት፡፡

የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ቃልኪዳን፡- ጻድቁ ባርከው ያፈለቁት ጸበላቸው ላበደ ሰው መድኃኒት ነው፡፡ ከመቃብራቸው ላይ የሚነሣውን አፈር ጻድቁ ባርከው ባፈለቁት ጸበላቸው ታሽቶ በእጃቸው #መስቀል ተባርኮና ታሽቶ የሚዘጋቸውን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን እምነታቸውን በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው ንብረቱን ሌባ ቀማኛ ዘራፊ አይሰርቀውም፤ የመኪና አደጋ አይደርስበትም፤ ጥይት አይመታውም፡፡ ‹‹በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው›› መባሉን ልብ ይሏል፡፡ ይኸውም ለጻድቁ የተሰጣቸው ታላቅ ቃልኪዳን ነው፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የጻድቁ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ በረከታቸው ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ፍሬ_ካህን

ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ፍሬ ካህን አረፉ።
ጻድቁን በመጀመሪያ ከጎጃም ተነሥተው በታዘዘ መልአክ መሪነት ትግራይ ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ሄደው መንነው መነኮሱ፡፡ ጻድቁ ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆኑ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ይታወቃሉ፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን ወንጌልን ሲሰብኩ ሙታንን እያስነሡ በሲኦል ውስጥ ስላለው መከራና ሥቃይ እንዲመሰክሩ ያደርጓቸው ነበር፡፡ ጻድቁ ሐይዳ ገዳም ታቦት ተቀርጾላቸው ገድል የተጻፈላቸው ቢሆንም ሙሉ ገድላቸው ታትሞ ለምእመኑ አልተዳረሰም፡፡ አቡነ ቶማስ ካረፉ በኋላ አቡነ ፍሬ ካህን ገዳማቸውን ተረክበው በጽድቅ መንገድ መነኮሳቱን አስተዳድረዋል፡፡

አቡነ ፍሬ ካህን አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኮሳቱ "ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ አድርገዋቸዋል፡፡

አባታችን ሽሬ ደብረ ሐይዳ አቡነ ፍሬ ካህን የተባለ ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ ገዳሙ ከአቡነ ቶማስ ዘሐይዳ ገዳም ጋር አንድ ነው፡፡ ወደዚህ ገዳም ውስጥ ሥጋና ቅቤ ተበልቶም ሆነ ተይዞ መውጣት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ አልታየሁም ተብሎ በድብቅ ሥጋ ተይዞ ቢገባ ሥጋው ይተላል፡፡ ሥጋና ቅቤ የበላ ሰውም ዕለቱን በድፍረት ወደ ገዳሙ ቢገባ ሆዱ በኃይል ይነፋል በዚህም ይታወቅበታል፡፡ ከብቶችም ቢሆኑ ወደ ገዳሙ አይወጡም፣ ማንም ሳይመልሳቸው ራሳቸው ይመለሳሉ፡፡ የአቡነ ፍሬ ካህን ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ነው፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ፍሬ ካህን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_ኪርያቆስ

በዚህች ቀን ከቆሮንቶስ አገር ቅዱስ አባት ኪርያቆስ አረፈ።

የዚህም አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና የከበሩ ናቸው የቤተክርስቲያንን ትምህርትና የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩት ከዚህም በኋላ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ጴጥሮስ አቀረቡት እርሱም በላዩ ጸልዮ አናጒንስጢስነት ሾመው ለአባ ጴጥሮስም የወንድሙ ልጅ ነው።

ከዚህም በኋላ ዘወትር መጻሕፍትን የሚያነብ የቃላቸውንም ትርጓሜ የሚመረምር የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓቷንና ሕጓን የሚያጸና ሆነ በትምህርቱና በእውቀቱም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ ኤጲስቆጶሱም መጻሕፍት ማንበብን እንዳያቋርጥ ያዝዘው ነበር እርሱም ለሕዝቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለኤጲስቆጶሱም በቤቱ ያነብለት ነበር። መጻሕፍትንም በሚያነብለት ጊዜ ኤጲስቆጶሱ በእርሱ ደስ ይለው ነበርና።

ዕድሜውም ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነ ጊዜ ሚስትን ያጩለት ዘንድ ወላጆቹ ጠየቁት እርሱ ግን ይህን አልወደደም ግን ከገዳማት ወዳንዱ ይሔድ ዘንድ እንዲአሰናብቱት ወላጆቹን ለመናቸው ከዚያም በኋላ አዘውትሮ ወደ ገዳማት የሚሄድና ወደ ወላጆቹ የሚመለስ ሆነ። መመላለሱም ከበዛ ዘንድ የከበረች የምንኲስናን ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ከኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ ከአባ ቄርሎስ ጋር ተገናኝቶ ስለ ምንኲስና ኀሳቡን ሁሉ ነገረው። እርሱም በጎ ሥራን ወደሃል አለው ታላቅ አባትም እንደሚሆንና በእርሱም የብዙዎች ነፍሳት ብሩሃን እንደሚሆኑ ትንቢት ተናገረለት።

ከዚህም በኋላ የመነኰሳት አባት ወደ ሆነ በፍልስጥዔም ወደ ሚኖር ወደ ክቡር አባ ሮማኖስ ላከው እርሱም በደስታ ተቀብሎ የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። የምንኵስናንም ሥርዓት ያስተምረው ዘንድ የሰይጣንንም ተንኮል ያስረዳው ዘንድ በዚያው ገዳም ለሚኖር አንድ አረጋዊ ሰጠው። ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት በስግደት በመትጋት በታላቅ ድካም በቀንና በሌሊት በገድል ተጸምዶ በትዕግሥት በትሕትና በቅንነት ኖረ።

#እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጥቶት ወደርሱ የሚመጡትን በሽተኞች ሁሉ የሚፈውሳቸው ሆነ የትሩፋቱና የቅድስናውም ዜና በሁሉ ቦታ ተሰማ ። የኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስም የክብር ባለቤት የሆነ #መንፈስ_ቅዱስን ስለ አቃለለ መቅዶንዮስ መቶ ሃምሳው ኤጲስቆጶሳት አንድነት ወደሚሰበሰቡበት ወደ ቊስጥንጥንያ በሚሔድ ጊዜ ይህን አባት ኪርያቆስን አባ ቄርሎስ ከእርሱ ጋር ወሰደው በላያቸው በአደረ #መንፈስ_ቅዱስ ስም ተከራክረው ከሀዲ መቅዶንዮስን ረቱት ከምእመናንም ለይተው አሳደዱት።
ከዚህም በኋላ በመልካም ሽምግልና #እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ። ከዕረፍቱም በኋላ #እግዚአብሔር ድንቆች የሆኑ ብዙ ተአምራትን ከሥጋው ገለጠ ከእርሳቸውም አንዱ ከኢየሩሳሌም ገዳማት በአንዱ ሥጋው ይኖራል። ከአረፈበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሥጋው አልተለወጠም ወደ ኢየሩሳሌም የሚሔዱ ሁሉ ያዩታል እነርሱም በቅርብ ጊዜ እንዳረፈ ያስባሉ እርሱ ግን ያረፈው ለአኖሬዎስና ለአርቃዴዎስ አባታቸው በሆነ በታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_አትናቴዎስና_እኅቱ_ኢራኢ

በዚችም ቀን አባ አትናቴዎስና እኅቱ ኢራኢ አረፉ። እሊህንም ቅዱሳን ከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው።

በማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ዕራቁታቸውን ከጉድጓድ ጨመራቸው በላያቸውም የጒድጓዱን አፍ ዘጋ በውስጧም ነፍሳቸውን አሳለፉ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዓምደ_ሚካኤል

በዚችም ቀን ለኢትዮጵያ ነገሥታት ለዘርዐ ያዕቆብ፣ ለበእደ ማርያም፣ ለእስክንድር የሠራዊት አለቃ የሆነ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል አረፈ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ገላውዴዎስ የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ ይልቁንም በሃይማኖትና በበጎ ሥራ የበለጸጉ ናቸው። ይህንንም ቅዱስ በቅዱሳን አርባዕቱ እንስሳ በዓል ወለዱት ስሙንም ዓምደ ሚካኤል ብለው ሰየሙት።

ከተወለደም አንድ ዓመት ሲሆነው ከቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከመንበሩ ከርሠ ሐመር ውስጥ ማንም ያየው ሳይኖር እየዳኸ ገብቶ ሦስት ቀን ሰነበተ ወላጆቹም እርሱ እንደሞተ ተጠራጥረው እያለቀሱለት ኖሩ።

ከዚህም በኋላ በሦስተኛው ቀን ቄሱ ሊዓጥን ገባ ዕጣንንም ሲፈልግ በከርሠ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን በሕይወት አገኘው በበታቹም ምንም ምን ጉድፈት አልነበረም። ቄሱም ለወላጆቹ ነገራቸው እነርሱም እጅግ ደስ እያላቸው መጥተው ከዚያ ወሰዱት።

ከዚያንም ጊዜ ጀምሮ በጥበብና በዕውቀት አደገ ነገሥታት ገዥ እስከ አደረጉት ድረስ በቤት ውስጥ በሚሠራው ላይ ሁሉ አሠለጠኑት። እርሱም ለድኆች በፍርዱና በምጽዋቱ አባት ሆናቸው በገንዘቡም አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ አደሰ በዘመኑም ሰላም ሆነ በጾሙና በጸሎቱ በምጽዋቱም በቅዱሳንም የጸሎት ርዳታ በወዲያም በወዲህም አገሮችን የሚያጠፉ ጠላቶችንና ዐመፀኞች ጠፉ። ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዙና ግብርን ገበሩ።

የዚህም ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ልቡ በ #እግዚአብሔር ፍቅር የታሠረ ነው በተጸለየበት ውኃ ሳይጠመቅና ሳይጠጣ አይመገብም ነበር ገንዘቡንም ሁሉ በምጽዋት ጨረሰ።

#እግዚአብሔርም በጎ ሥራውን በአየ ጊዜ እንዲፈተን ፈቀደለት ዐመፀኞች ሰዎችም በእርሱ ላይ ተነሡ እንዲገድለውም በንጉሥ ዘንድ በሐሰት ነገር ወነጀሉት ንጉሡ ግን እጅግ ስለሚወደው ራራለት በነገራቸውም በዘበዘቡትና በአስጨነቁትም ጊዜ ከጭንቀት የተነሣ ወደ ሩቅ አገር አሥሮ አጋዘው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም የሚራዳው ሆነ ሰማያዊ ኅብስት የወይን ጽዋ እያመጣለት ይመግበዋል።

ቅዱስ ቁርባንንም መቀበል በሚሻ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ የ #ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አምጥቶ ይመግበዋል። ከዚህም በኋላ እሊያ ነገረ ሠሪዎች ይገድሉት ዘንድ ንጉሥ እንዲፈቅድላቸው ተማከሩ በፈቀደላቸውም ጊዜ ወደ ንጉሥ የፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሉት።

በዚያችም ሌሊት #እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ መነኵሴ በድኑን ሊያይ ተነሥቶ ሔደ ሥጋውንም ሲያጥኑ ሦስት መላእክትን አገኛቸው። እርሱም እንዳልዋሸ በሕያው #እግዚአብሔር ስም እየማለ ይህን ተናገረ። ዳግመኛም የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድለት ብዙ ቀን የተመለከቱም አሉ።

ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ አዘነ ተጸጸተም በጎ ሥራውንም ሁሉ አሰበ እነዚያንም ሐሰተኞች ረገማቸው በሞትም ቀጣቸው ቅዱስ ዐምደ ሚካኤልም በአባቶቹ መቃብር አክብረው እንዲቀብሩት አዘዘ። እርሱ ቅዱስ እንደሆነ በበጎ ስም አጠራር እንዲጠሩት እንጂ ስሙን በክፉ እንዳይጠሩ አዋጅ አሳወጀ። መታሰቢያውንም አቆመለት ልጆቹንም አከበራቸው እጅግም ወደዳቸው።

ከዚህም በኋላ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ ከእርሱ ጋር ያለውን የአባቱ የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ከዚያ አፍልሰው ወደ አትሮንስ ማርያም እንዲወስዱትና በዚያ በነገሥታት መቃብር እንዲቀብሩት አዘዘ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ነአኩቶ_ለአብ_ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)

ዳግመኛም በዚችም ቀን የጻድቁ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነአኵቶ ለአብ መታሰቢያው።

ሃገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት። በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው።

ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል። ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው።

እርሱ ንጉሥ ነው። ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው።
ሁሉ በእጁ ነው። እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው።
እርሱ የጦር መሪ ነው። ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም።
እርሱን "ወደድንህ ሞትንልህ" የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት። ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት #ክርስቶስ ነበር።
የሃገር መሪ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው። ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም።

እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ "ጊዜ የለኝም" ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል፣ ያንጽ፣ በክህነቱ ያገለግል፣ ማዕጠንት ያጥን፣ ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር።

እኛ "ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል" ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ ...ጦር በፊት በኋላ በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውኃ በምድር ላይ ፈሷል። ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው።

#ለመሆኑ_ቅዱስ_ነአኩቶ_ለአብ_ማን_ነው?

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም ሁለተኛ ነው። እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናቸው። ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው።

እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር። ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች። ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው።

እዚያው ላይም "ነአኩቶ ለአብ" (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት። ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ።
#ኅዳር_4

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
በዚህችም ቀን የደማስቆው #ቅዱስ_ቶማስ አረፈ፣ #ቅዱስ_ያዕቆብና_ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ፣ #ቅዱሳን_አቢማኮስና_አዛርያኖስ በሰማዕትነት አረፉ፣ የአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር የሆኑት #አቡነ_አበይዶ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቶማስ_ዘደማስቆ

ኅዳር አራት በዚህችም ቀን የደማስቆ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቶማስ በግብጽና በሶርያ እስላ*ሞች በነገሡ ጊዜ በሰማዕትነት አረፈ።

ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው። ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና፣ ለቅስና፣ ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል። በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር።

ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የ #ክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም። በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐ*መድ ተከታዮች) ናቸው። 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ።

በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐ*መዳዊ "እንከራከር" አለው። ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐ*መድ ሐሰተኛነት ስለ #ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በኋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው።

በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመ*ዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው። ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ። "እንዴት እምነታችን እስል*ምናን ትሳደ**ባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት።

መኮንኑም "እሺ! #ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓ**ንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው። የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች።

ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው።
ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው።" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ። ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ያዕቆብ_ወዮሐንስ

በዚህችም ቀን ያዕቆብና የሀገረ ፋርስ ኤጲስቆጶስ ዮሐንስ የሐርመዝ ልጅ በሆነ በፋርስ ንጉሥ በሳቦር እጅ በሰማዕትነት አረፉ።

አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር። እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን) በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው። ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው።

ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ። ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው። ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል።

በኋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም። የ #ክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ እየናዘዙ ጠበቁላት። ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው።

በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው። ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ። አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት።

ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው። ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ።
"አምላክ አንድ #እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው። እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_አቢማኮስ_ወአዛርያኖስ

በዚህች ቀን ከሮሜ አገር ቅዱሳን አቢማኮስና አዛርያኖስ በሰማዕትነት አረፉ።

አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ። በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው። አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር።

በዘመኑ እንኳን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ መዘመር እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር። ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበትም አላውል አሉ።

ታላቅ ግፍ ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው #ክርስቶስን ያመልኩ ነበር። ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ።

መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ። "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት።

" #ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት። "የፈጠረ፣ ያከበረ፣ #ቅዱስ_ሥጋውን #ክቡር_ደሙን የሰጠ #ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት። በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው። በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አበይዶ

ዳግመኛም በዚህች ቀን የአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር የሆኑት የኢትዮጵያዊው አቡነ አበይዶ ዕረፍታቸው ነው፡፡ የታላቁ አባት የአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ አባ ዮሐኒ ዕረፍታቸው ኅዳር 5 ስለሆነና የአቡነ አበይዶም ታሪክ ከአባ ዮሐኒ ጋር የተገናኘ ስለሆነ በዚሁ ዕለት አንድ ላይ እናየዋለን፡፡ ኅዳር 4 ቀን ግን የአቡነ አበይዶ ዕረፍታቸው መሆኑን ብቻ ጠቅሰን እናልፋለን፡፡ ስንክሳሩም ስማቸውን ብቻ ጠቅሶት ያልፋል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_4 እና #ከገድላት_አንደበት)
#ኅዳር_5

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር አምስት በዚህች ቀን የደብረ ዓሣው #አባ_ዮሐኒ የተሰወሩበት፣ #አባ_አሞኒ_ዘናሕሶ ያረፉበት፣ #የቅዱስ_ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት፣ የሐዋርያው #ቅዱስ_ጢሞቴዎስ መታሰቢያ፣ #የቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት ሥጋው የፈለሰበት ዕለት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዮሐኒ_ዘደብረ_ዓሣ_ወአባ_አሞኒ_ዘናሕሶ

ኅዳር አምስት በዚህች ቀን የደብረ ዓሣው አባ ዮሐኒ የተሰወሩበት እና አባ አሞኒ ዘናሕሶ ያረፉበት ዕለት ነው።

አባ ዮሐኒ መጽሐፍ አባታቸውን ዘስዩመ ተንቤን እሁሁ ይላቸዋል፡፡ እናታቸው ደግሞ ዓመተ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ ደገኛ ምግብራቸው ያማሩ ሀገር ወዳድ ናቸው፡፡ አቡነ አሞኒ የካቲት 5 ቀን አክሱም ውስጥ ሲወለዱ ሰይጣናት የወላጆቻቸውን ቤት ከበው በማየታቸው እንደተወለዱ በእጃቸው ቢያመለክቱ በአንድ ጊዜ 60 ሰይጣናት ተሸንፈው እንደጢስ በነው ጠፍተዋል፡፡ አሞኒ ማለት አሸናፊ ማለት ነው፡፡ አባ አሞኒ የራስ ፀጉራቸው ልብስ መጎናጸፊያ ሆኖላቸው የኖሩ ታላቅና ቀደምት አባት ናቸው፡፡ በደመና ተጭነው ደብረ ዘይት ድረስ በመሄድ ከአባ እብሎይ ጋር ተገናኝተው ብዙ ምሥጢርን አውርተዋል፡፡ አባ ዮሐኒን ያሳደጉት አስተምረው ያሳደጓቸው አባ አሞኒ ናቸው፡፡ የእናቱን ጡት ፈጽሞ ጠብቶ የማያውቀውን የ #መንፈስ_ቅዱስ ልጃቸውን አባ ዮሐኒን እሳቸው እያጫወቱት የታዘዘ አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው ቶራ (ሰሳ) እያጠባችው ነው ያደገው፡፡

መነሻ ታሪኩም እንዲህ ነው፡- የተንቤን አውራጃ ገዥ የነበረው ሰው በዘመኑ ዐፄ ካሌብ የነበሩበት ዘመን ነበርና አብሯቸው ወደ ምድረ ኖባ ሄደው ሰባት ዓመታትን የፈጀ የጦር ዘመቻ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃዩ ነገሥታት ላይ አካሄዱ፡፡ የተንቤኑ አውራጃ ገዥም ወደ ዘመቻው ከሄደ ቆይቶ ነበርና ታናሽ ወንድሙ የገዥውን ሚስት ‹‹ወንድሜ የቀረው ሞቶ ነው እንደ ኦሪቱ ሕግ እኔው ላግባሽና ልጆቹን ላሳድግ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ባሌ ቢሞት ይነገረኝ ነበረ ዘመቻ የሄደው ሁሉ አልተመለሰም›› ብላ እምቢ ብትለው በግድ ተገናኛት፡፡ በዚህም ጊዜ አባ ዮሐኒ ተፀነሱ፡፡ በሚያዝያ 5 ቀንም ተወለዱ፡፡

ከዘጠኝ ወር በኋላ ባሏ ከዘመቻ መጣና ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ የአካባቢውም ሰው ወጥቶ በክብር ሲቀበለው ሚስቱ ግን ምጥ ተይዛ ታማ ስለነበር ወጥታ አልተቀበለችውም፡፡ ‹‹የት ሄደች? ምንስ ሆነች?›› ብሎ ሲጠይቅ ልጅ አይደብቅምና አንድ ሕፃን ‹‹አርግዛ ልትወልድ በምጥ ላይ ትገኛለች›› አለው፡፡ የአውራጃውም ገዥ ያለችበት ድረስ ሄዶ ቢያያት ያማረ ወንድ ልጅ ታቅፋ አገኛት፡፡ ከዚህም በኋላ ከቤቱ ምሰሶ ጋር ጥፍንግ አድርጎ አስሮ እየገረፋትና እያስጨነቃት ከማን እንዳረገዘች ጠየቃት፡፡ እርሷም የወንድሙን ምሥጢር ለመጠበቅና ወንድማማቾቹን ላለማጣላት ሥቃዩን ታግሳ ዝም አለች፡፡ በዚህ ቅጽበት የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል 40 ዓመት ሙሉ ዘግተው በበረሃ ለሚኖሩት ለአባ አሞኒ ተገለጠላቸው እንደ አውሎ ነፋስ አምዘግዝጎ ወስዶ አውራጃ አገረ ገዥው ቤት አደረሳቸው፡፡

እንደደረሱ ዓመተ ማርያም በጽኑ ድብደባና ግርፋት እየተሠቃየች እያለ አባ አሞኒ የጸጉራቸውን አጽፍ ለብሰው ራቁታቸውን ደጇ ላይ ቆመው አየቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ለባሏ ‹‹ያውና ከዚህ መነኩሴ ነው የወለድኩት››፣ አለችው፡፡ የአውራጃ አገረ ገዥውም አባ አሞኒን ይዞ ጽኑውን ግርፋት በወታደሮቹ አስገረፋቸው፡፡ በመቀጠልም ገና የእናቱን ወተት እንኳን ያልቀመሰውን ጨቅላ ሕፃን አንሥቶ ‹‹እንካ ልጅህን ይዘህ ጥፋ ከዚህ›› ብሎ ሰጣቸው፡፡ አባ አሞኒም በዚህ ጊዜ ‹‹ዮ ሀበኒ ዮ ሀበኒ›› አሉ፡፡ በትግርኛ እሽ ስጠኝ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ነው ሕፃኑ በኋላ ላይ ‹‹አባ ዮሐኒ›› የተባሉት፡፡ አባ አሞኒም ሕፃኑን ተረክበው ወደ ደብረ ዓሣ ተራራ ሥር ሄደው ልጁን ከወይራ ዛፍ ሥር አስተኝተው ‹‹አምላኬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ሆይ! ኃጢአቴን ተመራምረህ ይህንን ሕፃን የሰጠኸኝ አላጠባው ጡት የለኝ አላበላው እህል የለኝ›› ብለው የጨቅላው ሕፃን ነገር እጅግ ቢያስጨንቃቸው ምርር ብለው አለቀሱ፡፡ ጸሎታቸውንም እንደጨረሱ ተራራውን በ #መስቀል ምልክት ቢባርኩት በተራራው መሐል ላይ እንደመደብ ያለ አልጋ በተአምራት ተሠርቶ አገኙት፡፡ ሕፃኑንም ከዚያ አስተኝተው ድጋሚ ጸሎት ሲጀምሩ ቶራ (ሰሳ) መጥታ እግርና እግሯን አንፈራጣ ሕፃኑን አጠባችውና ሄደች፡፡

አባ አሞኒም በዚህ ደስ ተሰኝተው ሕፃኑን ‹‹የምግብህ ነገር ከተያዘ ግዴለም›› ብለው ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልዩ አድረው መለስ ቢሉ ዳግመኛም ሕፃኑን የታዘዘ ንስር አሞራ በክንፎቹ ጋርዶ አልብሶትና አቅፎት እንዳደረ ተመለከቱ፡፡ አባታችንም እጅግ ደስ ተኝተው #እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ቀን ቀን ቶራዋ እያጠባችው ሌሊት ሌሊት ንስር አሞራው አልብሶት እያደረ ሕፃኑ ሦስት ዓመት ሆነው፡፡ አባ አሞኒም ከሰባት ዓመቱ ጀምረው እስከ 12 ዓመቱ ድረስ ፊደል፣ ንባብ ከነ ትርጓሜው፣ ብሉይንና ሐዲስን፣ ምግባር ሃይማኖትን ሥርዓተ ቤተ ክርስያንን ሁሉ አስተማሩት፡፡

አባ አሞኒ ልጃቸው አድጎ 12 ዓመት ሲሆነው ከዚህም በኋላ ዲቁና ሊያሾሙትና አክሱም ጽዮን ወስደው ሊያስባርኩት ቤተ ካህናት ከተባለው ቦታ ይዘውት ሲሄዱ ልዩ ስሙ ሲሂታ ከሚባለው ቦታ ሲደርሱ ከወገባቸው በላይ እራቁታቸውን የሆኑ እንስራ የተሸከሙ ዓሥር ሴቶች አገኙ፡፡ አባ ዮሐኒም አባታቸውን ‹‹አባቴ እነዚህ ደረታቸው ላይ ቀንድ ያላቸው ጽጉራቸው የረዘመ ምንድናቸው? እንደእኛ የሆኑ መስህታን የሚባሉት እነዚህ ናቸውን?›› አሏቸው፡፡ አባ አሞኒም ‹‹አይደሉም ልጄ ዝም ብለህ ሂድ›› አሏቸው፡፡ በኋላ ግን ትዝ ሲላቸው ‹‹በዱር እንስሳት ያሳደኩት ልጄ ወንድና ሴት ለይቶ ሲያውቅ በዚያው ሊሳሳት አይደልምን?›› ብለው በማሰብ ዲቁናና ክህነቱ ይቅርበት ብለው ተመልሰው ወደ በዓታቸው ይዘውት ገቡ፡፡

ከዚህም በኋላ አባ አበይዶ ወደ አባ አሞኒ መጣና እሳቸውን ከአባ ዮሐኒ ጋር እያገለገሏቸው ተቀመጡ፡፡ ቅዱስ ዮሐኒ እየጻፈ ቅዱስ አበይዶ የሚጻፍበትን ቆዳ እያዘጋጁ ሦስቱም በአንድነት በተጋድሎ መቀመጥ ጀመሩ፡፡

አባ ዮሐኒ 20 ዓመት አባ አሞኒ ደግሞ 40 በሆናቸው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለአባ አሞኒ ተገለጠላቸውና ‹‹አሞኒ ሆይ ከእንግዲህስ #እግዚአብሔር ወደኔ ና ብሎሃል›› አላቸው፡፡ እሳቸውም ልጆቻቸውን አባ ዮሐኒንና አባ አበይዶን ጠርተው ‹‹በሉ እንግዲህ እኔ ወደ #እግዚአብሔር መሄዴ ነውና ጸልዩልኝ›› አሏቸው፡፡ ከማረፋቸውም በፊት አባ ዮሐኒን ለብቻቸው ጠርተው ‹‹አንተ አባ ዮሐኒ ካሁን በፊት ሲሂታ ላይ ያየሃቸው ሴቶች ናቸው፣ አዳምንም ከገነት ያስወጡ ናቸው፡፡ ወደፊትም እንደ እነርሱ ያለ የደረሰብህ እንደሆነ ካለህበት ገደል ተወርውረህ ውደቅ በባሕር ውስጥ ጥለቅ›› ብለው ነግረዋቸው በዛሬዋ ዕለት ኅዳር 5 ቀን በሰላም ዐረፉና ወደ ጠራቸው #እግዚአብሔር ሄዱ፡፡

አባ አሞኒ ካረፉ ከ12 ዓመት በኋላ የአባ ዮሐኒ ወላጅ እናታቸው የልጇን ነገር ስታጠና ኖራ ነበርና አሁን ባሏም ስለሞተ አባ አሞኒም ስላረፉ ልጇን ልታይ ከ32 ዓመት በኋላ መጣች፡፡ ቀሚስ ለብሳ ፀጉሯን ተሠርታ በሴትነቷ ልጇ ካለበት ቦታ በመሄድ ማነጋገር እንደማትችል ስላወቀች ፀጉሯን ተላጭታ የወንድ ልብስ ቁምጣ ለብሳ በሁለመናዋ ወንድ መስላ ወደ ደብረ ዓሣ ተራራ አመራች፡፡ እዚያም እንደደረሰች በቅዱሳን ሥርዓት መሥረት ሦስት ጊዜ ‹‹አውሎ ግሶን፣ አውሎ ግሶን፣ አውሎ ግሶን›› አለች፡፡ ሰይጣን ይህን ስም ሲሰማ 40 ክንድ
ይርቃል፡፡ የደብረ ዳሞ መነኮሳት እንደ ሰላምታ መለዋወጫ ይጠቀሙበታል፡፡ አባ ዮሐኒም ይህን ድምጽ ከውጭ በሰሙ ጊዜ ‹‹አንተ ማነህ?›› አሉ፡፡ እርሷም ‹‹ዓመተ መንፈስ ቅዱስ ነኝ›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም አንድም ድምፁዋ ወትሮ ከሚያውቁት ድምፅ ስተለየባቸው ደግሞም ትዝ ሲላቸው እነዚያ እንስራ አዝለው ደረታቸው ላይ ቀንድ ያላቸው ሆነው ውኃ ቀድተው ሲሄዱ በመነገድ ያዩአቸው ሴቶች ድምፅ ሆነባቸው፡፡ ደግሞም ‹‹ወልደ እከሌ፣ ክንፈ እከሌ›› ሲባል እንጂ ‹‹ዓመተ፣ ወለተ›› ሲባል ሰምተው አያውቁም ነበርና አባታቸው አባ አሞኒ የነገሯቸው ትዝ አላቸው፡፡ በዚያውም ቅጽበት የሚጽፉባትን ብዕር ጆሮአቸው ላይ እንደሰኩ 500 ሜትር ርዝመት ካለው ትልቅ ተራራ ላይ ራሳቸውን ቁልቁል ወረወሩ፡፡ ነገር ግን መሬት ሳይደርሱ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአየር ላይ እንዳሉ ተቀበላቸው፡፡ ብዕራቸው ግን መሬት ላይ ወድቃ ሸምበቆ ሆነች፡፡ ወዲያውም አባ ዮሐኒ ክንፍ አውጥተው ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ጎን ለጎን ሆነው በዛሬው ዕለት ኅዳር 5 ቀን ወደ ብሔረ ሕያዋን ይዟቸው ገባ፡፡

ብሔረ ሕያዋን ያሉ እነ ቅዱሳን ሄኖክና ኤልያስም ‹‹ሰው ከሚሞትበት ሀገር ሞት ወደሌለበት አገር ማን አመጣው?›› አሉ፡፡ መልአኩም በዚህ ጊዜ #እግዚአብሔር ባዘዘኝ ጊዜ እኔ ገብርኤል ነኝ ያመጣሁት›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም መልአኩ ‹‹አንተ ሄኖክ ምንም ንጹሕ ብትሆን በሥርዓተ ሥጋ ተወልደህ በሥርዓተ ሥጋ አድገህ ሚስት አግብተህ ወልደሃል፣ #እግዚአብሔርም እዚህ ያደረሰህ በንፅህናህ ነው፤ አንተም ኤልያስ ምንም ድንግል ብትሆን በሥርዓተ ሥጋ ተወልደህ በሥርዓተ ሥጋ አድገህ ከዚህ ደርሰሃል፤ ይህ አባ ዮሐኒ ግን ከተወለደ ጀምሮ የእናቱን ጡት አልቀመሰም፣ ቀን ቀን ሰሳ እያጠባችው ሌሊት ሌሊት ንስር አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው አድጓል እንጂ›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ቀጥሎም መልአኩ የአባ ዮሐኒን ገድል ዘርዝሮ ከነገራቸው በኋላ ሊሞት ያለበትንም የአሟሟቱን ነገር ከነገራቸው በኋላ ‹‹ታዲያስ እንዲህ ያለውን አምጥቼ ከብሔር ሕያዋን ባስገባው ፍርዴ እውነት አይደለምን?›› አላቸው፡፡ ቅዱሳን ሄኖክና ኤልያስም ይህን ጊዜ ‹‹ይገባዋል›› ብለው አባ ዮሐኒን በምስጋና ተቀበሉት፡፡

ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ደብረ ዓሣ ተመልሶ መጥቶ ለአባ አበይዶ ተገለጠላቸውና አባ ዮሐኒን ብሔረ ሕያዋን እንዳስገባው ነገራቸው፡፡ በመጀመሪያ ቅዱሳን ሄኖክና ኤልያስ አላስገባ ብለው እንደነበርና በኋላም መልአኩ ራሱ የአባ ዮሐኒን ገድላቸውን ከነገራቸው በኋላ በምስጋና እንደተቀበሉት ለአባ አበይዶ ነገራቸው፡፡ ቀጥሎም መልአኩ የአባ ዮሐኒን ገድላቸውን እንዲጽፉትና እንዲያስተምሩበት ለአባ አበይዶ አዘዛቸውና ዐረገ፡፡ አባ አበይዶም አባ ዮሐኒ ከገደሉ ተወርውረው ሲወደቁ አንድ ደስ የሚል ወንድ ሲቀበለው አይተው ነበርና አሁን መልአኩ ሲነግራቸው እጅግ ደስ አላቸው፡፡ አባ አበይዶም በመልአኩ በታዘዙት መሠረት የአባ ዮሐኒን ገድል ጻፉት፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ለንጊኖስ

በዚህች ቀን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በዕንጨት #መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ የቅዱስ ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ነው። ይህም ቅዱስ በ #ጌታችን ከአመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር ወንጌልን የሚሰብክ ሆነ ከሀድያን አይሁድም በላዩ ተነሡበት በመኳንንት ዘንድ በሐሰት ወንጅለው በቀጰዶቅያ አገር ራሱን አስቆረጡት ራሱንም ብቻውን ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱዋት። በኢየሩሳሌም የሚኖሩም አይሁድ በአዩዋት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሩዋት።

ከብዙ ቀኖችም በኋላ እንዲህ ሆነ በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዲት ሴት በቀጰዶቅያ አገር ነበረች ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምራ በተቆረጠበት ቦታ በመቆም ስለርሱ ታለቅስ ነበር ክብር ይግባውና በ #እግዚአብሔርም ፈቃድ የዚያች ሴት ዐይኖቿ ታወሩ።

ከዚህም በኋላ ምናልባት ዐይኖቿ ቢገለጡላት በማሰብ ከከበሩ ቦታዎችና ክብር ይግባውና ከ #ጌታችን መቃብር ለመባረክና ለመለመን ተነሥታ ልጅዋን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች። ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ በዚያ ልጅዋ ሞተ ኀዘንም ተጨመረባት ወደ አገርዋም መርቶ የሚያደርሳት አጣች ስለዚህም የመረረ ልቅሶን አለቀሰች ከኀዘኗም ብዛት የተነሣ ተኛች።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞተው ልጅዋ ጋር በሕልሟ አየችው። ዕገሌ ከሚባልም ቦታ ሒደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ አላት። ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ስለዚያ ቦታ ጠየቀች ሰዎችም ወደርሱ አደረሱዋት። ያንንም ቦታ በቆፈረች ጊዜ መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ ወጣ። ራሱ ወደአለችበትም ስትደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿም በዚያን ጊዜ ተገለጡላት #እግዚአብሔርንም አመሰገነችው።

ከዚህም በኋላ ከልጅዋ ሥጋ ጋር የቅዱስ ለንጊኖስን ራስ ወደ አገርዋ ወሰደቻት። በታላቅ ክብርም በአማረ ቦታ አኖረቻት።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሰማዕት_ቅዱስ_ጢሞቴዎስ

በዚህች ዕለት አሕዛብን ለሚያስተምር ለከበረ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ የሆነ የከበረ ሰማዕት ሐዋርያው ጢሞቴዎስ መታሰቢያው ነው። የዚህም ቅዱስ ልደቱና እድገቱ ልስጥራን ከሚባል አገር ነው አባቱም ከዋክብትን የሚያመልክ ዮናናዊ ነው እናቱ ግን በኦሪት ሕግ ጥላ ሥር ያለች ናት።

የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም በልስጥራን ሀገር በሰበከ ጊዜ ይህ ጢሞቴዎስ ስብከቱንና ትምህርቱን ሰማ #እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያደርጋቸውን ድንቆች ተአምራቶችን አይቶ እሊህም ተአምራቶች አስተዋዮችና ጥበበኞች የሚደነግጡባቸው ናቸው ስለዚህም ወደ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ሒዶ በእርሱ ትምህርት በክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመነ። በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም ተጠምቆ የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ ሆ። ወደ ብዙ አገሮችም ተከትሎት በመሔድ ከእርሱ ጋር ደከመ ታላቅ መከራና ብዙ ኀዘንም ደርሶበታል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኤፌሶን ውስጥ በአንዲት አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው።

በዚያንም ጊዜ ወደርሷ ገብቶ ለሰዎቿ በክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ሰበከ ብዙዎችንም ወደ ቀናች ሃይማኖት መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ከዚህም በኋላ በዙሪያዋ ወዳሉ ብዙዎች አገሮች በርቀትም ለሚገኙ አገሮችም የከበረ ወንጌልን ሰበከላቸው።

የከበረ ሐዋርያ ቅዱሴ ጳውሎስም ሁለት መጻሕፍቶችን ጽፎ ወደርሱ ልኳል እርሳቸውም ሕዝቡን የሚያስተምርባቸው ራሱም ከቢጽ ሐሳውያን የሚጠበቅባቸው ቅስና ወይም ዲቁና ሊሾም የሚገባውንና የማይገባውን የሚለይበት ክህነት በማይገባው እጁን እንዳይጭን የሚያስጠነቅቁ ናቸው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ደግሞ ለርሱ ተወዳጅ ልጁ አድርጎ ይጠራዋል መልእክቶቹንም በእርሱ እጅ ወደ አገሮች ልኳል።
በላያቸው የተሾመባቸውን የ #ክርስቶስን መንጋዎች ፈጽሞ በጠበቀ ጊዜ በትምህርቶቹ በተግሣጾቹና በድርሰቶቹ ልቡናቸውን ብሩህ አደረገ አይሁድንና ዮናናውያንን ይገሥጻቸውና ይዘልፋቸው ነበር እነርሱም ቀንተውበት ሁሉም በጠላትነት ተነሡበት ተሰብስበውም ጥር 23 ቀን ገደሉት ምእመናንም ሥጋውን አንሥተው ቀበሩት ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም እስከ ነገሠ በዚያው ኖረ እርሱም ስለ ሥጋው አስቦ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ በጥር ወር በሃያ ሰባት ቀን አፈለሰው በዚያችም ቀን በዓል አደረገለት።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎድሮስ (የሠራዊት አለቃ)

ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነው የሠራዊት አለቃ የቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕትነት የሥጋው ፍልሰት ሆነ። የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር።

ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ።

አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ #ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች።

ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው።

የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው።

ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቅዱስ ቴዎድሮስንም ጠርቶ ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ አለው።

ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ የበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና። ንጉሡም እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ አለው።

በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ ደሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በ #እግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ አላቸው። እነርሱም ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን አሉት እርሱም ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ አላቸው።

ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ አሉት።

ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው #ጌታዬ_አምላኬ_ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ_ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን።

ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በ #መስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለ #እግዚአብሔር_ኢየሱስ_ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ።

አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች ። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው።

በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው።

ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል #እግዚአብሔርም ይበቀልላታል አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና #ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው።

ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው።

ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ #እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል።

በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት።
በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ እነሆ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማውን ለሚያጠጣ፣ ወይም ለቤተክርስቲያንህ መባን መጻሕፍትንም ለሚሰጥ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስስለታለሁ። ገድልህንም የሚጽፈውን፣ ወይም የሚያነበውን፣ የሚሰማውን፣ ወይም የሚገዛውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ።

ከዚህም በኋላ ብዙዎች ከንጉሥ ሠራዊትና ከሕዝቡ ተሰብስበው በንጉሡ ላይ እንዲህ ብለው ጮኹበት አንተ ከሀዲ #እግዚአብሔር ያጥፋህ ከጠላቶቻችን ያዳነንን ኃያልና ጽኑዕ የሆነውን የከበረ ቴዎድሮስን ታሠቃየዋለህና ይህንንም ብለው በክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመኑ ያን ጊዜም ንጉሥ ተቆጥቶ ሁሉንም አስገደላቸው ሰማዕትም ሆኑ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ አዘዘ የብረት ዐልጋም አምጥተው ቅዱሱን በላዩ አስተኙት ከበታቹም እሳትን አነደዱ ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ ጸለየ አቤቱ ፈጣሪዬ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ምድጃ እንደ አዳንካቸው አድነኝ። ወዲያውኑም ያ እሳት ጠፋ እንደ ንጋት ጊዜ ቊርም ሆነ።

ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ክብር ይግባውና ከ #ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል የተሰጠህ ሆይ ጽና በርታ ያን ጊዜም ቅዱሱ ተነሥቶ በንጉሡ ፊት ቆመ እንዲህም አለው ክብር ይግባውና #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ አድኖኛልና አንተ ከሀዲ እፈር አለው። የንጉሡም የጭፍራ አለቃ ይህን በአየ ጊዜ ክቡር ቴዎድሮስ ከሚያመልከው ክብር ይግባውና ከ #ጌታ_ከኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ ጮኸ ርሱንም ራሱን አስቆረጠውና በሰማዕትነት ሞተ።

ቅዱስ ቴዎድሮስንም ብዙ ከአሠቃየውና ማሠቃየቱ ከሰለቸው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም እንዲአቃጥሉ አዘዘ። በ #ጌታችንም ፈቃድ ከእናቱ ደጅ ወስደው ሐምሌ 20 ቀን እራሱን ቆረጡ ከእርሱም ደም፣ ወተትም ፈሰሰ ታላቅ እሳትም አንድደው ሥጋውን በውስጡ ጨመሩ እሳቱም ከቶ አልነካውም። እናቱም ለወታደሮች ብዙ ወርቅ ሰጥታ ሥጋውን ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው እስከ መከራው ፍጻሜም በቤቷ ውስጥ አኖረችው።

በዚህችም ቀን የሠራዊት አለቃ ቴዎድሮስ ሥጋውን ከሀገረ ሰጥብ ወደ ሀገረ አስዩጥ ሥጋው አፍልሰውታል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_5_ጥርና_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)